አብን ለፕ/ መስፍን ወልደማርያም መንፈስ ይሰግድ ይሆን?


የአብን እጮኝነቱ ለማን ስለማን?
ከሥርጉተ© ሥላሴ 13.07.2018
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ)
„ልጄ ሆይ ተግሳጽን አትናቅ፤“
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፩)



የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አመራር አካሉን መሪ በጊዜያዊነት መርጧል ዶር ደሳለኝ ጫኔ ነገ ግን አይቀጥልም። "የባዶነት፤ ዬየለመነትን" የፕ/ መስፍን ወልደማርያምን የጡት ልጅ ሰማያዊ ፓርቲን ካስጠጋ ... ለነገሩ ጥርጊው ... 

ሰማያዊውም ጊዜያዊ ሊቀመ ነበር አቶ የሺዋስ አሰፋ አሉ አሁን በሊቀመንበርነት ነገ ግን አይቀጥሉም። መንገዱ የዱራኛ ነውና!

ቀደም ብዬ በዚህ ጉዳይ ላይ ጽፌያለሁ። ዛሬም እደግማዋለሁኝ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ የራስ ተሰማ ናደውን ሚና ለመጫወት ዘብርሃነ ኢትዮጵያን የእቴጌ ጣይቱን የግዞት ዘመን በምልሰት ዳግም ነፍሷን ለጥቃት እጅ ሊያሰጥ ወይንስ ለአማራ ሊቆም? ይህ ከሆነ ከሰማዬዊ ፓርቲ ትራፊ ስለምን አሰኘው? ለዛውም ቁልፍ ቦታው የተሰጠው የድርጅት ጉዳዩን ለሰማያዊ ፓርቲ መንፈስ ነው።

አቶ ጋሻው ምርሻ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ(የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የነበረ)እንዲይዙ የተደረገው ከሰማያዊ ፓርቲ መጡ ለሚባሉት ሰው ነው። ህምም እምም ነው። ይህን ጊዜ ብዙ ንቃቃት ተፈጥሯል ልክ እንደ ደረቀ የዋልካ ጭቃ።

ይህ መንገድ አንድነትን ፍርስርሱን አውጥቶ ታሪክ አልባ ያደረገው አሰቃቂ ድራማ ነበር። አንድነት ዶር. ነጋሶ ጊዳዳን፤ አቶ ሰዬ አብርሃምን፤ አቶ አስራት አብራሃምን በመጨረሻ አቶ ሃብታሙ አያሌውን ሳይቸግር ጤፍ ብድር የድርጀትን መርህ እዬጣሰ በበር በሰበር መርህ አሰገባ፤ ቀዩን ምንጣፍ አንጥፎ እልል ኩልልል እያለ መንበሩን አስረከበ። ራሱን ቀብሮ እንደ እናት ድርጀቱ እንደ ቅንጅት መራራ ስንብቱን ተጎነጨ።

ያ ሴራ ሃቀኞችን እዬገፋ፤ ወደ እስር እያስወረወረ፤ በሃቀኞች ላይ ዘመቻ እዬከፈተ፤ ንጹሃን እያሳደደ ለስንት ይሆናል የተባለ ድርጅ ይሄው ወናዋ ሆኖ ቀርቶ አቶ አንዱአለምን የመሰለ የዓላማና የመርህ ሰው ቤት መጠጊያ አጥቶ አሁን ባለው ሁኔታ የምናዬውን እያዬን ነው። ነገ አቋሙ ምን ሊሆን እንደሚችልም አይታወቅም። ከውጪም ከውስጥም ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ የሚያተራምሰው አማሹ መንፈስ አንድ ዓይነት ነው። ዛሬ ላይ ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልግም።

አቤቶ ሰማያዊ አዲሱን የለማ እና የገዱን መንፈስ ሲያጣጥል፤ ሲያብጠለጥል፤ ያልልኩ ተንጠራርቶ ተወጥሮ ሲኮፈስ፤ ሲናጥጥ፤ ሲዘመን ከራርሞ አሁን ለይቶለት ሠርግና መልሱን እዬጠበቀንለት ነው። ነገ ደግሞ ውጤቱን እና ክፍለቱን እና ፍርሰቱን ወይንም ትርተራውን እናያለን። ለዚህ ሴራ ነበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትንት ቀድመው የተባረሩት፤ ማገዶ የሆኑት። ይሄው ነው እፉኝቱ መንፈስ እሺ ካልክ ትዋጣለህ እንብኝ ካልክ ትከላለህ።

