የበቀል ሞት!

  • ·

ፎሪን ጠ/ ሚር አብይ አህመድን ሰብዕና አላወቀውም ወይንም አላጠናውም።
  • ከአፌ ቃል ፈቀቅ አትበል።“
    (ምሳሌ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፭)
    ከሥርጉተ ሥላሴ 14.07.2018
    (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላድን።)


  •       መነሻ።

awaze newsን ካነሳሁኝ ፎሪን ለአማራ ተጋድሎ የሰጠው ዕውቅና እና ክብር እጅግ አስደስቶኛል። በቃ „የነፃነት ሃይሉ“ የፉከራ እና የቀረርቶ ሞገድ ተንሳፎ የብል ራት ሆኖ ቀረልኝ። ተመስገን!

ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን … ዛሬ ጥዋት አዋዜን አዳመጥኩት፤ እናም ይህን መልስ ከስሩ ለጠፍኩኝ። ምን አልባት ታዳሚዎቼ ካለነበባችሁት፤ ካላገኛችሁት ብዬ በድጋሜ ብሎጌ ላይ መለጠፍ ግድ  አለኝ። 

በዚህ የዓለም አቀፉ አንጋፋ ጋዜጠኛ ትንተና ላይ ከግላዊ ስሜት በፍጹም ሁኔታ የራቁ ግን የነጠሩ እና የበለጡ እጅግ ብልህ የሆኖ የኢትዮጵያን ፖለቲካው መንፈስ በውል የመረመሩ ጉዳዮች ተነስተዋል። ጋዜጠኛ እንደዚህ ነው መሆን ያለበት። ከስሜት ርቆ ግን ፋክቶችን ፈልፍሎ አቅጣጫ ማመላከት፤ ቅን ጉዳዮች የበለጠ እንዲበረታቱ መሠረት ያለው ተግባር መከወን።

እንጂ የራስን ስሜት በሚገፋ ስጋውን እንደተነሳ ውሻ የህዝብን መንፈስ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ የሚመሩ ጫሪ ፤ ቆስቋሽ መንፈሶችን እያነካኩ ማቆሳሰል አይደለም። ከሁሉ በላይ አሁን ያለንበት ዘመን መሪ ያለበት ዘመን ነው። 

መሪ ነኝ ለሚለውም ተፎካካሪ ፓርቲ ሁሉ መሪ አልባ ሆኖ የኖረበት ረግረጋማ ጨቀጨቆች ተወግደው ጥርት ያለ ብሩህ የስውኛ መስመር የተዘረጋበት ነው … በተለመደው ዙረህ እቀፈኝ የመገዳዳል የመበቃቃል የቁርሾ ጠጅ መልስ እና ቅልቅል ያከተመበት አዲስ ዘመን ላይ እንገኛለን። ሰው ካሰበው ፈጣሪ ያሰበው አሸነፊ ሆኗል። ተመስገን። 

  • ስለ አዋዜ ዘገባ ያለኝ ምልከታ የሰጠሁትም የመልስ በስምምነት።

እርግጥ ነው ትንሽ ማጠናከሪያዎችን ጨምሬያለሁኝ። እድምታው ግን ይህን ይመስላል።

ጤና ይስጥልኝ ዓለም ዓቀፉ ጋዜጠኛ አቶ ዓለምነህ ዋሴ እንዴት አደርክ? መግቢያው የዛሬ ትንተናህ የፋክት ቤተኛ ነው።

 በማህበራዊ፤ በኢኮኖሚ፤ በፖለቲካ፤ በህግ ጉዳዮች ላይ ያሉ ፋክቶች አሉ። እንኝህ ፋክቶችን መሠረት አድርገው የሚነሱ የፍልስፍና፤ የምርምር፤ የጥልቅ ትንታኔ ግንዛቤዎች በቤተ መጸሐፍት እራሱን የቻለ ዲፓርትመንት አላቸው። ፋክት ተብለው ነው የሚጠቃለሉት። ስለሆነም  የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት ማዕቀፉ ዓላማ እና ግቡን በሚመለከት ፋክታዊ ትንተና ነበር። 

እጅግ አድርጌ የተመሰጥኩበት ነው። ሌላ አንድ ወሳኝ ጭብጥም አንስተሃል በተፈጥሮ የሚገኙ የአማራር ጸጋዎች እና የማህብረሰቡ መንፈሳዊ ቁርኝት የሚፈጥሩ አመኔታ የተጠቃሚነታችን ደረጃ፤ ይህም ሌላው ተነስቶ የማያወቅ ብልህ ትንታኔ ነው። 

