ብርሃነ እናት።

ብርሃነ እናት!
ከሥርጉተ ሥላሴ 03.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)
„ለእኔ ህይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነውና።
ጳውሎስ ወደ ፊሊጵስዮስ ሰዎች ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፳፩“


  • ውዶቼ እንዴት ናችሁ?

የደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ያስፈራል። የሰማዩ ሰላማዊ ሰልፍ አይሎ ሲወዚሻ ጠቆርቆር ባለ አዬር ታውዳለች። ያጉረመርማል በብልጭታ ማስጠንቀቂያው አዬል ብሏል፤ እቴጌ ጣዬም የለችም። ተጫጉላው ሆና ይሆናል።  የእሷ ነገር እንዲህ ነው ብቅ ጥልቅ፤ ጥልቅ ብቅ። አንጠልጣይ። ግን በሚገርም ሁኔታ ደግሞ ቤት ውስጥ ብርድ የለም። ውጪ ይዘንባል ቤት ደግሞ ይሞቃል። ሲዊዚሻ ከአውሮፓ የተለዬ የሚያደርጋት አንድ ቀን በርታ ያለ ሙቀት በቀጣዩ ቀን ደግሞ የሚያቀዘቅዝ አዬር በሚዛን ኑሩ ነው ምክሯ። ተባረኪ!
  • ምስክርነት

የኔዎቹ ቅኖቹ ፣--- ዛሬ ወደ ተጀመረው ርትሃዊ የወግ ገበታ ከማምራታችን በፊት አንድ ነገር ለመንገድ ልንገራችሁ ፈለግሁኝ። ይፈቀዳል አይደል? የተጀመረው ዕርስ ርትህ ይቀጥላል። ግን ማህል ላይ ጥበብ እና እኛን ስናዋድደው መልካምኛ ነው። አንድ ጊዜ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የእናታቸውን ህልም ስለ ሳቸው ራዕያዊ ነገር ሲገልጡ 7ኛ ንጉሥ ትሆናለህ ብላኝ ነበር ስላሉ በማጣጣል፤ በማሽሟጠጥ፤ በማቃለል የተመለከቱት ብዙ ነበሩ።

እኔ ደግሞ ወጣ ባለ ሁኔታ ነው የምመለከተው። በ እኔም የደረሰ ስላለ። አበይ ለመላ ቤተሰቡ ሁሉ ልጄ ሁለት አንጎል ጥምር ጭንቅላት አላት እያለ ነው ያሳደገኝ።  7 ዓመቴ ላይ ነው ጠረጵዛ ላይ ሆኜ በማንበብ ፕረዘንቴሽን ያስጀመረኝ። በመጻፍ በማንበብ ሃሳቦችን ውስጥ ስለማድረግም የጠበቀ መሰረት ጥሎልኛል። ለዛውም አብረው ቢቀጥሉ ኖሮ ዛሬ ሥርጉተ እንዲህ ሆና ባልቀረች ነበር።

የሆነ ሆኖ ለዚህም ነው የተስፋ በር መጸሐፌ የጻፍኩት ወላጆች የቤት ሥራቸውን መስራት እንዳለባች ለማስገንዘብ ነው። ምክንያቱም በኢትዮጵያ ከገጠር እስከ ከተማ ከዚህም አውሮፓ አገር እንዲሁ የማያቸው ነገሮች ወላጆች ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ ትምህርት ከትምህርት ቤት ውጪ አለማሳባቸው አሳስቦኝ ነው። በጣም ሰፊ ክፍተት አለ። ልጆች የሚቀረጹት ቤት ውስጥ ነው። የመጀመሪያዋ የህይወት ት/ ቤት ደግሞ እናት ናት። እናት የመጀመሪያዋ መምህርም ናት።