ሳትሞት በህይወት ከተረፍክም ዕድለኛ ነህ። ይህ ያው የተለመደው  የአፋኙ እና የአተራማሹ ሴራ ድፍርስ ድፍድፍ የተለመደ ድራማ ነው። ስለሆነም አንደ ፍጥርጥራቸው ይኳኳኑበት። ይንኳኩበት።
በአማራ ደም የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ዛሬ በተደራጀ መልኩ ተደራጀ ነገ ደግሞ ያልምንም ጥርጥር ይቀላቀላል ግንቦት 7። ትንሽ ቆይቶ የለመደበት እፉኝት ሲረገዝ አባቱን ሲወልድ ደግሞ እናቱን ገድሎ እሱ ይኮፈስበታል። ይህ ነው ድራማው። ኦሮሞ ላይማ ምን መንፈስ ትገኛለች። በእነአጅሬ ቤት ቀልድ የለም። በሞኙ አማራ ክንድ እንዲህ ዝምን ዝምንንም ይባል እንጂ ….

አቤቶ ሰማያዊ ገመናውን ተሸክሞ ብአዴን ሄዶ እንዳወያዬ ሁሉ አድምጫለሁኝ። ቀልዱን ማቆም ያስፈልጋል። ለነገሩ እስኪዋጥ ድረስ ነው እንዲህ የሚያረገርገው እንጂ ለዬትኛውም ድርጅት ታማኝነት ካልተፈጠረበት አይፈጥርበትም … … ስለምን ሰማያዊ ደፍሮ ደቡብ ክልል፤ ኢትዮ ሱማሌ ክልል፤ አፋር ክልል፤ ኦርምያ ክልል፤ ትግራይ ክልል ሄዶ አያዋያይም። ስሜን ኢትዮጵያ ያገለለ ድርጅት ጋር አይደለም ተዋህድኩ የሚለን? …. የት ያውቀዋልና አማራን?

አሁን ቀጣዩ ተዋጭ ደግሞ አቤቱ አብን ይሁናል። ቀጣዩ ውህደት በተለመደው በእንክብካቤ ይጀመራል። ቅድመ ሁኔታ አያስፈልገውም። መላሾው በሚዲያ ተሰጥቷል። እንደ ከብት አሞሌ። ማጫው ማይክ ነበር አዲሱ እጮኝኘው የሸለመው። አሁን የዶር ደስአለኝ ጫኔ ዕጣ ፈንታ ላይ ተንጠልጥሎ ቅብጥ እና ቅልጥ ነው፤ ነገ ደግሞ ይጠብቅ የአቶ ልደቱ አያሌው፤ የኢንጂነር ሃይሉ ሻውል የህይወት ምስቅልቅል ይጠብቀዋል። አዎን የተፈጠረበት ለዚህ ነውና።

የነለማ መንፈስ እዬገነነ ሲመጣ ነበር የቀስተ ዳመና መሥራች ፕ/ መስፍን ወልደማርያም ብትን አፈር ልመና ሰማያዊን ለመጠጋት የከነፉት። ያን ጊዜ ጽፌዋለሁኝ እኔው። ያ ጥንስስ ነው አሁን ባዶን ባለ እርሾ ለማድረግ በመንደፋደፍ ላይ የሚገኙት። አንድ ቀን ይሉኝታ፤ ማተብ የሚባል ነገር ያልፈጠረለት እፉኝት መንፈስ መሥራትም፤ ማደራጀትም፤ መሆንም ስለማይችል የሞቀ ጉልቻ ሲቀላውጥ ዕድሜ ልኩን እንዲህ ሆኖ ቀረ እፍረተ ቢስ …

እሺ አዲሱ የግንቦት 7 እጮኛ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አንተስ መቼ ነው የምትዋጣው? "ከአንድ አማራ ድርጅት" ጋር መቼ ነው ማጫ የምትማታው ... 

