ወጣቱ ለራሱ ሲል ለውጡን ይጠብቅ!

ለውጡ ለኢትዮጵያ
      ወጣቶች
የልብ አድርስ ነው።
„እጃችሁን ለእግዚአብሄር ስጡ፤ ለዘላለም ወደ
ተቀደሰው ወደ መቅደሱ ግቡ፤ ጽኑ ቁጣው
ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን እግዚአብሄርን አምልኩ።“
መጽሐፈ ዜና መዋል ምዕራፍ ፱፰ ቁጥር ፱
ከሥርጉተ© ሥላሴ Sergute©Selassie
  15.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።



·       ብታ።

ውዶቼ እንዴት ናችሁ ያቻላችሁ ፌስ ቡክ ያላችሁ ይህን መልዕክት ከፌስ ቡካችሁ ብትለጥፉልኝ ደስ ይለኛል። ምስጋናዬም ከንጹህ ልቤ እንሆ። ወጣቶች ከብክነት የማውጣት ትውልዳዊ ድርሻ አለብን። የእኛ ይበቃል። ወጣቶች የሚሸሹበት ምክንያት ሙሉ አቅም ስላላቸው ነው። ይህ ለውጥ የሚመራው የአብይ ካቢኔ ደግሞ በወጣቶች አቅም ለመጠቀም ስንዱ ነው። ስለምን? እርካቡን የያያዙት ወጣቶች ስለሆኑ። እነሱን የሚተካ ተከታይ ሃይል መፍጠርም ዋንኛ ዓላማቸው ስለሆነ። ጥቃቱ ደርሶባቸውም አይተውታል።

Ethiopia - Dr Abiy ahmed Synergy "መደመር" እዉነት ሲገለጥ


·       የወግ ገበታ።

ወጣትነት ዕድለኝነት ነው። ወጣትነት ሃያልነት ነው። ወጣትነት አቅማዊነት ነው። ወጣትነት ጉጉታምነት ነው። ወጣትነት ፍጥነትነት ነው። ወጣትነት ግንባር ቀደምትነት ነው። ወጣትነት ምናባዊነትም ነው። ወጣትነት ድፍረትነት ነው። ወጣትነት ችኩልነትም ነው። ወጣትነት ግብታዊነትም ነው። 

ወጣትነት ግንፍልተኝነትም ነው። ወጣትነት ስሜታዊነትም ነው። ወጣትነት እውቀት ፈላጊነትም ነው። ወጣትነት አዲሳዊነትም ነው። ወጣትንት ስኬታማዊነት ነው። ወጣትነት ፍቅራዊነትም ነው። ወጣትነት ትእግስት አልቦሽነትም ነው። ወጣትነት መሆንነትም ነው። ወጣትንት ጀግንነትም ነው። 

ወጣትነት መዝናናት ወዳጅነትም ነው።  ወጣትነት ተስፋ ቆራጭነትም ነው ከብዙ በጥቂቱ ወጣትነት ይህን የሚገልጽ ይመስለኛል። በነገራችን ላይ የወጣቶችም አደራጅ ነበርኩኝ በዘመነ ኢሠፓ። አንድ ጉልበታም ጥናትም አጥንተን ነበር ወጣቱ እና ህልሙ፤ ወጣቱ እና አቅሙ የሚል። ወጣትም ስለነበርኩኝ ስናጠቃልለው እራሴንም በጥናቱ ውጤት ውስጥ አግኝቸበታለሁኝ፤ ጥናቱን ለማካሄድ ያነሳሳኝም ያ ነበር።  

የሆነ ሆኖ ወጣቶችን አትቸኩሉ፤ ግብታዊ አትሁኑ፤ ትእግስት አልባ እትሁኑ፤ ስሜታዊ አትሁኑ ማለት አይቻልም። ይህ ሊሆን ግድ ስለሚለው። እነዚህ ባህሪያት በወጣትነት የግድ ሊታዩ የሚገባቸው ናቸው ተፈጥራዊ ነው። እርግጥ ነው በሥነ - ልቦና ጫና እና በሃይማኖታዊ ዶግማ ብዙ ከመመሰጥ የሚመጡ አደቦች ሊኖሩ እንደሚችሉ እንደ ተጠበቁ ሆኖ። ይህም በእኔ በራሴ ላይ የደረሰ ጉዳይ ነው። ብዙ ነገርም ያሳጣል።
  • ዋጋ

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ወጣት ሁሉንም ዋጋ የከፈለ፤ በከፈለው ዋጋ ልክ ግን ተጣቃሚ ያልሆነ ነው። ወጣቶች ለዬዘመኑ ራሳቸውን ገብረው አልፋዋል - ተሰውተዋል፤ እራሳቸውን ማግደዋል። ተዋናዮች ግን የትውናው አከተሮች ለዛ ዘመን ከእነሱ በእድሜ ከፍ ያሉት ብቻ ስለነበሩ መሪዎች የዛሬ 40/ 43 ዓመት ያዬናቸው መሪዎች ዛሬም አሉ እንዳሉ። ትንታጎቹ ተሰውተው ሲያልፉ እነሱ ግን አሉ፤ የሚገረመው አሁንም ያለው ወጣት እኛን አጬግዮ ግብር ከፋይ ይሆንልን ባዮችም መሆናቸው ነው። በጣም ይሉኝታ ቢሶችም ናቸው። ያሳዝናል።

ባለፉት 40/ 50 ዓመታት ብዙሃኑ ወጣት ግን ከሥምም ከታሪክም ከዝናም ተሰርዞ መክኖ ቀርቷል። በዛ ዘመን በዕድሜ ከፍ ያሉት ለዘመኑ እንምራ ቢሉ ትክክል ቢሆንም፤ በዛ ዘመን ለውጡን መርተው ለድል ሳያበቁ፤ እነሱም ሳይሰዉ በብልጠት ራሳቸውን ቤተሰባቸውን ጠብቅው ትውልዱን አባክነው፤ የእልፍ ወላጅን ማህጸን እና አብራክ አሳርረው እራሳቸውን ግን በጥንቃቄ ከብክበው ዛሬም የእነሱ ሥም እንሆ በዬሚዲያው ይዘከራል። ታሪክ ሰሪ እና ፈጣሪ ሆነው ይወደሳሉ።

የሚገርመው በዘመናቸው ለኖሩበት እና ለባከነው ጊዜ እና ትውልድ ተጠያቂ ሳይሆኑ፤ ሳይወቀሱ ሳይነቀሱ፤ ሳያዝኑለትም ለዛ ለባከነው ትውልዱ እንሆ ዛሬም ለሦስተኛው ትውልድ የሥልጣን ዘመንም ተፎካካሪ ሆነው ቀርበዋል። ተፎካካሪ ሆነው መቅረባቸው አይደለም የሚደንቅው 50 ሺህ የኦሮሞ እና የአማራ ወጣቶች ያመጡትን ለውጥ እኛ አምጥተነዋል፤ እኛ አስገኝተናዋል በማለትም የወጣቱን ለወጥ ሊነጥቁ ብዙ መታመሶችን አሳይተውናል አብሶ ኦሮምያ ላይ። ስለ ወጣት ተተኪ የፖለቲካ ሊሂቃን ሲነሳባቸውም መልስ የላቸውም አታንሱብም ባዮችም ናቸው። ስለምን ዘውዱ እስከ መቃብር የተሰላ ስለሆነ። 

እንደ እውነቱ ከሆነ ዕድላቸውን ሲያሾልኩ የቆዬቱ በዘመናቸው ለሰሩት መልካም ሆነ መልካም ያልሆነ ጉዳይ እንደ ፍጥርጥሩ ይሁን ተብሎ አሁን የሦስተኛው ትውልድ ወቅት ስለሆነ ስለሚጠፋውም ስለሚለማው ተወቃሽም ተነቃሽም ሊሆን የሚችለው ይህው ትውልድ ስለሆነ ቦታውን ለቀቅ ቢያደርጉ መልካም በሆነ ነበር። ግን አሁን በዛው በታቆረው መንፈስ ላይ ሆነው ዛሬም እንመራለን እንወዳደራለን ባዮች ናቸው። ይቻላቸው ይሆን በወረዛ ተስፋ?

