ኢትዮጵያን ቁምነገር የማድረግ ዓላማ!

ኢትዮጵያን ቁምነገር የማድረግ 
ዓላማ በመሆን ውስጥ ይታያል።
ሥርጉተ - ሥላሴ (Sergute©Sselassie)
31.03.2018 (ከጭምቷ ሲዊዚርላንድ።)

                                   „እግዚአብሄር የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዬ ነው።“ (መዝሙር ፲፭ ቁጥር ፭)





  • እፍታ። 

አዎን ይታያል። „አዎንታዊነት መሆን“ በልቡ ውስጥ ለተጻፈ ኢትዮጵያን ቁምነገር የማድረግ ዓላማ አለው። ይህም ማለት „አዎንታዊነት የመሆን ህግ“ በልቡ ለተጻፈ ኢትዮጵያን ቁምነገር የማድረግ ዓላማ ያለው ብቻ ነው። „አዎንታዊነት በመሆን“ ውስጥ መኖር አለ። በመኖር ውስጥም „መሆን“ አለ። በመኖር ውስጥ ያለው „መሆን“ ራሱን „መኖርን“ ለማኖር የተፈጠረ መሆኑን ያውቃል።
አንድ ሙሉዑ ሰብዕና ማለቴ የሞራል ስብራት የሌለበት „አዎንታዊ መሆንን“ ለማኖር በቅድሚያ „በአዎንታዊ መሆን“ ረቂቅ ምግባራዊ ስበት ውስጥ በዘላቂ ለመኖር ቁርጥ ውሳኔ ማድረግ ይጠበቅበታል። „መሆንን“ „መሆን“ የሚያደርገው „መሆን“ በዕውን „መሆንን“ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥርዓቶችን መከተል ሲቻል ብቻ ነው።

እያንዳንዱ የመኖር ክስተተ - ነገር የዬራሱ ሞራላዊ ወይንም ኢ- ሞራላዊ ሥርዓት አለው። ሞራላዊ ሥርዓት በራሱ የሚለግሰው ቁምነገር ዓላማን ለማሰካት በክስተቱ ውስጥ ሥርዓተ አልበኝነት ወይንም ኢ- ሞራላዊነት እንዳይከሰት የሚያደርግ ጥንቁቅ ወታደሩ ነው። እርግጥ የተጻፈም// ያልተጻፈም፤ ሃይማኖታዊ // መንግሥታዊ ወጋዊ ወይንም ልማዳዊ፤ ወይንም ባህላዊ ሊሆን ይችላል። አንዱ  በአንዱ ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ እንዳይሆን ወይንም አንዱ በሌላው ላይ የክስተቱ ተፈጥሮ ጨቋኝ እንዳይሆን እንደ አፈጣጠሩ እንያንዳንዱ ክስተት በሁሉም የህግጋት ሂደቶች በውርርስ ጥሰት ሳይኖር መከወን ይኖርባቸዋል።

ይህ ማለት እንዴት ነው? ያነሳሁት „መሆንን ማኖር“ ነው። „መሆን“ አንድ የሙሉዑ ሰብዕና ግንባታ ጥሬ ዕቃ ነው። ይህን ጥሬ ዕቃ ወደ ሰብዕና ግንባታ ስናመጣው „በመኖር“ ውስጥ ያሉ፤ የነበሩ ሰማያዊ ይሁኑ ሰው ሰራሽ ሥርዓትን ለመከተል መፍቀድ ይኖርበታል። „መሆን“ አዎንታዊ ነው። አዎንታዊ ሊሆን የሚችለው ግን „ምቀኝነት“ የሚባለውን አሉታዊ ጥላሸት የሥርዓቱን፤ የህግጋቱን፤ ድንጋጌ መጠዬፍ ሲቻል ብቻ ነው።
  • አዎንታዊነት መሆን ነው። 

