ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ ምህዳን ነውን ...?
ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ ምህዳን
ነውን የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስቴር ቅብዕ የሚሰጠው? እንዴት ተቀለደ? እንዴትስ ተደፈርን?! ንቀቱ ደንበር የለውም!
ከሥርጉተ ሥላሴ 01.03.2018 (ከጭምቷ -
ሲዊዘርላንድ)
„ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች“ (መዝሙረ
ዳዊት ምዕራፍ 67 ቁጥር 31)
- · በር።
ከኤርትራ የሚነሳ ወጀብ ሁልጊዜም መንፈሳችን
ከፋፍሎ፤ አቅማችን ተርትሮ ሲያዋጋን ኑሯል። አገር ብለዋል፤ ሆነዋል። ምን ይፈልጋሉ? ስለምን ከኢትዮጵያ እራስ መውረድ እንደማይፈቅዱት
ሚስጢሩ አንድ ነው። አቅም ያላት ኢትዮጵያን ከመፍራት የመነጨ
ነው። ትናንት የተፈጠረችው ኤርትራ ዛሬ ከ3 ሺህ ዘመን በላይ የታሪክ አውራ የሆነችውን የኢትዮጵያን ቅዱስ መንፈስ ለመምራት፤ አንበርክካም
ለመግዛት ትሻለች። አለማፈር። ልክንም አለማወቅ። ለነገሩ ኤርትራ በምታሰናዳው አጀንዳ እኮ ነው ሁለመናችን ስንገብር የኖረንው።
አቅማችን ለቁርሾ ስንቅ ስናጭ፤ ስንድር የኖርነው። በሃሳብ ገብታ ውጊያ ስንት አቅም ጊዜ እና መዋለ ንዋይ ፈሷል።
„ሁሉም የኢህአዴግ ምክርቤት አባላት ለግንባሩ ሊቀመንበርነት መወዳደር እንደሚችሉ ዘረኛው በረከት ስምኦን ገለፀ“
·
ኢትዮጵያን ሞታ የማዬት ናፍቆተኛው የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ
የመንፈስ ርግጫ።
„ለራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች።“ የማረተ ቆርቆሮ ተሸክሞ ዕድሜህ ይፍታህ በተባለለት በኤርትራ ህዝብ ላይ የበዬደው የፕ/ኢሳያስ
አፈወርቂ ካቢኒያዊ መንፈስ የወያኔ ሃርነት ትግራይን አዝሎ እና ከብክቦ ለዚህ ሁሉ መከራ እናት ሐገር ኢትዮጵያን መዳረጉ አልበቃ
ብሎ፤ ዛሬም በሰላዩ የቁርጥ ቀን ልጁ በአቶ በረከት ስምዖን አማካኝነት 4ኪሎ ገብቶ የጠ/ሚር ምርጫ ቀዳሚ ወሳኝ ሆኗል። ፕ/ ኢሳያሳያስ
አፈወርቂ መንግሥት አዝሎ ለወግ ለማዕረግ ያበቃው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ጋር በተፏከተበት እንኩሮ ዕሳቤ ሲሸነፍ የተለያዩ እርምጃዎችን
ወስዷል። ሁለቱንም ያጣላቸው ባለቤት የሌላት እናት ምድር የኢትዮጵያ ህዝብ ሐብት እና መዋለ መንፈስ በበላይነት የመዝረፍ አባዜ
ነው። ከዚህ በሆዋላ ነበረ ደግሞ በጦርነትም፤ በደንበር ይገባኛልም
ለሌላ መከራ ለ100ሺህ ኢትዮጵያውያን ዕልቂት ጦርነት የተጎሰመው። መምራት ካልቻልኩኝ ሞት ማዋጅ ብሎ ተነሳው የፕ / ኢሳያስ አፈወርቂ
መንፈስ የሰው ግድያ መጣል ዶክትሬኑ ነው። ይህም ቢሆን ኢትዮጵያን ጠቅልሎ ለመግዛት የሚያስችል አልሆነም። ከድህነት እርከን ሊያወጣው
አላስቻለውም። በባህር ተከቦ የሴራ ጉንጉን ማምረቱም የተፈለገውን ያህል የ4ኪሎውን በትረ መንግሥት ወንበር ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር
አላስቻለውም።
- · ዕምቅ - ህመም።
… ስለሆነም አይተኜው - አይደክሜው - አይታክቴው
ሴራው የመሪነቱን ሚና ለመጫወት ለተከፋችሁ ሁለ በሬ ክፍት ነው ብሎ አቅም ያላቸው ወጣ ሲሉ እያደነ አሰወገደ። ያም ሆኖ አሁንም
ተራው እስኪ ደርስ የሚጠበቅ ሌላ ተራኛ አዘጋጅቶ በወ/ሮ አና ጉምዝ ሰረገላ 4 ኪሎ ከች እላለሁ ሲል ኦህዲድ ፊሽካ ነፋ። ጨዋታው ተቀዬረ። ለዚህም ነበር አቤቶ
በረከት ስዕምዖን በአማራ እና በኦሮሞ ጉባኤ ላይ መገኝትን ያልፈቀዱት። ብዙ ጸሐፊዎች ስለምን ሌሎችስ ብሄረሰቦች አጀንዳችን አይሆንም
ይላሉ። በኦሮሞ እና በአማራ ማህበረሰብ አባ አዋጉ የኤርትራ መንግስት
የሴራ ውቅያኑስ ስላለ ነው። የትግራይ እና የሌላው እማ በአንድ ቅዱስ መንፈስ የሥርዬት ቃለ ምህዳን የታጠባል። የሰውን ልጅ የሚገዛው፤
የሚያስተዳድረው ንዑድ መንፈስ ነውና። በኦሮሞ እና በአማራ የነበረው እኮ የመሬት ይገባኛል አይደለም፤ አልነበረም የመንፈስ ጉዳይ፤
የሥነ - ልቦና ጉዳይ ነው። አሁንም ከትግራይ ማህበረሰብ የነጠለን ይሄው ነው። ይህ ደግሞ በአንድ ቅን፤ ቀና፤ ብልህ፤ ጥበባዊ
መንፈስ የተሸከምነው፤ ስንቃችን ይሁን ብለን የፈቀድልነትን ጥላቻ እና የበቀል ዳመና ይገፈፋል። ላይ የወጣው የተንጠራራ መንፈስ
ግማሽ መንገድ ይመጣል፤ ታች ላይ አቧራ ላይ የወደቀው የሚሊዮኖች ድምጽ መንፈስም ወደ ማህል ይገሰግሳል መገናኛው ፌርማ ኢትዮጵያዊነት፤
ሎሬታዊነት፤ ይድነቃቸዋዊነት፤ አፈወርቃዊነት፤ ሰዋዊነት፤ ተፈጥሯዊነት፤ እኛዊነት ወዘተ ይሆናል። ግን መንፈሳችን ለባዕድ ባንዳዊ
ተልዕኮ አውሰን ዕድላችን ካላሾለክን። „ልብ ያለው ሸብ“ የሚሉት
ጎንደሬዎች ለዚህ ነው።
ሌላው ይቅር ወሎ እና ትግራይ፤ ጎንደር እና ትግራይ
ተለያይተው ይቀራሉ ብሎ ማሰብ ቀርቶ በመላ ኢትዮጵያ በሥነ - ልቦና፤ በሃብት ክፍፍል፤ በዘበጠ አያያዝ የተጎዳው፤ የቆሰለው መንፈስ
ሊያገግም የሚችልበት ንዑድ ህሊና በመዳፍ አይኖርም ብሎ ማሰብ ጸሐይ አልተፈጠረችም የማለት ያህል ነው። ብዙ መንፈስን የሚያጥቡ
ተግባራት ይሠራበታል፤ ግን አሁንም ወያኔ ሃርነት ትግራይ የጫጉላ ጊዜውን ከሻብያ ስውር እና ግልጽ የሴራ መንጋጋ አውጥቶ ኢትዮጵያ
ችላ፤ ራሷን የማንቀሳቀስ አቅሟን ማወጅ ከቻለች ብቻ ነው። በብቁ ኢትዮጵውያን ክህሎት „ኩራት“ የሁላችን መታመን በንጽህና ስንቀበለው
ብቻ ይሆናል የምህረት ዓዋጁ መለከት ጸበል የሁላችን የሚሆነው። የህሊና ልቅናችን እንደ ህልሙ ሻብያ የትግራይ እርድን እንደ ቋመጠ
