በለው! የዶር አረጋይ የማንኪያ እና የእግራምሳህን አቅርቡልን አቤቱታ!

የዶር አረጋይ
በርሄ ማንኪያ።
„በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሄር ከወንዝ ፈሳሽ
 ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ እህሉን ይዋቃል፤ እናንተም
የእስራኤል ልጆች ሆይ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።“
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፯ ቁጥር ፲፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ (Sergute©Sselassie)
30.11.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

·       ብታ ትንሽ ስለማንኪያ አምድነት።

ዶር አረጋይ በርሄን በአካል አውቃቸዋለሁኝ። ቁንጥንጥ አለመሆናቸውን እወድላቸዋለሁኝ። ተናዳፊም አይደሉም። አንድ ነገር ከያዙ ግን ችኮ ናቸው።

·       ከበጎው ስነሳ።

ተስፋ አለመቁረጣቸውን አደንቀዋለሁኝ፤ ዛሬ ካልካዱት እኔ እራሴ በተገኘሁበት ስብሰባ በፈርንጆች አቆጣጠር በ90ዎቹ መጨረሻ ላይ ከዛ ዘመን ጀምሮ ነው ውጭ የሚኖሩ ጎንደሬዎች ከህሊናቸው ጋር የነበሩት። እና የስብሰባው ተሳታፊዎች የወልቃይት እና የጠገዴ የመሬት ዘረፋ እና ወረራ ሲጠዬቁ፤ ስህተት እንደነበርትክክል አልነበረም፤ ቦታው የጎንደር ነው ሲሉ በጆሮዬ አዳምጫለሁኝ። በወቅቱም በሉላዊ ሚዲያ ዜና ሰርቼበታለሁኝ። ዛሬ ደግሞ ዴሞካረፊው ስለተለወጡ ምን ሊሉ እንደሚችሉ ይደመጣሉ፤ መቼም እንደ ሽንብራ ቂጣ መጋለበጥ ነው፤ ለነገሩ ከአራና ጋር ተዋህደው የለምን? የአረና አቋም ደግሞ ይታወቃል። ወራራ፤ ዝርፊያ ክብሩ ሞገሱ ግርማው ነውና። ስለዚህ በዚህው የቀደመው አቋማቸውን እራሳቸው በራሳቸው ሸረውታል ማለት ነው። ፈረሶ መሰራት፤ ተሰርቶ መፍረስ።

ይልቅ አሁን አገር ከገቡ ያዬሁት ነገር የሰከነ ሂደት ለመከተል ያደረጉት ጥረት መልካም ነው ለስልትም አንጀት ለመብላትም ይሁን ከተደሞ የመነጬ። ለማወክ አለመነሳታቸው ጥሩ ነው። በአንድም በሌላም መንፈስን የሚከረኩሩ ነገሮችን በመነካካት አልበጠበጡም። ብጥብጥ የሚያስነሱ ነዳጅና ክብሪት ሃሳቦችን ሆነ መንፈሶችን ሲወተውቱ አላስተዋልኩኝም። እርግጥ መንትያቸው አቶ ግደይ ዘራጽዮን ያሉትን ብለውናል። የዘመን ሽክርኪት አልፏቸው ስለሄድ።

በሌላ በኩል ይህ ለውጥ ከዚህ ይደርሳል ብለው ካላሰቡት ሊሂቃን ወገኖች አንዱ ነበሩ ዶር አረጋይ በርሄ እና ድኢጅታቸው። ይህም መቼም አሊ አይባልም አያካድምም። እራሱ  የአማራን የህልውና ተጋድሎ ከቁጥር ያስገቡት አለነበርም። ጣና ኬኛንም እንዲሁ። ቀልባቸው በዚህ ዙሪያ ድርሽ አላለም። የአማራ እና የኦሮሞ የመንፈስ ግንኙት ምቾት አለመስጠቱ  የአይዲኦሎጂያቸው አንኳር ስለሆነ አይጠዬቁበትም። ነገም ካቻሉ ይሞክሩታል … 

በሌላ በኩል አንድ ነገር ከያዙ አይልቁም። ዕድሜም ዘመንም ይፈታዋል ብለው አያምኑንም። ከላይ እንደጠቀስኩት መንቻካ ናቸው፤ እንዲያውም ሲያገርሽባቸው አይቼ አንድ ጊዜ „ግርሻ“ የሚል ጹሑፍ ጽፌባቸው ነበር።

ጠላት ብለው በህሊናቸውን የፈረጁትን ማህበረሰብ ጋር አንድም ቀን ተስቷቸው እርቀ ሰላም ሲወርዱ በመንፈስ አይቼ አላውቅም፤ ይህ ሁሉ የዘር ጥፋት ተፈጽመ ተበደሉ በማለት አቋማቸውን ሲያስውቁ  አማራ ለሳቸው ገነት ውስጥ የባጀ ማህበረሰብ ነበር። ለነገሩ በነገረ አማራ እሳቸውም ሆኑ መንትያቸው አቶ ግደይ ዘራጽዮን ከተጠያቂዎች ውስጥ ናቸው። ይህን ደግሞ ታላቁ የእውነት አርበኛ በተደጋጋሚ ጊዜ አቶ ገ/መድህን አርያ መስክረውታል። ተወላጆችም በቤተሰብም እናውቀዋለን።

ስለዚህ ራሳቸውን ለማሸነፍ ገና ንስሃም መግባት፤ ፊደልም መቁጠር ያስፈልጋቸዋል ባይ ነኝ። ይልቅ አሁን አገር ከገቡ በዋላ አማራ ማለት ቢሳናቸውም ፋኖ እና ቄሮን አመስግነዋል። የመጀመሪያው ሊሂቅ መሆናቸው ናቸው ነው የአማራ ታገድሎ ለሳቸው በሰላም ወደ አገረ መመለሰ አስተዋፆ እንዳደረገ የመሰከሩ። በዚህ ልብ ይመርቅ ብለናል። እኔም አመስግኜ በሌላ 
ጹሁፍ ኮልሜያለሁ። ታሪክ ስለሆነ ሁሉ ነገር ተለቅሞ መያዝ አለበት።

