የሰርገኛ ጤፍ ጦርነት።

የሰርገኛ ጤፍ ጦርነት።
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 03.07.2018 (ከጭምቷ ሲዊዝ።)
„ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፣ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።“
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ  ፮ ቁጥር ፴፬)


  • ·       ንደ መክፈቻ።

ዛሬ ሲዊዝሻ ሳይቀናት ቀረ። ጨዋታውም ማራኪ አልነበረም። እንዲያውም በግልጽ ቋንቋ የዓለም ዋንጫ ውድድርም አይመስልም ነበር። የእኔ ሲዊዝ ባትኖር ኖሮ እስከ መጨረሻውም አልከታተለውም ነበር። አሰልቺ ነበር። ሲዊድንም ከማጥቃት ይልቅ፤ ከመጫወት ይልቅ 12 መረብ ጠባቂ አሰልፎ ነበር ጨዋታው የተጠናቀቀው። በር ዘግቶ ጨዋታ። 

በመጀመሪያ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ለሁለት ደቂቃ ያህል ሲዊዞች ጨዋታ ተጫውታዋል። ከዛ በተረፈ ግን ኳስም እንዳሻት፤ እግርም እንዳሰኛው፤ ጭንቅላትም ወደ ፈለገው ሲጎን ደቂቃው ተጠናቀቀ እና ሲዊድን አንዲት ግብ በአሳር አስገብቶ ለቀጣዩ ጨዋታ ቢያልፍም ያው ለዋንጫ አይደርስም ባይ ነኝ። ሁለቱም ቡድኖች የልብ አድርስ ነገር በጭራሽ አልሞከሩትም። አሁን ሲዊዝሻ የመኪና ጡሩንባ የለም፤ ጸጥ ረጭ ሁላችንም አለን። ቆቡም አልወለቀም፤ ምንኩስናችንም ይቀጥላል። ቆባችን ይጠብቅ ፈጣሪያችን። አሜን!
  • ·       የወግ ገበታ።

ዛሬ የተለያዩ አጫጭር ነገሮችን ሳደማምጥ ስርክራኪ ነገሮችን አዳመጥኩኝ። ያው "የሥም ግነቱ" ወደ አልተፈለገ አቅጣጫም ሊወስድ እንደሚችል ስጋት ቢጤ። እኔ እኮ ስለምን የቀደሙ ነገሮችን ለማጥናት እንደማይሞከር አይገባኝ። አሁን እከሌ ተከሌ ማለት ስልችቶኛል ደግሞም ፍርድ ለራስ ስለሆነ የተባጀበትን ታውቁታአለችሁ።

„አንባገነን“ ቢሆን የአፍሪካ ደም እያለበት ያነን ማሳብ ይከብደናል የሚሉ አዳምጫለሁኝ። በሌላም እንዲሁ አገር ቤት ከመግባት ጋር ወደ "አንባገነንነት"  እንዳሄደም ለመከላከል የሚልም አለበት። የዛሬውን ብቻ ስለምናይ እንጂ የቀደመውን የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጥረታቸውን፤ መንፈሳቸውን፤ ሰብዕናቸውን ለማጥናት ብንሞክር ጥርት ያለ አቋም ይዘን ፈጣሪንም አናስከፋም ነበር። እንደገናም አስፍስፈው ሊውጧቸው ለአሰቡ ክፉ መንፈሶችም አቅም አንፈጥርላቸውም ነበር። ምንም ክፍተት ሳንከፍት የክፎዎችን ልብ በዝምታ ብቻ መደብደብ በቻልንም ነበር።

ፈጣሪ ለሰው ልጅ ሁለት ሦስት ጊዜ ዕድል አይሰጥም። አንድ በር ይከፍታል። በዛ መጠቀም ከተቻለ ትጠቀማለህ። ከተሳነህ ይዘጋል። አሁን ሰፊ የሆነ የበቃችሁ ድምጽ እዮር እያሰማ ነው። ይህን የበቃችሁ ድምጽ እንደ ገሃዱ ዓለም ሳይሆን በመንፈስ እንደ ዕምነታችን ተቀብለን ለዚህ መትጋት ያስፈልጋል።