ኩም ሲያደረግ። ቀጣዩ የዒላማ ተኩስ የሚጠብቀው ሻብያ ይሄው ነውና። ለዚህ ደግሞ መዳህኒቱ ዘመን የሰጠን በሙሉ ኢትዮጵዊ አቅም
እና ችሎታ፤ ትእግስትና ትህትና „ሰውን“ ማዕከል ያደረገ ብቃትን የታጠቀው መንፈሰ ለማ፤ አብይ፤ ገዱ፤ አንባቸው ይወጣዋል። ታሪካዊ፤
ትውልዳዊ፤ ብሄራዊ፤ አህጉራዊ፤ ዓለማቀፋዊ ትልዕኮውን በአደራ አውጪነት አዲስ መጸሐፍ ይጽፋል። ጥበቡ የሰማይ እንጂ ሰው ሰራሽ
አይደለም። ብናዳምጠው። ስርክራኪ ነገሮችን ጥርግርግ ብለው መልክ የሚይዙበት ዋዜማ ላይ ነን። ፈቃደ እግዚአብሄር ከተደመጠ በማሸነፍ
ውስጥ ትርምሱ መልክ ይይዛል። ስጋት ድል ይነሳል። ኢትዮጵያ በአቅሟ
ልክ የአፍሪካ ብቁ ናሙና ትሆናለች። ይህ እንዳይሆን ነው ብርጌዱ የሻብያ 4 ኪሎ ላይ ጦርነቱን አሁን የከፈተው። የወያኔ
ሃርነት ትግራይ „የ ሻብያ ተለላኪ“ እያለ የሚያሰራቸውን ወገኖቹን የመንፈስ ነፃነት አውጆ ከውስጡ የተሸጎጠውን የ ኤርትራ ሰላይ
በቁጥጥሩ ሥር ያውል ይህ ነው የአንድነቱ ልዑል የዘራይ ደረስ ብሄራዊ፤
ትውልዳዊ፤ አደራዊ ጥሪ።
የፕ/ ኢሳያስን መንፈስን ተከትሎ ከመላ ኢትዮጵያ
ህዝብ ጋር ደም የተቀባው ወያኔ ሃርነት በሚያደርገው ተግባር የተደሰተው የአቶ በረከት ስምዖን መንፈስ ጎንደር ላይ ጭኖት የኖረውን
ቀንበር ዛሬ የመላ ህዝብ ሊያው፤ ሊያስተውለው እንዲችል የዋልድባ አበርንታት መከራ አዲስ ገድለኛ ምዕራፍ ከፍቷል። መከራው እራሱ
መጨረሻ የለሹን የሴራ ጥልቅት ፍንተው አድርጎ እያሳዬን ነው። በርቱ¡ ኢትዮጵያን አዳክማችሁ ታሪካችሁን አፍርሳችሁ የትግራይን ትውልድ ለነገ አንገቱን የደፋ፤
መንፈሱን ያጣ፤ በሰቀቀን እንዲኖር የሚያደርግ ግፍ ስተፈጸሙ ፋሲካዬ ነው ብሎ ታጥቆ የተነሳው የአባ ሲኦሉ የአይበርክቴ መንፈስ
ዛሬ ገመናው እንደ ቄጤማ ነስንሶታል። የ27 አመቱ ሴራ እንሆ ዛሬ የገመናውን ሆድ ዕቃው ተዘረገፈ። ኢትዮጵያዊ አቅም አንቱ፤ አህዱ
ሲል ጦርነቱ ባድመ ላይ ሳይሆን 4 ኪሎ ላይ ሆነ። ዕድምታው ይሄው ነው። ሚስጢሩም ይሄው ነው። ለዚህ መንፈስ ነው አሁን ጋሼና
ጃግሬ ተሁኖ ዶር አብይ አህመድ ላይ ዘመቻው አና ያለው። ለማም ተወዶ ተከብሮ ተፈቅሮ ተናፍቆ አይደለም። አይተናል ቆራጣ ክብር
ተነስቶት እንደ ነበር። የእኛ መንፈስ ነው ለክብሩ ለልቅናው ሌት ተቀን ተግተን በመረጃ ሞግተን መልክ አስይዘን በታኙን መንፈስ
ሁሉ ልክ ያስገባነው። የአሁኑ መታመስ የኤርትራ የሞት የሽረት ተጋድሎ ጃኬት ስለመሆኑም ጠንቅቀን እናውቃለን። ለማ ቢመረጥም ሌላ
እሳት ይነድ ነበር ትዳሩ ምንትሱ ቅብጥርሱ ኮፌሌ አድጋ ግን መባሉ ይታወቃል። ቅምጥ አቅሟ፤ ታታሪነቷ፤ ሥራ ህየወቷ ስለመሆኑ፤
እንደብረት የጸናች ስለመሆኗ ሳይሆን የዘር መቆፈሪያ ይገዛ ነበር። ከዚህ ዘር ቀዳማይ እመቤትን ማዬት አንሻም ተብሎ ሌላ ዘመቻ
ደግሞ ይሰላ ነበር። እንተዋወቃለን። መናጂያ፤ መበተኛ ነው የሚፈልገው። ኤርትራ የምትመራው ሁለት - ሦስት አራት ሐገርነት። ኢትዮጵያን
አፍርሶ ገናናዋን ኤርትራን ማዬት እና ማሳዬት። በቃ። በአደባባይ ትእግስትን ተደሟችን አድርገን እንጂ ሰምተነዋል። ሁሉን በዚህ
መሥመር አንፈርጅ ብዬም ተሟግቻለሁኝ። ስለዚህ ብቻ እያሰብን መንፈሳችን ለአሉታዊ ነገር አናባክን ብዬ ትህትናዊ ማሳሰቢያም ስጥቻለሁኝ።
- · የአሁኑ - ገመና፤
ወደ ቀደመው ስመለስ፤ ለነጻነታችሁ ከእኔ ወዲያ
ላሳር ያለው ሻብያ ድምጽን የማድመጥ ቃና የያዘ መስሎ የነጻነት ራህብተኞችን ጥግ እሆናለሁ ያለበት ጥምልምል ጥንግ ጥቅርሻማ ድርብ
ሴራ እንሆ ተጋለጠ። ይኸው በአደባባይ እርቃኑን ቀረ። ቅኖች ልባቸውን ሰጥተው ነፃነትን ናፍቀው ግን ጭንቅላታቸውን አቶ አንዳርጋቸው
ጽጌን ለቀረመት እርክክብ ሲፈጸም እንኳን ልብ ያላሉት አዚም ነበር። በቀደመው ጊዜም ዘመን የማይተካቸውን የኢትዮጵያን አርበኞች
ግንባር መሪ መኮንኖች እዛው ተገብርዋል። ኢንጂኒር ሳይንቲስት ቅጣው እጅጉ ያን የአርበኞች ፓርቲ ባይመሰርቱ፤ ራዕያቸውን ከናሳ
ሊቅነታቸው ጋር አዋዳው የኤርትራን መንግሥት አምነው ውስጣቸውን ቧ አድርገው የ ኢትዮጵያን ብሩህ ዕውቀታዊ ተስፋ ባያሳዩ ኖሮ፤
የሰውር ጥቃት ሰለባ አይሆኑም ነበር። የውስጥ ብቃታቸው እራድ አስይዞ ለሞት የዳረጋቸው ሚስጢር ይኸው ነው። አሁንም የዶር. አብይ
አህመድ ዘመቻ የዛ ልቅና መንፈስ ስለበጠበጠ ብቻ ነው። ዳግማዊ ቅጣው ስለተወለደ። ሁለቱም የከፋ ጅማ ልጆች ናቸው።
ለዚህም ነበር አብይ ኬኛ! ብዬ ስጽፍ የሴራው
ቦንዳ አቶ በረከት ስምዖን እንዲሁም ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ሊተኙላቸው እንደማይችሉ፤ እሳቸውም ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አበክሬ
በተደጋጋሚ ያስገነዘብኩት። ሳይንቲስት ኢንጂነር ቅጣውን የበላው አውሬ አሁንም አግጥጦ አሰፍስፎ መጥቷል። የቅጣው ህልፈት ውስጥህ
ገብቶ ያንገበገበህ ሁሉ አሁን ጠንክረህ ታግለህ አውሬውን ወደ ጉድጓዱ መመለስ ግዴታህ ነው። የቅጣው ደመላሽ ለመሆን ሴቷም ቀበቶዋን፤
ወንዱም ቀበቶውን ይፈትሽ። ይሄ ብሄራዊ ግዴታ ነው። „ሰማያዊ“ „እናት“ ፊልም መሥራት ብቻውን ለህልም አያበቃም። ራዕይህን እያደነ
ሲበላ ለነበረው የሻብያ አውሬ በማያዳግም ሁኔታ አይቀጡ ቅጣት መስጠት ዛሬ፤ አሁን በምንወስደው የእርምጃ ልክ ይወሰናል።
ሁሉም የተስፋዬ ገብረ ጃርት መንፈስ ሃብቴ ያለ
ሁሉ፤ ተራው ሲደርስ ያገኛታል፤ ዛሬ ለተስፋ ቅልጣን ያሰኘው ሁሉ፤ የነገ የእርድ ቅርጫ ባለተራ ነው። የሻብያ መንፈስ አይምሬ ነው።
ምን ተርፎ ታይቶ፤ ለዛ ቅን አንዳርጋቸው ጽጌም አልሆነም። ሁሉም ደሙ ተወደደም ተጠላም „ኢትዮጵያ“ የሚል ነው። ይህ ደግሞ ለኤርትራ