·       ኮነት በሚዲያ ነፃነት አብራክ።

ነፍሱን ይማረውና የእውነት አርበኛው ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ ጋር ለአንድ ከዚህ ግባ ለማይባል ጉዳይ አንድ አመት በአንድ አውሮፓዊ መጋዚን ላይ ሲሞገቱ አውቃለሁኝ። እንዲያውም እኔ ሙጉቱን ሲያጦዙት እኒህ ሰው የአገር መሪ ቢሆኑ የሚዲያ ነጻነት ጋር በምን አግባብ ሊግባቡ ነው ሁሉ እል ነበር። ችግር አለባቸው በሳቸው መንፈስ ውስጥ ያለውን የተከደነ ፍላጎት ፈርቅቆ የሚያውጣ አቅም ያለው ጋዜጠኛ ልክ እንደ ዋልታው ጋዜጠኛ አቶ ሥሜነህ ባይፈርስ አይነት ቢገጥማቸው ሥልጣን ከኖራቸው ከርቸሌ ነው የሚለቁት። ካለምንም ቅደመ ሁኔታ።  መቻል ብሎ ነገር አልፈጠረላቸውም። ማሰለፍ እንደ ሊሂቅ ብሎ ነገር አልሰራላቸውም።  ምንም የመቻቻል ክፍትት ቦታ የላቸውም በህሊናቸው ውስጥ። ፈጽሞም አልፈጠራላቸውም ድክመትን የመቀበል ሆነ አምኖ ለማረም መሳናዳት ሆነ ይቅርታም ለመጠዬቅ። 

በሳቸው ቤት ወቀሳን ነቀሳን ለማስተናገድ ዕድል የለም። በቃ ቅዱስ¡ ናቸው እጃቸውም መንፈሳቸውም ደም ያላፈሰሰ። በሌላ በኩል ዕድለኛም ናቸው በጫካ ዘመናቸው ለጠፋው የሰው ህይወት እስካሁን ልብ ያለው፤ አቅም ያለው፤ የሎቢ ተግባር ስላልተከናወን እነሆ ለቀጣይ ሥልጣን ለመጋራት ደግሞ ተኮልኩለዋል። እንዲያውም እንደ ጠ/ሚር አብይ አህምድ ገለጻማ ልምደዎትን ያገሩንም አለበት። ውስጤ እዬቆሰለ አዳምጨዋለሁኝ ይህን።

ገድሎ መቀብርን ነው እንዲያሰተምሩን የፈለጉት፤ ስለ ባዶ 6 የሰቆቀቃ ውሎ አመራር እንዲነግሩን? ወይንስ በ40 ዓመት ውስጥ አንድ ሰው ተተኪ አለማውጣትን መሃንነትን፤ ወይንስ አንዲት ሴት ሊሂቅ አለመፍጠርን ወናነትን፤ ወይንስ ስብስብን አቻቻሎ ለስኬት አለማብቃትን፤ ወይንስ ድርጅታቸውን በአቅም አጉልብተው በቂ አባላት እና አካላት አደረጃተው ውሃ እንቦጭነትን ይሆን? ወይንስ ሚዲያ ፈጥረው የተወሰነ የድርሻቸውን ለመወጣት ጥረት አላመዳረጋቸውን? እኮ ምኑን ነው እንዲያስተምሩ ይሆን ይፈለጉት? ከሳቸው አማካሪነት ከተፈለገ ሳጅን በረከት ከቅርብ አሉ አይደለምን? ባገኛቸው እሳቸውን እራሳቸውን ጠ/ሚር አብይ አህመድን እሞግታቸዋለሁኝ።

ከገዳይ ሰው ገድሎ መጨፈር ከሆነማ ስለምን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ይወቃሳል? ስልጣን ላይ ቢኖሩ የሚቀር ነገር አልነበረም። ደፍረው እንኳን እሳቸው የመሰረቱት ድርጅት ችግር ፈጥሯል አይሉም። ሰብዕዊነት ለሳቸው ቅርፊት ነው። ሰው ብሎ የሚነሳ መንፈስ የላቸውም።

ለዛውም አጥፈቻለሁኝ ማሩኝ ሳይሉ። ከቶ እንዲያው የጎንደር ሰው ከፍጥረት ዘር አልተቆጠረ ይሆን?እኔ ያለፈው ብቻ አይደለም በ27 ዓመት ለጠፋው ነፍስም አማራ አይታያቸውም ለሳቸው። እኔ በበቃኝ ከተውኳቸው ባጀሁኝ። ብቻ  የአሁኑ ማንኪያ፤ እግራም ሳይህን በተጨማሪም ጡጡ ይገዛልን ጨዋታ ገርሞኝ ነው መጻፍም የፈልገኩት። ሆድ ዕቃቸውን ለማየት ያስቻለ የብቃት መቅኖ ስለሆነ መጣፍ አለበት ብዬ የወሰንኩት። የ ኢትዮጵያ ህዝብ በገበርዲን እና በከረባተቸው ልክ አንጎላቸውንም ይለካው በማለት። 

ለመሆኑ በሥም የሚታወቅ፤ አድርሻው የሚታወቅ ስንት አክቲብ አባል አለው ድርጅታቸው ወይንስ ዓርማው እና ሰነዱ ይሆን ድርጅት የሚያሰኘው? ሁለት የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሥራች አባላት ናቸው ተጀምሮ እስኪጨረስ ለዲያስፖራው ተጨማሪ የቤት ሥራ የተደራጁት፤ ዛሬ ደግሞ ለአዲሱ ለውጥ በአዲስ ቦላሌ ከች ብለዋል። ለዛውም በልምዳቸው ትውልድ ሊታነጽበት?  
ለመሆኑ ከሳቸው መዳፍ ምን ሊማር ይሆን ትውልዱ? ሰውን ማዕከል የሚያደረግ ፍጡር እሳቸውን ቁጭ ብሎ የጫካ ተመክሮዎቸትን የሰው ግድያን፤ የዘር ጭፍጨፋን ይንገሩን የሚባለው? ኖረበት እኮ 27 ዓመት ሙሉ መከረኛው የኢትዮጵያ ህዝብ። ምነው እናትዬ ዶር አብይ አህመድ ምን አድርገን ተገኘን?