43 ዓመት የኖርንበት መጠራጠር እኮ ከበቂ በላይ ነው። አፍሪካ ደም ስላለበት አንድ ሰው አንባገነን አይሆንም። ማዲባ አፍሪካዊ ደም አላቸው ግን አንባገነን መሪ አልሆኑም። የሌሎች አገሮችን መሪዎችም ስናስብ አፍሪካዊ ደም ሳይኖርባቸው አንባገነኖች የነበሩም ነበሩ። ቀድሞ ነገር የጠራ ቋንቋ መጠቀም ስለማንችል እንጂ ዶር አብይ እኮ የሰባዕዊ መብትም ተሟጋች ናቸው።

የሰብዕዊ መብት ተሟገችነታቸው አንድን ዘርፍ ወይንም አንድን የህብረሰተሰብ ክፍል ነጥለው አይደለም። ሁሉንም የህብረተስብ ቤተሰብ ሰው በሚለው ማዕቀፍ ነው የሚያዩት። ይህም የዛሬ አይደለም። ሲፈጣሩ የተሰጣቸው ጸጋቸው ነው። የተመረቁበት የተፈጠሩበት። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊትም መልዕክትም ይዞ ነው የሚፈጠረው።

ይህም ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም አክቲቢስት ናቸው። የእጽዋቶቻችን DNN ተዘረፍን ብለው የሚጸጸቱ ናቸው። ይህም ብቻ አይደለም በምህዋር ምርምር የዛሬውን ዘመን የሚሞግት የጥበብ የሳይንስ ዓውድ ቦረና እና ዋልድባ አለን ብለው ስለ እሱ አጀንዳቸው ያደረጉ ናቸው። ወፎች ወንዞች ስለምን ሰላማቸው ይታወካል ብለው የሚቆረቆሩ ናቸው። የዛሬ 5 ዓመት እስራኤል አገር ከአቶ ደመቀ መኮነን ከመሩት ልዑክ ጋርም ሄደው የዛሬ 25 ዓመት ቪዥን የምታደርጋት ኢትዮጵያ ምን ትመስላለች ሲባሉ፤ ከዛ ባነሰ ጊዜ እኔ ቪዥን የማደርጋት ኢትዮጵያ ዕውን ትሆናለች ነበር ያሉት። በተጨማሪም ጥበብን ፍለጋ ወደ ሰለሞንም የሄደቸውን የንግሥት ሳባን መንፈስም መከተላቸውን ያመላክት ነበር መልሳቸው። 

አንድ የኮርያ ጋዜጠኛ ላቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ ምን ያህል እናት አገራቸውን ኢትዮጵያን የደማቸው ጉልላት እንደ ሆነች ያመላክታል። አንድ ጹሑፍ አንድ ቀን „ሰው ሰው የሚሸት“ መሪ ናፈቀኝ ይል ነበር። ፎቶው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ያሉበት ነው። እሳቸው እኮ ከተመረጡ በኋዋላ ነው ያ ጹሑፍ የተጻፈው አሁን ዛሬ  በአንድ ቃለ ምልልስ የተመኘሁትን አይቼ አገኘሁ ሲል አዳመጥኩት። የተማረ የተመራመረ የሚጥፍ ወገን ነው። ስለምን እንደምንቸኩል አላውቅም።  

ምን ለማለት ነው ትርፍ የሆኖ የሰብዕና ጥርጣሬዎችን ከላያችን ብንገፍ ፈጣሪም አይከፋብን። ልዝርዝርህ፤ ልምንዝርህ፤ ልበትንህ ብንለው እንኳን አንችለውም። ስንቱ ተዘርዝሮ ተንትኖ ያልቃል። ተግባሩ እኮ እዬወጣን ነው። በጣም በእርግጠኝነት እምናገረው ፍቅርን ስለምንሰጣቸው ቢያበረታቸው እንጂ ከተፈጥሮ ሰብዕናቸው አንዲትም ስንዝር አይቀንሱባትም።