መንግሥት ካቢኔ የመርዝ ቦንብ ነው። ከዓለም የትኛው ሐገር ይጥፋ ቢባል ካቢኔው ኢትዮጵያ ነው የሚለው። ህዝቡ ግን ምን አልባትም
በዓለም ደረጃ የጉርብትና ናሙና መሆኑን እኔ አራሴ አፌን ሞልቼ እመሰክረለታለሁኝ። ታናሽ ወንድሜ እንዲህ ይላል „ኤርትራውያን ለቤተሰባዊ
ኑሮ በተለይም ለእኛ ቤተሰብ ክፍላችን ናቸው“ ዕውነት ነው። እንዴት እነ ጋሼ ማህሪን፤ ጋሼ በዬነን፤ ጋሼ ልዑልን፤ ጋሼ ተስፋ-ማርያምን፤
አባ ገረማርያም ጎኔን፤ ጋሼ ጎይቶምን፤ አባ ተክሌን፤ አባ አካሉን፤ እትዬ ሽታዬን፤ እትዬ አልጋነሽን፤ የራሳቸውን የሴራው ተራራ
የአቶ በረከት ወላጆችን እናት ብሬን፤ አባ ዝምታን አቦይ ገ/ ህይወትን የፍቅር ጡት ጠጥተን ነው ያደገንው። አሳምረን እናውቃቸዋለን።
የማህበራዊ ኑሮ ማህንዲሶች ናቸው - ኤርትራውያን። በሽታው ያለ ከአናቱ ነው - ለዛውም በቅይጥ ማንነት።
- · ሚስጢር።
አቶ በረከት በባህርዳሩ ኮንፍረስ ያልተገኙበት
አብይ አጀንዳ የተረጋጋች ኢትዮጵያን መልክ ከሚያስዘው መሰረታዊ ችግር ስለተነሳ ነበር። ይህ የሚያሳያችሁ አይዋ ሳጥናኤል በረከት
ስምዖን እንዳሻቸው በሚፈነጩባት ጎንደር ላይ ምን ያህል የሲኦል መከራ ሙሉ 27 ዓመት ከዝነው እንደ ኖሩ መመልከት ይቻላል። በአማራ
ህዝብም ላይ የ27 ዓመቱ የመከራ ዘመን መራራነት በዚህ ሃዲድ ማዬት ይቻላል። ለዚህም ነው የኤርትራው መንግሥት እረዳቸዋለሁ የሚችላቸውን
ድርጅቶች የመንፈስ ማረፊያ አማራ መሬት ላይ በተለይም ጎንደር ላይ እንዲሆን የሚፈልገው። ማንም የአማራ መሬትን ሲመራ አልኖረም፤
አዲሱ ይሁን ደመቀ፤ ደመቀ ይሁን ገዱ ኢሳያስ ነው ሲመራ የኖረው በሲኦል በረከት ስምዖን የክፋት የስለላ ቱቦ የሽቦ መስምር።
ለዚህም ነው ብዙ ጊዜ የግንቦት 7 መንፈስ የብአዴን የውስጥ አዋቂ እንዲሆን፤ እንዲመስልም
ሲሳረበት የቆዬው። ሲታሰሩ፤ ሲገደሉ የኖሩት ንጹሃን አማራዎች የዚህ በቀል ማወራራጃ ስሌት ነው። አሁን በቀጥታ ከአማራ ክልል ወጥቶ
ኢትዮጵያን ሊታደግ ኦሮሚያ ክልል „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“
ብሎ ላይ ሲመጣ ድብልቅልቁ ወጣ። የሚጠበቀው የወ/ሮ አና መንፈስ ነበር። ያም ቦታውን እስኪይዝ እንጂ ድርድር የለም በኢሳያስ አፈወርቂ
የጃርት መንፈስ። ቋሚ አቋም፤ ቋሚ ውሳኔ፤ ቋሚ ሰብዕና የለም - ከአቦይ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ። መገላበጥ ነው እንደ ሽንብራ ቂጣ።
በዝማታቸው ውስጥ ያደባው የጋዳፊ ባህሪ ለኢትዮጵያ የመከራ ቀን ያሰላው ክፉ መንፈስ አይተኛም፤ አያንቀላፋም እስከ እልፈቱ። ሞቶ
እንኳን አጥንቱ አይተዋትም። አሁን አለ የተባለን የአማራ ሊሂቅ እንደ ጥላ እዬተከተለ ለእርድ ያቀረበው የስለላ መረብ ዛሬ ባለሰበው
ቦታ እና ሁኔታ ኢትዮጵያዊነት ከአማራ ክልል አልፎ የኦሮምያ የአፍ መክፈቻ ጥዑም ዜማ ሲሆን የዘመን ቦንብ ያሰጋው የአቶ ኢሳያስ
አፈወርቄ የስለላ ሴል ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ በቀድሞው ምርኮኛ በአቦ አባ ዱላ ገመዳ መንፈሱ ሰተት ብሎ ወደ 4ኪሎ እዬገሰገሰ
ነው።
እትብትን ከእትብ ጋር በታሪክ የጦር ሜዳ ላይ
ሲያዋድቅ የኖረው የሰላዩ ተስፋዬ ጃርቱ መንፈስ ሲደቅ ያን የማየት አቅምና አቅል ስላልሰራላቸው ነበር አቶ በረከት የቋያ ቁንጮ
በሆኑበት የባህርዳር ከተማ ጉባኤ ያልተገኙት። እንዴት ብለው ከአባ ገዳዎች ጋር ይታደሙ። ጋዳ ነበር። በምን የህሊና ሞራልና አቅም።
ይልቅ ጉዞው እንዲደናቀፍ ለኤርትራ መንፈስ ያደሩትን ለግንኙነቱ ሳንክ እንዲሆኑ አደራጀ፤ መራ። የባህርዳሩ የአማራና የኦሮሞ ጉባኤ እና ዜማው ያን ያህል የተመሰጥኩበት ለእኔ
ከኤርትራ አቅም በላይ ያላት ኢትዮጵያ በሥሯ ወድቃ የኖረችበት ማክተሚያ ዘመን እንደሚሆን ስለማውቅ ነበር። እኛን በእኛ አዋግቶ
ከድሆች ሐገር ተርታ በእኩልነት መሰለፏ ፋሲካው ለነበረው የሻብያ ካቢኔ ግን መራራ ኮሶ ነበር። ሲያዋጋ የከረመበት ዘመን የማክተሚያው
ዋዜማው በመሆኑ ነው በአማራ እና በኦሮሞ የባህርዳር ጉባኤ ላይ አቤቶ በረከት ስምዖን ሳይገኙ ሲቀሩ እንዳሻቸው በሚዳንሱበት በጎንደሩ
ጉባኤ ላይ ከወያኔ ሃርነት ባላንባራሶች ጋር የከተሙት ሚስጢርም ይሄው ነው። የታሪክ ዕውነታዎ ቆሞ የሚመሰከረው ቅርሰ ፋሲል፤ ዘረ
ግዮን፤ ትንግርተ ላሊበላ ባህርዳር ላይ በውህድ ደም ስለመበልጸጉ ታሪክን የሚያዘክር ገደል ዘመን ስለፈጸመ፤ ያን ገናና ጉልበታ
አቅም ለመፈታተን ብዙ ተጉዟል ይህ ሰላይ መንፈስ።
አሁን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ልብ ሰጥቶት፤ ወደ
ልቡ ቢመለስ የሴራ ቦንዳው አቶ በረከት ስምዖን የትግራይን ህዝብ ከሌላው ወገኑ ጋር ደም ያቃባውን ሴራ የመፍትሄ መንገድ ማዬት
ይችል በነበረ። የአቤቶ በረከት ስምዖን ኢትዮጵያን ሲሪያ ሆና
የማዬት ህልም ሰብሮ ኢትዮጵያም አቅም አላት፤ ያ አቅም የእኔም ነው ውስጤ ነው፤ ከአካሌ የወጣ የተገኘ ነው ማለት ከቻለ በውንም
እግዚአብሄር የነገን የእልቂት ቁር ሊያስታግስልን ተሰናድቷል ማለት ነው።
ከዚህ ላይ አንዲት ሃኪሜ ዶር. የሰጠችኝን ምክር
ላጋራ። „አንድ ወንዝ ሞልቶ ማሻገሪያ ሲመጣ አልፈልገውም አለ አንድ
ዋናተኛ፤ እናም ሊያድነው የመጣውን መርከብ መለሰው። ሁለተኛም ላከለት ይህም አይመጠነኝም ብሎ መለሰው፤ ሦስተኛም ላከለት ይህ ደግሞ
ጠበባ ነው አለና መለሰለት። በመጨረሻ ማዕብል ተነስቶ እሱንም አሰመጠው“ አለችኝ። ይህም ዕድልን በገፋህ ቁጥር ያን ዕድል
ደግሞ በቁመናው ማግኘት አይቻልም ነው ብሂሉ። ሃኪሞቼ አማካሪዎቼ ሁሉ የ ኢትዮጵያን ሴቶች ዕንባ ተጋሪዎች ናቸው። አቤቱ ወያኔ