ሥርዓት ሲባል ለ እኔ ትክክለኛም ትክክለኛም ያልሆኑ ሥርዓተ ምግባሮች አንዳሉ ነው የሚገባኝ። ለፍቅር ሥርዓት እንዳለው ሁሉም ለጥላቻም፤ ለትዕግስት ሥርዓት እንዳለው ሁሉ ለማጣቱም አሉት ብዬ አምናለሁ። አፈጻጸም ሂደታቸው፤ ጊዜ እና ሁኔታ የመያደርሱት ተጽዕኖ እንደተጠበቀ ሆኖ። ጦርነት እኮ ሰው መግደል ነው። አይደል? ሰው ለመግደል ይከፈታል በሩ። ወደ በሩ ገብቶ ለማሸነፍ ሥርዓት ህግ፤ አደረጃጀጀት እና አመራር አለው። የትኛው ትክክለኛ ጦርነት የትኛው ኢ - ትክክለኛ መሆኑ አይደለም መሰረታዊ ነገር። ለምሳሌ ጣሊያን ኢትዮጵያን አጥቅታ ለመውረር ስተነሳ ትክክለኛ ያልሆነ የጦርነት ውሳኔ ነበር። ለ እኛ ትክክለኛ ያልሆነው ለጣሊያን ታላቅነት ግን ጦርነቱ የተገባ ተደርጎ ስለተወሰደ በሥርዓት ተደራጅቶ ነው የተንቀሳቀሰው። እኛም ይህን ትክክለኛ ያልሆነ ጦርነት አስገድዶ ትክክለኝነት ማሸነፍ እንዲችል ተደራጀን። ሁለቱንም የጦርነት ዓይነቶች የተማራው ደግሞ በሥርዓት ነው። ተዚህ ላይ አንድ ነገር አዎንታዊ መሆን እንዳለ ሁሉ አሉታዊ መሆንም አለ። ደንበር ጥሶ ወረራን በእብሪት ማካሄድ አሉታዊ መሆን ነው። ድንበርን አላስጥስም ብሎ መከላከል ባለፈም ማጥቃት ደግሞ „አዎንታዊ መሆን“ ነው።

የትግራይ ገዢ የነበሩት አቶ አባይ ወልዱ ደንበር ጥሰው ጎንደር ከተማ ገብታው በመታበይ እና በማንኽሎኝነት በመኖሪያ ቤት ሰብዕናን በእጅጉ ተዳፍረው በጓዳቸው ላይ መከራውን አብሯቸው በተጋራው ላይ በኮ/ ደመቀ ዘውዱ ላይ የከፈቱት ጦርነት „አሉታዊ መሆን“ ሲሆን፤ በራሳቸው ጓዳቸው የተቃጣባቸውን ጥቃት ለመመከት ነፍሳቸውን ለማደን ኮ/ ደመቀ ዘውዱ ያደረጉት መከላከል ደግሞ „አዎንታዊ መሆን“ ነው። በተጨማሪም ትእቢተኛው የአቶ አባይ ወልዱ አመራር ነዳጅና ክብሪት አዘጋጅተው፤ ወጣቶችን አደራጅተው እና መርተው የመጀመሪያውን የጎንደር የርዕሰ መዲናነት ታላቅ የሚስጢር ርካብ የሆነውን፤ ጎንደርን የመሰረታት አምክንዮ የሆነውን የንግድ ማዕከል ቅዳሜ ገብያን ማቃጠል ደግሞ „አሉታዊ መሆን ነው።“ ካሳ አልቦሹ ትዕቢት ህግ ጥሰቱ በኢ - ሞራላዊ ሥርዓት እና አደረጃጅት በታቀደ የተከወነ ነበር። የሚገርመው ንግሥናው የብሄራቸው የተጋሩ ስለሆነ ሳይከሰሱ ሳይጠዬቁ አሁን አንባሳደር ለዛውም የአውስትራልያ እንደሆኑ እዬተሰማ ነው። አሁን ከዚህ ላይ „የአዎንታዊ መሆን“ ህግጋት ልዩ ጭቆና ድርሶበታል። ህግን ተላልፎ የተካሄደው ጥሰት በመንግሥት ደረጃ ማዬት ህጋዊነቱን ማዬት ይቻላል። አድሎም ጭቆናም መግለለም ብቻ ሳይሆን ግለላው ህገ - መንግሥቱንም ያካትታል። ህገ - መንግሥቱ ራሱ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ አፍ ውርዴት እና ጥሰት ደርሶበታል። በዚህ ስሌት ህገ መንግሥት የሚባለው የተኝተለጠለ ነገረ ዝምብሎ „ለአሉታዊ መሆን“ እና  ለኢ- ሞራላዊነት አገልጋይ እና ሎሌ ከሆነ አያስፈልግም ነበር። ቀጣዩ የኢትዮጵያ የቀዝቃዛው ጦርነት ሂደት የግንባር የጉጉስ ሜዳም ይኸው ነው። „አሉታዊ መሆን እና አዎንታዊ መሆን“ በሚኖራቸው የህግ አግባብ ፈተና ላይ ይቀመጣሉ።