አንተስ መቼ ነው በግንቦት 7 የምትሰለቀጠው? አንተስ መቼ ነው ከሁለት ከሦስት ተተረተርክ ተብለን የምንሰማው? ንገረና? ምን ያሽከረክርሃል? ምንስ ወዲህ እና ወዲህ ያደርግሃል። አይደለሁም አትበለኝ 20ሺህ ወጣት ነበር ለአማራ የህልውና ተጋድሎ የታሠረው አንድ ተዛ ጀግና መሪ አጥተህ ነው የሰማያዊ አሰረውሃ አተላ ያሰኘህን። ዕውነት ብነግርህ ቀበቶህን የፈታህው ያን ጊዜ ነው።

ያን የ20 ሺህ ካቴና አደራ፤ ያን የ26 የአንባጊዮርጊስ ህፃናት ደም፤ ያን 50 የባህርዳር ደም ከንቱ አስቀርተህ አደራውን ቅርጥም አድርገህ የበለኸው እሱን ያሰመርጥክ ዕለት ነው … አሁን ቀን ቁጥር እንደ እርጉዝ ለጌታህ … ሎሌ እና አንጋችም፤ አስተነጋጅም ለመሆን ጉንብስ ቀና ብለህ ሎሌነቱ የምትቀጠርበትን … የውል ሰነድ ፍጥምጥም የቀጣሪ አስቀጣሪህን የሰማያዊ ፓርቲን ደጀጠኝ ፍርፋሪ ለማኝ የምትሆንበትን. ይሄው ነው …

  • አቶ ጋሻው መርሻ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ(የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የነበሩ) ጉባኤውም ልብሱ ሰማያዊ ነው የነበረው በዚህ ነው። ኢሳት ላይም ተጠያቂው ሊቀመንበሩ ዶር ደሳለኝ ጫኔ ነበሩ የአቶ ልደቱ አያሌው ዕጣ እሰኪደርሳቸው ድረስ ተደምጠዋል፤ የት ያውቀዋል የአማራ ተጋድሎን ኢሳት? ንገሩን?! እኔ የአቶ ልደቱ አያሌው ፖለቲካ አካሄድ ግጥሜ አይደለም፤ ትናንትም ዛሬም። እሳቸው የድርጀቱ ሊቀመንብር ሳይሆኑ የመንግሥት ሚዲያ እሳቸውን ብቻ ነጥሎ የሚያስተናግድበት ሚስጢሩ አይገባኝም ነበር። 

  • በተጨማሪም እኛ በለማ በገዱ መንፈስ ስንተጋ እሳቸው ኢዲሱን መንፈስ ኢህአዴግ የተፎካካሪውን ሚና ወሰደ ብለው ቱጋታቸውን ሳዳምጥ ነበር። አሁን ያው እንደ ሌላው ደጋፊ እና አድናቂ ሆነዋል። ስለዚህ መንፈሳቸው ግጥሜ አይደለም፤ ይህ እንግዲህ በፖለቲካ ህይወታቸው ያለው አቋሜ ነው። በዘመነ አማራ ተጋድሎም ገላጩ እሳቸው ከሳጅን በረከት ስምዖን ጋር ነበር።

  • ·      ተዚህች ላይ።

በነገራችን ላይ የግንቦት 7 የትንሳኤ ራዲዮ ሳጅን በረከት ስምዖን ስልጣን ለቀቀ ብሎ የአማራ ህዝብ የብአዴን ጽ/ ቤትን በስልክ አጨናነቀው ብሎ የሠራው ዜና ሰሞኑን በባህርዳሩ ህዝባዊ ትዕይነትም፤ በሀምሌ 4ቱ የማርቆስ ህዝባዊ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ የወጣው ትንታጉ የአማራ ጀግና አፈር ለበሰ። 

ግርም ይል ነበር አማራ ገዳዩ ሥራ ለቀቀ ብሎ ሲጨንቀው ሲጠበው ታዬኝ እኮ? መሪ አልቦሽ ሚዲያቸው እራሱ እንዲህ በዬሁነቱ እዬወረደ ይፈጠፈጣል … የህዝብን ሥነ - ልቦና ማጥናት ከዬት ይመጣል … 

ግን የአማራ ወጣቶች ማቃጠል የአማራን መሬት በዘለቄታ መሠረት ለማስያዝ ጠቃሚ መንገድ አይደለም። ሰላማዊ በሆነ መነገድ ቁጣን መግለጽ ግን ይገባል። እንደገናም አቅም በተጣራ መረጃ ቢሆን መልካም ነው። ሌላውም በአማራ ተጋድሎ ሲያባጭል፤ ሲስቅ፤ ሲያብጠለጥል፤ ዕውቅና ሳይሰጥ ለባጀው ሁሉ ለመባጃው ታላቅ ትምህርት ነው። 