ዕድሉን አክብረህ ከጥቂቶቹ ተድላና ደስታ የነገን የምልዕት ትግራይ ቡቃያዎች ሥነ - ልቦና እናዳይጠቀጠቅ፤ የበቀል ማወራራጃ እንዳይሆን
ማሰቡ በጥልቀት በእጅጉ ያስፈልጋል። ፍቅርን የሰነቀ ፍቅርን ያወርሳል። በቀልን የሰነቀ በቀልን ያወርሳል።
የሻብያ ከቢኔ ሰላዩ አሁን መርከብህን አትጠቀምበት፤
ማዕበሉ ይዋጥህና ቆሜለታለሁ የምትለው ህዝብ አብሮ ሲሰምጥ ታሪክህ ነው እያለ ነው - ለአንተው ለአቤቱ ወያኔ። ለዚህ ደግሞ በሻብያ
የስለላ መረብ የማይፈነቀል ድንጋይ የለም፤ አይኖርምም። ብዙ ሚሊዮኖች ዶላሮች ተግተው እዬሰሩበት ነው። እንደምሰማውም አቦ አባ
ዱላ ገመዳም የኤርትራው ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ የመንፈስን ትዕዛዝን በተጠንቀቅ እዬጠበቁ እንዳሉ ነው። ሃፍረት። እኔ የሰውነታቸውን
ግዝፍት ከጭንቅላታቸው ጋር እንዳመዛዝነው ረድቶኛል - መረጃው። ቅል የሰውን ልጅ ሲሸከም አይነት። በረከትን የተቀበለ ነፍስ ሁሉ፤
መልክዕ-ምድራዊ አቀማመጧ ሳይቀር የኤርትራውን ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂን እንደተቀበለ ይወቀው። የአማራን መሬት ቀጥ አድርጎ ሲመራ
የነበረው የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ መንፈስ ነው። ፈጦ እንዲህ ሲመጣ ጭብጡን መግለጽ ግድ ይላል። ለዚህም ነው „የነጻነት ሃይል ነኝ“
የሚለው ሁሉ አማራ መሬት እና መንፈስ ላይ ሊወርድ የማያስችለው። ትክሻው ያ ነው። በግራ በቀኝ አረስቶ የሚሆነው ለዚህም ነው አማራ
መሬት ላይ ድምጽ በተሰማ ቁጥር አለሁ እያለ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የሶቆቃ የሙከራ ማዕከል የአማራ እናት እዬወለደች ስታስረክብ
የተኖረው። ጭፍጨፋው፤ እስራቱ፤ እንግልቱ ለዚህ ሴራ ነበር። መሬው አስተዳዳሪው አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው። አሁንማ ብለው ብለው
„ትግሬ፤ አማራ ገዳይ¡“ የሆነ ከአዴኃን ድርጅት
መስርተው በዛ ሲፎከር ሁሉ አዳምጫለሁኝ። „አማራው ተደራጅቷል ትጥቅም
አለው“ ይለናል ልበ ቢሱ። አድጊነቱን አሽኮኮ ያለው ማፈሪያ። ትግሬ በመግደል ሥርዓት አይቀዬርም። ሥርዓት የሚቀዬረው በበቃ
የህሊና መሰናዶ ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ ኦህዲድ ተክህኖበታል። ሥርዓት በበቃ የህሊና አቅም ይለወጣል እንጂ በተናጠል እዬነጠልክ
የሰው ልጅን ያህል ክቡር ፍጡር እንደ ሚዲያቋ በመግድል እና የህዝብ አንጡራ የነገ ቅርስ በማቃጠል አይለወጥም። ለነገሩ ሰው መግደል
የሚያስፎክር ሰብዕና አይደለም፤ዲያቢሎስነት ነው። ሊያጠቃህ መሳሪያ ይዞ ሲመጣ ነፍስ ለማዳን የግድ ነው። ግን 7 ሚሊዮን የኢህድግ
አባላትን ገድለህ ድል ማሰብ፤ ያውም በተዝረከረከ አደረጃጅት በ21ኛው ምዕተ ዓመት ጮርቃነት ነው። ይህ የኤርትራ መንግስት አይዲዎሎጂ
የዛሬ 40 ዓመት ላይ እንደታቆረ፤ እዬዳከረ ያለ መሆኑን ያሳያናል። ዝቅጠትና ተስፋ መቁረጥም ነው። ዘመን ጥሎት ሄዷል አሱ ከዛው
በፉከራ ዲሪቶ ይማቅቃል።
አቅሙ፤ ውርዱና ስፋቱ በቃ ይሄው ነው። በህሊና
ሥራማ እዬነው እኮ። የቀዳዳውን ብዛትና ልክ። ተወትፎ፣ ተወትፎ ጎርንቶ ቀርቷል። በአማራ መሬት ላይ አለሁኝ መጣሁኝ እያለ ጌታዋን
የታማመነች በቅሎ እንዲሉ በሰላዩ አቶ በረከት ስምዖን ሲንደፋደፍ፤ አስማራ ላይ ይህን ደውይ መንፈስ ተክሎ የሻብያ ካቢኔ ሲወራጭ፤
አሁን የለማ መንፈስ ከች አለ። ዱብ እዳ ነበር። ይህም ሲያደናብረው እንደ ገና ማርኮ ጉድጓድ ሲያስቆፍረው ከነበረው ክሽፍ መንፈስ
ደግሞ ለድጋሜ ጉድጓድ ቆፈራ አካፋ እና ዶማህን ተሸከም ብሎ በመንፈስ እዬነዳው እንደሆነ እዬተደመጠ ነው። አንገት መድፋት ክብር
ከሆነ፤ ምርኮኝነት ሲሳይ ከሆነ ለኦቦ አባ ዱላ ገመዳ የህሊና ኩፍስ እልፍኝ፤
ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ቀን ከሳቸው
መዳፍ ወጥቶ ብቁ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ከሚመጣ ስድስት ሞት ቢሞቱ ይምርጣሉ። በሁሉ ሞክረው ኢትዮጵያ መዳኛዋ ብቻ ሳይሆን ከመከራዋ
ጋር የምትታረቅብት የፈውስ ዘመን ሊመጣ ዋዜማ ላይ ሲሆን የአቦይ ኢሳያስ አፈወርቂ ስልትና ስትራቴጂውን ቀይሮ በሽንጥ 4 ኪሎ ላይ
ሰተት ብሎ ገባ። የኤርትራ መንግሥት ሲያላግጥ የነበረበት ነጠላ ቅኝት ስብርብሩ ሲወጣ እንሆ ዓይኑን አፍጥጦ ኢትዮጵያን እመራለሁ
ጠ/ሚር እኔ እመረጥላሁኝ ብሎ ሰተት ብሎ ቤተ መንግሥት 4 ኪሎ ገብቷል። „አዝዬ እንዳስገባሁት ወያኔን ቀብሩንም እኔ አሸክመዋለሁ“
በማለት የፎከረውን ፉከራ በስልት ገብቶ ብቸኛ ሰላዩ በአቦይ በረከት ስምዖን ልቡን ገጥሞ ወያኔ ሃርነት ትግራይን እንደ ቀደመው
እንደ አጋሰስ እዬጫነው ነው። በዛ ሰሞን ራሱ ውጥረቱ ሲነግስ ግብጽን የሙጥኝ ብሎ ሁሉ ነበር። አውሬው አይተኛም። ሞቶውም የሚነስተው
ይሄው ነው „ኢትዮጵያዊነት“ ሞገደኛ የሚስጢር ዓዕማዳዊ ቅዱስ
መንፈስ መስቀል እንዳዬ ዲያቢሎስ ያባትተዋል። ሁሉም ነገር ከሸፈ። ሁሉም ሙከራ አፈር ድሜ ጋጠ። መጠጊያ የመንፈስ አቅም እና ልቅና
መክኖ እፍ ብትን ትን አለ። ሁሉም መንገድ ተዘጋ። ለማ፤ ገዱ አብይ እና አንቤ የ ግንባሩን በስጋት ሥ/አሰ ሲያንቀጠቅጡት ምርኩዙ
ሁሉ አልሰራም። በግድያም፤ በፉከራም፤ በነጭ አምልኮም፤ መሰል የተስፋዬ ገበረ ጀርት ልሳን ፈጥሮ በማመስ እና በማተራመስም ሁሉም
ግብዕቱ ሲፈጸም አሁን የመጨረሻውን የአልሞት ባይ ተጋድሎውን ቀጥሏል … ረኪሎ ላይ። የ ኢትዮጵያ ህዝብ ሊያውቀው የሚገባ ቁም ነገር
አቦይ ኢሳያስ አፈወርቂ ቤተ መንግሥት ውስጥ መሆኑን ልብ ማለት ነው። ጦርነት ላይ ነን።