አሁን ወደ ቀደመው ስመለስ „ምቅኝነትም“ አንደ ተፈጥሮው የራሱ ኢ - ሞራላዊ ሥርዓት አሉት። ስለዚህም „ምቀኝነትን“ አላስጠጋውም ለማለት የምቀኝነትን ኢ - ሞራላዊ ሥርዓቶችን ለማውቅ መፍቀድን፤ ሥርዓቶች የሚያመጡትን ቀውሶች መረዳትን ይጠይቃል። ምቀኝነት ገዢ መሬትን ሳያገኝ ሙት መሬት ላይ እንዲቀር ማድረግ የሚቻለው „የምቀኝነትን“ ኢ - ሞራላዊ ሥርዓቶቹ የሚያስከትሉትን ቁስለቶች እና ኪሳራዎችን የእኔ ብሎ መመርምር ግድ ሲል ብቻ ነው። አብሶ ሐገራዊ ሲሆን ደግሞ ግዙፍ ንደቶችን ስለሚያስከትል አትኩሮቱ ሙሉዕ፤ በዕወቀትና በስልት መሆን ይኖርበታል። ዙሮ ደግሞ ተሸናፊ አድርጎ ባሪያው እንዳያደርግም በእጅጉ መጠንቀቅ የሚያስፈልገውም የጉዳቱ ልክ፤ የጦሱን መጠን „የምቀኝነት መዳረሻውን“ መመርምር ሲቻል ብቻ ነው። ምቀኝነት ከሰው በ እጅጉ ያሳንሳል። የፈለገ አይነት ብቃት በብቃት ይነባበር ምቀኝነት ያለው ሰብዕና ከሰብዕነት ደረጃው መመጣጠን አለመቻሉ ነው የምቀኝነት ሎሌ የሚያደርገው። ያለው አለው ግን „ምቀኝነትን“ ምራኝ ካለ አለኝ የሚለው ዋጋው የሚራረደው በዛው በወረደው ስብዕና ልክ ይሆናል። ስብራቱ ቀና ብሎ ለመቆም ወጌሻም አይኖረውም። ስለዚህም „ከምቀኝነት“ አዟሪት መውጣት ክብርን ቅርፊት መድረጉን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል።

በዚህ ሂደት ማለፍ ከልተቻለ „ምቀኝነትን“ በመጥላት ብቻ „ምቀኛ“ አለመሆን አይቻልም። አንድ የማህበራዊ ሥነ - ተፈጥሯዊ ክስተት ለመቀበልም ሆነ ለማግለልም መጀመሪያውን ነገር እራሱን እንደ ተፈጥሮው ማድመጥ ግድ ይላል ‚ አውንታዊ ይሁን‘ አሉታዊ። የሚፈጥራቸውን መጠራቅቅ በማስተዋል መመርም ያስፈልጋል። ትርፍና ኪሳራው ሚዛን ሊገዛለት ይገባል። በስሜቱ ውስጥ ያሉና ሊገጥሙ የሚችሉ የፈተና አይነቶችን መፈተሽ የግድ ያስፈልጋል። ራስንም በዛ መጠራቅቅ ውስጥ ላለማስገኝት ወይንም ለማራቅ ከተፈለገ። „ምቀኝነትን እጠላዋለሁ“ ማለቱ በቂ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን „የምቀኝነት“ ተባባሪ ላለመሆን ሊያድን ስለማያስችል „ኢ ሞራላዊ የሆነውን ምቀኝነት“ ጠንቅቆ ከሥረ መሰረቱ ማወቅ ያስፈልጋል። ተባባሪ አለመሆንን ለመፍቀድ ክፉውን ምቀኝት እና መረቦችን ለመበጣጣስ ማወቁ ነው ቀዳሚው አብይ ሰው የመሆን በትረ ጉዳይ ሊሆን የሚገባው - እንደ ሥርጉተ። ምቀኝነት ከበታችነት ስሜት የሚመነጭ ብቻ ሳይሆን አቅምን ያልመጠነ ምኞትም የሚያመጣው በመሆኑ ሳይኖሩበት ቆይቶ ስሜትን የሚነካኩ ነገሮች ሲከሰቱ ተጠቂ ሊያደርግ ይችላል። በሽታም ነው። ፈውሱ ግን በእጅ ነው። „አውንታዊ“ መሆን።
ሌላ አንድ ምሳሌ ተዚህ ላይ ልከል „ሀዘን“ አይወደድም። ግን ሰውና „ሀዘን“ ተለያይተው አያውቁም። ሊለያዩም አይችሉም። „ሀዘን“ የበለጠ የውስጥ የሚሆነው ወይንም የሚታወቀው ግን በራስ ውስጥ ሲደርስ ብቻ ነው።

