ማርከሻ!
የብላሽ ግርሻ - ማርከሻ!
ሥርጉተ ሥላሴ(Sergute©Sselassie)
27.02.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)
27.02.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)
„እግዚአብሄርም አለ ሰውን በመልካችን
እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር አለ።“
( ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፩ ቁጥር፳፮።)
እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር አለ።“
( ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፩ ቁጥር፳፮።)
ይድረስ ለጸሐፊ ሰርጸ ደስታ እንደምን አሉልን? በንጹህ ህሊና እና በፍጹም ቅንነት
ሰላምታዬ ይድረሰዎት እላለሁ እኔ እህተዎት ሥርጉተ ሥላሴ ከዚህ ከኮሽ አይሊቷ ሲዊዝዬ።
ሰላምታዬ ይድረሰዎት እላለሁ እኔ እህተዎት ሥርጉተ ሥላሴ ከዚህ ከኮሽ አይሊቷ ሲዊዝዬ።
„ማስጠንቀቂያ
ለዶ/ር አብይ አህመድ! (ሰርፀ ደስታ)“ በለው! እንዲህ
ነው ማስጠንቀቂያ¡ ስለ አበዙት ትንሽ ሃሳበዎት ሊደፈር ይገባል። ግርሻን ፌጦ ስለሚያስፈልገው።
ንግግር ተስጥዖ ነው። ክህሎቱ ደግሞ በስልጠና የሚገኝ ነው። የሚገርመው ዶር አብይ አህመድ ተናገሪ ብቻ ሳይሆኑ ብቁ አድማጭም ናቸው።
ይህም ብቻ አይደለም ራዲዮ ጋዜጠኛ ስልጠና ላይ የድምጽ መግራት ልዩ ኮርስ አለው። ይህም ጸጋቸው ነው። ቃናው፤ ለዛው፤ የ እጅ
እንቅሰቃሴው፤ የ አትኩረት ሁነቱ፤ የፊድ ባክ ቁጥጥሩና አስተዳደሩ ብቁ ነው። እሚወጣለት የለም። በራሳቸው ውስጥ የሚኖረ ናቸው።ሙግት
ላይ ተናጋሪ ተሁኑ ማድመጥ ካልተፈቀደ የንግግር ጥበብ ሥነ - ምግባሩ አይፈቅድም። የሆነ ሆኖ እርስዎ የሄዱበት መንገድ ያሳፍራል።
- · ወዳጄ --- እንዲህ።
የፈለጉትን ዕውነት ነው ብለው መከተል ብቻ ሳይሆን
ማምለክ መብተዎት ነው። ከቻሉም መሬት ላይ የሚሆነውን ማድረግ። ድርጅታዊ ነፍስ አዬር ላይ አይፈጠርም - በስልክ፤ ሰብሉ በሞባይል
- አይሰበሰብም፤ ተልዕኮውንም - በናቴል አያሳካም። መደራጀት እና ያደራጁትን ለመምራት በሚያስችል መልክ የህሊና ብቃቱን ፈጥሮና
አፋፍቶ፤ ውስጥን እያደራጁና እያበቁ ማደራጀት የዕድሜ ልክ ትምህርት ቤት ነው። ማደራጀት የመዋለ ዕድሜ የቤት ሥራ ነው። በዬቀኑ
እንደ እንቁላል መፈልፈያ ማሽን በማያልቅ የሥም ግብር እዬደለዙ የኢትዮጵያ እናቶች ለባሩድ ግብር የሚያቀርቡበት ዘመን መጠናቀቅ
አለበት። የግድ!
- · ሥህን።
የትንፋሽን አቅምን ማባከን ከሲሪያ ጋር ነው አምመዝነው።
መከራውን ታድሜበታለሁ፤ ዕንባው የእኔ ብዬ ተከታትያለሁ እና። እናት የትም ቦታ እናት ናት። እኔ የእናቴን ዕንባ ማዬት እንደማልፈቅደው
ሁሉ የሌላውም እናት ስታለቅስ ማዬት አልፈልግም። አሁን እናት ልጇ ተገድሎ ከሬሳው ተቀምጣ የተደበደበችበት አንባ ላይ ሌላ እሬሳ
እና እልቂት አይናፍቀኝም። ይህ ድሎት እና ቤሎ ናፈቀኝ ነው። ሃላፊነት በፍጹም ሁኔታም የጎደለው ነው። የትውልዱን መታጨድ ከቶውንም
አጀንዳው ያልሆነ ዘመናይነት ሃዘን የጎዳው መንፈሴ ይጸየፈዋል። የሰውን ልጅ ጭንቅላትን ውሻ ይዞ የመጣበትን የእርስ በርስ እልቂት በአይኔ አይቼ የዕድሜ ልክ የማህጸን በሽተኛ መሆኔ ካላስተማረኝ
እኔ ሰው ስለመሆኔ እራሴን መፈተሽ አለብኝ። ስለሆነም የኢትዮጵያ ሴቶች መከራ እንዲቀጥል ጋሻ ጃግሬ አልሆንም። ይህን መሰል ጉዞም
አለበረታታም። ደክሞኛል! የተመኘሁትን የረጋ ሰዋዊ መንፈስ የሚያደምጥ መሆንን በተስፋ አልማለሁኝ። ይህ መንፈስ እንዲታወክ አልሻም።
„ለማላውቀው አጀንዳ አልጮህም!“
- · ወደ ቀደመው ስመለስ።
የማከብርዎት በዚህ ጹሁፍ የጻፉት ተነቧል። የባለፈውንም
አቶ ለማ መግርሳ ኦሮሚያን ቢለቁ ስጋተዎት የዶር አብይ አህመድ አቅም ሊመጥነው አለመቻሉን አጋድመው ነግረውናል። ወሸኔ ብለናል¡ በሌሎች ጉዳዮች ተጠምጄ ነው እንጂ ዛሬ የምልክለዎት ሊንኮች ያን ጊዜ ልልክለዎት ያሰባሰብኩት ነበር። እና ያ ለኦሮምያ