 ምን አለ በክብር አቶ ገ/መድህን አርያን በግል ታጋይነት ጋብዘው ልክ እንደ ክብረት ብርቱካን ሜዴቅሳ፤ ልክ እንደ ኮ/ ጎሹ ወልዴ እጃቸውን ጨብጠው ዕውነትን ፍንድቅድቅ ቢያደርጓት። ደጉ ገ/መድህን አርያ እኮ የእውነት አክቲብሲት ናቸው። እስቲ ልደትን በቤተመንግሥተዎት ፈርሰስ ያደርጉልን የዕውነት አባትን አቶ ገ/መደህን አርያን፤ በማህላችሁ እርሰዎ እና ዶር ለማ መገርሳ አስቀምጣችሁ እስኪ እንያቸው። ልክ ለብርቴ እንዳደረጋችሁት። አለነዎት እስከ በሏቸው። እንኳንም ኖሩልን በሏቸው። ክብር እስኪ አግኝተው ዓይናችን ይይ። ሾመት አይፈልጉም። ብቻ የ እረፍት ጊዜያቸውን ማሰመር ብቻ ነው ከዚህ ትውልድ የሚያስፈልገው። ለ እውነት ራሰቸውን የሰጡ አቡነ ጵጥሮስ ናቸው ልክ እንደ አቡነ አብርሃም። 

አማራ መሬት ላይ ደማቅ አቀበባል በነቂስ ወጥቶ ሊያደርግ የሚጋባው ለእኒህ ዘመን ለማይራሳቸው ቅዱስ አባት ነው። እጬጌ የሰብዕዊ መብት ተሟጋች ናቸው። ምርጥ ዜጋ ከተባለ አቶ ገ/መድህን አርያ ናቸው። ሳያመልጡን ክብር ስለሚገባቸው ክብር ሊሰጣቸው ይገባል። ለትግራይ ህዝብም ዘውዱ ናቸው። እሳቸው ስላሉ ሚዛን እንድጠብቅ እንገደዳለን። ተቋም ናቸው። አይከንም ናቸው። 

የኢትዮጵያ ህዝብ ይማር ልምድ ከተባለ ከእሳቸው እንጂ ከዶር አረጋይ በርሄ ሊሆን አይገባም። ዕውነት በተቀበረችበት ዘመን ዋቢዋ እኒህ ቅዱስ አባት ብቻ ነበሩ። አይዟችሁ ያሉን። የራስ ተሰማ ናደው ሴራ ጠ/ሚር ጽ/ቤት ካላንኳኳ ኳኳቴው ካላናወጠው እኒህ ብርቅ ኢትዮጵያዊ ክብር ሊያገኙ ይገባል። ከመካራችን ጋር አብረው የነበሩ ንጹህ ልብ ያላቸውም ናቸው። ሌላው ማደናገሪያ ማሳቻ ነው የነበረው። ፌክ። 

ከእነ ዶር አረጋይ በርሄ ተመክሮ? ምጥ እና ማጥ፤ ዳጥና መከራ። ለዛው ለወንበሩ ለዝናው እንደ ለእንክብካቤው ለቁልምጫው ከሆነ የጠ/ሚር ቢሮ እንደ ፍጠርጥሩ እንጂ እንደ ገና ቁስል መቆስቀስ የተገባ አይሆንም። ልዩነቱ እኮ ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር የሥልጣን የክብር ጉዳይ እንጂ የአይዲኦሎጂ አይደለም። አሁን የአብይ ካቢኔ ይህን እሸከማለሁ ከላ መልካም ደንደስ እንመኝለታለን፤ አቦይ ስብሃትን ሸኝቶ ሌላ ሥልጡን እና ዘመናይ ባርነት ከናፈቀው። እትጌ ትግራይማ ፈርዶባታል። ትብስን ታስተናግድ። እኔ እንዲያው ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ከሙታን መደር የተነሱ ያህል ነው የሚሰማኝ። ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ሞቱ እምለው አቶ ገ/መድህን አርያ የመሪ ያህል የክብር አቀባባል ተደርጎላቸው በቤተ መንግሥት ሳይ ብቻ ነው። አማራ አብሶ ጎንደር በደስታ አቅም ያለው ሁሉ እንዲቀበላቸው ይሆናል። ጀግና ናቸው የምዕት! ቅኔ ናቸው ልክ እንደ ዶር ለማ መገርሳ የምዕት። ለእኔ ጌጤ ናቸው! ለእኔ ጉልላቴ ናቸው!

·       በሰተሆነ። 

ይልቅ ዶር አረጋይ በርሄ የሚለዩት ከ27 ዓመቱ ከዘራፈው ውስጥ የሌሉበት መሆኑ ነው። ይህም ቢሆን ዘረፋ የወያኔ ሃርነት ዶክተሪኑ መሆኑን ልባቸው አሳምሮ ያውቀዋል። ምን ሲዘርፉ እንደ ነበር? አሁን ስኢፈርት ቢጠዬቁ ምልሻቸው ወጋ ጠቀም ጠራጠሮ ነው የሚሆነው።

በትግል ዘመናቸው ያ ደሃ ገበሬ የወሎ እና የጎንደር ገበሬ ላዩ ውሃ ታቹ ውሃ በሆነ ዋልካ ሲማቅቅ ባጅቶ የካቲት በመጣ ቁጥር የማሌሊት ወራራ ነው የነበረው። ይህን በስማ በለው ሳይሆን እኔ በ80 ዎቹ መግቢያ ላይ ያዬሁትን ነው እምናገረው። ምስክርም ነኝ።