ምሳሌ /// እስረኛ ያለው ቤተሰብ እስረኛውን ባዬ ቁጥር፤ ወይንም ስለ እስረኛ በሰማ ቁጥር፤ ወይንም ስለእስረኝነት ህግጋቱን ባጠና ቁጥር ውስጡ ሰላም ያጣል። መንፈሱ በእኔነት ይተዋካል - እኔ ብሆን ብሎ የእኔ ይለዋል። ሰቀቀኑን ባሻጋሪ አይደለም የሚመለከተው። ያ የእስረኛ የቅርብ ሰው ኑሮው ራሱ የሚተነፍሰው በነገረ እስረኛ ቧንቧ ይሆናል። ስለዚህ እሱም እራሱ የእስረኝነት መንፈስ ቀጥተኛ ቤተኛ // ቤተሰብ ነው ማለት ነው። በኑሮው፤ በህይወቱ መኖሩ በራሱ፤ እስር በተፈጥሮው ጣዕሙ መራራ ስለመሆኑ ያውቀዋል፤ ስለምን አካሉ የእኔ የሚለው ታስሯል እና። ይህ እንግዲህ ለቤተሰቡ ነው።

ለራሱ የግበረ ምላሽ ዳታው ለካቴና ቤተኛው ደግሞ ከዚህ የላቀ ከቤተሰቡም፤ ከቅርብ ሰዎችም፤ ከተሟጋቾቹም በላይ በጥልቅነቱ ይለያል። ተጠቂ ነውና። በዚህ መንፈስ ዙሪያ ለሚታደሙ ታዳሚዎች ደግሞ የዳታው ቀረቤታ እና እርቀት በሰው ልጅ የሰብዕና አገነባብ ልክ የሚወስን ይሆናል። ሚዛኑን የሚሰጠው የሰው ተፈጥሮ ሰዋዊነት እና ተፈጥሯዊነት ስለሆነ። ሰብዕናው ለተኮላሸበት ሰቀቀኑን ታይቶም ተደምጦም በአካል አይቶትም ቢሆን ከምንም ላይቆጥረው ይቻላል። አሽዋነት።
ተፈጥሯዊነት በብዙ መልኩ ስስነቱ ወይንም ደንዳነቱ እንደ አስተዳደጉ ወይንም እንደ ስብዕና የስሜት ውስጣዊ አወቃቀር አደረጃጀት እና አመራር እና ተመክሮ ስለሆነ። አልዝንም ካለ አንድ ሰብዕና አለማዘን፤ አላስተውሰውም ካለ አለማስታውስ ስለሚቻል። የራስ ፈቃድ ጉዳይ ነው። ለዚህ ነው ቀደምቶቹ „ድርብ አንጀት“ የሚሉት፤ በዚህ ዙሪያ ፆታ አይለይም - ለእኔ። ስሱን ደግሞ ተባዕትም ቢሆን „እናት አንጀት“ የሚሉትም ለዚህ ነው አቨው/ እምው። „ሀዘኔታ“ በተፈጣሮ ለሴቶች በልጦ የተሰጠ ይምሰል እንጂ ከሴቶች የተሻሉ ስስ አንጀት ያላቸው ተብዕትም አሉ ግን ውስጣቸው የአደባባይ አይደለም። ለዚህም ነው የቅኔው ልዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህ „ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ“ በማለት ጥልቀነቱን ያመሳጠረልን። ትንሽ እስኪ ከቅኔው ንጉሥ  ስንኛት …
·         ሎሬቱ የተፈጥሮ ስዋሰው። 