የማይመጥን መንፈስ ከሆነ ለማይመጥን መንፈስ „መልፈስፈሱን¡ ሆነ አስመሳይነቱን¡“ መጠበቅ ነው። በቃ። በኋዋላ እንደያሚፍሩበት ግን አስረግጬ እነግረወታለሁኝ። ይልቅ
በዚህ ግርግር አፍሶ መልቀም እንዳይሆን ይጸልዩ ሰው ከሆኑ። የቅንጅት ዕጣ ፈንታ በአመራር ጥበብ ጀማሪነት ነው የከሸፈው። አብይ
ብቻውን አይደለም። አብሮ አንድ የማይበገር ገሃዱ ዓለም የማይቆጣጠረው ረቂቅ መንፈስ አለው። በተፈጥሮ ባለሁለት ጭንቅላት ነው። ድርብ ህሊና ነው ያለው። እሱ ሥራ ሲጀምር አሱ ራሱ ባሊህ ያለለው ቅዱስ መንፈስ አብሮት ይሰለፍና ዝክንትሉን
ሁሉ ጠራርጎ ጥራቱን የሚያስጠብቅለት ሞገዳማ ሰማያዊ ተስጥዖ አለው።
ይህ መንፈስ አብሮት የሰራውን ሰው ያፈላልጉና አንድ ቅሬታ ያለው ሠራተኛ፤ ሌባና ሰነፍ ካልሆነ በስተቀር ካገኙ አንገቴን እሰጣለሁኝ።
ጥረት ካለ መረጃው መዳፍ ነው። የኢትዮጵያ የነገ የፍቅር ቀን ለናፈቀው የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። በዛ ላይ ዕድሜ ለጓድ ገ/መድህን
በርጋ የማዬትን ጥበብ ውስጥን ሸልሞኛል።
·
መክሊት።
እናታችን ክርስቶስ ሰምራ እኮ ሰው ናት። የሰው
ልጆች መብት ቅዱስ ግሎባል ተሟጋች። ፈጣሪዋን „በገህንም ፍጡርህን
ከምትቀቅል ስለምን ይህን ከሚያደርገው ዲያቢሎስ ጋር ቁጭ ብለህ አትደራደርም“ ብላ የሞገተች ጀግና ቅድስት እናት ናት።
አባታቸን አቡነ ተ/ሃይማኖት ገድላቸው አንደሚነግረን
ገና ለጋ እንዳሉ ነበር „አህዱ አብ ቅዱስ፤ አህዱ ወልድ ቅዱስ፤ አህዱ መንፈስቅዱስ ቅዱስ“ ብለው ፈጣሪን ያመሰገኑት። ዕምነቱ
ካለዎት ለማ እና አብይ ሚስጢረ ሥላሴ ናቸው። „እግዚአብሄርም አለ
ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር አለ።“ „እግዚአብሄርም አለ“ አሃታዊነት። „ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር አለ።“ ሦስትነትን። ከእነሱ ጋር አማራ በመሆናቸው ምክንያት ብቻ በውጩም ሆነ በሀገር
ውስጡም አቅማቸው ታግቶ የተቀመጡ ሌሎች የድርጊት አርበኞች አሉን ገዱአንባው። ገድል የተባለለት „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ መንፈሱ የተገለጠው ቤንሻጉል ላይ ወይንም
አዋሳ ላይ ወይንም ሐረርጌ ላይ አልበረም። ግዮን ላይ ነበር። የሊቀ- ሊቃውንቱን የፕ/ ፍቅሬ ቶሌሳ ትንቢት ይፈጸም ዘንድ። የኦህዲድ
ግርማ ሞጋስ ብሄራዊ ሆነ ህብራዊ መልክ የያዘው ቀለሙ፤ መሰረታዊ ምክንያቱ የአቶ ገዱ አንድአርጋቸው፤ የዶር አንባቸው እና የአቶ
ንጉሡ ጥላሁን ሌሎችም ቅን ባልደራባዎች አክሎ በጎዘጎዙት የመንፈስ ብቃት ነው። እንዲህ የኢትዮጵያ የገድ አንዳዊ መንገድ የተገኘው ከዚህ ጽንስ ነው። ለዛውም ይህ
ጉዞ ያልተወደደ ነበር። ዛሬ ለማዋያን በሆኑ ደሞቻቸው ተወግዞ ነበር እኮ። የሆነ ሆኑ ይህ ልቅና የሰው ሥራ አልነበረም። የፈጣሪ
ጥበብ እንጂ። አሁን ስለ አባ ሌጦ አቶ በረከት ስምዖን ወሳኔ ሰው ይጨነቃል። ለእነኝህ የአማራ ደም ላላቸው ንጹሃን ጉዳያቸው አይደለም
የሥላሴ ሚስጢር ይጠብቅላቸዋል - ዘላቂ ዓላማቸውን። ገድል ፈጻሚዎች እነሱ ናቸው። የምህረት ዓዋጅ ነፍሱ እንዲገባ ቤት ለእንግዳ
ያሉት ፈቅደውና ወደው በክብር ነበር።
- · „የሂሳብ ቅለት“
አዬ መሳይሻ። „ሂሳቡ ቀላል ነው“ ሌላው ጋዜጠኛ መሳዩ „ሂሳቡ ቀላል ነው“ ሲል የጻፈውን አንብቤዋለሁ። ዴንማርክ መሰለኝ
በተገጣጣሚ ቤት ሥራ ከአውሮፓ ዕውቅና ያላት። በቃ የመሳዩ ዕድምታ ልኩ እስተዚህ ነው። ሱቅ ተሂዶ ሰው መግዛት። ለዛውም ድርጁ ህሊና ያለው።
የተለያዩ የመኪና መሳሪያዎችን ገጣጥሞ ቆርቆሮና ብረትን መኪና ማድረግ። „ፍልስፍና“ ቀላል ነው የማለት ያህል ነው።
የአልበርት አንስታይ ቲወሪ የሸቀጥ ዕድምታ ነው እንደማለት።
- · የእነ አቤቱ ትርታ።
እርስዎ ደገፍኩት የሚሉት ሃሳብ መጀመሪያ አቦ
ለማ መግርሳ ለማለት ይድፈር - ሚዲያው። ሌላውን መብቱ ነው „የኦሮሞ ዜጋ“ ስለመኖሩ አከራካሪ አይደለም። ማሰብ እና ማለም መብትም
ስለሆነ። ንግሥናው ትቶ ገዳም የገባ ንጉሥ የነበራት ሐገር ናት ኢትዮጵያ። ለሶሻሊዝም የመንፈስ ጣዖት አምላኪዎች ት/ቤት ከፍቶላቸዋል