- · የብሶት - እስረኞች።
ውጭም ኤሉሄ የሚሉ ወኪሎቹ አሉት። ይህ ለደቂቃ
ኢትዮጵያ የሚለው ቃል መስማት የማይሻው የወልዮሽ መንፈስ። ጡረታ መውጣትን አይፈቅዱትም። ዛሬም ያነኩራሉ። የትውልዱ ብክነት ትዳሬ
ብለው ይዘውታል። ኢትዮጵያን አንገቷን አስረው ወደ ሞት የጎተቷት ሻ/ዳዊት ወ/ጊዮርጊሰ ያ የመከራ ደባ ሳይጸጽታቸው፤ ያ ሳያሸማቅቃቸው፤
ይቅርታም ሳይጠይቁበት በኦሮሞው፤ በአፋሩ፤ በሲዳሞዎ ህብረት ተንጠላጥለው የሻብያን መንፈስ ማንጠላጠል ቢያልሙትም አልሰራ ያለውን
ህልም „አማራ ነኝ“ ብለው „አንድ አማራ“ የሚል የሲኦል ጸበለ ጻዲቅ ድንኳን ጣሉ። በዚህም መንፈስ ሲበትኑ፤ አቅምን ሲፈታተኑ
ሲያምሱና ሲያተራምሱ ሰንብተው አሁን ደግሞ፤ ኦህዲድ ሐገራዊ ራዕይ አለኝ ብሎ ህዝቡን በምላዕት አንቀሳቅሶ ጉልበቱ፤ አይደፈሬነቱን
ሲዩ ምርኩዛቸውን ይዘው ለኢትዮጵያዊ ህልውና ተሟጋች ሆነው ብቅ አሉ። ቅኖችን አስለፈው ከች ብለዋል። ለመሆኑ አማራነታቸው ዛሬ
ከ27 ዓመት የእልቂት ጉዞ በሀዋላ ነው ትዝ የሚላቸው? የወያኔ
ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ በአማራ መቃብር ላይ ታላቋን ትግራይ ሪፕብሊክን እንመስርታለን ነው የሚለው“ ህጋዊ ዕውቅና አሰጥተው
4 ኪሎውን ርክክብ ሲፈጽሙ ከቶ የት ነበሩ ተኝተው ነበረ ወይን እንደ ቅዱሳኑ ተሰውረው? ንገሩኝ ባይ። http://www.satenaw.com/amharic/archives/51852
„ሁሉም መስማት ያለበ እኛን በማዘናጋት እየተሰሩ ያሉ ሴራዎች | ዶ/ር ዲማ ነገዎ፣ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስና ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው“
አባ ቅንዬ ህብርም ለሻብያ ህልመኛ ለሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ድምጽ ሆኗል። አልገባውም። አልተረዳውም። የማንን አከርካሪ ለመስበር
እንደሆነ። ስለማን እንደተ ቆመ፤ ስለተስፋዬ ጃርቱ፤ ስለበረከት ሴራው ስለ ሻብያው ካቢኔ ልሳንነት ስለመሆኑ። ራሳቸው ሴራ መሆናቸውን
ለአፍታም ሊያስቡት አልፈለጉም። ግን ምን አለበት እንደ ክቡር ዶር ካሳ ከበደ እንደ አከበርናቸው ክውን ብለው ቢቀመጡ። አሁን እኮ
የንሰሃ ጊዜ ነው። ምን አለ ከአቶ ሰዬ አብርሃም የተደሞ ምግባር
ትንሽ ለመማር ቢፈቅዱ። ይህን ያህል መንደፋደፉን ያመጣው፤ ሁሉ አምቆ ቀን ቆርጦ የነበረውን የውጪው እና የሀገር ውስጡን የሻብያ
ህልም ድር ብጥስጥሱን ያውጣው የለማ፤ የአብይ፤ የገዱ፤ የአንባቸው ሞገዳማ መንፈስ ድንጋጤ ነው። ኢትዮጵያ አቅም አላት።
ለዛውም ብቁ ወጣት ያልሻገት መንፈስ ያለው፤ ሽሁራር የበላውን የሶሻሊዝምን አይዲዮሎጂን አጨቅንጥሮ የጣለ፤ ፍቅርን ሰንቆ ፍቅርን
ሊያውጅ የተሰናዳ። ጥገኛ ትውስት ለ ኢትዮጵያ ወጣት አያስፈልገውም። ተቋም እኮ ከፍተዋል እነኝህ በልህ የፖለቲካ ሊሂቃን። በቆረጣ
አይታሰብም፤ በነጭ ጫናም አይሆንም። ሁሉም አንቴነው ከብሩህ መንፈሱ ላይ አሳርፏል። ይበቃል ለማያውቁት አጀንዳ መማሰን።
በአውሮፓ ህብረት ይሁን ፓርላማ ይሁንታ የታሰበው
አልሆን ሲል፤ የመጨረሻውን ዕድል የኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያን ገዳይ መንፈስ ይዞ ብቅ ብሏል ግራ ቀኙ ድውይ መንፈስ። ጠረኑ
እጅግ ደማናማ ሆኖ ነበር የሰነበተው። ቀለብ የሚሰፈርለት ሁሉ ዘመቻውን ልክ እንደ አቦይ በረከት ስምዖን ሲያጧጥፈው ነበር የከረመው።
ቃለ ምልልሱም አውዱም ያ ጭጋጋማ የስቃይና የሮሮ ናፍቆተኛ ድምጸት ነበር። ስለ እናንተስ ምን መሬት ምንስ ቀዬ ይችላችሁ ይሆን።
ዕድሜ ሙሉ ሴራ! እንዴት ይቀፋል? እንዴትስ ይጎመዝዛል። አይበቃም። በዘመኑ ለሚጠፉም ለሚለሙም ነገሮች ዘመኑ ለፈቀዳላቸው ወጣቶች
መሆን አለበት። ጡሮታ የሚባል ነገር አለ። እሰኪ ጡረታ ለመውጣት
አስቡ። ትናንት ኖራችሁ፤ ዛሬ ደግሞ ኑሩ ተብሎ ለተፈቀደላቸው ወጣቶች የፖለቲካውን መድረክ ለቀቅ አድርጉ። ለጥፋቱም ለድህነቱም
ቦታውን ዕድሉ ወታቶች ይሰጣቸው እና ይታዩ። ይፈተሹ። ካላፉም ራይት፤ ከወደቁም ኤክስ ስጧቸው እንደ ግርጫው። በቃ በሰው ዘመን
የኛ ነው ብላችሁ አትበጥብጡ። ቅን መንፈስ፤ በጎ አዬር ህሊናችሁ ይቀበል ዘንድ ፈጣሪያችሁን ጠይቁ። ቢማለዳችሁ! አማራም ትንታግ
የአማራ ወጣት አለው- ከራሱ ውረዱ። የእናንትን ቀንበር ለመሸከም ዛሬ አይፈቅድም! ወጣቱን ልቀቁት! የሚሞትም የሚሰቀልም እሱ ነው፤
ለሚሞትለት፤ ለሚሰቀለልት ዓላማ ቡራኬው የእሱ እንጂ የሶፋ ቤተኛ አይደለም። ቀይ ምንጣፍ አዘጋጅቶም አይጠብቅም። ቁርጣችሁን እውቁ
ርዕዮት ዓለማችሁ ፈርሷል። ተቀብሯል። ሶሻሊዝም መሞት ብቻ ሳይሆን
ተቃጥሎ አመድ መሆን ያለበት ርዕዮት ነው። የትውልድ እርድ አልባ ፍስሃ የሌለው ክፉ አውሬያዊ መንፈስ። እና፤ እናማ የምንሰጣችሁን
አክብሮት አትፈታተኑት። እናንተን እናውቃችሁለን። ትንሳዔ ሳይሆን በተለይ ለአማራ ቀብር ያወጃችሁ ስለመሆናችሁ ትናንትም ዛሬም።
ቢሮው እኮ ሞባይል ላይ መሆኑን እናውቃለን። ይህ ለድል እንደማያበቃ ውስጥወት ያውቀዋል። በተመክሮ የጸደቀው ድርጁው መንፈስዎት
መሬት ላይ ተፈትኖ ታይቷል። ዛሬ ግን አዬር ላይ ንፋስን ማመኑ … እእ ለዘረ ኢሠፓ ልጆች አይመቸንም - ቤተኞች ነበርን እንደ
ማለት። ለክተነዋል። መርምረነዋል። ያውቁታል ብዬ አስባለሁኝ የጓድ ገ/ድህን በርጋ የበኽር ልጁ ነኝ። እሱ ኮትኩቶ ላሳደገው መንፈስ
የማንኛውም የድርጅት ቁመና ውስጥ ለማዬት፤ ለመስፈር፤ ይዘቱ አቅሙ ስለመብሰሉ ለመፈተሽ የሚያግደው አንዳችም ነገር የለም። ስለዚህ
ኦህዲድን የሚመጥን አንድም ድርጅት የለም!