አንድ ቁም ነገር ከአብይ መንፈስ የተሻለ መንፈስ አማራ መጠበቅ የለበትም። ለዛ መንፈስ አጥር ቅጥር መሆን አለበት አማራ፤ ዘብ መቆምም አለበት - አማራ። የአማራ ወጣት ሁሉም። ሁሉም አንተን መስጥሮ ጠልቶ ነው የኖሮው - ያለውም። … ወደፊትም ከኦህዴድ በስተቀር የአንተን ጠረን የወደደ ያከበረ ያነገሠ ይኖራል ብለህ አታስበው። አይኖርም።

ዘመን ሲደግም በተለመደው ማባጨል። አይሰለቼው አያልቀበት እፍረትም አልሰራለትም። አሁንም አማራ ሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ለፐ/ መስፍን ወልደማርያም ትዕይንት ተዋናይነቱን በዬለምነቱ ያስነካው ... 

ያን ጊዜም ቢሆን በዘመነ ቅንጅት ባዶ እጁን ለመጣ ለቀስተደማና ክብር እና ሞገስ መሆን ያን ያህል ማህበራዊ መሠረት እርቃን የሚያሰቀር ዘመቻ የሚያስኬድ አልነበርም። ቢያንስ ይሉኝታ የሚባል ነገር አለ። በድርጅት እሰጣ ገብ መኖሩ አንዱ ታጣፊ አልጋ መሆኑ ቢገጥምም ለዛ ለቀደመው መጠጊያነት ግን ግርማ እና ሞገስ የሥነ - ልቦና ማለቴ ነው ያበቃው ኢዴፓ ነበር።

መኢህአድም ዕጣው ይሄው ነው የሆነው። ሁለቱም በቅንነት ቀስተደማና ፓርቲን አስጠጎ ባዶ እጁን የመጣው በአገር ውስጥም በውጭም ተደናቂ ተከባሪ ሆነ። 

እነኛን ሁላችንም በመንፈሳችን እንድናገል ተደረገን። አይጥመንም ዛሬም የእነሱ ነገር በዛ ዘመቻ ምክንያት ህሊናችን በጥቁር ስለሳላቸው ግንቦት 7። 

ጎንደሬዎቹ የመሰረቱት የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ያን ያህል ከ35 ዓመት በላይ ታግሎ፤ በቅንጅት ዘመን ውግዘ ተርዮስ ተብሎ ተገሎ፤ በኋዋላም ቃል መጠጊያ ሲያጣ እጄን አውጣኝ ተብሎ ጅሉ ጎንደር ለክፉ ቀን ደሙን የገበረበትን፤ ጀግንነቱን፤ ክብሩን፤ ታሪኩን የትም ለማያውቀው ለግንቦት 7 አስረከብ። እኛም ንጽህና ይኖራል ብለን ደገፍን። መተባባር ሃይል ነው ብለን አመነው ግንቦት 7። መታማናችን ሸለምነው። ያው ቅንነት ጅልነትም ነውና። በመጨረሻ መሥራቾች ተባረው፤ ተሳደው፤ ታሰረው ተሰውተው መና ቀሩ። አሁን ተደራዳሪውም እሱ አቤቶ ግንቦት 7 ሆነ ጎንደር ወድቆ ቀረ። እንመሰግናለን እንኳን አልፈጠራላቸውም። 

አሁን ደግሞ በአማራ ተጋድሎ የነበረው ጉግስ ይታወቃል። በዛ ደም እና መከራ አልፌ ተደራጀሁ ያለው አብን ያ ሁሉ ሺህ የህልውናው ታጋይ እያለ አሰርውሃ አሰኝቶት የሰማያውውን ቅራሪ ለቀማ ሔደ። ነገም ውህደቱ ብቻ ሳይሆን መወጡ አይቀሬ ነው። መዋጡ ብቻ ሳይሆን ከሁለት ከሦስት መተርትሩ አይቀሬ ነው። መተርተሩ ብቻ አይደለም ቅኖች ዋጋ አልባ ሆነው መበተናቸው አይቀሬ ነው። ይህን ሁሉ መከራ አይቀሬነቱን በእርግጠኝነት ነው የምናገረው ዛሬ።

እንደገና ደግሞ ለግንቦት 7 የጎንደር እናት ልጅ ታቀርባለችን? እንደገና ለናቃት - ለረገጣት - ታሪኳን ለቀማት - በአውሮፕላን እንድትደበደብ ለዘመተባት ለወሰነባትስ አብራ ከጎን ልትቆም ነውን ግራማዊት ጎንደር? በቀጥታ እንደማይመጣ ይታወቃል ግንቦት 7 መጀመሪያ ተሰውሮ ነው፤ አቅም ብቅ ሲል ነው አለሁ የሚለው፤ ይሄ ዓለም ያወቀው ገሃድ ነገር ነው። በስል መገባቱ አይቀሬ ነው…