ውበታማ ዘመኑ የለማ ተቋም የሚባል። የህሊናው ሥልጣኔን ተርጓሚ
ቢያገኝ ነግሯቸዋል „ኳስ ጨዋታ ሜዳ ላይ አጥቂ / አጥቂ እንጂ ተከላካይ ቦታ አይመደብም፤ ተከለካዩ / ተከላካይ ቦታ እንጂ አጥቂ ቦታ
አይመድብም፤ ጎል ጠበቂው ማህል ተጫዋች አይሆንም“ ብሎ። ይህ ከተደረገ ቡድኑ ሜዳ መግባት የለበትም። ማልያም መልበስ፤ ለመሸነፍ ለምን ትጥቁን አሳመረ አንደማለት …
- · ተዚህ ላይ …
አሁን ኦህዲድ ተፎካካሪዎቹ አብረውት እንዲሰሩ
ይፈልጋል - ከልቡ። እንደ ተፈጣሯቸው። ግን ፈቃዱ ቦሌ ላይ እንደሚመለሱ ያውቃል። አሁን ከእሱ አቅም ውጪ የሆኑ ጫናዎችን እዬፈጠሩ
የሚያውኩት መንፈሶች አደብ የነሳቸውም ይህን ሚስጢር ለማድመጥ ባለ መፍቀዳቸው ነው። ሰብል ሳይደክሙበት አይታፈስም። ለፍላጎቱ ማስፈጸሚያ
ማነቆ የት ላይ እንዳለ ድርጁው መንፈስ አጥንቶታል። ጣልቃ ገብነቱን የሚገታለት ጉልበታም አቅም፤ የልቡን ለማድረስ የሚያስችል እኔውን
ማግኘት ይሻል። እሱ የሚችለው በክልሉ ብቻ ነው። ለዛውም በጫና። ግን እንደ ዶር መራራ ጉዲና አፋኝ ህግ፤ በህግ አግባብ አስኪነሳ
ድረስ ከመጠበቅ ለሚዲያ ፍጆታ ብሎ፤ ወይንም ለነጭ አምልኮ ጫና ብሎ ፊት ለፊት ሄዶ አይላተምም የለማ ቅዱስ መንፈስ። አደብ የገዛ
እና የተረጋጋ ልስልስ ነው። ስታስቡት እራሱ አይጠገብም። አሁን አጋዚ አያደርገውና አንድ ነገር ቢያደርጋቸው ማን ተጠያቂ ሊሆን
ነው? ኦህዲድ? እእ። እራሳቸው ናቸው። ከኮነሬል ደመቀ ዘውዱ የመንፈስ እርጋታ ብቃት መማር አልተቻለም። ለኮነሬሉ አቀባባል ምኑም
አይደለም። ውሰጡን ተቀምቷል። ያን በህግ አግባብ ጥያቄውን መሳፈጸም
ደግሞ እስር ቤት በመግባት አለመሆኑን አሳምሮ ያውቃል። በሂደቱ የተሰዉት እናቶች ማህጸን ሰቆቃ የእኔ ብሎታል። ቢያንስ መስዋዕትነት
መቀነስ መርሁ ነው የብልሁ መኮነን። የኮ/ ጀግንነት ከሃምሌ 5ቱ አብዮ አብዮት በላይ ነው የተደሞው ጥልቀት። ፈጣሪ እንዲህ አደብ
የገዛ መሪ ለአማራነት ቅናዊ መንፈስ ስለሰጠ ይመስገን። አንገታችን አላስደፋንም። ስመለስ ወደ ጉዳዬ … ኦህዲድ እንደ ድርጅት ሲታይ
ደግሞ ለወሰነው ውሳኔ ተፈጻሚነት ለዛ የሚያበቃውን የህሊና አቅም ከፌድራል እስከ መሰረት የማስያዝ ሂደት ማስቀደም ነው የፖለቲካ
ሳይንቲስትንት ጥበቡ። ቃልአባይ መሆንን አልፈለገም። ዕድምታ ቤት አብረን የተደሞ ጊዜ ያስፈልጋል። ከመንጨቧረቅ። ለዚህ ነው እኔ ኦህዲድ እንደ ድርጅት አቅሙ ብሄራዊ
ሐገራዊ ሃላፊነትን የመረከብ ሙሉ ቁመና ላይ ነው የምለው። ኢትዮጵያ ትድናለች። ከእንባዋም ትፈወሳለች። ለዚህ ቅኖቹ ተግተን እንሰራበታለን።
·
ልባም ነገር።
እኔ ሳውቃቸው ዶር መራራ ጉዲና እሳቸውን ብቻ
ነው። ዕጣ ነፍሳቸውን። አሁንም ከስንት ዓመት በኋዋላ እማያቸው እሳቸውን ዕጣ ነፍሳቸውን ብቻ ነው። በቃለ ምልልስ የማዳምጣቸው
ወገኖች አሉኝ፤ ግን አቅሙን አላመጡትም። አምጠው አልወለዱትም። አቦ በቀለ ገርባ ሰብዕናቸው ይመስጥል። እሳቸው ግን የሌላ ፓርቲ
ሃብት ናቸው። እኔ የጠዬኩትን ጥያቄንም፤ እጨቀጭቃቸው የነበረውን ዓውራ አመክንዮ ነገር ነበር የራዲዮ ጋዜጠኛ በነበርኩበት ጊዜ
- በማህያ። (ዛሬም ሲሰኘኝ የምሰራበት የአዋቂወችና የልጆች የጸጋዬ ገ/ መድህን የራዲዮ አዘጋጅነቴ በግል መብቱ የተጠበቀ ነው
- ይከፍለበታል) እስከ ዛሪዋ ዕለት ድረስ አልመለሱትም፤ አንዲት ሴት ማፍራት አልቻሉም። ይህን ያክል ዘመን አንዲት ብቁ ሴት የማፍራት
የፖለቲካ ሳይንቲስት ልህቅናቸው ሥጦታውን ሴት ተተኪ የሀገር ብቁ መሪ የምትሆን አልሸለመንም።
አያደርገው እንጂ ፕ/ በዬነ ጵጥሮስ አንድ ነገር
ቢሆን ዘር አልባ ይሆናሉ። ለማ እንዲህ አይደለም። እሱን አራሱ ብቻ ሳይሁን እሱን ለሚተካው ሰው፤ አንድ ነገር ብሆን ብሎ ቆጥቦ
ያሰቀመጣቸውን እያዬን ነው። ለተተኪው ተተኪም መሰናዶ ማሟላት ሌላው የለማ መንፈስ ዝግጁነት አዲስ ሥልጣኔያዊ ክህሎት ነው። ልክ
እንደ ኳስ ተጫዋቾች። በተለይም የጀርመን መንገድን ተከትሏል። እኔ ደጋፊያቸው ስልሆንኩ ነው ይህን እምከታታለው - የጀርመኖችን።
ቋሚም ግንኙነት አለኝ። ሰው አቅሙን አሟልቶ የማዘጋጀት ነገር የነፍስ ያህል ሊሠራበት የሚገባ የማደራጀት ተግባር ነው። በተከታታይ፤