የጠ/ ሚር አብይ አህምድ እናት እመት ትዝታ ወልዴ ያን ማለታቸው ልጃቸው እያንዳንዷን ደቂቃ እንዳያበክኑ መሠረቱን በ አ ዕምሯቸው አስቀምጠዋል። ከሁሉ በላይ የ አገር መሪ መሆን አገርን ከመወደድ ጋር በጽኑ ኪዳን አዋውለውላቸዋል። እነ አቶ ሃብታሙ አያሌው እና ሌሎችም ኢትዮጵያዊነትን ዶር ጥላሁን ገሰሰ እና ጠቢቡ ቴወድረስ ካሳሁን አዋሷቸው አይደል የሚሉን። አላጋጮች ናቸው የዚህ ጉድ ማህብርተኞች። ቁንጽሎች። ዕውነቱ ግን እናታቸው ናቸው በህሊናቸው የቀረጹላቸው። ስለ ኢት ጵያ ከልጅነታቸው ጀምሮ በተቆርቋሪነት እንዲያድጉ አድርገዋቸዋል።

 በዚህ ውስጥ የአገር መሪነት ሰብዕና አብሯቸው እንዲያድግ አድርገዋቸዋል። ይህ እንግዲህ እንደ መጸሐፍ ገልጠን ማንበብ የማንችለው እጅግ ጥልቅ እና ረቂቅ ጉዳይ ነው። በዛ ላይ የሴቶችን ጥልቅ የቪዥን፤ የምናብ ርቀትም አብሮ ስላደገ በዬትኛውም ሁኔታ የሚያገኟቸውን ሴቶች በዚህ የውስጥ የመለወጥ አቅም ነው የሚቀበሏቸው። ይህ ቀላል እንዳይመስላችሁ። ለዚህም ነው በሴቶች ብቃት ላይ በፍጹም ሁኔታ የተለዬ አቅም ያለው ቋሚ ዕምነት ያለቸው።

አሁን ወደ እኔ እናት ስመጣ እናቴ ደጎችንም ፈጥሯል ፈጣሪ ለማለት የምታስችል ናት። በቃ ሌላ አላወረሰችንም ደግነት ነው። ቅነት የሚባል የለም። ለሰው ሥጦታ መስጠት ታላቁ ባህሏ ነው። ብቻዋን የምትደሰትበት ምንም አይነት ሁኔታ የለም። እናቴ አጭር ስለሆነች ስፒል ጫማ ነው ምታዘወትረው። እና ለእኔ ጨርቅ ውስጥ ታስገባ እና አረማመድ ታስተምረኛለች። ከልጅነቴ ጀምሮ ከራሴ ላይ ቀሌቤ ስለማስር ደግሞ ለዛ የሚሆን ነገር ስታገኝ ትገዛልኛለች። ደስታዬን ምርጫዬን ትጠብቅልኛለች። ዛሬም ቀልቤ አልባ አልወጣም በልብሴ በፖርሳዬ ልክ ቀልቤ አልኝ። ዛሬ የምለጥፈው ፎቶ ሁለት ልብስ ተገዛ፤ አንዱ ተቀደደ ማንገቻው እራሱ እኔ የሠራሁት ነው ከተቀደደው። ቀሪው ደግሞ የራሴ ቀልቤ ነው። ይህ የደስታ ስሜቴን ያዘለቀችው እናቴ ናት። አልከለከለችኝም ልጅ እያለሁኝ።

በሌላ በኩል ዛሬ ሳስበው ቴሌቪዥን ሳታይ ነው ሞድ አረማመድ ታስተመረኝ የነበረው። በጫማዋ ውስጥ ጨርቅ ትሞላ እና ታስተመረኛለች ስል በትክክል ነው የምታስተምረኝ። ኢሠፓ ካኪ ነው የሚለበሰው። የ እኔ ካኪ ከ አስመራ ይመታል ያው የካታሎግ ደንበኛ ነኝ ከ ስብሰባ መደበኛ ውጭ ያለው የዘወትር ልብሴ በዲዛን ነው የሚሠራው የነበረው። ካኪ አይመስልም ነበር።

ዛሬ በነገሬ ሁሉ ዲዛይን መስረታዊ መለያዬ ነው። ግጥሞቼን ሥሰራ ፊደላትም ሞድ ውስጥ አስገብቼ ነው። ይህ እንግዲህ በዓለም የመጀመሪያው ነው። እርእሳቸውም ነፃነታቸውን ጠብቄ ከፈለጉት ቦታ ነው። አልተጫናኳቸው። ስለምን እናቴ በነፃነት ስላሰደገችኝ በነገሬ ሁሉ ነፃነቴን አላስደፈርም። ምንም ይቀር እንጂ ልብ እንዲገጠምልኝ አልፈቅደም። በራሴ መንገድ እና መርህ ነው የምመራው።