·
የአቅም መቅኖ ዲታነት።
የለማ መንፈስ ካለ አቦይ ኢሳያስ አፈወርቂ ገዳይ
መንፈስ ኢትዮጵያን አለሁሽ እንደሚላት ይታወቃል። ለዛውም በበቃ እና በጸደቀ አቅም። ዕድሉን ካገኘ ብቸኛው መንገድ የዴሞክራሲ ጠራጊ
መንፈስ አይደፈሬ ነው አቅሙ። ቃለ ምልሶቹ ጥቃት አየስገቡም፤ ስንጥር የላቸውም። በ27 ዓመቱ ሙት የወያኔ አገዛዝ ጨቋኝ ዘረኛ
አገዛዝ ታሪክ እስከነሙሉ አቅም፤ ስለቅዱስ ውክልና በሁሉም መስክ ተደራጅቶ የወጣ፤ በተመክሮ የበሰለ ድርጁ ፓርቲ ኢትዮጵያ አግኝታ
አታወቅም ነበር። በፍጹም። ማደራጀት ከራስ ነው የሚጀምረው። እንኳንስ ሥ/አሰ ማዕከላዊ ኮሜቴ አባላት ሳይቀሩ በሙሉ የብቃት መሰረት
ላይ እሰከ ተተኪያቸው ብቃት ጉድ በሚያሰኝ ሁኔታ ተደራጅተዋል። እግዚአብሄርም የረዳቸው ይመስለኛል። መንፈሳቸውም፤ ህሊናቸውም ሥነ
- ልቦናቸውም፤ ድርጅታቸው አቅማቸው ኦህዲዶች ወጥ ነው። ተዛነፍ አይደለም። ኦህዲድ በሙሉ ብቃት ተደራጅቷል። በተለያዬ የሃላፊነት
ደረጃ የሚገኙ አካላቱ የሚያደርጉት ቃለ ምልለስ፤ የሚሰጡት መረጃ፤ ሁሉ ወጥ ነው። ጠንቃቃ ነው። ደመነፍስ አይደለም። ደንጋጣ አይደለም። ወይንም ግብታዊነት አይጎበኘውም። የሰከነ፤ የተረጋጋ ሃሳብን
ዓላማ እና ግብን የሰነቀ ፏፋቴ ነው። ዴክራሲ ነፍሱ ከነመንፈሱ መሬት ላይ እዬታዬ ነው። ይህን ደግሞ እያዬን ብቻ ሳይሆን እየተደሰትን
እያጠናነው ነው። በልምድ የዳበሩት እና የሰከኑት በሌሎችም እኛ በማናውቃቸው ብቃቶች አንቱ የተባሉት የተከበሩት ሻ/ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ
የአሁኑ ሩጫ ይሄን መንፈስ መቅኖ ለማሳጣት፤ የውስጥ ሰላሙን ለማወክ ነው። በይፋ እና በአደባባይ ኢሳያስ አፈወርቂ ጠ/ሚር ይሁንልን
ነው - ዕወጃው። ይበቃ ነበር ሰው ዕድሜ ልኩን እንዲህ በትብትብ ማንነት መባዘን። ለዛውም ለእልቂት። ለትርምስ፤ ኢትዮጵያ ደክማ
ለማዬት መኳተን። ማህከነ!
- · የኢህአድግ - ምክር - ቤት - ሆይ!
አንተስ የኢህአድግ ምክር ቤት ከነነፍስህ አለህ
ወይንስ ሙተሃል? ደመ-ነፍስህን ነህ ወይንስ ከሩህ ጋር ነህ? የኢሳያስ/ የሻብያ መንፈስ መጫዋቻ መሆንህን ትሻለህ ወይንስ ትጸየፈዋለህ?
ያ ራሱን መቻል የተሳነው ወዝዋዛ መንፈስ እንዲገዛህ፤ እንዲነዳህ ፈቅደህ ባርነትን ትፈቅዳለህ ወይንስ በራስህ ብቁ አቅም እና ችሎታ
ጥበብህን ለጥበብህ ትሸልማለህ። በቃኝ! የአባት ነው። እንብኝ የደም ነው! አልደፈረም የአደራ ነው! የአይሆንም - የ እትብት መለያ
ነው። ደመ ቁጡነት የራስህ ነው፤ ሃብትህ! ቁመህ እዬሄድክ የሻብያ ጋሬ እና የኢሳያስ አፈወርቂ መኮፈሻ ሰረጋላ ለመሆን ትፈቅዳለህን?
ግን ያ የጥቁር አንበሳ ደም ጥሎህ ሸሸ ወይንስ ሸቀጥከውን?
- · የኢህአድግ - ምክር - ቤት - ሆይ - ሴራውን - አፈር - አስግጠው!
የተሴረብህን የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ አሽቀንጥረህ
ጥለህ፤ ይህን ጥሰህ፤ በጣጥሰህ መጣል የአደራ ግዴታህ ነው። የድንጋይ ጉልቻ አለመሆነህን „ሰው“ መሆንህን „ሰው“ ነኝ ብለህ በትግልህ
አንተነትህን አስመስከር። የአደዋን ድል ሸጬና ለውጬ ለውርዴት በኢሳያስ ሥር በርከክ አልልም ብለህ አሸነፈው። ማን አባቱ ደፍሮኝ
ብለህ በቁጭት እና በጦፈ ወኔ የምትነሳበት ወቅት አሁን ነው። ጀግና መሆን ዛሬ ፈተና ውስጥ ነው። በራስህ ላይ ቤንዚን አርከፍክፈህ
የ100 ሚሊዮንን እንባ ትታደጋላህ ወይንስ የኢሳያስ መንፈስ የዘለዓለም ባሪያና አገልጋይ ትሆናለህ? ራሱን መቻል ተስኖት ሚሊዮን
ልጆችን ለባህር ስንቅና መስዋዕትነት ለሚያቀርበው ውርዴ መንፈስ ሥር ወድቀህ የርግጫ ቀንበር ለመሸከም ትክሻህን ታደላድለላህ፤ ወይንስ
አባቶችህ እና እናቶችህ እንደ አስተማሩህ የአድዋን ገድል ፈጽመህ አፍሪካን ሊመራ የሚችለውን ኢትዮጵያዊ አቅምህን ክብርና ግርማ
ሞገስ ሰጥተህ፤ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ራስህን ነፃ ታወጣለህ? ዘራይ ደረሰን፤ አቢዲሳ አጋን አምጠህ ትወልዳለህ ወይንስ ሁለተኛ
ጊዜ ተገድለህ እንጦርጦስ ጀግኖችህን ትቀብራቸዋለህ? የዘመናት የኢትዮጵያ መከራ ምንጩ የኤርትራ ጉዳይ ነው። ዛሬ አሁን ዘመኑ ነው በቃ የማለት። የራስህ ንጡር ብሩህ ህሊና ያለው ልጅ አለህ፤ የራስህ
ንጹህ ደምህ ብቁ አለህ፤ የራስህ መንፈስ በጸና ኢትዮጵያ መሰረት ላይ የደመቀ ክብር አለህ። ትችላለህ! ቁረጥ! ወስን! ከብር ካሰኘህ፤
ታሪክ ካሰኘህ።
የምርጫ ህግህን ደንብህ አንተ እና አንተ ብቻ
እንጂ የተስፋዬ ገበር ጊንጥ፤ የበረከት ጋኔን፤ የሻብያ ስንኩል ሳጥናኤል እንዲመራህ ከፈቀድ እውነትም ሙተሃል። እራሱ ሻብያ የት
ስለሚያውቀው ዴሞክራሴ ሊያታገልና ሊታገልልህመንፈስህን ትሸልመዋለህን? ቃሉን እኮ አያውቀውም እንኳንስ ተግባሩን።
ስንት ነህ 180 …? ከቶ ይዘጋጅ 180 የውርዴት
የቀብር ጉድጓግ? ያ አንተ የአፍሪካን ብቻ ሳይሆን የጥቁርን ድል አድራጊነት መንፈስ ማህንዲስ ለሻብያ ልታንበረከክ? አይደረገምምምምም?