በትጋት። ሌላው ለማ ማንን እንደሚታገል ሲያውቅ በጀብድ አይደለም። በጥበባዊ አያያዝ ነው። አጠገቡ ድግሞ ጠንካራ በተመክሮ ያሰበለች፤
በዕውቅት የለማች የትዳርም አጋር አለች። ዘመኑን አድማጭ ነው ገናና መንፈሱ። ዕምነቱን የጣለበት መንፈስ አሱን በልጦ ሄዶ የማህበረሰቡ
ኩራት ሲሆን ማዬት የለማ ተፈጥሮ ምድራዊ ወይንስ ሰማያዊ ያሰኛል? የእሱን ሪኮመንዴሽን አንገት አስደፊ እንዳይሆን ተጠብቦበታል
የፖለቲካ ሳይንስ ሊሂቁ። ለማ የዘመን ሚስጢር ነው - ሥጦታም።
መንፈሱን አንበጥብጠው። ቅዱስ መንገዱን ክትር እዬሰራን አንወከው። ፈጣሪ የበቃችሁን ቃልኪዳኑን ያጥፋል። 27 ዓመት ተኖረ እኮ፤
17 ዓመቱም ሲደመር 44። ዛሬ ሰው በአንድ ቀን እንዲመረት እንሻለን። ችግሩም እፍ ተብሎ አንዲለቃላቅ እንሻለን። መከራ …. ማብቃቱንም
በአንድ ማዕልት ሱሪ በአንገት ይሁን ባዬች ነን። … ህመም።
በአንድ ወቅት የኛ ድምጾች የፓርላማ አባል ነበሩ፤
ዶር መራራ ጉዲና፤ ፕ/ በዬነ ጴጥሮስ፤ አቶ ግርማ … ተዚህ ላይ ማገናዘቢያ ማቅረብ እሻለሁኝ። የመንፈስ ግንባታ ሆነ ሚዛን የማስጠበቅ
ተልዕኮ የጨበራ ተዝካር ስላልሆነ።
„የጋዜጠኛ ሃኒ ማስታዋወሻ“ ጸሐፊ አቶ ፍቅር
ስንትአየሁ እንዲህ ይሉናል …. http://ethioforum.org/amharic/%E1%8B%B6%E1%8A%AD%E1%89%B0%E1%88%AD
„ዶክተር አቢይ አህመድ ማን ናቸዉ?“ በሚለው የዶር አብይ አህመድን የህይወት ታሪክ
ለመመርምር ያደረጉትን ጥረት ከገለጹበት የተወሰደ ነው። „የፓርላማ ተሳትፎ“ „በየትኛውና ለምን ያህል የፓርላማ ዘመን የህዝብ ተወካይ ሆነው እንደሰሩ ባይገልፅም የአብይ አህመድ ስም ከፓርላማ ጋርም እንደሚያያዝ ቀደም ብሎ በአዲስ አበባው ሸገር ሬድዮ ጣቢያ፣ በአሁን ሰዓት ደግሞ በስደት ላይ ባሉ ጋዜጠኞች በሚሰናዳው ዋዜማ ሬድዮ ላይ የምትሰራው ሀኒ ሰለሞን ፓርላማ ለመዘገብ በሄደችበት ወቅት የነበራትን ትዝብት አስመልክቶ በብሎግ የሰፈረ አንድ ፅሁፍ የሀኒን ምልከታ እንደሚከተለው አስቀምጦታል፡፡“ “ሀኒ በፌስቡክ ገጽዋ ላይም በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ላይ ተደጋጋሚ ትችቶች በመሰንዘር ትታወቃለች፡፡ ነገር ግን ልክ የዛሬ ዓመት አከባቢ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዳዲስ ሚኒስትሮቻቸውን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ለየት ያለ አስተያየት አሰፈረች፡፡ ሀኒ ወደእንቅልፋሙ ፓርላማ ስታመራ ቀልቧን የሚስቡ አንድ ሞጋች የፓርላማ አባል ነበሩ፡፡ ብዙ ጊዜ ባለስልጣናት እንዲጸድቅላቸው አንጠልጥለው የሚመጡትን ያልተደራጀ ሰነድ የሚያብጠለጥሉትና በነጻነት እንደልባቸው የሚናገሩት እኚህ ሰው ብቻ እንደሆኑ ሀኒ በጽሁፏ ላይ ትጠቅሳለች፡፡ ታዲያ በእለቱ በሚኒስትርነት ከተሾሙት ዝርዝር ውስጥ የእኚህን ሰው ስም ትሰማለች፡፡ እናም በኢህአዴግ እድሉ ከተሰጣቸው ለውጥ ሊያመጡ እንደሚችሉና ተስፋ ብናደርግ እንደማይከፋ ትነግረናለች፡፡” ጋዜጠኝነት
እንዲህ ይተረጎማል፤ ቀድሞ አቅምን በተስፋ መመጠን።
እኔም እላለሁኝ አጋጣሚውን
ሲያጋኙ ተደማጭነትን ማብቀል የባለቤቱ ግዴታዊ አቅም ነው። ከዛ አይደለም ሺህ ሚሊዮን መንፈስ ይራባል። ግን መንፈሳዊ ድጋፍ ሸቀጥ
አይደለም አይሸመትም አይቀናም። በአቅም ልክ የሚገኝ ረቂቅ ብቃት ነው።
·
የለማው ማልሚያ።
አቦ ለማ መግርሳ ግን ያውቃሉ። ለዛውም የሙያ
ልጃቸው ናቸው ለዶር. መራራ ጉዲና። የለማ መንፈስ ሃሳቡ ከግቡ ሳይደር ቅጭት እንዳይደርስበት፤ ወጌሻ ፍለጋም እንዳይኳትን - ለዛውም
ከተገኘ፤ የተልዕኮውን ሰራዊቱን በሙሉ አቅም እና ጉልበት መሰረት አስይዟል። በመንፈስም። ሄሮድስ መለስ ሞቱ አንድስም እንኳን ተተኪ
ማግኘት አልተቻለም። የተሻለ ልናገኝ እንችል ነበር ከነተጋሩ። ምን አልባት ቅን የሆነ ሰውኛ መንፈስ ያለው። ወጣቶቹን ስፈትሽ አግሬሲብ
ናቸው። የእኛ ጠረን የለባቸውም። ቁጡ፤ ተናዳጅ ሆነዋል። እያጣናቸው ነው። ይህን መንፈስ በትሁት ሥነ - ምግባር ገርቶ ወደ መኖር
ለማምጣት ፊት ለፊት ግማድ ነው። ገና ብዙ ሥራ አለበት የአብይ መንፈስ። ለዛውም ዕድሉ ከተገኘ። ፈጣሪ በቃችሁ ካለን። ድንግልዬ