እነ ማሌሊት ሳይደክሙ፤ ሳያርሱ፤ ሳያለስልሱ፤ ሳይጎለጉሉ፤ ሳያጭዱ፤ ዘር ሳያወጡ፤ ሳይከምሩ እህሉ ምርቱን ይዘርፉት ነበር፤ የሚከፍለውን ቀረጥም ባንኮችን ይዘርፉት ነበር፤ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ት/ቤቶችን፤ ክሊኒኮችን ያፈርሱ ያቀጥሉ ነበር፤ ድልድዩን ይሰብሩ ነበር። ያ ማለት ለነፃነት ተጋድሎ ማድረግ ነበር ለተጋሩ ሰማዕታት¡ ያ ማለት ደሃ አገርን ለማዳን የሚደርግ ተጋድሎ ነበር¡ የወልቃይት የጠገዴ እና የትግራይ አዛውንታት የታሪክ አዋቂዎች ደግሞ ባዶ 6 ይከዘኑ ነበር። 

ብቻ ለነፃነት ትግሉ ከእውር ቤት አንድ አይና ብርቅ ሆኖ በዬዘመኑ በሚነሳ ስበስብ የትግራይ ተወካይ ተቃዋሚ ሆነው በመቅረብ "የትግራይ ህዝብ የሚገባውን ያህል አልተጠቀም" መርሃቸውን ሸጓጉጠው ይዘው ከች ይላሉ። በሰው ዘር ጥፋት ክስመት ያፈጠጠ ነገር ሲመጣ ለእሳቸው የሲሶ ግምደላ ይመቻል። መሸፈኛቸው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሳይሆን ኢህአዴግ ሲሉ ይሸብልሉታል። ዋናውን ማዕከላዊ ጉዳይ መንካት አትደፈርም። 

አውራው ፓርቲ ማን እንደሆነ እንኳንስ ለሳቸው ጀማሪ ፖለቲከኛም ያውቀዋል። የሆነ ሆኖ ቀን የሚሰጠው መልካም ነገር ስላለ የአቤል ጮኸትም እዮርን ስለሚንኳኳ በአንድም በሌላም ፍርዱን ይሰጥበታል። ፍርድ እኔ ከመሬት ጠብቄም አላውቅም። ይህ የመዳህኒታ ዓለም የቤት ሥራ ነው የሰው ግፍም እንዳለው ግን ሳልጠቅስ አላልፍም። ቀን እራሱ ይመልሰዋል።

ግርም ያለኝ ደግሞ አሁን እሳቸው በአንድ ወቅት ድጋፍ አሰባስባለሁ ብለው ፊርማ ብቻ እኮ ነው። አመራሩ ብቻ ፈርሞ አከተመ። 6 ሰው ብቻ። ከዛ በስንት ምጥ 30/32 ፊርማ በመላ ዓለም ተገኘች። ጠብ ጠብ ብላ የተጠራቀመችው ናት። ይህም ብርቅ እና ድንቅ ሆኖ ሚዲያውን ሁሉ ሲያጨናንቀው ነበር።
ያን ያህል ዓመት ታገልኩ ያለ ድርጅት ስለምን ሲባሉ ሁሉንም ወያኔ ሃርነት ትግራይ ይዞብናል አሉ። ያን ለማሸነፍ እኮ ነበር እኮ የተደራጁት። እስኪ ነፍስ ያለው ጉባኤ ያካሄዱበትን ቀን ይንገሩን አባል ከኖራቸው። እስኪ እሳቸውን የሚተኩ ወጣቶችን ያሳዩን፤ እስኪ አንዲት አንስት ሊሂቅ ያሳዩን? አብነት ማለት እኮ ይኸው ነው። ሲመሰረትም የነበሩት ናቸው አሁን እምናያቸው።

ተጋሩ በሙሉ በማህበረ ትግራይ የተሰባሰበ ነው። የእነሱን ስብሰባ ተገኝቼ አይቸዋለሁኝ በ ዓለም አቀፍ ሚዲያ እሰራ በነበረበት ወቅት። በጣም ብዙ እና ለመስጠትም የማይሳስቱ አባላት ነበሩበት። የተቃዋሚንም የራሱንም የወያኔ ሃርነትንም ተገኝቼ እዘግብ ነበር። 

የሳቸውን ግን ከኢትዮጵውያን ጋር በሚደረገው ስብሰባ ጠጋ ብለው ተጣብቀው ካልሆነ ተከብረው የኖሩት የእኔ የሚሉት፤ ልብ ሞልቶ የሚያናገር አይደለም አባል ደጋፊ እንኳን አላዬንም አልሰማነም። በወያኔ ሃርነት ትግራይ በውጭ አገር ተጽእኖ ለመፍጠር አይፈቅዱትም ውስጠ ወይራ መንገዱ ይኼው ነው።

በሌላ በኩል ህብረት ኢተፖድህ መጣ ሲባል ደግሞ አባል ናቸው። በኢተፖድህም በሸንጎም ነበሩበት። በዬዘመኑ ሥማቸው ከጫዋታ ውጭ እንዳይሆን፤ እንዳይረሳ ዳማ ሲጫወቱ ከራርመው አሁን በስተመጨረሻ ደግሞ ግንቦት 7ትን ከወቀሳ ወጥተው አንድ የግንቦት 7 መንፈስ በዛጋጀው ጉባኤም ላይ  ስሜን አሜሪካ እንዲሁ ገላጭ ነበሩ። በዬጊዜው መቼም ሥም አያልቅም በብሄራዊ ሥም በተደራጀ አንድ ስብስብ አማካኝነት። የሆነ ሆኖ ዕድሜ ለአማራ የህልውና ታገድሎ እሳቸውንም ነጻ አውጥቶ ይኸው ደግሞ በአዲስ ገበርዲን አገር 
ገብተው ይንፈራሰሳሉ።

ይህ ለሁሉ የተደረገው ለሳቸውም እንደ ዜጋ መብታቸው ቢሆንም አሁንም የለመዱትን ጨዋታ በዓዋጅ ማስከበር ፈልገዋል። ክብርን በማንኪያ ይሰናዳለን፤  በአዲስ ስብስብ ደግሞ ደመቅቀን ቦግ እንበልበት ሲሉ ተደምጠዋል። እሳቸው የቆሙት፤ የሚንገበግባቸው፤ የሚያርመጠምጣቸው የተደራጁትም ለትግራይ ህዝብ እንጂ ለኢትዮጵያ አይደለም። ስለዚህ ከአረናቸው ጋር እዛው እንደ ፍጥርጥራቸው። ለነገሩ ዙሮ ግጥም ሆኖ ከ አረና ጋር ከሆኑ ከመድረግ ከሥሙ ጋር አበረው እንደ መሆን ያሰኛል? መሰለኝ? ምን መሰለኝ ነው እንጂ? የአቶ ዳውድ ኢብሳውም ደገሞ በጎን ከ ኦፌኮን ጋር አለበት? 