ቤት ውስጥም አከራዮቼን አስፈቅጄ ደስ በሚለኝ ቀለም በዲዛይን በቀለም ገነት አንድርጌ እኖራለሁኝ ቤቴን። የፈለገች ጠባብ፤ ካንፕ ውስጥ ይሁን። ጥበብ መኖርን የሚያሳምር የመኖር ንጹሕ አዬር ነው። አሁን እነዚህን ሁለት ግጥሞች ትመለከቷቸው ዘንድ በተከታታይ ተለጥፈዋል።

ይሄ ማለት ወላጆች በልጅነት በህሊናችን የሚዘሩት መልካም ነገር መልካም ዘርን፤ ክፉ ከሆነ ደግሞ ክፉ ዘርን ይተካል እና ወላጆች ልጆችን ማብላት ማጠት ብቻ ሳይሆን ስለወደፊቱ ህይወታቸው ራያን የመቅረጽ፤ የማደራጀት፤ የመምራት ታላቅ ማህበረሰባዊ ድርሻ አለባችሁ ነው ቁም ነገሩ።

እርግጥ ነው በሴራው ፖለቲካ ግርዶሽ ምክንያት መጸሐፍቶቼ ታሽጋው ስቶር ለዛሬው ያሞቃሉ አንድ የተባረከ ቅዱስ መንፈስ ግን ነገ አደባባይ ያወጣዋል። በነገራችን ላይ በነፃ የላኩላቸው ወገኖቼ ሳይቀሩ መድረኩ አክሰሱ አጋጣሚው እያላቸው አፍነው አስቀምጠውታል። ወይም አቃጥለውት ይሆናል። እኛ እንዲህ ነን። በነፃ ልሰጣቸው የወሰድኩላቸው ደግሞ እቁብ ሳይሰጡት ይዥው ተመልሻለሁኝ። ግን አንድ ቀን መፍትሄ ያገኛል። የሆነ ሆኖ ሆኖ … ይሄው አይዋ እንቅልፍ …

እንቅልፍፍፍፍፍፍፍፍ-ዶፍ-አታንደፋደፍ-አትደፍ፤ቅርፍ-ግርድፍድፍ-ንፍርፍር
እንቅልፍፍፍፍፍፍ  ፍ
እንቅልፍፍፍፍፍ      ፍፍ
እንቅልፍፍፍፍ           ፍፍ
እንቅልፍፍፍ                ፍፍ
አንቅልፍ                 እንቅልፍ
እንቅልፍ- አታውርድ ቸነፈር-ወኔንን አትቀርፍፍፍ፤አቅልን አታጨማትር-ጸጋን አትወርፍ
ከእኔ ወረድ በል-እኮ-እፍፍፍፍፍ-በል አንት ቀረፈፍፍፍፍ-አታንቀራ ፍ ፍ ፍ ፍ፤
አታንኮራፋ ለቀቅ አድርገኝ … እፍ በል እፍ ከዓይን
ንቃትን አትቀፍቅፍ አንተ የቡጀሌ እርፍ ቅርንፍ
ሁሌ እንቅልፍ ቅፍፍፍፍፍፍ … የሞት እድፍ …..


·       መቀፍፈቀፍ ... እድገትን ማጨናገፍ፤ እድገትን መግታት፤
·       የዋናውን ግንድ ቅርንጫፎቹን መልምሎ ባዶ ማሰቀረት
·         ተጣፈ፣---  መሰከረም 24 ቀን 2002 ዓ.ም - ሲዊዘርላንድ
·         ተስፋ መጽሐፌ ላይ ገጽ 20 ይገኛል።
·         እርእሱ እንቅልፍ ነው።  
·         ዋናው ቁም ነገር ባቡሩ እዬፈጠነ ነው አብረን ለመጓዝ አናቀላፋ ነው ቁም ነገሩ።፡


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።