የሰቆቃው ጴጥሮስን ሰምዕትነት፤ የሎሬቱን ዘመን ዝለቅ ብላ ምርቃቷን ከለገሰችን። እውነቱን ብናገር የአብይ መንፈስ ዕድሉ ከተሰጠው
„ስለ ድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች/ ሴቶች“ አምልከውን መራር
ደብዳቤ ተግ አደርገዋለሁኝ። ዕንባዬ ዋቢ ይኖረዋል ብዬ አስባለሁኝ። በፖለቲካ አስተሳሰቡ አንድም ነፍስ አደጋ ላይ እንደማይወድቅ፤
ግድያም እንደሚቆም፤ ሰራዊቱ ሀገር ጠባቂ ስለሆነ ወደ ካንፑ ተመልሶ ካለ ስጋት ወህ የሚባልበት አንዲት ጉልበታም ቃለምህዳን እጠብቃለሁኝ።
·
የሆነ ሆኖ፤
ሶሻሊዝም እንዲህ ነው ተቋምህን ሳትገነባ እራስህን
ተቋም አድርገህ „ሥምህን“ ይዘህ ትኖራለህ። ስታልፍም ዓላማህ አብሮህ ያልፋል። በቃ መራራ ሥንብት። ግንቦት 7 አንዲን የሚተካ
መንፈስ ሥላልሰራበት አላገኘም። ለዚህም ነው ይህ ሁሉ ዝብርቅርቅ። እንጂ አንቱ የተባለ ነበር ግንቦት 7። ሥሙ ብቻ ራድ የሚያስዝ።
ጭንቅላቱን ካቴና በለው፤ ቀጥ አለ። የለማ መንፈስ ግን እንዲህ አይደለም። ተተኪው ዋና አጀንዳ ነው። መሬቱን አለመልቀቅ የተወሰነበትም
ምንጩን ከአናቱ በተከታታይነት ህሊናን በሙሉ በብቃት የማበልጸግ ተልዕኮው ግዙፍ ስለሆነ። አባይ ምንጭ አለው። ምንጩ ከደረቀ እንኳስ
ለግብጽ ለራሱም አይሆንም - ለማ ይሄ ነው። ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ጋር ውድድር አለበት፤ ከራሱ ማህበረሰብ ከተፈጠሩት ጋርም
መሰሉ ይኖራል። ድርብ ተጋድሎ። ሌሎችም የአንድነት ሃይሎች አይዲዎሎጃቸው ቢኮሰመንም መፍጨርጨራቸው አይቀርም። ያው የኦህዲድ ውሳኔ
ግባ- ዕቱን ፈጽሞላቸዋል። ይሄ ብሄራዊ ከሆነ ጉዳቸው ፈላ ነው። በግልም አብሶ አማራ መሬት ተወዳዳሪዎች ይኖራሉ፤ መድረኩ ከሰፋ፤
ለ አንድነት ሃይል አማራ ማገዶ መሆን ስሌለበት። ስለዚህ ሁሉንም በለስላሳ መንፈስ በተግባር አቅሙ ማሸነፍ የሚያስችለው አቅሙ ብረት
መዝጊያ ጄኒራል ሲኖረው ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ ተጠብቦበታል።
·
ስለነገ ቸር ተመኝ ቸር እንድታገኝ ነው እና … አደቡ
ቢኖር …
የተጎዱ ሚሊዮን ነፍሶች በለስላሳ ይቅርታ አንደሚታከሙ፤
አይዟችሁ ኢትዮጵያ የእናንተም ናት እንደሚባሉ፤ በሌሉበት ሞት የተፈረደባቸው፤ የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው ሁሉ የቤተሰቦቻቸው
የሥነ - ልቦና የጭንቅ ጊዜ እንደሚያከትም፤ የህብረተሰቡ ጥያቄ በዕቅድ እና በመርህ ደረጃ እንደሚፈታ፤ ተፈጥሮን ቀፍዳጅ ወዘተረፈ
ህግጋት እንደሚሻሩ፤ በሰው ልጅ ተፈጥሮ የጭካኔ የመርምር ሥራ የሚካሄድበት የበቀል ማምረቻ ካንፓኒዎች መልክ የሚይዙበት፤ አብሶ
ክንፈ የደህነንት ማዕከል ውስጥ ህግ የማያወቃቸው አስረኞች
ባሊህ የሚባሉበት፤ ህግ በዜግነት የሚመሠረትበት፤ የሚመራበት፤ „ሰዋዊነት እና ተፈጥሯዊነት“ የመንፈስ ጌታ እንደሚሆኑ ትእግስትን
ለጊዜ ሸልሜ በተደሞ እታደምበታለሁ። የ43 ዓመት የመከራ ጉዞ በአንድ ማዕልት ድምጥማጡ እንደማይጠፋ የማደራጀት ህይወቱን ስለኖርኩት
አውቀዋለሁኝ። ጥቃቅን የግድፈት ክስተቶች ሁሉ በተከሰቱ ቁጥር መንፈሴን ደንጋጭ አድርጌ አብሬ መታመስ ሳይሆን መሰረቱን በሚያስተካክሉ
ጉልበታም እርምጃዎች ላይ አተኩራለሁኝ።
በታወቀም ይሁን ባልተወቀ ቦታ የታሰሩ ግፈኞች
የበቀል ሱሰኞች መፈተኛ ያደረጓቸው ወገኖቼ ሁሉ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ
ከእይዟችሁ አክብሮታዊ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ጋር ከምድረ ሲኦል ይፍታችሁ የሚባልበትን ዘመን እንፍቃለሁኝ። አቅም ያለው፤
ሃሳብ ያለው የሚፈራ ሳይሆን እንደ ልዩ ደጀን የሚታይበት፤ የመደማመጥ ጊዜን በአጽህኖተ ተስፋ እመኛለሁኝ። በግልም የቂም፤ የቁርሾ፤
የጥላቻ ዘግናኝ ወቅት መቃብር የሚወርድበትን ቀን ሽው ይለኛል። ከተፈጥሯችን ጋር ተጣልተናል። ዓይናቸውን ብቻ ይዘው የወጡ መከረኞች
እኮ እኩል አጀንዳችን ሊሆኑ አልቻሉም።
ቸር ወሬ እንድሰማ ጆሮዬን ቀና አድርጌ ለዘመነ