·       ድልን አሳልፎ ስለ አለመስጠት።

ፖለቲካ የመወመስን እቅም ነው። ህግ በማርቀቅ፤ ህግ በማጽደቅ፤ ህግ በማስፈጸም እረገድ ወጣቱ በስማ በለው ሳይሆን እርሱን የሚወክል ሃይል አቅም ሊኖረው ግድ ይላል። ወጣቶቹ እነሱ ያሉት በዘመናቸው ነው። በሃሳብ ደረጃ እንኳን ከግራ ፍልስፍና አራማጆች ጋር ሊቀራረብ የሚችል አመክንዮ የለም። እንኳንስ የወጣቱን የፍላጎት ውክልና ሊያቀነቀን ለዛ ሊተጋ ቀርቶ። ስለ እኔ እማውቀው እኔ እንጂ ሌላ አይደለም እና። 

አንድም የፖለቲካ ድርጅት ይሁን የሲቢክስ ድርጅት እዚህ ዴሞክራሲን ነፃነትን ሲለማመድ አሳይቶን አያውቅም። ሲያፍን፤ ሲያስገልል፤ ሲያሳድም፤ አቅምን ቀብሮ ሲያስቀር፤ ሲያሳድድ፤ የግልን እና የማህበራዊ ሰላምን ሲያውክ መኖሩን እኔው እመሰክራለሁኝ።  

የኢትዮጵያ ነኝ የሚል ሚዲያ ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ዜጋን እኩል ማዬት ከተሳነው ስለ እሳር ወይንም ስለ እንጨት መደረጃቱን ራሱን ይጠይቅ። ልብስ እንጂ የዜጋ የክት እና የዘወትር የለውም እና።  

ግራ የሚመራው ተቋም ሁሉ እንዲህ ነው። መሆን ላይ ወገቤን ነው። እሱ የማያደረገውን እሱ ያለስራውን ነው አዬር ላይ ሆኖ የሚናፍቀው። ሌላውን ሲያብጠልጥል አንትስ ቢባል መልስ የለውም። ግን ሙግቱን ስሚፈራ በዬደረሰበት ሃሳብን ፈርቶ እና ሸሽቶ ይኖራል። አቅም አለኝ የሚለው ሞጋችን አ ሃሳብ በማገድ እና በደቦ በማሳገድ ሁሉን ጠቅልሎ በመያዝ ነው። ስለሆነም የኢትዮጵያ ወጣቶች ያላዩት አገር ባይነፍቃቸው መልካም ነው።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ራሳቸውን ሊወክሉ የሚችሉ መንፈሶችን አሁን ስላገኙ የመሪም ሮል ሞዴሌ እዮር ስለሰጣቸው እነሱን መከተል ነጋቸውን የራሳቸው ለማድረግ ትልቁ መሳሪያቸው ነው። አሁን ያሉት የፖለቲካ መሪዎች ቅርቦቻቸው ሊሆኑ ይገባል። የእኛ ሊሏቸውም ይገባል። ስለምን? ወጣቶች ናቸው። ቋንቋው እራሱ ያግባባል። አንድ በድርጅት ህይወት ያልኖረ ሰው እና በድርጅት ህይወት ውስጥ የኖረ ሰው ለደቂቃ መግባባት አይችልም። መግባቢያ ቋንቋ ስለማይኖር።

ከሁሉ በላይ የአሁኖቹ መሪዎች ከግራ ፍልስፍና ጋር ቁርኝትም የላቸውም። የግራ ፍልስፍና አቅምን እንደ ጦር የሚፈራ በሸር እና በሴራ ቁርሾ የበከተ ነው። ትብትብ ነው። ባህሬ የለሽ ነው። ግጭት አምንጪ እና ግጭት ፈጣሪ ነው። ዝም ብላችሁ ቁጭ ብላችሁ ብታጠኑት የግጭቶች ምንጮች ሁሉ ከግራ ርዕዮት አቀንቃኞች የሚመጡ ናቸው። የትርምስ አውዶች ሁሉ የግራ ቅኝቶች ናቸው። ቀናዎች አይደሉም። አዎንታዊነትን እንደ ጦር ነው የሚፈሩት።

ግራዎች መምራት እንጂ መመራትን ፈጽሞ አይፈቅዱም፤ ቁንጥንጦች ናቸው ስክነት ያንሳቸዋል። ማቻቻል ግብራቸው አይደለም። ግራዎች በልጠው መታዬት እንጂ የሚበልጠኝ ይፈጠራል ብለው አያምኑም፤ ስለዚህም ነው ይህ ለውጥ ሲመጣ ሰራዊቶቻቸውን አሰልፈው በወጀብ ጠልፈው ለመጣል በረቀቀ ሁኔታ ቀዝቃዘውን ጦርነት ሲያካሂዱት የባጁት። 

ለውጥ ነው አሁን ለእነሱም መልስ የሰጠው። እነሱንም ነጻ አውጠቷል። ጊዜው እዬረዘመ ሲሄድ እያለቁ ከመሄድም አድኗቸዋል። ተማልዷቸዋል። አላቅማቸው የገቡት ቃል እንደ ዋላለ መቅረቱ ሲያቅትተው ጣሩን እያዩ ሹልክ ብለው አሁን በመደመር ፍልስፍና ነኝም/ አለሁም/ የለሁም ብለው ይገኛሉ።

ግራ የአቅመኛ ጣውንተኛ ስለሆነ በቅሎ ስለማይዘልቅ እዬከሰመ -- እያረረ --- እዬኮሰመነ --- እዬቀነሰ ነው የሚሄደው። ስለምን? በ አዲስ ዕሳቤ መተካትን አዲስ ሃሳብን አፍላቂ አምክንዮ በጽኑ ስለሚፈራ። 

እስቲ ልተካ ብሎ ቢያደርገው እንኳን በዓይነ ቁራኛ ጥበቃው አይቀሬ ነው። ለዚህ ነው አረና ከዛ የግራ ፍልስፍና አረንቋ ለመውጣት አቅም ያነሰው። እንደነ ዶር ለማው መንፈስ አረና ብሄራዊ የመሆን ዕድሉ የነጠፈ ነው። አሁን ላይ ኦፌኮንም ይህን መሰል ዕጣ ላይ ነው የሚያገኘው።