እኔም እሰራበታለሁኝ። እኔ ኢትዮጵያ በተፃፈም ባልተፃፍም ህግ ትተዳደራለች ተፈፃሚውም ያተልፃፈው ነው ምክንያቱም ህዝቡ የፈቀደው ስለሚሆን እያልኩ ቡዙ ጊዜ እጽፋለሁኝ።

የፎሪን ዘገባ እና ትንታኔ ከደህንነት ጋር በተገናዘበ መልኩም የሚታይ ቢሆንም የትንተናው አስኳል ግን የዶር አብይ አህመድን ሰብዕና በጥልቀት ያለማወቅ ችግር ይመለሰለኛል፤ የብዙ ሰው ግድፍት ምንጩ ይሄው ነበር። 

ሰብዕናቸው ለማናቸውም አይነት ንግድ የተፈጠረ አይደለም። ሰብዕናቸው ያለ ሸፍጥ ሰውን ማስደስት፤ ሰውን ማቀራረብ፤ ሰውን በራሱ ውስጥ ታርቆ እንዲኖር እና ሰላሙን እንዲገኝ መፍቀድ ነው።

ሌላው ጥቁርነታቸው እና አፍሪካዊነተቸው ሌላም የተመሰጠረ ግብረ ምላሽ አለበት። አፍሪካ ሁሉ እያላት የሁሉም ነገር ተጠማኝ መሆኗ ያልተማቻቸው ሰው ናቸው። 

የመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ድርሻ በዓለም ሉላዊ ተሳትፎም አስፈላጊ ግን ዕውቅናው ስስ መሆነ፤ የአፍሪካ ቀንድ እና የአፍሪካ ቀንድ አገሮች በጂኦ ፖለቲካል ጸጋቸው ለዛሬ አይደለም ለ50 ዓመት ወደፊት ሊኖራቸው የሚችለው ግራጫማ ዕጣ ፈንታ ከባለቤትነታቸው ሊያወጣቸው ስለመቻሉ፤ በምናብ ከሆነ ቦታ ላይ የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ከእንቅልፋቸው እንዲነቁ ደወል መሆን ነው። ይሄንን እያነሳሱ ነው፤ ደግሞ ተሳክቶላቸዋል። 

አሁን የኤርትራ ይህንንም ሃላፊነት የእኔ እንድትለው ለማድረግ ማስቻል አንዱ ትልቁ ግባቸው ነው። ይሄ የዛሬ እንዳይመስለህ የቆዬ ህልም ነው። አሁን መሪ ስለሆኑ አቅም እንዲያገኝ አደረጉት፤  
ሌላው የኤርትራውያን የኢትዮጵውያን ዕጣ ፈንታ የስደት እና ውቅያኖስ ውስጥ አብሮ ቀብር መዋል የቆጠቆጣቸው ጉዳይ ነው።

ስለዚህ ይህን ዛሬ ቢጀመር ነገ ልጆቻችን በተከታይነት ሊወርሱት እንዲችሉ መሰረት ለማስያዝ ነው። ፎሪን እንዳነሳው ሳይሆን  በአብይ ሰብዕና ውስጥ በማጥቃት እና ለማጥቃት በማሴር ላይ የተመረኮዘ አይደለም። በፍጹም ሁኔታ ሰውን ተፈጥሮን ማዕከል አድርጎ የተነሳ ነው። ትግራይን የማግለል ኤርትራን የማቅረብ ከጫፋቸው የማይደርስ ጉዳይ ነው። 

በዶር አብይ አህመድ በክቡርነታቸው ዘንድ ሰው እኩል ነው። የሚጠሏቸውን፤ የሚያሳድዷቸውን፤ ሊገድሏቸው ያሴሩትንም ቢሆን ሰይጣን አሳሳታቸው ብለው የሚያምኑ ፈርሃ እግዚብሄር ያላቸው ሥጦታም ናቸው። ልክ እንደ እናታችን ቅደስት ክርስቶስ ሰምራ። ምርቃት የምትለው ዓይነት መሪ ናቸው።