ቃና አቃናለሁ። ተስፋ ጥሩ ነው። ተስፋ ያውላል፤ ያሳድራል፤ ያኖራል፤ ያለማል፤ ያጸድቃል። ከእስር ቤት የሚወጡት ወገኖቼ እኮ በጠላት
ሐገር በጦርነት ተማርከው ታስረው የተፈቱ ነው የሚመስሉት። ለጉዳታቸው ቃል የለኝም። ቀረብ አድርጌ ጋዜጠኛ አስክንድር ነጋን፤ አቶ
አንዱ አለምን አራጌን የእማዋይን ፎቶዋን፤ የጫልትሻን በትካዜ ተፈታ እንኳን መወረር ሳይ መኖሬን ስለጠላሁት ገጻቸውን እያዬሁ ቃለ
ምልልሱን ማድመጡን መድፈር አልቻልኩኝም። ሰው በሐገሩ እንዲህ ባይታዋር? አቤቱ! መፈታታቸው እራሱ ደስታቸውን ሙሉዑ አላደረገውም።
ደስታቸውን የቀማው ሲኦል ውስጥ ያሉት ነፍሶች ጉዳይ ነው። እንጂ ወንበር አይደለም። ለዚህም ነው እማዋይ እና ትእግስት አንወጣም
ያሉት። እማዋይ እናት ናት ልጆቿን ጥላ ወጥታ ምን ደስታ ህይወትስ ሲኖር። ብቻ አይናቸውን ማዬትን እንደመልካም ነገር ሳስበው፤
ግን ደስታቸውን ለመፍጠር አጀንዳው ከባድ ስለመሆኑ ሳስብ ፈተና ቢሆንም የአብይ መንፈስ፤ የለማ መንፈስ፤ የገዱ መንፈስ … አቅሙን
በአቅሙ ከሰከነ ይሆናልን ብዬ ማሰብ መልካም ነው። ቢያንስ ለጤናዬ ስል። እንዳልሰበር።
·
ተመክሮዬ የሰጠኝ።
ሌላም ጓድ ገ/መድህን በርጋ የሚባል ሰው አወቃለሁ።
የሀገር ውስጥ ንግድ ሚ/ር ቋሚ/ ይሁን ም/ ሚር ነበር። እረስቸዋለሁ። ብቻ መጀመሪያ የጎንደር ክ/ሀገር የኢሠፓ የድርጅት ጉዳይ
ሃላፊ፤ በኋላም የሚዛን ተፈሪ ኢሠፓ ኮሚቴ አንደኛ ጸሐፊ ነበር። ገብሬ የመጀመሪያ ሥራው ያይሃል። በቃ ማዬት። ትንሽ ጊዜ ነው የምትበቃው።
ከአንድ የጎጆ ቤት እሳር ውስጥ አንድ ሳር የመምዘዝ ያህል ነበር እኔ ለእሱ የሪሰርች ሥራ ሲንቦልነት ሲወስን። ያን ጊዜ ከንግስት
ይርጋም አንሳለሁ። ሰውነቴም ቀጫጫ አንገቴ ብቻ የሚታይ ነበር። ወገብ ያልሰራልኝ ነበርኩኝ። ገብሬ ከመረጠህ በኋዋላ አንተ የአብራኩ
ክፋይ ነህ። እውሃ እያጠጣ በተስማሚ ቦታ እንድትበቅል ያደርግሃል። በተገኘው ዕድል ሁሉ ሁለመናህ የሚፋፈበትን መንገድ በር ይከፍትልሃል።
„ማድመጥ“ መፈጠሩን የምታዬው በገብሬ ወስጥ ነው። እራሱ „ማድመጥ“ የሚባለውን ስሜት ትዳስሰዋለህ፤ ከነሙሉ ቁመናው ታዬዋለህ።
ፍጹም አድማጭ ነው። በገ/መድህን በርጋ ቤት ደከመኝ የለም። ማትራስ ይሰጥሃል አዛው እያደርክ ትሰራለህ። ሥራ ከሌለህ ያመሃል።
ስትታመም ቶሎ መዳንህ የሚናፍቀህ ለስራህ ስለመድረስህ ነው። ሙሉ ስብዕናን በፍቅር ይሸልምሃል።
ከዚያ በኋዋላ በፈለገ ጦርነት ቀውጢ ውስጥ ሁን
አትሸነፍም። ህሊናህን፤ መንፈስህን፤ አቅልህን፤ ሥነ - ልቦናህን፤ ስሜትህን አይበገሬ አድርጎ ይገነበልሃል። ድርጁ ነህ። ዋሻ ውስጥ
ሆነህ እራስህን አደራጅተህ ትኖራለህ። መከራ ውስጥ ሆነህ መከራህን ሰፍስፍ ብለህ ወደኸው በደስታ ትኖራለህ። ጠንቃቀነትህ ኦክስጅንህ
ይሆናል። በዬትኛውም መድረክ ህዝብ ማደራጀት እና የመምራት ክህሎቱን በመፍጠር ይጠበብሃል። የሪሰርቹ ፊገር ነህ አንተ ለእሱ። በአንተ
ላይ ነው ሪሰርቹን የሚሠራው። ከዛ ሲጨርስ ይለቅሃል። ጠበቂ አትሻም። በሁሉም መስክ። ዕድገትህ ፍጠንቱን አንተ እራሱ አታውቀውም።
እኔ እና ሁለት ወንድሞቼ አንዱ ካናዳ አንዱ ላስቤጋስ የእሱ ልጆች ለመሆን ቅርብ ነን። ከሥሩ ነበርን። የበኽሯ ግን ሥርጉተ ነበረች።
አባቴ ውስጤን ሲያደራጀው የቆጠበው አንዳችም የክህሎት ቅብብል አልነበረም። አጀንዳው ነበርኩኝ። አኔን ሲያኝ እንኳን ተደሞውን አሁን
አዬዋለሁኝ። ጓድ ገ/መድህን በርጋ ጉራጌ ባይሆን ገብሬ በአማካሪነት ኦህዲድ ውስጥ እዬሠራ ነው እል ነበር። በህይወት ኑሮ ቃሉን
ብሰማ እንዴት ደስ ይለኛል። በኢሠፓ ውስጥ ኢዴአፓ የሚባል አንጃ ፈጥሮ ማዕከላዊ እያለ ነው ኢሠፓ የፈረሰው። ሄጄ እርግጥ አይቸዋለሁ፤
ከፍርሻው በኋዋላ ግን አላገኘሁትም የኢትዮጵያ ያህል ይንፍቀኛል። ስለምን? እኔን በሙሉነት ስለሰጠኝ። በዚያ ሁሉ ጦርነት ውስጥ
ሆኖ የሚጠሉትን ይንከባከባል፤ ያዳምጣል፤ የተሻለ አቅም እንዲኖራቸው ተግቶ ይሰራል። ቅን ሰው ነበር። ጥበብም።
አሁን በኦህዲድ ትውልድ እንዲህ ያለ የፖለቲካ
ብስለት፤ ልቅና ሳስብ ገብሬን በምለስት አስበዋለሁኝ። እርግጥ ጊዜ ባይበላቸው አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን በማደራጀት ህይወት ውስጥ