ከቻሉ አቅሙ ካላቸው ደግሞ በህብረ ብሄር ከተዳራጁት ጋር የተጽዕኖ ፈጣሪዎች ማህበር መመስረት ነው። አባልማ የለም። አገርም ውጭ አገርም። ውጪ አገር ያለው ቤተ ተጋሩ አንድም ገለልተኛ፤ ሌላውም የወያኔ ሃርነት አባል እና ደጋፊ ነው።

ግርም የሚለው እጅግም የሚደንቀው እሳቸው ሞክረዎት ያልተሳከውን ስብስብ አሁን መንግስት በአዋጅ አንድ ያድርገን  ዓይነት ጥያቄ አቅርበዋል። የተኮረኮመ ማፈሪያ! መቼም የአብይ መንፈስ ፈርዶበታል። ለስንቱ ጉዳይ ምርኩዝ ሆኖ ይዘለቀው እንደሆን እኔ አላውቅም።

መንግሥት የማስገደድ ምን መብት አለው? አይችልም። ሃሳብ ማቅረብ ይችላል። ፈርሶ ለመሰራት ተሰርቶ ለመፍረስ የፈቀደ ካለ ደግሞ በፈቃዱ የሚከውነው ነው። ለነገሩ ከመድረክ ሰዎች ጋር ሆነ ከኢህአፓ ሳይከፋፈል እንዲሁም ከመኢሶን ጋር አብረው ነበሩ፤ ከሸንጎ ጋርም ሰብሳቢ ነበሩ። እና ምን ተገኜ? በዬመዘኑ ሲሾለኩ ነው የሚታዩት። ከ አረና ጋርም ነገ ይታያል? 

አቅም ጥበብ ብልሃት ቢኖራቸው ባላ እና ወጋግራ ሆነው ህብረቱን ስብስቡን ማዳን በቻሉ ነበር። አንድ ሰው እኮ ነው ይህን ሁሉ ታምር እዬሰራ ያለው ዶር አብይ አህመድ። ከእኛም አልፎ አፍሪካ ላይ ተጽዕኖ እዬፈጠረ ነው። አውሮፓ ላይ ሳይቀር በአንድም በሌላም መንፈሱ ጠረን አለበት። አሁን ጆርጂያ ላይ የመጀመሪያ ሴት ፕሬዚዳንት ሰሞኑን መመረጣቸውን አዳምጫለሁኝ። ዓለምን እራሷ ወደ አልተነካ የአቅም ዕምቅ ጉልላት እዬመራት ነው የአሮን በትር።

እንዴት ዕድሜ ልኩን በትግል የቆዬ ሰው እሱ ያልቻለውን መሰባሰብ እኛን አሰበሳበህ አንድ አድርገህ ተፎካካሪህ አድርገህ አውጣን ይላል የሚፎካከረውን ኢህአዴግን? ልክ እንደ አቶ ትእግስቱ አውል እና እንደ አቶ አዬለ ጫሚሶ እንሁላችሁ ዓይነት እኮ ነው? በኢህዴግ ፍላጎት መደራጀት ካሰኛቸው ከዛው ከወያኔ ሃርነት ጋር ተዋህዶ እንደ ኦዴግ ከ አዴፓ ጋር እንዳደረውገው በዛ በ አቋራጭ መምጣት ነው። በቃ። ህብረ ብሄር ለመሆን ግን አይቻልም። 

ኢህአፓ፤ ግንቦት 7፤ ሰማያዊ፤ መኢህድ ከፈቀዱ ለዛውም ሰፊ የህሊና ተግባር ተከናውኖ። የኢተፖድህ ሁለተኛ ጉባኤ ነበሩበት አይደል ዶር አረጋይ በርሄ? አጀንዳ ማጽደቅ አቅቶ እንዴት ሲታመሱ እንዳደሩ እንደዋሉ? እንዴት ሲታመሱ እንደ ሰነበቱ? ነበርኩበት እኮ እኔው እራሴ ሥርጉተ ሥላሴ? በሦስተኛው ቀን ህዝብ ተሰብስቦ ማጣፊያው እንዴት እንዳጠረ አውቃለሁኝ?

ብቻ የአሁኑ ማንኪያ ግዙልን ይህን ጉድ ነጮቹ ሲሰሙት እንዲያው ምን ይሉ ይሆን? ሁል ጊዜ በማንኪያ? በዚህ ገለጻቸው አቅም የሌላቸው መሆነንም እገረ መንገዱን ነገረውናል። ለዚህም ነው ሥርጉትሻ ተፎካካሪ/ ተቃዋሚ/ ተቀናቃኝ እራሱ መሪ አገኝ ብላ የጻፈችው።

ለዚህ ነው እኔ ለውጡን ከጥዋቱ ከጣና ኬኛ ጀምሬ የደገፍኩት። ለዚህ ነው ሥርጉተ ሥላሴ ለማውያን የሆነችው። በሌለ አቅም ሰማይ ላይ መና መጠበቅ ብቻ ሳይሆን በንፋስ አቅጣጫ የነፃነት ነፍስ ማደር መዋል ስለማይችል፤ በሞገድ ብርጌድም አገር መምራት ስለማይችል። እበዛኛውን የፖለቲካ አካሄድም አሳምሬም ስለማውቀው። ከረባት ገበርዲን ጥበብን አያመጣም። ምን አልባት ከረባት ከአንገት ከዋለ ጀምሮ ያለው ዕድሜ ይቆጠር ካልተባለ በስተቀር። በዚህ ነው ህዝብ በሳይበር ጤነኛውን መንፈስ ሳይቀር ባለፈው ዓመት በወጀብ ሲንጠው አቀርጦ ለማስቀርት ሲታታር የነበረው። እራሳቸውን አሰባስበው አንድ አድኢገው መሞገት የደካማቸው ሊመሩት?ሃፍረት ነው ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን አሰባስቦ አንድ ያድርገን ማለት። ውርዴትም ነው። እነዚህ ናቸው እንግዲህ ኢህአዴግን ተፎካካረው አሸንፈው አገር የሚመሩት። ጡጦ በዬፌርማታው የሚያስፈልጋቸው። ኪሳራ! 