ስለምን? ችግኙ የበቀለው ከግራው ፍልስፋና ዘር አጥፊ እና አምካኝ ርዕዮት ነውና። ከአረና በስተጀረባው የወያኔ ሃርነት ትግራይ የግራ ማንፌስቶ የኢሰብዐዊ አዛውንታት አሉበት። ተዋህድኩ ሲልም እዛው እሱ በእሱውን የሙጥኝ ብሎ ነው። ለዚህ ነው የተዳረጀበት አይዲኦሎጂ መላ እጥ አጥቶ ራሱ የወለሌ ገበታ ላይ ያለው። ስለሆነም በብሄራዊ ደረጃ እንደ ለማው እና አብይ መንፈስ አንዲት ነጠላ ፍቅርን ከዞጉ ውጪ ማግኘት አይችልም፤ ከግራ ፖለቲካ ጋር ፍቺ ያልፈጸመ ስለሆነ። ሰው ከሚለው ታላቅ ፍጡር የመነሳት አቅሙም ስስ ነው። የሰው ልጅ ስቃይ አይጎረብጠውምና። 

የለማው ይሁን የአብይ መንፈስ እኮ የዞግ ድርጅት ያበቀለው ነው ግን ሰዋዊ ተፈጥሯዊ የመሆን አቅሙ ከፍ አለና ፍቅርን በገፍ ተንበርክኮ ዛቀ። ታሪክ ያነበበው የተረጎመው ያመሳጠረው የክህሎት ልህቅና ነው ያተዬው። ለዚህን ነው ብጹዕ አባታችን አቡን ዮሖንስ የስሜን ጎንደር አገር ስብከት ሊቀ ጳጳስ „የሆነው ሁሉ ከትርጉም በላይ ነው“ ያሉት።   

እንደ ግራ ፍልስፍና አቅምን የሚፈራ ከቶም የለም። የግራ ርዕዮቱ ኢንትሪግ ነው። ግራ ማብቀል ተፈጥሮው አይደለም፤ መተካት ሳይሆን ቁምነገሩ ቡቃያን መንቀል እና ማምከን ነው። ጠቃሚ የሚባለው ነገር ግራ ሰውን አምልኮ ለዘላለም መኖር ነው። በአድማ የሚፈራውን አቅም ማሳዳድ እና ማዋከብ ነው። እንዲያም ሲል መጨረስ ነው።

ይህን በዚህ ዘመን ታድጎናል። ጥበቃ ክብር ምስጋና ማድረግ ደግሞ ከእኛ ይጠበቃል። እግዚአብሄር ኢትዮጵያን እንዴት እንደሚወዳት ተመልከቸበታለሁኝ። ከብዙ የማንገፋው ማዕት ነው የወጣነው። ተመስገን!

ይህን የሰማይ ዱብ ዕዳ አውርዶ ሁሉንም ልኩን አሳያዘው። ጀርመኖችን ያዳነ አምላክ ነው ኢትዮጵያንም የተማለዳት። ጀርመን ይህን ሁሉ አቅም ባለቤት ያደረገው ከግራ ርዕዮት ጋር ንከኪ ያላቸውን ፍልስፍናዎችን ሁሉ አክ እንትፍ በማለቱ ነው።

ከእንግዲህ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቃን አክተሮች ለዘለቄታ ህልመኝነት ትውልዱን የማያበክኑበት ዘመን ማክተሚያው ላይ ነን። ዘመናች እጅግ ውብ፤ እጅግ የሚማርክ፤ እጅግም የሚጓጓ ነው። ዘመናችን ሰዋዊነት፤ ተፈጠሯዊነት የሰፈነበት ነገን ለወጣቱ በመልካም ሞራል ለመገንባት የተሰናዳ ነው።

እርግጥ ነው አብሶ ኦሮምያ ላይ ወጣቶች ዘመናቸውን እራሱ እዬወጉት፤ የግራ ርዕዮት ሰለባ ሆነው ምርኩዝ ያዢ መሆን አምሯቸው ዕድላቸውን አቃጥለው እዬሞቁት ነው። ይህ ተራው ወጣት ብቻ ሳይሆን ኦዴፓ ውስጥ ያሉ ኦነግውያንም ያን ቅርስ ውርስ አድርገው አፍራሽነትን እያስከነዱት ነው። ይህ መቼም አለመታደል ነው። 

በዚህ የሚያኮራኝ የአማራ ወጣት ነው። የአማራ ወጣት ከልቡ ለውጡን ተቀብሎታል። ዛሬም የእሱ፤ ነገም የእሱ ስለመሆኑ ጠንቅቆ ገብቶታል። ስለሆነም ለውጡን የእኔ ብሎ ተቀብሎታል። የራሱን ቤት ለማቃጠል አልተባባረም የአማራ ወጣት። እርግጥ ነው ኦነግውያን ያሰሉትን ጥልፍ የሚያሳምር ጉዳይ ብአዴን ላይ የለም ማለት ግን አልችልም።

ሰፊው የአማራ ወጣት ይሁን ህዝብ ግን የረዳው ብልህነቱን አስመስክሯል። ይህን ልዩ የዘመን ስጦታ አማራ እንዲያጣጥመው ያደረገው ህብረ ብሄር በሚባል ፓርቲ በዘበኝነት ብቻ መኖሩ ነው። ህብረ ብሄር በሚባለው የግራ ፍልስፍና የ አማራ ሊቅ ወጥቶበት ስለማያውቅ፤ አማራ ተረ እግረኛ ስለነበር የግራ አራማጅ ፈላስሞች ሊቀ ሊቃውንታት ሁሉ የሌላ ብሄረሰብ አባሎች ስለሆኑ አሁን አማራ መሬት ላይ ለማንኮር አልታደሉም። አማራም ፈጣሪ ተማለደው።

የኦሮሞ ወጣቶች እና ታዳጊ ወጣቶች ግን የራሱ አያቶች ስለሆኑ የድሮም የዛሬው ሊሂቃኑ የራሳቸውን ጊዜ አቃጥለው ትውልድን አምክነው አሁንም ሦስተኛውን ትውልድ እንንዳህ ባዮች ናቸው። የሚገርመው ተቀብለዋቸዋልም። ትግራይም ላይ ያለው ተፎካካሪ ይሁን ራሱ ህውሃት ይኸው ነው።

መተካካት ብሎ ነገር የለም ነው በግራ ፖለቲካ ፍልስፍና። ሁልጊዜ ቁንጮነት ግን በዓይን ቅድንድብነት ነው። ጡረታ የሚባል በግራ ፖለቲካ የለም። ለአዛውንቶች ማህበረ ፖለቲካ የዘውድ ሥርዓት ነው። የዘውድ ሥርዓት ይቃወማሉ እነሱ ግን ዘውዳቸውን ከደፉ 40/20 ዓመት ሞላቸው። ዕድሜውን ቢሰጣቸውም ይቀጥላሉ 50/60 እያሉ … ሳምሶናዊነት እና ገብርዲንን የሙጥኝ ብለው ይቀጥላሉ። 

አማካሪነት እኮ ትልቅ የአደራ አንኳር ጉዳይ ነበር። ወይ ደግሞ በሰብዕዊ መብት ዙሪያ መትጋት። የፖለቲካ ስልጣን ግን የአዲሳዊነትን ፈጠራን ይጠይቃል እንጂ የኩሬ ውሃን አይማጸንም።