„… ‘ርቅ ነው ወንድ ልጅ እንባው
ደም ነው፣ ፍም ነው እሚያነባው፤
ንጥር ህዋስ ነው፣ ሰቆቃው
ረቂቅ ነው ምሥጢር ነው ጣሩ፣--- ብቻውን ነው የሚፈታው።“
ይህ ልቅና ይህ ክስተታዊ ትርጓሜ ብላቴው እያንዳንዱን የተፈጥሮን ስሜታዊ አመክንዮ ሆነ ክስተት ውስጣዊነት በፍልስፍና ጥበብ ያነበበት ምስባኩ ነው። ይህን ለተቀበለ ሌሎች ሥርዓቶችን ማወቅን ይጠይቀዋል። ለምሳሌ „ርህርህና“ ለምልክት ልውሰድ - ማያያዣም እንዲሆነኝ …

„ርህርህናም“ ስለተፈለገ የሚታፈስ አይደለም። ፈተናው ብዙ ከመሆኑም በላይ ራሱን ያሸነፈ ብቻ የሚያገኘው ፍሬ ነገር ነው። አሁን በዚህ „ርህርህና“ ውስጥ „የመሆን አዎንታዊነት“ ተፈጥሮ ስበቱ እና ግጭቱ በራሱ ጊዜ የሚፈጥረው ውብ ትዕይንት አለ። ርህርህና ጸጋም ነው ተፈጥሮም ነው። ተፈጥሯዊነቱ ለሁላችን የተሰጠን መሆኑ ሲሆን፤ ጸጋነቱ ደግሞ „በመሆን „ውስጥ የመተርጎም አቅምን ያመለክታል። ጭካኔ የተጫነው ተፈጥሮ „ርህርህናዊ“ ተፈጥሮውን ደምስሶ እና ቀብሮ ነው። „በርህራሄ“ መቃብር ላይ ነው የጭካኔ ማህበረተኞች አግናባት የሚገነቡት ምሳሌ ወያኔ ሃርነት ትግራይን ማንሳት ይቻልል። ጭካኔን እያዩ ዝምታ በራሱ ከፈፃሚው ያልተለዬ ማህበርተኝነት ነው። በዚህ ዙሪያ የሚታደሙ ወይንም የሚሸከረከሩ ነገሮች ሁሉ ዕውነትን ግርዶሽ ማልበስ ሊሆን ይችላል። ያው „ርህርህናን““ አመድ አድርጎ፤ „ርህርህናን“ ግጦ ንግሥናውን ለጭካኔ፤ እጬጌነቱን ለአረመኔነት እንዲሆን መፍቀድ ማለት ነው። ይህ ማለት በተባባሪው ሥነ - ልቦና ውስጥ የተሰጠው „ሞራላዊው ርህርህና“ አረም ወይንም ሙጃ ውጦታል ማለት ነው። „በርህርህና“ ውስጥ ኢትዮጵያን ማዬት ሲቻል ኢትዮጵያን ማዳን ቀዳሚ ዓላማ ይሆናል።

ቀዳሚው ዓላማ ሐገር አለኝ ከሚል ይነሳል። ሐገር አለኝ ሲባልም ዓለም አቀፍ ዕውቅና በተሰጠው መልከ ምድራዊ አቀማመጥ ውስጥ ያለ የሰወች ማህበርተኛ አባልተኛ ነኝ ብሎ ማመንን ይጠይቃል። በዛ መልዕክምድር ውስጥ የማህበር ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ማህበራትም አሉ። ሁሉም እንደ አፈጣጠሩ፤ እንደ ዞጉ እንደ ማለት … ለምሳሌ የእንሰሳት ማህበር፤ የወንዞች ማህበር፤ የተራሮች ማህበር፤  የ እጽዋት ማህበር፤ የማዕድናት ማህበር፤ የወቅታት ማህበር፤ የዘመናት ማህበር  ወዘተ … ስለዚህ ኢትዮጵያ ስትባል በዚህ ሁሉ የተፈጥሮ ቅመም የተቀመመች ምጥን ናት ማለት ነው።
 