ምን አለ አርፈው ቢቀመጡ? ምንስ አለ በቃኝን ቢያውቁት? ለዚህ ነው እኔ ፓርቲ የሚባል ነገር የለም እምለው። አሁን እግዚአብሄር ይመሰገን አቶ ሌንጮ ለታ ይህንኑ አበክረው ገልጸውታል „ቡድን እንጂ የታዋቂ ግለሰቦች ስብሰብ እንጂ የፖለቲካ ፓርቲ አለ ብዬ አለምንም" ያሉት። ለነገሩ ዶር መራራ ጉዲናም ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲ አለመኖሩንም የተጽዕኖ ፈጣሪዎች የአንድነት መንግሥት ሽል ይዘውም ብቅ ሲሉ ነግረውናል። የጫዋታ ማሟያ ብቻ። በቃ ዝም ብሎ መኮፈስ። 

አሁን ለዶክተር አረጋይ በርሄ ወደ ትግራይ ሄዶ መኖርም መቀመጥም ጋዳ ስለሆነ በብሄራዊነት ሥም አዲስ አባባ ደግሞ በአዲስ ከረባት ብቅ ማለት ተፈለገ። መቼ በርክቶ አውቆ ነውና ስብበስብስ ቅንጅትስ ጥምረቱስ ግንባሩስ ተብዬው። አሁን እኮ መሬት ላይ መድረክ ራሱ የለም። ሁለቱ መንትዮሽ መኖር እንደ ስብስብ ሊታይ አይገባም። ጓደኝነት ነው እኔ የዶር መራራ ጉዲናም ሆነ የፕ/ በዬነ ጴጥሮስ ጉዳይ። ለዛውም ዕድሜ ልካቸውን በወቀሳ ብቻ። ደግ ነገርን ደግ ለማለት የማይችሉ የፖለቲካም የዳማ ጫዋታ። ትክ የላቸው ትርፍ የላቸው። በቃ ልክ እንደ አንድ የቤተሰብ ማህበር ነው እኔ የማዬው መድርኩን። ያፈራው፤ ያሰበለው ነገር የለም። ለውጪ ሚዲያ ግን ትልቅ ሆኖ ይታያል። 

የሚገረመው የጠ/ሚር ቢሮ እኛ ግዙፍ ነን እና ለይቱ ይዬንም አለበት። ሥም ከሆነ በሚዲያ ወርድ ሲልካ አለን ከሆነ አዎን። አቅም ጥበብ የደራጀ መሆን ግን የለም። የተደራጀ አይነ ገብ ቢሮ እንኳን የለም። የልጆች የጨዋታ ሜዳ ነው የሚመስለው ያዬነው ቢሮ? እና አገር መምራት? የግል ይሁን የድርጀት በዚህ መንፈስ ልክ ኢትዮጵያ ትውልድ እንዴት ማነጽ ይቻላል? 



የሆነ ሆኖ ዶር አረጋይ በርሄ ከማን ጋር በምን ሁኔታ ሊሰባሰቡ እንደሚችሉ እግዚአብሄር ይወቀው። የአማራ ድርጅቶች ከሆኑ ከእንግዲህ ልባቸውንም መንፈሳቸውን መጋለቢያ የሚያደርጉ አይሆንም። የውጪ መአህድ ጤናማ መንፈስ ስላለው ከብአዴን ጋር የሚዋህድበትን ሁኔታ ቢያመቻች መልካም ነው። ከልቡ እና ከእውነቱ ጋር ሆኖ። 

ለነገሩ ከስብሰባው ላይ ርጉውን ዶር አፈወርቅ ተሾመን አላዬኋቸውም። ከቀደመው መአህድ ጋር አብረን ልንሰራ ወደ ቤታችን ገብተናል ሲሉ አዳምጫለሁኝ ፋና ላይ በነበራቸው የግለት እና የበዛ የመጫን ቃለ ምልልስ። 
እኔ መአህድ ስለመኖሩም አገር ቤት አላውቅም። መፍትሄው ግን የውጩ መአህድ ወይ ከአብን ጋር ወይ  ከብአዴን ጋር መዋህድ ግድ ይለዋል። በዬቦታው እንደ ድመት አራስ ቦታ መምድምድ የተገባ ስላልሆነ። 

·       ተሰባሰቡ ዳግሚያ ደወል።

ሌላው የጠ/ሚር አብይ አህመድ ተሰባሰቡ ጉዳይ ነው። ምን የማይተዋወቅ ድርጅት እኮ የለም? አንድ ብቻ ነው ሰማያዊ። ሲሳባሰቡ ሲበተኑ፤ ሲፈርሱ ሲሰሩ ነው የኖሩት። ሲያፈሱ ሲለቅሙ፤ የለቀሙትን ደግሞው ሲያፈሱ እኛንም ሲታክቱን ነው የኖሩት። የሚያስዝነው ሲሳበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ይገናኛሉ፤ ሲለያዩ ደግሞ ከመቃብርህ እንዳልቆም ተባብለው ይለያያሉ። ዕውነትም የሆነ ነገር ቢሆን እንኳን የተለዬው ከሆነ አውነቱን የማዬት ህሊና ስደት ላይ ነው የባጀው። የራስ ብቻ ነው ትክክል፤ ፍጹም ጻድቅ። 

 ለዚህ ነው እኔ አቶ ሂደትን በ213/ 21014 አፈንጫኽን ላስን፤  በቅርቡ ከጣና ኬኛ ከኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ግለት እና የወል የሚዲያ ወከባ ጋር አያይዤ ደግሞ እጬጌው ሂደትን የጻፍኩት።