አብሶ ለአብይ ፍልስፍና ጋር ልቆ ወጥቶ ተፎካካሪ መሆን ጋዳ ነው - ዛሬ ላይ። አይችሉትም። ዕድሜውን ሙሉ የተሰናዳ መንፈስ እንዲህ በኩሬ ውሃ ዋና የሚረታ ይሆናል ውቅያኖሱ የመሆን አቅም ተብሎ አይታሰብም። ዛሬ ሉላዊ ዓለም ዲጅታል ዘመን ነው። ይህም ራሱ ሌለው ፈታኝ ጉዳይ ነው። አንድም የፖለቲካ ሊሂቅ የዚህ ባለሙያ አይደለም። ዶር አብይ አህመድ ግን ናቸው።

አንድም የፖለቲካ ሊሂቅ በተባበሩት መንግስታት የግዴታ ማዕቀፍ ውስጥ ቤተኛ የሆነ የለም ጠ/ሚር አብይ ግን ናቸው፤ አንድም የፖለቲካ ሊሂቅ ከመከላከያ ሳይንስ ጋር ትውውቅ የለውም ዶር አብይ አህመድ ግን ከተራ ውትድርና እስከ ከፍተኛ መኮነንንት ተሳትፈዋል። አንድም ሊሂቅ የመከለከያ የደህነነት ባለሙያ አይደለም እሳቸው ግን መሥራችም አደራጅም መሪም ናቸው። እንዲያውም የዲጅታል አባት ነው የሚባሉት።

ስለዚህ ይህን አቅም ጥሶ ለማለፍ አቅበት ነው። ለዚህ ነው ግርግሩም፤ መፈንቅሉም፤ ግድያውም ተሰልቶ የነበረው። አስቀድሞም አቅማቸው ተፈርቶ ነው በተናጠል ያ ሁሉ ወጀብ የባጀው። ቢሮውን ማደራጀት ያልቻለው ሁሉ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል የባጀው።

                           ወዘተረፈ ችግር ላለባት ኢትዮጵያ።

የአብይ መንፈስ እኮ ሳይንቲስት ነው ለብዙ ልብ ላለው አምክንዮ።  ቦረናን ዋልድባን ገዳም ያለመ … የሴቶችን የህሊና ብቃት በጥልቅት የተመራመረ … እኔ የአዬር ላይ የፖለቲካ ድርጅት ቢኖረኝ  በአዋጅ አፈርሰው ነበር። 

ምክንያቱም ህልሜ እንዲህ ዓይነት መሪ ኢትዮጵያ እንዲኖራት ነበር። ካገኘች ስለምን እደክማለሁኝ። ስለምንስ የትውልድ መንፈስ ወጥ በሆነ ሁኔታ አቅሙን ለአገሩ ማዋል ሲገባ ይበተናል፤ ይባክናል?ኦነግውያን ተልዕኮ ስላላቸው ነው እንደ ባላንጣ የሚያዮዋት ኢትዮጵያን ነውና፤ ኢትዮጵያን ያለ ግን መሪውን አግኝቷል። 

ለዛ አጥር ቅጥር አቅም መሆን እንጂ የምን ሌላ ምህንድስና ያሰመኛል፤ ቢኖርማ ኖሮ እስካሁን አንድ ሆነው ስንት ታምር በተፈጠረ፤ አብረው መሰንበት እንኳን የማይችሉ ናቸው። ተጣመርን፤ ተቀላቀልን አጨብጭቡልን ሞገዱ ፉጭቱ … ፊርማው ሳይደርቅ ደግሞ ተበተን አውግዙልን …

ይህን ሁሉ ነገር ወጣቱ በአስተውሎት ማዬት፤ ማጥናት፤ መወሰን ይኖርበታል። ለናሙና የሚቀርብ ህብረት፤ ቅንጅት ጥምረት የለም። አመራር ማለት ይህን አጽንቶ ለድል ማብቃት እንጂ እንዳልቦካ እንጀራ በዬጊዜው መፍረክረክ አይደለም። እንምራ አገር የሚባለው በዚህ ሙርቅርቅ አቅም ነው። 

ለአጃቢነት ለመናጆ በስም የተፈጠሩ እንኳን ከእወጃቸው ወዲያ የሉም አሁን አንድ አማራ የለም፤ አረንጓዴ ፓርቲ የለም፤ የአማራ የወጣቶች ክንፍ የለም … የዚህ ሁሉ ችግሩ የማደራጀት ክህሎት አቅም ማነስ ነው። የመሪነት አቅም ተስጦዖ ምክንትም ነው።

·       ጨለማምን የሚነፍቅ ዲያቢሎስ ብቻ ነው።

የአማራ ወጣት ያ የጨለማ ጊዜ አይናፍቀውም። የአማራ ወጣት /ታዳጊ ወጣት ዘሩ የመከነበትን ድቅድቅ ዘመን ሽው አይለውም። ፈጽሞ! የአማራ ወጣት / ታዲጊ ወጣት የተገፋበት፤ የተጨፈጨፈበት፤ የተገለለበት ዘመን ዳግም እንዳይመጣ በርትቶ መሪዎቹን ደግፏል። ከውስጡ ተቀብሏቸዋል።

በአማራ ተጋድሎ የሙዚዬም አከባበር ዕለት ጥላው ላይ የዶር ለማ መገርሳ ፎቶ ነበር። ይህ መቼም የታምር ያህል ነው ለእኔ። ይህ የሚያሳዬን የአማራ ወጣት እና ሌላው ያለውን የሰፋ የህሊና የማስተዋል የአቅም ልዩነት ነው። አቅም የለውን ብጡል የትም ቦታ አማራ ይንፍቃል። እንግዲውስ አሁንም አማራ ይፈናቃላል፤ ይገደላል፤ በፎቅ ይወረወራል።

ልብ ህሊና ያለው አማራ ግን ያ ስለምን መሆኑን ተረድቶታል። ቅኔነተ ማለት ይህ የአስተውሎት ድንግልና ነው። ስለሆነም ለማን መሪዬ ብሏል። ቀደም ባለው ጊዜ በቀለ ገርባ መሬዬ ብሎ እንደ ወጣው ሁሉ። አብይን ዞቢዞ…  መላዕክ ነው የሚላቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድን። በሐምሌው ዝምታ ጭንቅ ላይ ነበረች ጎንደር፤ ምስላቸው ሲታይ ደህንነታቸው ሲደመጥም በልዩ ሁኔታ ፈጣሪ ተመስግኖበታል። ሻማም በዬቤቱ ተበርቶበታል። 

የሚገርመው አሁን ከሆነ የመተማ ደንበር ጉዳይ፤ የኮ/ ደመቀ ዘውዱ ከነቤተሰቡ የደምስሱት ጉዳይ እና የማዳን ተልዕኮው ከተሰማ ወዲህ ዓይናሞራቸው ተገልጦ አቶ ደመቀ መኮነን ጎንደርን አዘውትረዋል። ይህ መልካም ነገር ነው። „ነገር በዓይን ይገባል“ ይላሉ ጎንደሮች ሲተርቱ።

