ልጥፎች

ክፍል አምስት - ርትህ።

ምስል
ርትህ። ክፍል አምስት። ከሥርጉተ ሥላሴ02.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) „ዪሚያስታርቁ ብፁዕና ናቸው የእግዚአብሄር ልጆች ይባላሉና።“ (ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፱) ·          መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=_WVc5bXyb5c „ጠ / ሚ ዶ / ር አብይ አህመድ ከአፋር ህዝብ ጋር ያደረጉት ሙሉ ውይይት PM Dr Abiy Ahmed discusses with the people of Afar“ በዚህ ውስጥ የሠማራውን ጉባኤ መዳሰስ የምፈልገው ከ20.38 ባለው ደቂቃ ብቻ ያደመጥኩትን ነው። ቀሪው ክ/ጊዜ ደግሞ ይቀጥላል ማለት ነው። ይህን እማደርግበት ዋናው ምክንያት ዛሬ ያለው የለውጥ ተስፋ እና እኛ ያለን መጣጠም መቀራረብ እንዲኖረው ለማድረግ ነው። ክፍተት ከኖረም መገጠም ስለሚያስፈልገው ነው። ·        ተጠቃሚና ጥቅሙ ትልልፍ። በዚህ በአፋሩ ስብሰባ የአፋሩ ጉባኤ አልተጠቀምነም የሚል ዕድምታ ቢደመጥም አፋር የተጠቀመበትን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ለማመሳከሪያነት አንስተዋል። አውሮፕላን ማረፊያው እና የተሰበሰቡበትን አዳራሽ እንደ ምስክር አቅረበዋል። ይሄ ከሆነ ስለምን ትግራይ አልተጠቀመም የሚለውን አገላለጻቸውን በዚህ መነጸር ሊያመዛዝኑት እንደማይፍለጉ ብዙም ግልጽ አይደለም ለእኔ። ብሶትን ለማቀጣጠል ክብሪት መሆኑን መድፈር ባይችሉም ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከመጣ በ ኋ ዋላ የተወለዱት ልጆች ሳይቀሩ ደግሜ የተወለድኩ ያህል ይሰማኛል ያሉበት ምክንያት ጥናት ሊደረግበት ይገባል። ከዚህ በላይ በራብ ውስጥ፤ በሞት ውስጥ፤ በመፈናቀል ውስጥ ያለ ህዝብ ከዚህው ሥርዓት ጋር እዬሠሩ ተስፋዬ ብሎ ሊደግፋቸው፤ አይዞህ ሊላቸው የሚፈልግበትን መሠረ

እናት መቅድመ ት/ ቤት ናት!

ምስል
እናት መቅደመ ት/ቤት ናት! ከሥርጉተ ሥላሴ 03.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) „ፍቅራችሁ  በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ።“ (ወደ ፊልጵስዩስ ምዕራፍ ፩ ቁጥር  ፲፩ ።) ቀልቤ እና እኔ እንዲህ እና እንዲህ ነን! ውዶቼ እንዴት ናችሁ? መሰረተ ሃሰቡን ደግሜዋለሁ መነሻ መሰረቱን። ምክንያቱም የጹሁፌ ታዳሚዎች አንዱን አንብበው ሌላውን ሳያነቡ የሚቀሩ ስላሉ። የእኔ እናት እብዬ እኔን በዲዛይን በሞድ ውስጥ እንዴት እንዳሳደገችኝ እና አባቴ አበይ ከመጻህፍት ጋር እንዴት እንድቆራኝ አድርጎ ስለሳደግኝ የሁለቱንም ጥረት ግጥሜ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።  መጻፉን ከአበይ ጥረት ዲዛይኑን ደግሞ ከእብዬ ፍልቀት አስተጋብሬ እንዴት እንዳቀርብኩት ማዬት ይቻላል። የእኔ ትልቁ ቁምነገር የትም ቦታ ስሄድ፤ ስገኝ ለመማር መፍቀዴ ነው። እንጂ ዕድሉን አግኘቼ ዩንቨርስቲ አልገባሁም። ግን የደረጃ ተማሪ ብቻ ሳይልሆን ሰቃይም ነበርኩ። አንብቤ ስለማይደክመኝ። አሁን ዛሬ ስነሳ ራሴን አሞኝ ነበር ግን መጻፍ ስጀምር አምላካችሁ አለ ብን አለ …     ግን ለተረገጡ የደህና ናችሁ ወይ ክብረቶቼ ? ዛሬ ያስፈራል። የሰማዩ ሰላማዊ ሰልፍ አይሎ ሲወዚሻ ጠቆርቆር ባለ አዬር ታውዳለች። ያጉረመርማል በብልጭታ ማስጠንቀቂያው አዬል ብሏል፤ እቴጌ ጣዬም የለችም። ተጫጉላው ሆና ይሆናል።  የእሷ ነገር እንዲህ ነው ብቅ ጥልቅ፤ ጥልቅ ብቅ። አንጠልጣይ። ግን በሚገርም ሁኔታ ደግሞ ቤት ውስጥ ብርድ የለም። ውጪ ይዘንባል ቤት ደግሞ ይሞቃል። ሲዊዚሻ ከአውሮፓ የተለዬ የሚያደርጋት አንድ ቀን በርታ ያለ ሙቀት በቀጣዩ ቀን ደግሞ የሚያቀዘቅዝ አዬር በሚዛን ኑሩ ነው ምክሯ። ተባረኪ! ·        ምስክርነት። የኔ

