"እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች የሚበያረታ"
ነገም ትዘልቂያለሽ።
„እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች የሚበያረታ በኮረብታዎችም የሚያቆመኝ እግዚአብሄር ነው።“
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፴፫)
ከሥርጉተ ሥላሴ 07.05.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)
ነገም ትዘልቂያለሽ።
*****
እኔን ያስደሰተኝ - ፍጥረተ-ነገርሽ
ጥብቅና መቆምሽ - ለዛች ለእስትንፋስሽ።
ቀጨሬ መጨሬ፤ - ምናምንቴን ትተሽ
አርቲውን ቡርቲውን - ወደ ጎን አድረገሽ፤
ሁለመናሽ ጠርቶ ጻዳማ ሆነሽ፤
ትናንትም የነበርሽ፤ - ነገም ታብቢያለሽ።
እንዳበራሽ ፀሐይ፤ - ነገም ትዘልቂያለሽ
ዕውነት ለዝንታዓለም ፀድቀሽ ትኖሪያለሽ።
· ተጣፈ ---- 1985 ዓ.ም ድል ገብያ ገብርኤል አዲስ አበባ።
· ከመክሊት የግጥም መድብል መጸሐፌ የተወሰደ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