አማራነት መገለጫው ህብርነቱን ማዬት ማስተዋል ከተቻለ ይህ ዘመን ብቻ ቁሞ አስተምሯል ወደ 13ኛው ምዕተ ዘመን ሳንሄድ። ቅዱስ ያሬድ፤ ፈላስማው ዘረያዕቆብን አላስቀምጥ አለሳቆም ያለ እትብታቸው የተቀበረበት መሬት በአንድም በሌላም ሲያሳድዳቸው እጁን ዘርግቶ የተቀበለው የአማራ ቀዬ ጎንደር ነው።

·       ግርም የሚለኝ።

አሁን ዶር ለማ መገርሳ ምናቸው ይጠላል? ለመሆኑ ይጠገባሉን? እሳቸውን በማወክ፤ እሳቸውን በሸታ ላይ በመጣል የኦሮሞ ወጣቶችን ብክነት ያለሙ ሊሂቃን ሁሉ ቀን አብረው ሲገነቡ ውለው ማታ ሲንዱ ያድራሉ። በመንፈስ ለማን ሲያሳድዱ። ነብይ በአገሩ አይከበርም እና። 

ጎንደር ደግሞ ናልኝ ለማ ሆይ አለ! እንደ ፈላስማው ዘርዕያቆብ፤ እንደ እጬጌው ቅዱስ ያሬድ። ኦሮምያ ላይ በምንም ሁኔታ ከኦነግ ዓርማ ውጪ የለማ መንፈስን የያዘ ፎቶ አይወጣም፤ ጎንደር ግን የተጋድሎውን መዘክር ሲያስመርቅ አደረገው እና ስርክራኪውን ሁሉ አሸነፈው። አዬ ጎንደር የልብ አድርስ እኮ ነው!

የኦሮሞ ወጣቶች ነብይ በአገሩ አይከበር ሆኖባቸው፤ ዶር አብይ አህመድን እና የዶር ለማ መገርሳን አመራር ለማሳጣት ነበር ያን ትዕይነት ህዝብ ያደረጉት። "ኦነግ ትጥቅ አይፈታም" ብሎ እሰከ መወጣት ያደረሳቸው። 

አማራ መሬት ግን ይህ የለም። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ኤርትራ የነበረው ከብአዴን ጋር ነው በማስተዋል ነው የተዋህደው። ካለምንም ቅደመ ሁኔታ። የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር አዋራም አርበኛ ዘመነ ካሴም ተዋህዷል። ጉደኛ ወጣት ነው።

አደብ እና አማራ የተመሳጠሩበት ዘመን ትናንት ብቻ ሳይሆን ዛሬም እዬታዬ ነው። አማራነት መንፈስ ነው ሲሉ አንድ ሊሂቅ አዳምጫለሁኝ። ዕውነትም ነው። ዘመኑ የመጣው ለፍትህ፤ ለእኩልነት፤ ለአዲስ ሰዋዊ እና ተፈጥሯዊ ሥርዓት ግንባታ ከሆነ ስለምን የሰው ሃይል፤ ስለምን ገንዘብ፤ ስለምን መንፈስ ይባክናል?
አብሶ ወጣቱ ለራሱ በራሱ ትግል ያመጣውን ለውጥ የመጠበቅ፤ የመንከባከብ ግዴታ አለበት።

ለውጡ ቅርበቱ ለወጣቱ ነው። ለዚህም ነው አዛውንት የፖለቲካ ሊሂቃን እያወኩት ያለው። ምክንያቱም ሥርዓት ከተዘረጋ ነግሦ ቁንጮ ሆኖ ለዘላለም መኖር ያከትማል እና። አቅም እንጂ ሥም እና ዝና ምንም ስለመሆናቸው ሥርዓቱ ከተዘረጋ በራሱ ጊዜ መቅኖ ያሳጣዋል።

ይህ ለውጥ ልባም ነው። ይህ ለውጥ ልባም የሆነበት መሰረታዊ ምክንያት የነበረው ኢሰብዐዊ ሥርዓት በዓዋጅ ሳይሆን፤ በግርግር፤ በእወቁልኝ የሞገድ ፕሮፓጋድንዳ ሳይሆን በስልት ነው ንዶ ቀፎውን ነው ያስቀረው። ስለምን? መውጫ መግቢያውን የሚያውቁት የራሱ አካል ውስጥ የወጡ ፈርጦች ስለሚመሩት።

ብዙ ሰዎች የህውሃት ማንፌሰቶ ማህበርተኞችን ማሰር ቀድሞ መኖር ነበረበት የሚሉ አልጠፉም። ይህ ለዶር ለማ መገርሳ እና ለዶር አብይ አህመድ ጠፈቷቸው አይደለም። ይህን ማድረግ በሚችሉበት ወቅት ለነጻነት እታገላለሁ የሚለው ሁሉ ተጨማሪ የቤት ሥራ እና ጫና በመፍጠር መዋቅር የመናድ ተግባር ነው የፈጸመው። አስቸኳይ ጊዜውን ጥሶ ነቀምት ላይ ስብሰባ መጥራት ኦፌኮን ያቀደው ያደረገውም ጉዳይ ነበር።

አቅም አግኝቶ ለውጡ አትኩሮቱ እንዳይሰበሰብ እና ከዋናው ሥረ ግንድ መከራ ላይ እንዳያተኩር ለነፃነት፤ ለዴሚክራሲ እታገላለሁ የሚለው ሚዲያ ሁሉ፤ አለ የተባለው ተንታኝ እና ጸሐፊ፤ ጋዜጠኛ ሁሉ ሞገዱን የለቀቀው በእነሱ ላይ ነበር። በትክክል ግራው ይፈልግ በነበረው መስመር ቀጥ ብሎ ገብቶ ነው እነሱን ጠልፎ ለመጣል የታገለው።

"የሽግግር መንግሥት፤ የተጽዕኖ ፈጣሪ መንግሥት፤ ቃል ብቻውን ምንም አያደርግም፡ ወዘተ …  ስለዚህ ለእነዚህ የዘመን ፈርጦች ንድፉን በስክነት ለማካሄድ አቅም ያዋጣላቸው የለም። ለእኛ ደግፈናል ነው ለምዕራባውያን ተስፋ ቢስ ለውጥ ነው ነበር የጓዳው ምክክር ራሱ የነበረው። 

እራሱ የኢትዮ ኤርትራ ስምንነት አልተፈለገም ነበር። አይሳካምም ተብሎ ነበር።

የባድመ ዕድምታ በሥርጉተ ዕይታ። 

እስረኞችም ለመያዦ እዛ ሲኦል ቢቆዬ ይፈለግ ነበር። ገማናችን እኮ ብዙ ነው። ቀድሞ ነገር በሲቢሉም በወታደራዊ ዘርፍም የደህንነት ሊሂቃን በሙሴነት ወደ ፊት ሲመጡ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ታሪካዊ ወቅትም ነው። 

ይህ ዕድል በተለያዬ ጊዜ እንደጠቀስኩት ወርቃማ ጊዜ ነው። ዋናውን ግንድ ለመጣል ሥሩን፤ ቅርንጫፎችን ማስወገድ፤ ከዛ ግንዱ ውሃ እና የጸሀይ ብርሃን ብድር መሄድ የማይችልበትን ሁኔታ መዝጋት ነበር ምህንድስናው።