ብርሃነ እናት።

ምስል
ብርሃነ እናት! ከሥርጉተ ሥላሴ 03.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) „ለእኔ ህይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነውና። ጳውሎስ ወደ ፊሊጵስዮስ ሰዎች ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፳፩“ ውዶቼ እንዴት ናችሁ ? የደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ያስፈራል። የሰማዩ ሰላማዊ ሰልፍ አይሎ ሲወዚሻ ጠቆርቆር ባለ አዬር ታውዳለች። ያጉረመርማል በብልጭታ ማስጠንቀቂያው አዬል ብሏል፤ እቴጌ ጣዬም የለችም። ተጫጉላው ሆና ይሆናል።  የእሷ ነገር እንዲህ ነው ብቅ ጥልቅ፤ ጥልቅ ብቅ። አንጠልጣይ። ግን በሚገርም ሁኔታ ደግሞ ቤት ውስጥ ብርድ የለም። ውጪ ይዘንባል ቤት ደግሞ ይሞቃል። ሲዊዚሻ ከአውሮፓ የተለዬ የሚያደርጋት አንድ ቀን በርታ ያለ ሙቀት በቀጣዩ ቀን ደግሞ የሚያቀዘቅዝ አዬር በሚዛን ኑሩ ነው ምክሯ። ተባረኪ! ምስክርነት ። የኔዎቹ ቅኖቹ ፣--- ዛሬ ወደ ተጀመረው ርትሃዊ የወግ ገበታ ከማምራታችን በፊት አንድ ነገር ለመንገድ ልንገራችሁ ፈለግሁኝ። ይፈቀዳል አይደል? የተጀመረው ዕርስ ርትህ ይቀጥላል። ግን ማህል ላይ ጥበብ እና እኛን ስናዋድደው መልካምኛ ነው። አንድ ጊዜ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የእናታቸውን ህልም ስለ ሳቸው ራዕያዊ ነገር ሲገልጡ 7ኛ ንጉሥ ትሆናለህ ብላኝ ነበር ስላሉ በማጣጣል፤ በማሽሟጠጥ፤ በማቃለል የተመለከቱት ብዙ ነበሩ። እኔ ደግሞ ወጣ ባለ ሁኔታ ነው የምመለከተው። በ እኔም የደረሰ ስላለ። አበይ ለመላ ቤተሰቡ ሁሉ ልጄ ሁለት አንጎል ጥምር ጭንቅላት አላት እያለ ነው ያሳደገኝ።  7 ዓመቴ ላይ ነው ጠረጵዛ ላይ ሆኜ በማንበብ ፕረዘንቴሽን ያስጀመረኝ። በመጻፍ በማንበብ ሃሳቦችን ውስጥ ስለማድረግም የጠበቀ መሰረት ጥሎልኛል። ለዛውም አብረው ቢቀጥሉ ኖሮ ዛሬ ሥርጉተ እንዲህ ሆና ባልቀረች ነበር። የሆነ ሆኖ ለ

ዳማዊ ቀን እና ጠይም ዕንቁዎች ያሉበት የቤልጀሙ ቡድን ለሩብ ...

