"እግዚአብሄር የህዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ ያዕቆብ ደስ ይለዋል"
ፅናት አልከኝ?
„እግዚአብሄር የህዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፣ እስራልም ሐሤት ያደርጋል።“
(መዝሙር ፲፫ ቁጥር ፲)
ከሥርጉተ ሥላሴ (Sergute©Sselassie)
07.05. 2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላድ)
07.05. 2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላድ)
***
እህ ፅናት ...
ላትፀና ፅናት ያልከው፤
ዬት አግኝተህ ተጋጠምከው?
በፍልሚያውስ ምን ተገኘ?!
ምን ተነግሮ? ምን ተሰኘ?
እንዲው ታዲያ ...
በደፈናው ፅናት ያልከኝ፤
ፅናትማ ወዬት ሊገኝ?
ካልዘርኽው ዬት ተገኝቶ?
ካላረምከው ምን አፍርቶ?
አበራይተህ ካልከወንከው፤
የወዛ አይደል ከጎዳና የምታፍሰው።
እቴ አሱ ...
መቼ ሆነና ሜዳ በቀል?
ወይንስ አይደል አጉራ- በቀል፤
በስተዳሪ አይነቀል ።
እህ ፅናት ...
ፅናትም ወዴት ይገኝ?
ቢሆንማ ... ከችግሬ ከጥበቴ ከአሳሬ
ከጭንቀቴ፤
መፍትሄ ነበር ለህይወቴ።
እኮ ፅናት ...
ፅናትማ ተዬት ይገኝ?
ብችልማ ... ከጩኸቴ ከሮሮዬ፤
ቢሳካማ ... ከለቅሶዬ ከምሾዬ፤
ቁልፌ ነበር መክፈቻዬ።
ታዲያ ፅናት ...
ፅናት አልከኝ!
ፅናትማ እንዴት ይገኝ?!
አዎን ... ፅናት ...
ከዝቀጩ፤ ከአረንቋው
ከውድቅቱ፤ ከደብዛዛው፤
ከብልጭታው፤ ከጉምጉምታው፤
ከፍንድቅድቁ፤ ከጭራው፤
ከፍሰሃው፤ ከብሥራቱ፤
ይጋራዋል ከእያይነቱ።
አያ አጅሬ ...
ጭራ የለሽ፤ ውለ-ቢስ ነው - መቋጠሪያው
ቀልብ-ቢስ ነው፡ የእስትንፋሱ መናኽሪያው።
ከመክሊት የግጥም መድብል መጸሐፌ የተወሰደ።
1985 ዓ.ም መካኒሳ አዲስ አበባ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