ይህ ደግሞ በትልቁ የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ጉዞ ከአናት ጉዳይ መጀመሩን ልብ አላልነውም እንጂ ትልቁን ድርሻ ተወጥቶታል። ኤርትራ ጋር ስምምነት ባይኖር ለውጡ የጀርባ አጥንት አይኖረውም ነበር። እጥፍ ድል ነበር ያ ያቀዳጀው ስምምነቱ። 

ኤርትራ ያስጠጋቻቸውም ተፎካካሪ/ ተቃዋሚ/ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ሁሉ መሪ ተገኝቷል ብትፈልጉ ትጣቅችሁን ፈታችሁ አገራችሁ ግቡ ባትፈልጉ ትጥቃችሁን ፈታችሁ ከዚህ ተቀመጡ ብላ ወሰነች እትጌ ኤርትራ። ይህ ከብልህነትም በላይ ሥርዎ ጥበብ ነው። እራሱ ግንኙነቱ የግብር ይውጣ ሳይሆን በንጹህ መንፈስ ታቅዶ ልብ የተሸለመው ነው። ትወልድን የማበርከት ተግባር ነው የተከወነው።

በሌላ በኩል የታላቋ ትግራይ ትግርኝ መንፈስ ጥግ ሲያጣ ባጣ ቆዬኝ ኤርትራ አድርጎ ወደዛ የሚደረገውን ሙከራ አከርካሪው እንዳይነሳ ሆኖ ተመታ - ፈለሰም፤ 

ሌላው የአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ ለአፍሪካውያን አጀንዳ አልነበረምይህም በጥምርት በጥሞና ባሊህ ተባለ። የአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ጭንቅላት አጀንዳ የነበረው እኔ እንደማስታውስው በደርግ ጊዜ ነበር። በሚገባ የኢሠፓ ካድሬዎች በመደበኛም ይወያዩበት ነበር። ፖለቲካ ት/ቤትም በዘመኑ ባህሬ ክፍለ ጊዜ ይሰጥ ነበር።፡በዘመነ ኢህዴግ ግን ጣፊያ ነበር አጀንዳው።

  
ሌላም ዕጹብ ድንቅ ጉዳይ አለ የሱማሌ ጉዳይ። ጅጅጋ ለብዙ ነገር ሊንክ ነው። ሊንክነቱ ለአውንታዊ ከሆነ ለለውጡ ልብ ነው። አሉታዊነቱ ቀጥሎ ቢሆን ግን ለውጡ ተስፋ ቢስ ይሆን ነበር። እናም ባልተለመደ ሁኔታ ነው የአቶ ሙስጦፋ ዑመር ወደ ስልጣን መምጣት የተከወነው እዮራዊ ታምራቱ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የሚመራት መመንፈስ ስጦታው፤ ልቅናው ክህሎቱ የአንድ የትውልድ ዘመን ያህል ነው። 

በዚህ የህውሃታዊያን ሴራ ብቻ ሳይሆን የኦነግውያን፤ የጃውርውያን ህልመኞችም አንገት የቆረጠ እርምጃ ነበር። ያልታሰበ ዱብዳው መጠነ ሰፊ ነው። በሁሉም ዘርፍ።

እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስተር ሚኒስተሯ  ወደ ፊት ሲመጡ ጫጫታ ነበር። ጫጫታው ከህውሃታዊ የህዋስ ጎራ ነበር። ቃለ ምልልሱም ለዛ ነበር ሆን ተብሎ የተከወነው። ውስጣቸውን ለወያኔ ሃርነት አኩራፊዎች ለማሳዬት እና ለማሳጣትም ነበር። በሌላ በኩል ከእጃችን ወጣ ዓይነትም ነበር። ልባሞቹ ግን አንድ ያለሙት ጉዳይ መኖሩን አሁን አሳይተውናል።

ርትህ በሚል እርእስ ከክፍል አንድ እስከ 7 ይመስለኛል የዶር አብይ አህመድ የመጨረሻው የክልል ውይይታቸው አፋር  ነበር፤ እና የፖሊሲ አቅጣጫ ያመላከተ ውይይት ስለነበር፤ በሌላ በኩልም አፋር ላይ ሳይሆን ትግራይ ላይ የሚካሄድ ይመስል ነበር የታሳታፊዎች ዕድምታ። ልክ ቤንሻንጉል ጉምዝ ያዬሁት መንፈስ ነበር ካዛም ያዬሁት። ስለዚህም በሰፊ አትኩሮት የጉብኝታቸውን ማጠቃለያ ነበር የሰራሁት።

እናም ጠለቅ ባለ ሁኔታ ነበር ጉዳዩን ያዬሁት። ያ ቦታ ጊዜ የሚጠብቅ ፈንጅ የተጠመደበት ነበር። አሁን ሰሞኑን መልክ ለማሳያዝ ጉዞ ተጀምሯል። ገዢ መሬቱን የአብይ መንፈስ ተቆጣጥሮታል እንደ ማለት። እልልታ በሐሴት። ዕጹብ ድንቅም ነው። ሻታ የሚዞሩ ስርክራኪዎችም ነበሩበት ሚዲያ ላይ እማስተውላቸው። እነሱም ልካቸውን አግኝተዋል። ቀሪው ቤንሻንጉል እና ሀረሬ ነው። ሀረሬ ላይ ኦነግውያን፤ ቤንሻጉል ላይ ኦነግውያን እና ህውሃታውያን የመንፈስ ተከል አላቸው እሱም የጊዜ ጉዳይ ነው።

·       ጥበብን የናፈቀው ማህበረሰብ ሊያደርገው የሚገባው።

ይህ የአመራር ጥበብ በዬትኛውም ዘመን ያልታዬ /ለ እኛ ትውልድ/፤ ያልነበረ አዲስ ውልደት አዲስ መንገድ ነው። አዲስ ቅዬሳ ነው። ምህንድስናው ልዩ ነው። ይመስጣል፤ ጥሞናንም ይመግባል። ይህ ዘመን የትውልዱ መባከን ለሚያርመጠምጥን እንደ ገና የመወለድ  Renaissance ያህል ነው።

የዚህ ለውጥ ኪናዊ ጥበቡ ብዙ ቤተሰብ ሳትይጎዳ መርዙን እያጣራ፤ የተበከለውን ብቻ ነቅሎ ማውጣት ነው። የእኛ ስለሆኑ ብቻ ነው የማይገባን እንጂ የሌላ አገር ዜጋ ቢሆን እያንዳንዱ ወር መጽሐፍ ያሳትም ነበር። ይህን ሮል ሞዴል ነው ወጣቱ ሊከተል፤ የእኔ ሊለው የሚገባ። ለወጣቱ እያንዳንዱ ቀን ተቋም ነው። እያንዳንዱ ንግግር የትምህርት ሌሰን ነው። ወጣቶች በንግግሮች ላይ ሊወያዩበት ሊመክሩበት ይገባል።