ምስል
ጠይም ዕንቁዎች ያሉበት የቤልጀሙ ቡድን ለሩብ ፍጻሜ አለፈ። ከሥርጉተ ሥላሴ 03.07.2018 (ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዕን ናቸው፡ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። (የማቴወስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፲) የቀኑን ጨዋታ አልተከታተልኩትም። ብራዚል ለሩብ ፍጻሜ እንዳለፈ ፊፋ ሪፖርት ላይ አንብቤያለሁኝ። የምሽቱን ግን በርጋ ተከታትዬዋለሁኝ። ቤልጀም እና ጃፓኖች ነበሩ የተጋጠሙት። የመጀመሪያው የእረፍት ክ/ ጊዜ ላይ ጀፓኖች በሚገርም ብቃት ተንቀስቃሰዋል። እስኪገርመኝ ድረስ። ፈጽሞ እንዲህ አለጠበቅኳቸውም ነበር። ፍጥነታቸው፣ የመከላከል ሆነ የማጥቃት ውህደታዊ እንቅስስቃሴያቸው በአግራሞት ነበር የተከታተልኩት። ለዛውም ከቤልጄም ጋር … ህም! እርግጥ ነው ከ2014 የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ጀምሮ ቤልጀሞች የተከደነ ብቃት እንዳላቸው አስተውያለሁኝ። በ2016 ፈረንሳይ አገር ተካሄዶ በነበረው የአውሮፓ የዋንጫ ጨዋታም አስደሳች የአጨዋወት ስልት እና ሙሉ ሞራላዊ ሥነ - ምግባር እንዳላቸው በተጨማሪነት አይቻለሁኝ። እንዲያውም ያን ጊዜ ቤልጀም እና ፈረንሳይ የቦን ጥቃት ሰለባ ስለነበሩ ብዙ መከራ ያሳለፉ ስለሆኑ ከሁለቱ አገሮች ለአንዱ ዋንጫው ቢሆን የህዝቡን መከፋት ሚዛናዊ ያደርገዋል የሚል ህልም ነበረኝ።  ነገር ግን ዋንጫውን ፖርቹጋል ወሰደ። ፈረንሳዮች አጅግ ብርቱዎች ነበሩ በለስ ሳይቀናቸው ቀረ። ዘንድሮም እኔ ለቤልጄም ያው መስል ህልም አለኝ። ያው ከሲዊዝሻ ባይበልጥብኝም። ነገ ቀን ላይ ሲዊዝሻ ከሲወዲን ጋር ግጥሚያ አለባት። በሻማ ብርሃን ነው እምታደመው። መቼም መነኩሲያዋ ሲወዝ ቆቧን አውልቃ ለሩብ ፍጻሜ ካለፈች የእኔውም አይቀርለትም ...ፌስታው ከልክ በላይ ይሆናል።   በዛሬው

ክፍል አራት ርትህ።

ምስል
ርትህ። ክፍል አራት። ከሥርጉተ © ሥላሴ 01.06.2018 (ከመንኩሲያዋ ሲዊዘርላንድ።) „የሚምሩ ብብፁዓን ናቸው ይማራሉ እና“ (የማቴወስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፯) ·        መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=_WVc5bXyb5c ጠ / ሚ ዶ / ር አብይ አህመድ ከአፋር ህዝብ ጋር ያደረጉት ሙሉ ውይይት PM Dr Abiy Ahmed discusses with the people of Afar ·        የወግ ገበታ። ውዶቼ ቀደም ሲል የነሳ ኋ ዋቸው ከክፍል አንድ እስከ ሦስት ድረስ ለመነሻ መዳረሻ የሚሆኑትን ብቻ ስለነበር ሊንኩ አለጠፍኩትም ነበር። አሁን በዚህ በክፍል አራት የምናዬው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሠመራ በነበረው ጉባኤ ላይ የሰጡትን መልስ አስኳል ጉዳዮችን ማዬት ስለሚያስፈልግ ነው። በዚህ ክፍል እስከ መግቢያዋ ላይ ያለችውን ጥላቻን ብቻን ማዬት ብንችል ብያለሁኝ አሁን። እንዳይበዛ እንዲሁም አሰልቺም እንዳይሆን። „ሰው ጠልተህ መተኛት አትችልም። ሌሊቱን ሰውዬው በሌለበት ስትቃጠል ነው የምታድረው። እሱ አያይህም። ያለህበትን ሁኔታ አያውቅም። አንተ ግን ስትቃጠል ታድራለህ። ከዚህ ውጪ መወጣት አለበት። ሰውን ለመጥላት መሮጥ ነገርን ለማሰብ  አዕምሮአችን ማበላሸት የለብንም! ጊዜያችን ማጥፋት የለብንም! እኛ ምን እንደርጋለን? ሰው እንወዳለን! ሰው እናቀርባለን! እስከተቻለን ድረስ ሰውን እንረዳለን። ነገር ግን የሚጠሉን ሰዎች እንደሚኖሩ እናውቃለን። ዓለም እንዲህ ስለሆነች። ሰዎች ሲጠሉህ አንተም ቁልቁል ተመልሰህ ጥላቻ ውስጥ ከገባህ በእነሱ ሜዳ ውስጥ ገብተህ እዬተጫወትክ ነው ማለት ነው። የጦር ሜዳው