የአቅምን ፈጣራ ተጠብበውበታል። ሁለት ጊዜ መድረክ ላይ ተገናኝተን ነበር። አንድ ጊዜ የቅንጅት ምስረታ በሲዊዝ አሳቸውም እኔ የመወያያ
ሃሳብ አቅራቢዎች ነበርን። ሲዊዝ ውሰጥ የፖለቲካ ሰው መሆኔ የታወቀው ያን ጊዜ ነበር። ሁለተኛው ግንቦት 7 መሥራች ጉባኤውን ፍራንክፈርት
አማይን ላይ ሲያካሂድ እሳቸው በገላጭነት እኔ በሰብሳቢነት አብረን ተገናኘን። ለሁለተኛ ጊዜ። የገብሬ ልጅ ጥቂት ጊዜ ብቻ ያሰፍልገኝ
ስለነበር እኒህ ሰው ገብሬን ይመስላሉ ለማለት አልተቸገራትም። አዬኋዋቸው አውቅኳቸው። የስልክ የኢሜል ግንኙነት አልነበረኝም። ምን
ለማግኘት? አይስፈልገኝም ነበር፤ አሁን ያ ታላቅ መንፈስ ግዞት ላይ ነው ያለው። ኢትዮጵያ መፍትሄዋን ከበቀል ጭካኔያዊ ጫካ መስፈታት
አለባት። አሁኑኑ! እሱም ዜጋዋ ነው። የልጅ የክትና የዘወትር የለውም። በሃሳቡ ልዩነት የተቀጣው ዘመን የትውልድ ዕዳ ነው።
የሆነ ሆኖ ቃሉን አልደግመውም። ጸሐፊ አቶ ሰርጸ
የሄዱበትን መስመር ጥሶ የሚወጣ ለአፍሪካ ኩራት እና ተመስጋኝነት የሚያጎናጽፍ የተግባር ዓራት ዓይናማ ትጉኽ ገበሬ ይኖራታል። ለጥቁሮችም
መከታና ጋሻ። ይህ ነው የሥላሴው ሚስጢር ዕድምታ። ከዚህ በላይ መሄድ አላስፈለገኝም ላለፈው ጹሑፎት ያሰናደሁትን ምርኩዝ እለጥፍና
አስነበታለሁኝ። ከዚህ ጹሑፍ በሆዋላም ያሻወቱን ካልደከመወት ይጫሩ። ፍሬ ካገኙ። ቀድሞውንም የአብይን መንፈስ አልተቀበሉትም። ለኦሮምያ
ብቁ ያልሆነ ሰው ሀገር ሲመራ ጊዜ ያሰተምረዎታል። ምንአልባት አሁን የአማራ ዘር ያላቸው ብቻ ሳይሆን አማራነቱ መነሻው መሠረቱ
የዘር ግንዱ መረጃ ከተገኜ ደግሞ ሌላ የጦርነት ዓውድ የምንጠብቀው ይሆናል። ምን አልባት ውልብልቢቱ ከተገኘ እሱ ይሆናል ነውጥ
ያስነሳው። አይዋ ጊዜ አባ ዝምታ ግን ገድልን በተግባር አንቆጥቁጦ ያሳያችሁዋል። በጣም በርግጠኝነት!
·
ከእስር ለተለለቀቁ አርበኞቻን በሙሉ።
በተረፈ ከእስር ቤት የወጡ ቅኖቹ አርበኞች በተለይም
ከልባቸው ሆነው ሂደቱን መከታታል አለባቸው። ኮ/ደመቀ ዘውዱ ለውጩ ፖለቲካ ምልክት አይደለም። የእናንተ ከእስር መለቀቅም መርዶ
ነው የሆነው። የትኛውም ስብስብ ዕዱልን ቢያገኝ ወያኔ ከሰራው በከፋ ሁኔታ በተለይ የአማራ መከራ ይቀጥላል። ስለሆነም ለማ - አብ - ገዱ - አንቤ መንፈሱ አንድ እና ወጥ ነውና በውስጥነት ተገስ
ብላችሁ አድምጡት። እኔ አሁን ውጪ ካሉት ሚዲያዎች የአማራ ማስ ሚዲያ ቢያናድድኝም ይጥመኛል። „አማራ“ ከሚለው መንፈስ ጋር ፍቅር ይዞኛል። አማራነቴን ወድጀዋለሁኝ።
ማዳመጥ ካለብኝ እኔ አማራን ሚዲያ እና ኦቢኤን ቴሌቪዥን ብቻ ነው። ራዲዮ ከተባለ ህብር እና ቢቢኤን፤ ቃለ ምልልስ ከሆነ ደግሞ
ኤስቢኤስ ወይንም ሙግት ከኖረ የአሜርካ እና የጀርምን ድምጽ፤ ህሊናዬ ታስረው የተፈቱት ደስታ የጋራ ባልሆነበት ዘመን ሌላውን የማድመጥ
አቅም የለውም። በውነቱ አቃተኝ። ፈተነኝ። ፈተለኝም። ሰው መሆን አራሱ ጦርነት ታውጆበታል። ሌላ የስቃይ ነጋሪት ይጠበቃል። ልክ
እንደ ቆሼ ሥም - የለሽ ሴራ። ሌላ ተጨማሪ እሰረኛ ማየት ተናፈቀ …
·
ለእኔ።
ከሁለቱ አይንሽ የትኛው፤ ከሁለቱ የአፍንጫ ቀዳዳሽ
የትኛው፤ ከሁለቱ ጆሮሽ የትኛው፤ ከአጭሩ እና ከረጅሙ አንጀትሽ የትኛው ይወገድ ብባል፤ ሁለቱንም አልሻም ነው የምላው። ለእኔ ለማም
አብይ፤ አብይም ለማ ነው፤ ሁለትዮሹ አመራር በአሃታዊ መንፈስ ነው ለመሪነት የተዘጋጀው። ስለሁለቱ እኩል ነው ስሟገት የነበርኩት።
እግዚአብሄር እማመሰግነው ሁለት ወጣቶች በዬራሳቸው ቀለም እና ውበት ብሄራዊ ሃላፊነትን ለመቀበል ብቁና ምጡቅ አቅም ያላቸው ስለመሆኑ
ከመሞቴ በፊት አምላኬ ስለ አሳዬኝ አመሰግነዋለሁኝ። ደስታዬ ከወጣቱ በመሆኑም ደግሞ ድርብ ነው። ዘመኑን መርቶ በዘመኑ ተወቃሽ
መሆን የአባት ነው። ዕድሉን ሳያገኝ ወጣቱ ትውልድ በዙር የወቀሳ ናዳ የሚሸከምበት ዘመን በመቀዬሩም ደስታ ብቻ ሳይሆን ሐሴቴ በዕሴት
ሙሉዑ ዘኩሉ ሆነ። ዘመኑን ራሱ መምራት አለበት - ወጣቱ። ለኪሳራው ወቀሳ፤ ለትርፉ ምስጋና መቀበል የእሱ እንዲሆን መታታር አለበት።
የራሱ ነው ዕድሉ እና። ተመስገን! ፍቅር የሰው ቀለም ነው!