የፖለቲካ ልህቅና የአማራር ስልት፤ ክህሎት እና ጥበብ ኦን ላይን ት/ቤት ተከፍቶለታል - ለወጣቱ። የሚገርመው ኢትዮጵያ ያታዳጊ ወጣቶች አገር ሆና ነው እኔ እማዬት። ይህ ዕድል አይደለም ጃፓናኖች ጀርመኖችም አላገኙትም። ኢትዮጵያ ግን አሁን ያለችበት ሁኔታ እጅግ የሚገርም ነው አዲሱ ተተኪ ትውልድ ከ16 ዓመት በታች ነው። እናም ተስፋዋ ብዙ ነው። ሰው እኮ ሃብት ነው። ይህን የሰው ሃብት የሚፈራው የግራ ፖለቲካ ብቻ ነው።

ስለምን? አዲሱ ቀንበጥ ትውልድ የፖለቲካ ሥልጣን መንበሩን እይዛለሁ እንዳይል ስለሚሰጋ። አሁን ያሉት የለውጥ ሐዋርያት ግን የሚተጉት ለዛ ነው። ስለዚህ ለእሱ እዬሰሩ ያሉት ወጣት ሊሂቃን ሳያወላዳ፤ ሳያመናታ፤ መንፈሱን ሳይበትን ወጣቱ ልቡን ህሊናውም መሸለም አለበት። 

የሚሸልመው ለራሱ ፍላጎት ማስፈጸሚያ መዋለ መንፈስን በማዋጣት ነው። ወጣቱ ራሱን ተጻሮ መቆም አይኖርበትም። እነዚህ ፈርጦች ተተክሎ ተቆልፎ የኖረውን የሥልጣን ጥመኝነት ዘመን ማክተሚያ መሰረት እዬጣሉለት ነው - ብልሆቹ። ነገን እያሳመሩለት እያበጁለት ነው። እናም ይህ የሚጠቅመው ለራሱ ለወጣቱ እና ለታዳጊ ወጣቶች ነው።  

የአማራ ወጣቶች አንድነት፤ ህብረ ብሄር በሚባሉ ድርጅቶች በጠበንጃ ያዥነት እና አቅም በመሆን ሁሉንም ሆነዋል ለ50 ዓመት ለዘለቀ ተቀቀልዋል። አሁን የህብረ ብሄር የግራ ፖለቲካ አራማጆች አገር ገብተዋል። ደግነቱ መሪዎቹ አማራዎች ባለመሆናቸው አሁን አማራ መሬት ላይ እንደ ኦነግ የማወክ ዕጣ ፈንታቸው ዝግ ነው። መስመር አያገኙም። በዚህም የአብይ ሌጋሲ እድለኛ ሆኗል።

ስለዚህ ነው አማራ በአሃቲ መንፈስ ለውጡን የደገፈ፤ ከለውጡ ጎን የቆመው መሰረታዊ ምክንያቱ ይህ ነው። ለዚህስ እንኳንም በግራው ፖለቲካ አራማጆች አማራ ሊቀ ሊሂቃን እንዳይወጡ መታገቱ በስውር አሁን ስለጠቀመ ተመስገን ብያለሁኝ። ለማወክ አንድ ቀንጣ ነፍስ ወይፈናዊ መንፈስ ብቻ ይበቃል።  

አሁን ባለው የአማራ ብሄርተኝነት ገዳይም የአብይ ካቢኔ ከአለፈው ወር ጀምሮ እዬሄደበት ያለው መንገዱ ወዝ አለው። የስሜን አሜሪካ ጉዞ እና ዕድምታው ያልተገባ ዕውቅና ሊያሰገኝ ያቻለውን ትርፍ የልቤ ያለው ይመስላል የአብይ ካቢኔ። ያን ጊዜ ኦሮሞን በድርጅቶቹ በአክቲቢስቶቹ አክብሮ አማራ ግን  በኢትዮጵያዊነት ብቻ ቀጥል ነበር ትልሙ። ትልቅ የታሪክ ግድፈት ነበረበት። 

ገደል የፈጹሙ የአማራ አክቲቢስቶች ጸሐፍት ጋዜጠኞችን ያገለለ ነበር እርምጃው። ጉዞው አስኳሉን ስቶ ነበር መጪ ያለው። እኔም ብዙ አቤቱታ አቅርቤያለሁኝ። መሬት ላይ ያለውን ነገር ከዴያስፖራው ጋር ለማዋህድ ስልቱም ሆነ ጥበቡ የተመጣጠን አልነበረም። በ እጅጉ የተዛባ ክፍተት ነበረው። 

በዛ ክፍተት ነው የአብይን መንፈስ ያልተቀበለው ብአዴን ውስጥ ተሸፍኖ የተቀመጠው ረቂቅ አቶ ጃዋር መሃመድ ኢትዮጵያ ሲገባ ሌላ ያፈነገጠ መስመር ለመፍጠር ታልሞ የነበረው። አብይ የ አማራን የህለውና ተጋድሎ ገናና መንፈሱ የእኔ ብሎት ስላልነበር አቅሙን ለሌላ ለመሸለም ዕድል እራሱ የአብይ መንፈስ ሸልሞት ነበር። እራሱን ተጻሮ ነው የቆመው የለማ ሆነ የአብይ መንፈስ። 

ሁለተኛው የሰላማዊ ሰልፉ ዕድምታም ይህ ነበር። የሚያቆስል እርምጃ ነበር የተወሰደው። የአማራ የህልውና የማንነት ታገድሎ ባለቤት እያለው በስማ በለው ለሌላ ዝና ክብር እንዲያደገድግ መደረጉ ህምም ነበር። ያ ራሱን የገበረ ተጋድሎ ለስጦታ መቅረብ በፍጹም አልነበረበትም። ማስተዋል ስንጥቅ ሲፈጠር ያማል። 

የሆነ ሆኖ አሁን የአብይ ካቤን ልክ እንደ "ጣና ኬኛ" አንቴናውን ያዞረበት አገባብ ብልህነቱን ማመሳጠር ብቻ ሳይሆን የለውጡን አውራ መንፈስ ህሊና ለማግኘት መንገድ እንደ ጀመረ ያመለክታል። እኔም አብዝቼ ጩኼበታለሁኝ። መሬት ላይ ካለው እውነት ያፈነገጠ ጉዞ ነበር ለመጓዝ ያለመው የአብይ ካቢኔ በስሜን አሜሪካ ጉዞው።

አሁን የአብይ መንፈስ ወደ አማራ ሲያደላ ለዚህም ነው ትግራይ ላይ አዲስ የአማራ እና የትግራይ የሊሂቃን የሰላም ኮንፈረንስ የሚል በዩንቨርሰቲዎች የተጀመረው። 

የሆነ ሆኖ ተጠቃሚው ተጎጁ ያውቀዋል እና ፍሬውን የምናዬው ይሆናል፤ የዘር ፍሬዬን አንኮላሹልኝ፤ ባዕቴ የተመሰረተበትን በነዳጅ አቃጣሉልኝ፤ ወረራው በእርግጫ ይቀጥልልኝ፤ ልጆቼን ጥፍራቸውን አውልቁልኝ፤ ዘራቸውን አፍልሱልኝ፤ ወረራው አልበቃም እና በመጠነ ሰፊ እስኪ ወደ አባጃሌም ከች ብሎልኝ በማለት አማራ እንደማይደራደር ይታዋቃል። እኛም አንተኛም። 