ኢትዮጵያን ቁምነገር የማድረግ ዓላማ ኢትዮጵያዊ መሆንን ይጠይቃል ሲባልም፤ በሁለመናዋ ውስጥ ባለማበላለጥ መክተምን ይጠይቃል ማለት ነው። „አውንታዊ መሆን!“ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ ማመንን። ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ መቀበልን። ኢትዮጵያዊነት ያሉትን ሥርዓቶች ማጥናትን ከልብ ይጠይቃል። ለምሳሌ የአድዋ ድል አንዱ „የ አዎንታዊነት መሆን“ መለኪያ ነው። በዓደዋ ድል ውስጥ ሰዋዊነትም ተፈጥሯዊነትም የሚሰጡት ማናቸውም ክስተታዊ አመክንዮዎች ሥርዓታቸው፤ ውህደታቸው፤ ወጥነታቸው „አውኦንአተዊ መሆን“ መቻላቸው በዓላማቸው ውስጥ መገኘታቸው ነው የድሉ ፊድል ገበታ።

ድል ይወደዳል። ድል ይናፈቃል። ድል የምኞት ሚዛን ነው። ድል ይህሊና ግድግዳ ነው። ድል የመፈልግ ፍላጎት ነው። ድል የመኖር „መሆን“ የመጨረሻው እርከን ነው። ድልን ማግኘት የሚቻለው ግን „በመሆን“ ውስጥ ነው። በመሆን ውስጥ መልካም የሆኑ/ ያልሆኑም ገጠመኞች ሊኖሩ እንደሚችሉም ልብ ማለት ያስፈልጋል። „ በአዎንታዊ በመሆን“ ውስጥ ያሉ የድንጋጌዎች አንቀፃት በመልካም አጋጣሚዎች ብቻ የተደወሩ አይደሉም። „መሆን“ ጌጡ መከራም ነውና።
„በአዎንታዊ መሆን“ ውስጥ ያሉ ሥነ - ምግባሮችን በመቀበል፤ በመወደድ፤ በመፍቀድ፤ በማጥናት፤ በመመርመር በህገ - ልቦና ጽፎ ምራኝ በማለት የሚገኝ መሆን ነው ለምለም ሊሆን የሚችለው። ኢትዮጵያዊነትን በልቡ ለጻፈ ኢትዮጵያዊ ድል ማድረግ የሚያስችለውን መሳሪያ በአእምሮው ሥልጡንነት መከውን አያቅተውም። ኢትዮጵያዊነት ቁምነገር ነው። ቁምነገሩን ቧልት የሚሆነው ከሚስጢር መነሳት ሲያቅት ወይንም ሲሳን ብቻ ነው።

አድዋ ድል ነው። አድዋ ሚስጢር ነው። የአድዋ ድል እኛን ሠርቶናል ብሎ በመቀበል ተሚስጢር አብራክ እና ማህጸን ለፈቀደ የመሆን አርበኛ ኢትዮጵያን ቁምነገር የማድረግ ዓላማው ስኬታማ ይሆናል። የሂሳብ ሳይንቲስትም አያስፈልገውም።
ይህ ውስጥን የሚፈትሽ፤ የሚመረምር፤ የሚያግባባ፤ የሚያማትር፤ የሚያደምጥ፤ የሚፈትሽ „አውንታዊ መሆን“ „መሆን“ የሚችለው ከዐድዋ ድል መነሳት ሲቻለው ብቻ ነው። መሆን የሚገለጠው ድሉን ድል ያደረገው „የመሆን“ አርበኞች ትንግርታዊ ክስተታቸውን አንድ በአንድ በተናጠል ከነሙሉዑ ሥርዐታቸው ማጥናት ሲቻል ብቻ ነው። ዕውቅና በመስጠት - በአክብሮት እና በትህትና።
የአድዋ ድል ብቻውን እኮ አፍሪካውያን፤ እኛ ጥቁሮች በዩንቨርስቲ ደረጃ እንደ አንድ የሙያ ዘርፍ ልክ እንደ ቁጥር፤ እንደ ተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት ሥርዓት ተነድፎለት እንደ አንድ የቀለም ትምህርት ሊመረቁበት የሚገባ ንጥር ክስተት ነው። „ታሪክ“ ውስጥ ዓደዋ ድል አለ ቀደም ባለው ጊዜ። ግን ራሱን ችሎ መሰጠት ይኖርበታል። ኢትዮጵያን ከፍ ወደ አለ ደረጃ ማሸጋጋር ዓላማም ግብ ከሆነ። አልጀመርነውም። የችግራችን አታካችነት ምክንያታዊ ጭብጥም ከዚህ የመነሳት አቅማችን ስልብነት ነው። ሙግቶች የመንፈስ ማህለቃቸውን የሳቱ ናቸው። የኖኽ መርከባቸውን ጥለው ነው ኢትዮጵያን ለመግዛት የሚታሰበው።
ክስተቱ በማለት ወይንም በሚዲያ ማሟቂያነት ወይንም እለቱን በጭብጨባ አጅቦ ለማሳለፍ ሳይሆን „በመሆን“ ውስጥ መፈተሽ አለበት። አድዋ ድል የሰሚናሮች፤ የሚዚዮሞች፤ የመጸሐፍቶች፤ የኪናዊ ታምራቶች፤ የወርክሾፖች ሁሉ አንጎል ብቻ ሳይሆን ስሜት የሚሰጥ አዕምሮም መሆን አለበት። ትምህርተ - ዓድዋ ድል የሰማይ የአምልኮ የገደል መጸሐፍ ነው - ለእኔ።
 