አማራነቴን ያገለለ መንፈስ ሁሉ ክፍሌ አይደለም። አማራነቴን ሰወደው በውስጤ እንዳሻው በክብር እንዲንሸራሸር ፈቅጀለት ነው።
·
የእነ አባ ቅንይ የእኛዊነት አርበኞች ዕድምታ።
https://ethioexplorer.com/%E1%8B%B6%E1%8A%AD%E1%89%B0%E1%88%AD-
ዶክተር አቢይ አህመድ ማን ናቸዉ? (ፍቅር ስንታየሁ)
አዲሱ
የዶ/ር አቢይ መንገድ (ወንድወሰን ተክሉ - የኢትዮሚዲያ አምደኛ)
ከዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ስሰራ የማልወዳቸው 5 ነገሮች
ሰውየው! ሚኒስተር አይመስልም – (ቃልኪዳን ኃይሉ)
·
ሰዋዊነት ከኖረ … በዚህ ውስጥ የዶር. አብይ አህመድ
„አስመሳይነታቸውን¡“ ማዬት ይችላሉ … ውድ ጸሐፊ አቶ ሰርጸ ደስታ።
Ethiopia Dr abiy ahmed በመጀመሪያ ካፖርትህን አዉልቅ
https://www.youtube.com/watch?v=qD9EeCFEraA&t=87s
stic news
Ethiopia Dr abiy ahmed በመጀመሪያ
ካፖርትህን
አዉልቅ
Ethiopia - New Dr Abiy - አንድ ሰዉ ብቻዉን መለወጥ ይችላል!
https://www.youtube.com/watch?v=0IJZIQdb3Uc
Dr. Abiy Ahmed - አዲሱ ትውልድ ምን አድርጓል?
Abiy Zema - New music Video 2018 -
Dedicated to Dr. Abiy Ahmed Ali
የስው ህሊና ስለመኑሩ ቢመሰክር? ዶክተር አቢይ አህመድ ማን ናቸዉ? (ፍቅር ስንታየሁ)
Ethiopia Dr abiy ahmed
በመጀመሪያ ካፖርትህን አዉልቅ
Ethiopia - Dr Abiy ኢትዮጵያን ማሸጋገር ይቻላል!
Ethiopia Dr abiy የሰዉ ልጆች ልዩ ብቃት ክፍል አንድ
Ethiopia Dr abiy የሰዉ ልጆች ልዩ ብቃት ክፍል ሁለት
ስለሴት ተማራሚዎች
አብረን እንሩጥ
ልብ
የሚነካ
አስገራሚ
ንግግር Dr abiy ahmed # mind set
93,243 views
ethiopia dr abiy አብይ አህመድ ስለሙስና 2
AGENDA
ጋዜጠኛ አንተነህ ከበደ ስለ ዶ/ር አብይ ክፍል 1
ዶክተር አብይ አህመድ ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር አድርገዉት ከነበረዉ ቆይታ የተቀነጨብ AGENDA
D.R Abiy speech
ኢትዮጵያ - ሚኒስትሩ በንባብ ለሕይወት ላይ / Ethiopian Minister about Reading and Life,
Ato Abiy Ahmed.
Dr Abiy Ahmed interview with Amhara TV
Abiy ahmed speech at Gonder part 1
Dr Abiy Ahmed about social media, አብይ
አህመድ፣ ሶሻል ሚዲያን
ልናቆመው አንችልም
Abiy ahmed speech on Unity
Ethiopia Abiy Ahmed ስደተኛዉ
ጋዜጠኛ ስለ ዶ/ሩ
ስለ 1 ለ
5 ዶ/ር አብይ
አህመድ
Ethiopia Dr Abiy ሳይንሳዊ
ትንታኔ 1
Tech Science TV
Program Episode 39
Social Capital
Ethiopia: Exclusive
Interview with Dr. Abiy Ahmed on the direction of Ethiopian Politics
Dr. Abiy Mohammed ሕዝብን የሚያረጋጋ ንግግር ተናገሩ
ሰበር : ለማ መገርሳ እና ዶ/ር አብይ አህመድ በድጋሚ ታሪክ ሰሩ
·
እንደ መከወኛ።
በተረፈ ስለተዘቅዝቃ ተስቅላ እዬተደበደበች ስላቅን ለማድመጥ ስለተገደደችው ለጋ ወጣት
ጫልትሻ፤ ቀንበጥ ጥፍሯ ሲወልቅ በመርዝ ደንዝዛ ስለተሰቃዬቸው ንግስትሻ፤ ጡቷ ሲተለተል የመስቃ በረድ ለረበባት እሩጉዋ እማዋይ፤
አምጣ ወልዳ በሱዳን ወታደር ልጇን በዬዕለቱ ስለ-ምትገብራዋ የጋንቤላ እናት ሁሉ፤ ልጇ በቤንዚን እራሱን ሲቃጥል ጢሱን ተንትርሳ
ለምታልፍ የየኔ ሰው ገብሬ ምስኪን እማማ፤ በልጇ እሬሳ ላይ ተቀምጣ ለምትደበድብ ምንዱብ ታድሎሻ፤ በህዝብ ማህል የዘር ማፍሪያ
በጥርስ ስትጎትት ካለሃጢቱ ስለተሰዋው ጽንስ ስለደራዋ የመከራ ቤተኛ እህት እናት፤ በሱዳን ወታደሮች ለከፈን ያልበቁ ህጻነት በጅምላ
ሲጨፈጨፉ ላዬች የአንባ ጊዮርጊስ እናት፤ ባህርዳር ላይ በረድፍ ለተጨፈጨፉ ሰምዕታት እናት - እህት - አክስት - ሚስት ጭንቀቱ
ካለዎት የአብይና ትርጉሙነት የዛሬ፤ ሰውሰራሽ፤ መሰረት አልባ ስለመሆኑ ያስተካክለዋል ዝበቱን ብዬ አስባለሁኝ፤ ቅንነትን ካልፈሩት
ወይንም ካልተደበቁበት። አብይ የድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች ተሟጋች ነው። ስለ እኩልነታችን ብቃታችነን በአደባባይ የመሰከረ
ሰማዕታችን፤ ገድላችንም ነው። ከእኔ መንፈስ አብይን መቼውንም ቢሆን ፈንቅሎ የሚወጣ አንዳችም ሃይል የለም ከሞት በስተቀር። ስሞትም
አማደርገውን አውቃለሁኝ። ኑዛዜ ይኖረኛል። ደህና ይሰንብቱልኝ።
„ለሰከንድ የኢትዮጵያ አንድነት ጥያቄ ውስጥ አይገባም“ ከፓን አፍሪካዊስቱ እና ስለጥቁርነት ተሟጋቹ ከሆኑት
(ከዶር አብይ አህመድ - የተወሰደ።)
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ
የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
የኔዎቹ ወስጥን ለመተርጎን ከውስጥ መነሳት የሚቻለው
ነፃነት ከራብን ብቻ ነው።
መሸቢያ ጊዜ ከልብ መደማመጥ ጋር ይሁን ብለናል።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