እኔ ግንቦት 7 ብሆን ውስጤን አውቃለሁኝ። ብጣመርም፤ በቀላቀልም፤ ብዋህድም፤ መምራት አቅሙ እንደሌለኝ ስለማውቅ ተልዕኮዬ የኢትዮጵያን የምሥራች ማዬት ነው፤ ፕሮጀክት ነኝ ብያለሁኝ፤ ፖሊሲም የለለኝም በዚህው ነው ተልዕኮን ፈጽሜያለሁኝ ብዬ በክብር፤ በግርማ ሞገስ ትግሉን እሰናበት ነበር። 

አሁን ደግሞ አይኔን በጥሬጨው አሽቼ ለሌላ ትርምስ ደግሞ አዲስ የሴራ ቧንቧ ከምከፍት… ፍዳዋ ነው መቼም አላዛሯ ኢትዮጵያ … ሞቅ ባለ ቁጥር ሞቅ ወደ አለው ጠጋ፤ እንደገናም ሰው ለቀማ አቅም ለቀማ፤ ሥም ለቀማ … ፍርሰት ንነድት ግለት ፍረጃ ... አቅመ ቢስና ሰነፍን ተሸክሞ ግን እስከ መቼ? 

ይልቅ በተለመደው መንገድ ሙያዊውን አገልግሎት ማበርከቱ የተሻለ ነበር። የተሻለ ክብርም በሚሊዮኖች ያስገኝ ነበር። ልባችንም ይቅር ይለው ነበር። 

ግንቦት 7 ዕድልም የለውም። የደረሰበት ሁሉ ህውከት እና ብጥብጥ ፍርሰት ነው። ቅብዕም አልተሰጠውም። በዛ ላይ ለመምራትም፤ ለማስተዳደርም፤ ለማደራጀትም፤ ለማሰበሳሰብ፤ እቅም ለመፍጠርም፤ በጭንቅ ጊዜ ብልህ እና በሳል እርምጃዎችን ለመውሰድም፤ አዲስ ሃሳብ ለማፍለቅም፤ ለማቀናበርም፤ በስክነት ጉዳዮችን ለማየትም፤ ለማያያዝም፤ አርቆ ለመተለም ለመተንበይ በውነቱ አቅም የለውም።

አንድ በጎ ነገር ተፈጠረ ሲባል ቅኖች እምነታቸውን በመታመን ውስጥ ለሌለ ድርጅት ሲገብሩት ነው የኖሩት። አንድም ቀን ግንቦት 7 በቃሉ አግኝተነው አናውቅም። ሲጨንቀው አንድ ብጥብጥ ይፈጥራል። አንዲት እሳት ይጭራል፤ ብጥበጣው ህውከቱ ይሄው ነው። በብጥበጣ እና በሁከት ነው ዕድሜውን የሚስቀጥለው። 
አሁን ዲሲ ላይ የሚታዬውም ይሄው ነው። ምን አይነት መርዝ መንፈስ ነው?

ንጹህ ቢሆን፤ ሙሉ አቅም እንዳሰብኩት በልኩ ቢኖረውማ ከምንም ከማንም ብላይ እረመጡን ደፍራ የረገጠችው ሥርጉተ ሥላሴ ነበረች። ግን መሪ ለመሆን አለመቻሉን አጥናሁት ከልቤ ሆኜ። መሥራት አይወድም። ሰነፍ ነው! ሃሳብም የለውም።

ሥራ እርሙ ስለሆነ ሁልጊዜ ከሞቀው ሄዶ ይጣዳል፤ ይውጣል ወይ ያፈርሳል ወይ ይበትናል። በነፃነት ፍለጋ ታሪክ ድርጅቶችን በማፍረስ እና በመበተን እረገድ ግንቦት 7 አብነት ነው። ወያኔ ሃርነትን ትግራይን በማፈረስ ሊከስ አቅምም ሞራል የለውም ግንቦት 7 ስለምናውቀው፤ ስላጠናነው። እሱም የተሻለ ሆኖ ስላላገኘነው። ቅኖች እንዲያውም አብረው ሆነው መዋለ ዕድሚያቸው ባከነ።