ጀግንነትህን ሻብያ ሰኔል እና ቹቻ፤ ሳጥን ጨምሮ አዘጋጅቶ እዬጠበቀው ነው። ከንቀት በላይ ነው ይሄ። ያ መቅኖው ያለቅ የኤርትራ
ካቢኔ አንተን እምራለሁ ብሎ ማሰቡ በራሱ ድፍረትም ውርዴትም ነው። ትቆማልህ ወይንስ ትተኛለህ?! ትራመዳለህ ወይንስ ታቱ ትላለህ?!
ተጋድመህ ትታረዳለህ ወይንስ ሴራውን አርደህ የድል ርካብህ ላይ ራስህን ታስከበራለህ?! የበታችነትን ታጥቀህ የበረከት መንፈስ ሎሌ
ትሆናለህ ወይንስ አንቅረህ ተፍተህ ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስገድደህ የኢሳያስ አፈወርቂን ህልመኛ፤ አዋኪ መንፈስ
ሁሉ ጥቃትን ትግተዋለህ?! ውርዴት ትጠጣለህ ወይንስ እንደ አባቶችህ/ እናቶችህ ጀግንነትን ትታጠቃለህ?! የኢሳያስ መንፈስ እንደ
እቃ መታዬትህ እራሱ መሞትህን፤ „ድንጋይ“ ነህ ብሎ እንዲህ መዘባበቱ ክብርህን ዝቅ ማድረጉን ከልብህ እሰበው። ሻብያ ሲሰኜኝ የምፈልጥህ፤
ሲያሰኘኝ የማንከበልለህ እኔው ነኝ ሰላዬ ምን ሊሆን ሥራው እያለህ ነው። የበታችነትህን እዬነገረህ ነው፤ 27 ዓመት ሙሉ እዬመራ
ሲያጫርስህ የኖረው የሻብያ መንፈስ ነው እኮ። የሻብያ መንፈስ በማናቸውም ጊዜና ወቅት የማይተኛልህ መሆኑን ጥስህ ለመውጣት የምትደርገው
ተጋድሎህ ብቻ „ሰው“ መሆንህን ያውጃል። ዛሬ ያለው ውጊያ በአቅምህ በመዳፍህ ነው። መሞትም ካለብህ ሙት። ጥለህለት ውጣ! እንቢኝ!
አሻም! ካለከው ትውልድን ታሪክ በወርቅ ቀለም ትጽፋለህ። በህግህ በደንብህ ባጸደቅከው እንጂ ሻብያ በሚሰጥህ አዲስ ልቅላቂ እንዳትቦጫረቅ።
ልኩን የምታሳውቀው አሁን ነው። ባድመን ሲያልም 4 ኪሎ ላይ አከርካሪውን ሰብረህ ሴረኛውን ባንዳ አቶ በረከት ህልም እንኩትኩቱን
አውጥተህ ቅበረው።
- · የወኔ - ጉዳይ - ነው ለምክር ቤቱ!
ምርጫው አንድና አንድ ነው፤ የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ
ኢትዮጵያን እንዲመሯት ይለፍ መስጠት፤ ይህም ማለት ትናንት የተፈጠረች ሐገር ለዛውም ያ ውሽልሽል የሻብያ ካቢኔን ክብር ማጎናጸፍ
ወይንም የኢትዮጵያን ትሁት ድምጽ ይዞ በሙሉ አቅም ዝግጁ የሆነውን የአደራ ሁነኛ ኦህዲድ ኢትዮጵያን እንደሚራ መፍቀድ። የጦርነት
ግንባሩ ትግሉ ሁለት ብቻ ነው። ፍልሚያው ለይቶለታል። ለመጨረሻው ለማይታወቅ መከራ መሰናዳት ወይንም ለሚታወቅ ብርሃን መታገል?
እንደ ከብት እዬተነዱ ጉድጓዱን ህይወት መቀላቀል ወይንም ተስፋን ሰንቆ ለድል መብቃት። የቱ ይሆን ለምክር ቤቱ ትውልዳዊ ድርሻው?
የወኔ ጉዳይ ነው። የደም ጉዳይ ነው። ግን አንድ ነገር ኢትዮጵያዊ ወኔ አለን ወይንስ ለባርነት ሳህል ላይ ለማሽላ አጨዳ?
- · እውነቱ።
የራሱን አገር ለመምራት ወርዱም ቁመናም ያልቻለ
መንፈስ ኢትዮጵያን ያህል የነጻነት ዕንቁ፤ የአፍሪካ ዓርማ፤ የአፍሪካኒዝም መሥራች፤ የዓለም ህዝብ መገኛ፤ የጥቁር ህዝብ ብቸኛ
ኩራት በመሬቱ፤ በቀዩ፤ በገዛ ምድሩ ለባዕድ መንፈስ ያውም ለደካማው ለኤርትራ ካቢኔ ለበረከት ሽሁራር የበላው መንፈስ እጅ መውደቅ?
ሞት ይሻላል!
·
ይድረስ - ለአቦ - አባ ዱላ ገመዳ፤
እንዴት ሰነበቱ። የሚጎፈንን ነገር እዬሰማሁኝ
ነው። ግን የሚሊዮን ድምጽን ግብዕት ሲፈጸም ከቶ እንደ አንድ የትውልዱ ቤተኛ ምን ይሰማዎት ይሆን? መታመናችን ክደው ቤንዚን አርከፍክፈው
ሲያቃጥሉት ከቶ ከዬትኛው የህሊናዎት ጓዳ ይደበቁ ይሆን? መታመን በዚህ ዘመን ሲሸሽ ለዚያውም ለድንኳን ኑሮ ይመቻል ወይንስ ይነስታል?
አዝኛለሁኝ! የራስዎት የእኔ የሚሉት ህሊና ግን በዚህ ዕድሜ
ሊኖረዎት ካልቻለ እስከ መቼ እንጠብቅ ይላሉ? ግን ህሊና የሚገዛበት ቦታ ቢያፈላልጉ ምን ይመስለወታል። የደከሙለት ኦህዲድ ድርጅት
አቅሙ እኛን መንፈሱ ሲገዛን እንዴት እርስዎ ተፃራሪ ሆነው ይቀርባሉ? አባት ልጁን ይባላልን?!
ከቶ እረሱትን የሻብያን ድርብ፤ ድርብርብ፤ ንብርብር
የጉድጓድ የቁፋሮውን እፍረት? በደል ይረሳል ወይንስ ህሊናን ይገምሳል? ምነው በሀገር ጤና ድጋሚ ጉድጓድ ቁፋሮ እና የማሽላ አጨዳ
አሰኘዎት? ክሽፈት ወይንስ ሽንፈት? ኤርትራ ነገረ ኦሮሞን የመምራት በምን አቅሟ፤ አያዋርዱት የመጡበትን ማህበረሰብ። የሴራው ቦንዳ
አቶ በረከት ስምዖን ህሊና ግጥምዎት ከሆነ ስለምን ማመልከቻ አያስገቡም ለድጋሚ ምርኮኝነት? ግን እርስዎ የእኛ ነዎት ወይንስ የሻብያ?
ላዋረደውት ታሪክ እንደ ገና ያረገርጋሉን? ታሪክን ስንት ጊዜ ይተላለፉት? ለዛውም ዛሬ? ለሻብያ ምርኮኝነቱን ስለምን ቤተ-መንግሥት
ላይ ሆነው ናፈቁት?
መቼስ ለጠ/ሚር ቦታ እንደማይመጡኑ እርስዎም ያውቁታል?