ምኑ ሲናፍቅ ይሆን የዛ የጨለማ 27 ዓመት ድቅድቅ። ለአማራ ጠላት ራስ እግሩ እንዲያበቅል የተደረገበት፤ ያ አልበቃ ብሎ አሁን ቅማንት እያሉ የሚያምሱትን አወያይ ነን ያሉት ይልቅ ቢዳኙት መልካም ነው።፡

ዘራፊነት ወራሪነት አሳዳጅነት ጠያፍ መሆኑ ፈርሃ እግዚአብሄር// ፈርሃ አላህ ላለው ህዝብ መንገርም አስፈላጊ አይደለም። ቂም ትውልድ ባያበረክትም ነገር ግን ተኝተህ በለኝ የማለት ድልድይነት ግን አክትሟል። „በሞኝ ክንድ ዘንዶ ተልክቶበት“ አይቷል እና አማራ። 

አማራ ለራሱ የፖለቲካ ልቅና መትጋት ይኖርበታል። መወሰንን በስማ በለው ሳይሆን እራሱ በጥበቡ በቅኔነቱ ልክ ቦታውን ይዞ መከውን ይገባዋል። አባቶቹም ያደረጉት ይህንኑ ነው። 

አማራ መረማመጃነቱን መቀበር ይኖርበታል። አማራ ሴት ሊሂቅ፤ አማራ ወጣት ሊሂቅ፤ አማራ ጎልማሳ ሊሂቃኑን ዓይኑ እንዲይ የሚጋረጥበትን የጉሮሮ አጥንት ሁሉ አስወግዶ፤ ራሱን በራሱ አንጥሮ ማውጣት ይኖርበታል። በዚህ ድርድር የለም። ኢትዮጵያም የአማራ ሊሂቅ ንጥረ ነገር ጥሪኝ ያስፈልጋታል። 27 ዓመት ተቀልዷል። አሁን በቃ ማለት ይገባል ልግጫውን። የዶር ገዱ አንዳርጋቸው በዚህ ዘርፍ ያላቸውን ስስ ሌጋሲ አማራ መቀበል አይገባውም። 

አማራ ልብ ስላለው ማንን በማቅረብ ለማን አቅም ማዋጣት እንዳለበት ልብ መካሪው አምላክ ይነግራዋል። መከራን ለኖረበት ህዝብ መካሪም፤ ወንጌላዊውም ቁራናዊም አያስፈልገውም። ሃይማኖቶችም ድሮም ነበሩ፤ ምስላቸው ነበር የተቀመጠው። በዛ ድቅድቅ የጨለማ ዘመን ወንጌልን ቁራን ያሉማ ለካቴና ነው የተማገዱት።

ስለሆነም ጥቅሙን የሚጻረረው ተጠቃሚው የኦሮሞ ወጣት ያወጣኛል ባለው መንገድ መጪ ማለት ይቻላል፤ አማራ ግን ጥቅሙን የሚያስከብረለት ዘመን ዋዜማ ላይ ስለሚገኝ ለውጡን የመጠበቅ፤ የእኔ የማለት፤ የመንከባከብ፤ ዘብ የመቆም ግዴታው ነው። 

ይህ ዘመን ለአማራ ልጅ የማይደራደረበት ምርጫው ነው። ከበላዬ ላይ ተቀምጠህ ምራኝንም ትቶ ራሱ ገብቶ ጥቅሙን ማስከበር ይኖርበታል። ወሳኝ ሃይልነቱን ማሳዬት ይኖርበታል። ሥልጣን ቧልት አይደለም። የህልውና ጉዳይ ነው። 

ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ዴሲ ላይ የተናገሩትን ሞኘዎትን ይፈለጉ ይበላቸው - አማራ። ለዚህ ነው አዴፓ ለማለት እኔ እማልደፈረው ብአዴንም እምለው። ኦህዴድ ግን ኦዴፓ ቢባል የ7 ወሩ ትንታግ ተግባሩ መስካሪ ነው። አጀንዳ ያጡት የራሱ ሊሂቃን ስለሚያውኩት ነው እንጂ አብሶ የለማ መንፈስ ቀና እና ፍቅር ናት። 

ይልቅ በብሄራዊ መሪነት ብቁ የሆኑ እና ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ መሪዎቹ በሁለገብ ብቃታቸው ሥመ ጥር የሆኑ ናቸው። ኢትዮጵያ ትጥማቸዋለች። ሲቀበሏትም ለማምሻ ብለው አይደለም። ከውስጣቸውም ነው። ለአማራ የማንነት ተጋድሎ ዕውቅናው ውጥን ቢሆንም አጠቃላይ አገራዊ በሆነው ፋይዳው ግን አቻ የሌለው አቅም ነው ያለው የአብይ ሌጋሲ ከሙሉ የስልት የጥበብ አምክንዮ ጋር።

ለዚህም ነው ጎንደሬዋ አማራዋ ሥርጉትሻ ዛሬ ሳይሆን ተዛሬ ዓመት ጀምሮ ተግታ ስትታገል የኖረችው። ብስል እና ጥሬ፤ ጮርቃ እና ለጋ፤ ፍሬ እና አንክርዳድ የመለዬት ሰው የመሆን ጉዳይ ነበርና። 

ህዳር እና ታህሳስን ስናሰብ ያለፈውን ዓመት ማለቴ ነው በብዕረ ሥርጉተ በሳታናው ብራና እንዲህ ነበር፤ ለታሪክ ነው እዚህ ግንቦት 01.2018 የተለጠፈው እንጂ የተጣፈው በ2017 ህዳር እና ታህሳስ ላይ ነው፤ ለዛውም ጠ/ሚር አብይ አህመድ በቅጡ ሥማቸው ጎልቶ ሳይወጣ …

https://sergute.blogspot.com/2018/06/blog-post_68.html

https://sergute.blogspot.com/2018/05/18_2.html

https://sergute.blogspot.com/2018/05/18_2.html

https://sergute.blogspot.com/2018/05/24.html

https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_26.html

https://sergute.blogspot.com/2018/05/20.html

https://sergute.blogspot.com/2018/05/01.html

https://sergute.blogspot.com/2018/05/05.html

https://sergute.blogspot.com/2018/05/10_2.html

https://sergute.blogspot.com/2018/05/06.html

https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_17.html

https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_38.html

https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_87.html

https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_72.html

 

ሁሉም የአማራ ልጅ እኔም አሰምነው ጽጌ ነኝ ብሎ ሁሉም ወታደር ሆኖ ለውጡን ከሚያጠቁ አስተሳሰቦች፤ ሳንኮች ጋር ፊት ለፊት በመጋፈጥ ለውጡ ያለመውን አዲስ ሥርዓት ግንባታን ለመሳካት መትጋት ይኖርበታል። የነገ ሰው ይበልን አምላካችን። አሜን!  

ወጣትነት ከማስተዋል ጋር ከተፋታ ዕንቁ ዕድሉን ያጣል!
ወጣትነት ሙቀቱን በሙሉ አቅሙ ለአብይ ሌጋሲ ማዋል ይጠበቅበታል!
ወጣት የንፋስ ህልምን ሳይሆን ዘመንሰጥ ሽልማቱን፤ ጌጡን የመጠበቅ ግዴታ አለበት!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

ማለፊያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።