ስለምን? ተፈጥሯቸው አይፈቅደም። በፍጹም ሁኔታ የምናፍቃችሁ የአገሬ ልጆች አንባገነን መሪ ይሆናሉ ብላችሁ አትሰቡት። የአማራቸው ካሉም ሲያምራቸው ይቅር ነው። አይደለም ለኢትዮጵያ ለአፍሪካም ኢትዮጵያ መሬት ላይ የሰዋዊነት፤ የተፈጥሯዊነት መርህ በድርጊት ይከውነበታል። ተቋም ይከፈታል። ኢትዮጵያ በከበረ የሰው ልጆች አያያዝ ናሙና እንደምትሆኑ  እምኑኝ። እንዲህ ስል ሊከብዳችሁ ይችላል። 

ውዶቼ እባካችሁን አይከብዳችሁ? ከእኛ በላይ እያንዳንዱን የዓለም የሰባዕዊ መብት ድንጋጌዎች ያውቋቸዋል፤ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ እና እንክብካቤንም በሚገባ የተረዱ መሪ ናቸው። ሰዋዊ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊ መሪ ናቸው።

ለአማንያን እንዲህ ተቀድሰው፤ ተባርከው የሚፈጠሩ ቅዱሳን እንዳሉን እናውቃለን። እናታቸን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ፤ አባታችን አቡነ ተ/ ሃይማኖት፤ አባታችን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ወዘተ …

„አንባገነን“ የሚለው ራሱ ቃሉን በሳቸው ህይወት ለመጠቀም ይመዘምዛል። ሰብዕናቸው የተለዬ ነው። ሥነ - ልቦናቸውም የጠራ ነው። በጣም ሩቅ ናቸው። እንዲያውም ከሚታወቀው ሰብዕናቸው ይልቅ የማናውቀው ሰብዕናቸው ደግነታቸው ይበልጣል።

ለምሳሌ ለጋስ ናቸው። የቸገረውን በመርዳትብቻ አይደለም ልምዳቸውን፤ ተመክሯቸውን ክህሎታቸውን ለማከፋል አይሰስቱም። ሁሉም በዛ ውስጥ ሰልጥኖ እሳቸውን በልጦ እንዲወጣ የሚታትሩ ቅን ናቸው። እኛ የኖርንበት ፖለቲካ ደግሞ ወይ የለንም ቢኖርንም ሁሉን ለመስጠት ፈቃደኞች አይደለንም። በተቀማጭ የተቀመጠ ነው። ስስታሞች ነን። 

አቅም ያለው ሲወጣም ጦርነት ማወጃችን ያው ሁሉም አርኬቡን ይጠይቅ፤ ምን እዬለቀመ ሲለጥፍ እንደ ነበረ። እንዲጨናጎል ተግተን ሰራን። ተው እያልኩኝ። ማን ይስማ? ማን ያዳምጥ። ቅንነታቸው ነው ያተረፋቸው እንጂ እንደ ክፉዎችማ ቢሆን አምልጠውን ነበር።  ነገም ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ አይታወቅም። ጦርነቱ የእርስበርስ ነው። ጦርነቱ የሠርገኛ ጤፍ ጉዳይ ነው።
  • ·       ጥን

ይሄ ጹሑፍ መጋቢት ላይ ለጠ/ ሚር ሲወዳደሩ ለሙግት የሠራሁት ነው። ሊንኮችን ጥቄቶችን ለጥፌ ስለነበር ማዬት ይቻላል። ሰብዕናቸው ለመተርጎም ይከብዳል።
  • ·       ሊና

  • ·       ብይ የኢትዮጵያ ፍላጎት ማጠቃለያ።

አገራዊ ጉዳይ አጀንዳችን ከሆነ ሁሉንም ጊዜ ሰጥቶ ማጥናት ይጠይቃል። ያን ማጥናት ካልተቻለ ዝንጣፊ ነው የምንሆነው። በፍጹም ሁኔታ መታመንን ሳንስስት ልንለግሳቸው ይገባል። አንባገነን አይሆኑም። በፍጹም። ቃሉ ራሱ ከሳቸው ጋር መለካለክ እና ማነካካት ሃጢያት ነው። ይህ ደግሞ ገና የኦህዴድ ጽ/ ቤት ሃላፊ ሳሉ ለሰራሁት አብይ ኬኛ 6ኛ ክፍል ማጠቃለያው ነው። 

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
የኔዎቹ  ኑሩልኝ። ማለፊያ ጊዜ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁኝ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።