ዓለም አቀፍ ጉባኤ ለመታደም ትልቅ ቹቻ ገመድ አለ - እንግሊዘኛ
ቋንቋ የሚባል። ጥናትም ይጠይቃል የዓለምን ፖለቲካ በዬደቂቃው
ብቻ ሳይሆን በምልሰትም ት/ቤት መግባትን ይሻል። የዕዬለቱ ለውጥ ደግሞ ድርብ ነው - ፈታኝም። በዓለም ያለውን የፖለቲካ ፍሰትም
ማገናዘብ ካልተቻለ ኢትዮጵያን በፖለቲካ ብቃት እና ልህቅና መምራት እጅግ ከባድ ነው - መርግ መሸከም። ዜናው እኮ የግሎባሉ ማለቴ
ነው በእንግሊዘኛ ነው የሚሠራው። ሌላው ምርኮኝነት ስብዕና ቢያልፍም ግን ይህን ጠበሳ ተሸክሞ ደፍሮ ለዛውም ያን ሰፊ ማህበረሰብ
የኦሮሞ ውክል ምልክት ሆኖ ጠ/ሚር መሆን የጄ/ አብዲሳ አጋን ክብር የሚዳፈር ይሆናል - አይመስለዎትም? ያዋርዳል። ባይሆን ከአለም
አቀፉ ሚዲያ ዞር ያለችውን የሸሽጉኝ ቦታ የሙጥኝ ማለቱ፤ እንዲያሰነብትልተው ሸር ጉዱን ጠበቅ ማድረጉን ይበጃል። መቼም የ66ቱ
አባዜ በቃኝ ወንበር የማይታሰብ ስለሆነ። እባካዎት ይለመኑኝ -- የእርስው የምርኮኝነት ዘመን ጠበሳ በዓለም መድረክ መናኘት የለበትም።
የኦሮሞን ማህበረስብ አንገት ያስደፋል፤ ኢትዮጵውያንን ያሸማቃል። የእነ ዲነግዴ፤ የነ አባ ባልቻ አባ ነፍሶን፤ የሃይለማርያም ማሞን
የጦሩን ገበሬ የስንቱ የጀግና መሬት ለመሸማቀቅ አይሰናዱ - እባከዎትን? ዓለም አቀፍ ሚደያዎች እዬቆፈሩ እያወጡ ጉድ ይሰሩዎታል።
ስለሆነም የእርሰውን የምርኮኝነት ዘመን በጥበብ ደም ለመመለስ የተሰናዳውን የለማን አብይን ንቁ፤ ብቁ ቅዱስ መንፈስ ጥቃት አውጪ
ስለመሆኑ ይሰቡት - በትህትና። ይህ መንፈስ ቢያኮራ፤ ተስፋ ቢጣልበት እንጂ በፍጹም ሁኔታ ድጋሚ አንገት የምንደፋበት አይሆንም።
ልብ ከተሰራለዎት።
ውስጤን ባሳዬወት ጥሩ የፖለቲካ አክሮባቲስት ነው
የሆኑት። ልክ እንደ አቶ አብርሃም ያዬህ። ዓፄ የሆንስ መተማ ላይ አጼ ቴወድሮስ
መቅደላ ላይ ብዙ ያልተዜመላቸው ጓድ ገዛህኝ ወርቄ እስከ በኽር ልጃቸው አርማጭሆ ላይ እኮ የተሰውቱ የህሊናም፤ አካልም ምርኮኝነትን በጽኑ ተጸይፈው ነው። ለወንበር ተብሎ ሁልጊዜ ታሪከዎት
እንዴት የባዶ ኮዳ ሸክመኛ ይሆናል? አያዝኑለትም? አንዴት ለምርኮኝነት ለዛውም ለሥልጣን ለሄሮድስ መለስ ዜናዊ ላልሆነ ወንበር?
መጥኔ ለእርስው? በተረፈ በእርስዎ ዙሪያ ይህ የመጨረሻዬ ይሆናል። ወደቁም ተነሱም፤ መሳቂያ ሆኑም ተዋራጅ። ተላላፊም ሆኑ ተከፋይ።
ከተሳካ ሹመት ያዳብር¡¡
·
ለቅዱሳኑ የኢትዮጵያ እስላምና እና ክርስቲያን ወገኖቼ
ሁሉ።
የባድመ ጦርነት 4 ኪሎ ሊሆን ተቃርቧል። የእርስ
በርሱ ጦርነት በአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ልሳን በሆኑት በሰላዩ አቶ በረከት ስምዖን ሞት ታውጇል። ይህን መልክ ለማስያዝ ደግሞ እግዚአብሄር
የእርቅና የምህረት እጁን በኦህዲድ መንፈስ አዘጋጅቷል። ጸሎታችሁ፤ ስግደታችሁ፤ ሱባኤያችሁ፤ ድዋችሁ አንጀት አርስ፤ የልብ አድርስ
ነውና፤ ኢትዮጵያ ወደ መቃብር እንዳትወረወር እባካችሁ ቤታችሁን ዘግታችሁ ከመንፈሷ ጋር ሁናችሁም በለቅሶ እና በተደሞ ፈጣሪያችን
አማኑኤልን/ አላህን ትማጸኑት ዘንድ ከእግራችሁ ላይ ወድቄ እለምናችሁ - አለሁኝ። እማጸናችሁ አለሁኝ። ማልቀስ - መታመም - መቁስል
- ደክሞኛል - የዕውነት። ይህ መልክ ከያዘልኝ በቀጥታ እማመራው „ፍቅራዊነት“ የሚል የህሊና ላውዲሪ ቤት መክፈት ይሆናል። ደግሞም
ይሳካል።
- · ብርታት የሚሰጠኝ የህሊና መቅኖዬ፤
ለትውልዱ ቅናዊ መንፈስ አንባ/ አባትም የሆኑት
የስሜት ተኮር ፍልስፍና የሐገር አዱኛ ዶር ምህረት ደበበ የMind Set አርበኛ አቅደው የጀመሩት የአንድ ሺህ ኢትዮጵውያን መንፈስን
የመግራት ጉባኤ ላይ፤ የቅንነት ቅዱስ ውይይት ላይ ተገኝተው እጅግ ለሰውኛ ፍልስፍና እና ተፈጥሮ ቅርብ የሆነ ንግግር ያደረጉት
የዶር አብይ አህመድ መንፈስ ዛሬ 193, 045 ንጹሃን እንደታደሙበት አይቻለሁኝ። ይህ የሚያሳኝ ኢትዮጵያ የፍቅር ቤት እንደሆነች
ነው። የ ኢትዮጵያ ህዝብ፤ ቅንነት፤ መልካምነት፤ አዎንታዊነት እንደ ናፈቀው ነው። ፍቅርን የሚመራ ሙሴ ብቻ ነው የሚያስፈልገን።
ቅኖች ከተባረከቱ፤ ጥላቻን የሚጸዬፉ ከበዙ፤ ቂምን ዘመዴ አይደለህም የሚሉ ንጹሃን ከበረከቱ ፍቅር ማንፌሰቷችን ይሆናል። ፍቅር
የማይችለው ከቶውንም የማይፈታውም የመከራ ዓይነት የለም። ፍቅር ቀለሙ ተፈጣሯዊ ነው። ፍቅር እናት ሆዱ ነው። ሁሉ ይቻለዋል። ስለዚህ
ሃሳቤን ጣል አድርጌ በዚህ ላይ መትጋት እችላለሁኝ። መንፈሴም ይሰበሰባል። ጤናዬንም አገኛለሁኝ። ዕንባም ይቆማል። ለእኔ ትንሳዔ
የምለው ይሄን ነው። ግን የውስጤን ፍላጎት በትጋት የእኛ የሚል የቡድን ለማ መንፈስ ኢትዮጵያ ከተሸለመች ብቻ። እንጸልይ በቃችሁ
እንዲለን። የወጡት እንዲመለሱ። የቆሰሉት ነፍሶች ሁሉ እንዲፈወሱ፤ በሰው እጅ ያሉት እንዲለቀቁ፤ ሞት፤ ግድያ፤ አፈና፤ ጭፍጨፋ፤
መጠራጠር በምደራችን እንዲጠፋ፤ ያንዣበበው የበቀል ደመና እንዲገፈፈ … ይርዳን አምላካችን እና ጌታችን አማኑኤል። አሜን!
„ልብ የሚነካ አስገራሚ ንግግር Dr abiy ahmed # mind set“
- · መውጫ በር።
የኔዎቹ ፍልሚያውን የሚረታው የጸሎት ትጋት ነው።
ጉልበታችን፤ አቅማችን በጸሎት ላይ ማዋል ይኖርብናል። የእኔ ብለን ውስጣችን ለዕንባችን ከለገስን ሁሉን ነገር አሟልቶ ተስፋችን
ጥግ ሊያስዝ የኦህዲድን የኖህ መርከብ ፈጣሪያችን አዘጋጅቶልናል። ነገ የብሩህ ቀን ዋዜማ ነው ግን የጸሎት ጥበቃ ይሻል። ኑሩልኝ።
ፍቅሬ ከመንፈሴ፤ አክብሮቴም ከሩሄ ነው።
„አቤቱ ውሃ አስከ ነፍሴ ደርሶብኛል እና አድነኝ፤“
(መዝ. ምዕራፍ ፷፰ ቁጥር ፩)
„በጩኽት ደከምኩ፤ ጉሮሮዬም ሰለለ፤ አምላኬን
ስጠብቅ ዓይኖቼም ፈዘዘዙ።“ (መዝ. ምዕራፍ ፷፰ ቁጥር ፫)
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ - በፍቅራዊነት ልዕልና!
ዘለዓለማዊ ሞትና መከራ ለኢትዮጵያ ሳይታክት ለሚያውጅላት፤
የክፋት ጄኒራል ለኢሳያስ አፈወርቂ ክፉ መንፈስ ይሁንልኝ! አሜን!
መሸቢያ ጊዜ - አክብሪያችሁ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