የሆነ ሆኖ ለምርጫ ቢሰባሰቡ ከምርጫው ማግስት ይፈርሳሉ፤ ሲፈርሱ ችግሩ ደጋፊዎቻቸው ከሁለት ተከፍለው ጉግስ ይገጥማሉ፤ ይህ አማረኝ ከሆነ የውጩ መከራ አገር ቤት ደግሞ ገብቶ ይመሰኝ ካለ የአብይ ካቢኔ ይሞክረው። ሰላማዊ ህይወት ብቻ ሳይሆን ውጭ ተወልደው የሚያድጉ ህጻናት መንፈስ ሲናወጥ ነው የኖረው በእነሱ ትርምስ። ከቅንጅት ወዲህ የተወለዱትን ልጆች እኔ እዚህ ሲዊዝ አላውቃቸውም። ሲወዝ ትንሽ አገር ስለሆነች በብዙ ሁኔታ ማወቅ ይቻል ነበር። የማውቃቸው ልጆችም ባገኛቸው አለያቸውም። በእነሱ ምክንያት ህዝብ ተለያይቷል። የትውልድ ብክነት በዬደረሱበት።  

ምን ይደረግ? 

እኔ የምለው ለውጡ ራሱ እዬጠራ ሲሄድ አይደለም ነፍስ የሌላቸው ነፍስ አለን የሚሉትም የአብይን እጅግ የዘለቀ ብርቱ የማስተዋል ጸጋ የተሰጠውን አቃፊ እና አሰባበሳቢ መንፈስ ልቆ የሚወጣ ስለማይኖር እይተጠቃለሉ ይሄዳሉ።  የሚሾልኩትም እዬሾለኩ ባለማህያዎች ማለት ነው። አቅም ያላቸው ሊሂቃንም በአማካሪነት፤ በመንግሥት መዋቅር እዬተመዳቡ ይጣጠሉ ወዘተ … ከዛ አላዛሯ ኢትዮጵያ እንደ ብሄረሶቦቿ ብዛት የ80 መከራ ጭጋግ መልክ ይይዛል። የትወልዱ ብክነት ፌርማታ ይኖራዋል፤ የድምጽ አልባዎቹ  የኢትዮጵያ 
እናቶችም መከራ በቃህ ይሆናል።

አብክሬ እምገልጸው ቢሰባሰቡም አይዘልቁም። ጊዜም የለም እኮ አሁን። የውጮቹ የለመዱትን አገር ቤት ይዘው ስለሚገቡ ስብስቡም አይዘልቅም፤
 ቢቆይ ቢቆይ አስከ ምርጫው መባቻ ነው ከዛ ይፍርሳሉ። ለዛውም ተወጋግዘው። ምክንያቱም ሁሉም ገበርዲን እና ከረባት ለብሰው ተወካይ መባል እንጂ ስለተዳረጁበት ዓላማ አይደለም ጉዳያቸው። ስለ ትወልዱ ብክነትም ጉዳያቸው አይደለም። ስለዝናቸው ስለክብራቸው ብቻ ነው የሚተጉት።

አሁን እራሱ በሳቸው በጠ/ሚር አብይ አህመድ ጋር መሰብሰቡ እራሱ አቁንጥንጧቸዋል። አደብ አጡ! መንፈሳቸው ችኩል ነው። ስልቹም ነው! አልተሰበሰብን ስሞታ ነበር። ሲሰበስቧቸው ደግሞ ስለምን ከሌሎቹ ጋር አብረን ተሰበሰብን ደግሞ አለበት?

በቃህም ደክሟህልም፤ የምርጫ ቦርዷ ሰብሳቢ ትሰብሰብንም አለበት። ይህ ማለት ለደጋፊዎቻቸው በጠ/ሚር አብይ አህመድ ሰብሳቢነት ከታች ሆነው ሊታዩ አይፈቅዱም።  እኩል ታች ከሆነ ግን ነፍሳቸው እረፍት ታገኛለች። እረብ ይላሉ።ይህ ነው ሚስጢሩ። ግን ግድ ነው አሁን ኢትዮጵያ በአንድ ጠ/ሚር ነው የምትመራው። ተደራቢ አለ ከተባለ ደግሞ ዶር ለማ መገርሳ ይሆናሉ። ቢሆኑም የዲሞክራሲ ት/ቤት በኢትዮጵያ የከፈቱ የመጀመሪያው የፖለቲካ ሳይንቲስት ማንዴላ ስለሆኑ መንፈሳችን ደስ ብሎን እናስተናግደዋለን።

ስለዚህ ግድ ይላል መመራት በአብይ ሌጋሲ። በጓዳ ለሚደረገው ግን ግድ አይሰጣቸውም ሊሂቃኑ። አብዩ ይሰብስብ ስለማይታይ አደባባይ ስለማይወጣ። እንዲህ አደባባይ ከሆነ ግን ክብር ዝቅ ይላል። ለዚህ ነው ፎቶው ከአብይ ጎን  መለጠፍ፤ ሚዲያ ላይ አብሮ ማድረግ ሲታይ የባጀው። 

አቅም ያለው እኮ ምልጃ መላሾ አያስፈልገውም። የአብይ ሆነ የለማ //  የገዱ ሆነ የአንባቸው መንፈስ እኮ ፕሮፖጋንዲስት እሰልፎ አልነበርም የተማገድንለት። አቅሙ ነው።  አሁን እኔ ስለ አቶ ሌንጮ ለታ ፖለቲካዊ ለውጥ አመስግኜ እምጽፈው ተቀስቅሼ አይደለም። አሁን ከሆነ እንዲያውም እኔ የ አብይን መንፈስ ብቻ ነው እማዳምጣው፤ ሙግት ሲኖር አገር ቤት ላይ አዳምጣለሁኝ። በተረፈ እንደ ቀደመው ሁሉ አይደመጠም ጊዜም አላባክንም። 
  