አንድ ሰብዕና ተዛሬ ላይ ቆሞ ዛሬ ላለበት መሬት ያበቃው ሰንደቁን የአሻቦ መቋጠሪያ በማድረግ አይደለም። ወይንም የካቴና ራት ተደርጎ አይደለም። ወይንም የቁንጫን ማወራረጃ፤ የዱላህ ጅራፍ መወጣጫ ሆኖ አይደለም። ክብሩ የተገኘው የመለከቱ ግርማ እና ጃኖ ከሆነው በብሄራዊ ሰንደቅዓላማው ነው። ንጡሁ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅዓላማው ነው አንተን/ አንቺን ሰው አድርጎ ዐወርቶሃል/ ሠርቶሃል። ይህ ሰንደቅ „በመሆን“ ውስጥ መፈተሽ አለበት። የኢትዮጵያ ቁምነገር ያለው ከዚህ የሰማይ ጸጋ ብቻ ነው እና። የአፍሪካ የጥቁር ህዝብ የነፃነት ግርማ ሞገስ ያለው ከዚህ ጥልቅ ረቂቅ ነፍስ ውስጥ ነውና። ዛሬ የአፍሪካው ህብረት ጽ/ቤት መዲና መሆን ያስቻለው ይሄው የማይገሰስ ገናና ታሪክ ነው። የታሪኩ ሐዋርያ ደግሞ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ መለከት ነው። አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ነጋሪት ነው። አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ የሰማይ ድንጋጌ ነው። አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ህግ ነው። ሊደፈርም ከጫፉ ሊደረስም የማይገባ የነፍሳት የሥነ - ልቦና ገነታዊ ማደሪያ ማህደር ነው። 

ዛሬ ስንሰደድ ዜግነት ስንባል „ኢትዮጵያዊ“ የሚያስበለን ሌላ ምንም ሳይሆን ያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የሰጠን ሰማያዊ ጸጋ ብቻ እና ብቻ ነው። ዛሬ ዶር. ቴወድሮስ አድሃኖም የዓለሙ የጤና ጥበቃ ሚ/ር ያደረጋቸው ትግሬነታቸው ወይንም ዶክተሬታቸው ወይንም ዓይነ ገብ መሆናቸው አይደለም። ኢትዮጵያ ከምትባል ሐገር ውስጥ በመፈጠራቸው በዛም የዜግነት ዕድሉ ኑሯቸው ውጪ ሐገር ሄደው በመማራቸው፤ ተመልሰውም በኖረቸው ሐገር ውስጥ ዕድል አግኝተው በመሥራታቸው ነው። ይህን ያደረገው ጉግል ወይንም ዩቱብ አይደለም። የዚህ ሚስጢር አናት „በመሆን“ ውስጥ የከተመው የዓደዋ ገድል ለእኛ ሙሉ ዜግነት ስለፈረመልን ብቻ እና ብቻ ነው። ያ ድል ሜዳ ላይ የታፈስ ወይንም ወንዝ ዳር የተቸረፈስ አሽዋ አይደለም። መኖር ያፈራቸው፤ ተፈጥሮ የለገሳቸው የሰው ልጆች በሙሉ „አመላቸውን በጉያቸው“ አድረገው ግን ሞራላቸውን ከእነ ሙሉ ሥነ - ምግባራቸው በብሄራዊ ቅንነት ቀምረው፤ እንሳሳት ሳይቀሩ በፈጸሙት የወል የፍቅራዊነት፤ የሐገራዊነት ተጋድሎ የተገኘ የደም እና የአጥንት ነባቢት ነው። የዚህ ምግባር ሊጋባው፤ አሳለፊው፤ አሰላፊውም ደግሞ ልሙጡ ዓርማ አረንጓዴ ቢጫ እና ቀይ ብሄራዊ ሰንደቃችን ብቻ ነው።