እያንዳንዱን ፎቷቸው ሲታይ ሰውን ሲያገኙ ደስተኛ ናቸው። ለሰው ኮስታራ፣ ትእቢተኛ፣ ገረጭራጫና ብስጩ አይደሉም። እርግጥ ነው የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት በዚህ መልክ መቋጨቱ እኔ በግሌ ለነበረኝ ስጋት ትልቁ ተራራ ተንዶልኛል። 

መተማመንን አግኝቸበታለሁኝ። አጋራቸው እረዳታቸው ይሆኑላቸዋል፤ ስለዚህ የኤርትራ መንግሥት ምን ያደርጉ ይሆን ብዬ የምጠራጠረው ነገር በፍጹም ሁኔታ ከእኔ ተወግዷል። በመሃል ያለው ግንኙት ግን እርሾውም እንጀራውም ፍቅር ነው።

አሁን እኮ የወያኔ ሃርነት ትግራይ አይዲወሎጂ ብቻ ሳይሆን የ3ሺህ ዘመን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጠቅላላ አወቃቀርና አደረጃጃት ነው መሉ ለሙሉ ነው እዬተቀዬረ ያለው። ዬድርጅቶች ካድሬዎች ያልገባቸው ይሄው ጉዳይ ነው። ጋዜጠኞችም ያልጋባቸው ይሄው ነው። ተንታኞችም አረባ እና ቆቦ የሚረግጡ በዚህ ምክንያት ነው። ይህ ለ66ቱ የፖለቲካ ቅኝት ሁሉ መብረቅ ነው።

አቶ ዳውድ ይብሳም ይህ ስለቀረባቸው ነው አሁን ጦርነት ያወጁት፤ ሌላውም የሚያምሰን በዚኸው ምክንያት ነው ዶክተሪኑ ስለምን ተደፈረ ነው … ከሁሉ በላይ የዚህ ዓለም ዓቀፍ ዕውቅና ምንጩ የቄሮ እና የአማራ የህልውና ተጋድሎ ታሪክ በመሆኑ እሱን ገልብጠው የራሳቸው ታሪክ ለማድረግም ጭምር ነው። 

በዚህ ላይ ቄሮም የአማራ ማንነት የህልውና ተጋድሎም ድሉን አሳልፎ ላለመስጠት ከገዱ እና ከለማ መንፈስ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ መሰለፍ ይኖርበታል። ታሪኩን አዝልቆ ልጅ ልጅ ማውረስ አለበት።

ቄሮም ይሁን የአማራ ተጋድሎ በምንም መልኩ ይህን የደሙን የመስዋዕትነት ዋጋውን ለሽግግር መንግስት ለቅብጥርሶ ለምንትሶ ማዋል የለበትም። ሁለቱም ተጋድሎዎች ገድለኛ ሙሴ አግኝተዋል። ከገድለኛ ሙሴያቸው ጋር ማናቸውን መከራ ተሸከመው ታሪካቸውን ማዝለቅ ይኖርባቸዋል።

ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለራሷ ለኤርትራም የተስፋ ብርሃን ነው … ሌላው የቁሱ፤ የቀይ ምንጣፉ፤ የዲኮሩ፤ የድንበሩ ጉዳይ ትርፍ ነው። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥልጣን አያያዝ እና አጠቃቀም አማራር እና ሂደቱ ሙሉ ለሙለ በአዲስ ቅኝት ውስጥ ነው።  የተፎከካሪ መሪዎች አራሱ መሪ ሃሳብ አልነበራቸውም። መሪም አልነበራቸውም። 

ወቅቱን ዘመኑን የሚመጥን የመንፈስ አቅም አልነበራቸው። አንድ ጠ/ ሚር በ100 ቀን የከወነው አመርቂ የመንፈስ እርካታ በ43 ዓመት አለዬነውም።

አሁን አይደለም ለኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሞተር የሚሆን አዲስ ሰውኛ ተፈጥሮኛ መሪ ተገኝቷል። የፓን አፍሪካኒዘም እንደገና መወለድ በንድፈ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን መሬት የረገጡ የተግባር ሥንኞች የሚሰነኑበት ዘመን ነው። ዶር አብይ አህመድ ሙሴነታቸው ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ነው። እናትዬ የወደድኩት ትንተና ነው ወንድምዓለም። የሞተው በቀል ነው። አመስግንሃለሁኝ። አክብሪህ።

አብይ ሰላማዊ መንፈስ ነው!
የኔወቹ ኑሩልኝ።

ማለፊያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።