የሆነ ሆኖ ይህን መሰሉን የአደባባይ ታች ሆኖ መሰብሰበን ሊሂቃኑ የሚፈሩት ሁሉችም ጠ/ሚር አድርገው ራሳቸውን አኮፍሰው ነው ድርጅት የሚፈጥሩት። በሥር መሆን ቢቻል እኮ ቅንጅትም አይፈርስም፤ ሰማያዊም አይከፋፈልም ነበር። አሁንም ያሉት እንሱው ናቸው እስኪ ይታያሉ ዶር አረጋይ በርሄ በዶር መራራ ሥር ወይንም በፕ/ ብርሃኑ ነጋ ሥር ሲሆኑ፤ ወይንም ፕ/ ብርሃኑ ነጋ በአቶ የሺዋስ ወይንም በዶር መራራ ጉዲና ሥር ሲሆኑ፤ ወይንም ዶር መራራ ጉዲና በአቶ የሺዋስ ሥር ሲሆኑ መቼም ጥምረት ሲፈጠር እንደ አገርዊ ንቅናቂ ሦስት ሊቀመናብርት ቧልት አይኖርም ተብሎ ይታሰባል። መቼም አሁን የሽወዳ ፖለቲካ፤ የብለጠት ፖለቲካ ሆነ አለ የሚባለው አቅም አደባባይ እዬዋለ እያዬነው ነው።

እኛም እሚያሰቆመን ስሌለ እንጥፈዋለን፤ ሲያስፈልገንም በድምጥ እንመጣለን ለሙግቱ ማለት ነው። አሁን አገር ቤትም እንደ ጋዜጠኛ አቶ ሥሜነህ ባይፈርስ የመሰለ የልብ አድርስ ደፋር የፋክት ሰው ስላለ ወለም ዘለም የለም ዝርግፍግፉ ውልቅልቁ ይወጣል ልክ እንደ ትናቱ የአቶ አብረሃም ደስታ ውሎ። የተዋህደውም የአቶ አረጋይ በርሄ ድርጅት አብሮ ነው መንፈሱ የታናደው። አፋፍ ላይ ነው ነፍሰ ሥጋው። ዓላማውን ከማያውቅ ጋር እንዴት ውህደት እንደተፈጸመ እራሱ የታሪክ ጥቅርሻ ቅርሻም ነው።  

ብቻ እኔ ሁልጊዜም ሰነፎች ናቸው፤ በርታ ያለ ሥራ አይወዱም፤ ጠንካራ ስራ አይፈልጉም ብዬ ስጽፍ ቀልድ ይመስላችሁ ነበር። አሁን ማንኪያውን ግዙልን መጣ በእነ ዶር አረጋይ በርሄ። ከ40 ዓመት በላይ ተምክሮ እንዲህ ነው …. ተቃዋሚን / ተፎካካሪን/ ተቀናቃኝን በአዋጅ አንድ አድርጉልን፤ ሊቀመንበር ጸሐፊውንም እንዳሻችሁ እናንተው ደልድሉን። ጉዲ ሰዲ፤ ወይ ማዕልቲ፤ ጉድ በል ጎንደር….

መከረኛዋ አላዛሯ ኢትዮጵያ የዘመኑ ወጣት ሙሴዎችን የሰጠን አማላክ የተመሰገን ይሁን። አሜን! ይህ ባይሆን ኮከብ ቆጠራ ላይ እንደቸከልን ዕድሜ ዘመናችን ያልፍ ነበር። 

ዛሬ የኔ ውቦች የዘመቻ ቀን ነው በፌስ ቡካችሁ ፊርማውን አካሂዱት ከ100% በላይ ቢመጣም አደራ አታቋርጡት እሺ ውዶቼ፤ ይኸው ሊንኩ ፈረም ፈረም ፈርም ፈርም … እንርዳው ቅኑን የምህርት መንፈስ።

Ethiopia’s PM, Tinubu, others nominated for the African Leadership Magazine Persons of the Year 2018

ሌላውንማ እያያችሁት ነው። አሁን እኔ ስቸከችክ የባጀሁት ይገባችሁዋል ብዬም አስባለሁኝ። ራሱን መሰብሰብ፤ ራሱም በጋራ አጀንዳ ማደራጀት፤ ራሱን ማስታረቅ፤ ራሱን አሸንፎ ማስገኝት ያልቻለ መከራ ተሽክማ የኖረችው አገራችን እንሆ መጋራጃው ተቀዶ ጉዱ አደባባይ ላይ ዋለ።

ሌላው ዓይነ ጠባቡ ደግሞ ሁሉንም ሰብሰበህ ዕውቅና መስጠትህ የተጋባ ስላልሆነ ነጭ ለበሽ እና ዲርቶ ይለይም አለበት። ምን ችግር አለው ምርጫው ዴሞክራሲ ከሆነ እኮ እያንዘረዘረ ይለዬዋል። በዚህ በአሁኑ ውይይት እኮ ታዳሚው ውጭ ያለው በበቃኝ ውሳኔው ሳይበር ላይ አስተያዬቱን ድምጹን እዬሰጠበት ነው። እባክህ አብዩ አትድከምብን እያለ ነው?  

ይግርማል ሁለተኛ ትራክ ፎቅና ምድር ቤት ይዘጋጅልን? እኔ እብልጣለሁኝ እኔ ከሌሎች አናሳዎች ጋር አብሬ ልሰበስበ አልችልም፤ አንደኛ ደረጃ መንበር ይዘጋጅልን? ስስታምነት። ገማናው ብዙ ነው። አብረው ቡና መጣጠት አይችሉም እኮ፤ አብረው በአንድ ጉድብ ውስጥ ሆነው መከራን ታገሱ ቢባሉ አይችሉትም፤ አይችሉበትም ስንዱም አይደሉም - ሥም የለሾች! አንዳቸው ለሌላቸው መመስከር አይችሉበትም። 

ከአንዱ ድርጅት ውስጥ ያለ አቅም ጎልቶ ከወጣበት ላይ መንፈሱን ማሰረፍ ወንጀል ነው። "ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው" ፈቀደ ተብሎ እኮ ቋጠሮ ድህረ ገጽ ተውቅሶ መልስ ጽፎበታል። እኛ እንዲህ ነን። መልካምነትን ከራስ አሳልፈን ለማዬት ፈቃዱም አቅሙም የለም። በዚህ ማህል ኢትዮጵያ ባለቤት አልባ 
መሆኗ ማዬት ይቻላል። 
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
ውዶቼ ኑሩልኝኝኝኝኝኝ ማለፊያ የተግባር ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።