ያ ድል አብሮ አንድ ሆኖ ኢትዮጵያን ቁምነገር አድርጎ የመነሳት ዓላማ ያስገኘው እጹብ ድንቅ „የመሆን“ ረቂቅ ሥርዓታዊ አፈጻጸም አመራር፤ አደረጃጃት፤ ጥበብ፤ የጦር ስልት አዋቂነት፤ ሩቅን የማሰብ ተስጥዖ ክንውን ያስገኘው የገድሎች ገድል፤ የታምሮች ታምር፤ የሊቆች ሊቅ፤ የትንግርቶች ትንግርት ነው። „መሆን“ በዚህ በዓድዋ ድል ውስጥ ችሎት ላይ ቢቀመጥ ከነ ሥርዓቱ ብቻ ሳይሆን ከነሙሉ ምግባሩ ተገኝቷል። ቀድም ብዬ ያነሳሁት „ርህርህናም“ ዓለምን ያስደመመ የአመራር „ርህርህና“ ተከውኗል። ምርኳኛ የተሰተናገደው ኢትዮጵያ መሬት ላይ „ርህርህና“ በተፈጥሮው በተቀዳጀው ሥርዓተ - ህግ ነበር የተዳደረው።
ወደ ማጠቃለያው ስመጣ ኢትዮጵያን መውደድ ብቻ በቂ አይደለም፤ ቁጭቱ ኢትዮጵያን ቁምነገር የማድረግ ዓላማ ላለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ አድዋን በልብ መጻፍ ይጠይቃል። ቁጭ ብሎ ማጥነት። ዓደዋን በመደበኛ ት/ ቤት ለመማር መፈቀድን በ አጽህኖት ይጠይቃል። በኢትዮጵያ ውስጥ በአለድርሻ አካል ነኝ የሚል ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ይሁን ሊሂቅ ይህን ሳይቀብል ቢያስበው ጥረቱ የእንቧይ ካብ ነው። ታሪክ አልባ ነው የሚሆነው፤ ውጤቱም የሚለካው በዚኸው ልክ ነው።
ስለሆነም „መሆንን“ እንደ ተቋም በውስጡ ሊማረው ሲፈቅደው ብቻ ነው የልቡ ድል። መፍቀድም ብቻውን በቂ አይደለም። ስንዱ መሆንን ይጠይቃል። ስንዱ መሆን ብቻ አይበቃም እንደ ኮርስ መጸሐፍት ማጥናትም ይጠይቃል። ይህም አይበቃም ወደ ድርጊት ለማሸጋጋር መቁረጥ ይጠይቃል። ይህም ግብ አይሆንም። የቆረጡለትን ነገር „በመሆን“ ውስጥ ማኖር ያስፈልጋል። ለእለቱ ይብቃኝ ስለታደማችሁ በቀለሜ ውስጥ ያለውን ኑሩልኝን ልሸልም።

·     ዚብራ እና ዕሳቤው።

Anteneh Part 2

·     ሰዋዊነት እና ተፈጥሯዊነት።

Ethiopia - Dr Abiy እንዴት ሰዉ 1% ልዩነት ይሰቃያል?!
·         ቁጭት።

Ethiopia - Dr Abiy ፈረንጆቹን አሸማቆ መለሳቸዉ!!

·         የሰብዕና ሚና ከጽናት ምሰሶ ፍልቀት።

Ethiopia - New Dr Abiy - አንድ ሰዉ ብቻዉን መለወጥ ይችላል!

https://www.youtube.com/watch?v=3xAtKoIPh6E&t=2s

እድልን በታማኝነት መጠቀም ያስፈልጋል!


እግዚአብሄር ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።



    

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።