ህውከት ብራና ላይ፤ ህውከት ማይክ ላይ፤ ህውከት በማህበራዊ ኑሯችን ላይ፤ ህውከት በመክሊታችን ላይ፤ ህውከት በሚበልጡ ሊሂቃን ላይ በተመሳሳይ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ባልተሻለ ሁኔታ እንዲያውም በሰለጠነ ሁኔታ ነው የሚፈጽመው ግንቦት 7 ነው።

ያልተጋጨው ግልሰብ ታታሪ፤ ጸሐፊ፤ ጋዜጠኛ፤ ድርጅት ማን አለና? ማን_? ሁሉን ጨርሶ ጓዙን ጠቅልሎ በኦህዴድ ላይ ሁሉ ዘምቶ ነበር … እነ አጅሬ በ90 ደቂቃ ኢንተቤ ሚስጢር ቆርጠው ገብተው ህልሙን አፈር ድሜ እያስጋጡት ነው እንጂ … 

አሁን በዶር አብይ አህመድ ላይ የወረደው በረድ …. ለወደፊቱም  ለኢትዮጵያ ጤናማ የፖለቲካ ስምረት ግንቦት 7 የደረሰበት የነካው ጠረን ሁሉ መከራ ነው  … ስላም አይሰጥም። ምክንያቱም ያቺ የፕሬዚዳንትን ወንበር ፕሬዚዳንታዊ መርህ እንዲኖር ያለማትን ቤተ መንግሥት ሳያገኝ ተመርቶ በሰላም ያድራል ተብሎ አይታሰብም … በፍጹም። ውስጡ የተከደነ ያልተከፈተ የሚንተከተክ እንትን አለበት … እዚህ የሚያምሰን የእሱ መንፈስ ነው …

የሆነ ሆኖ ጊዜ መልካም ነው አሁን ማጣፊያው አጠረው። የአብይ ካቢኔ እንዲቀለበስም ተግቶ ሠርቷል ከሰማያዊ ፓርቲ ጋራ በመሆን። ሌሎችንም ጫሪ ሃሳቦችን እያደራጀ እና አዬመራ፤ ግን አልተሳካለትም።

ገና የአብይ መንፈስ አህዱ ሲል ነበር ዘመቻውን ያጧጧፈው በካድሬዎቹ ግን ዕድሜ ለጀግናው የሳተናው ድህረ ገጽ ሞግተን እረታነው። አሳምረን አሸነፍነው። ዛሬ ፕሮዎቹ ተገደው የአብይን መንፈስ ሲያድኑ ይውላሉ፤ ባዶ ነበር የሚቀሩት ቢቀጥሉበት።

ሰነፉ አመክንዮው የሞገድ ተጠማኝ ብቻ መሆኑን አፈር ድሜ አስጋጥነው። አምሮበት እንኳን አልተሸነፈም … ጉድ ነው የሆነው። እንደዋለለ አቦ ሌንጫ ደግሞ በተጨማሪነት ጉድ ሰሩት …

አሁን ማህል ቤት ሲዋልል ኤርትራ የአልጀርሱን ስምምነት ውሳኔ የተሰጣትን የምሥራች መባቻ አትቀበልም በማለት ካድሬዎችቹን አሰማርቶ ቀሰቀሰ፤ ምን ይሁን መና ከሰማይ ያመጣል የሚሉ እልፍ የእኔ ቢጤ ሞኞች እና አዕላፋት ቅኖች የእውነት ሌት ተቀን ስለእሱ ስለሚተትሩ ምን ይመለስ? ወገቡ ተያዘ። እኛም ሞገትነው። እናም አሸነፍነው። 

አሁን የት ይድረስ ምን ይሁን? ለክፉ ቀን ብሎ ያስጠጋውን አቤቶ ሰማያዊ ጋር ደግሞ ተዋህድኩ አለን። አያልቅበት። መቼም የፖለቲካ ሊሂቃኑ ምን ይስቁበት …

ውሸቱን ተናግሮ አምኖ ተቀብሎ። ከተኮፈሰበት ወርዶ። ያመሰውን፤ ያተራመሰውን፤ የገመሰውን ህዝብ ይቅርታ ጠይቆ፤ የበተነን ሰብስቦ እርቅ አውርዶ፤ ፓሊሲ ቀርፆ፤ ፕሮግራም እና ደንብ ነድፎ መሬት ላይ ወርዶ እራሱን ከህዝብ ጋር አገናኝቶ፤ አባላትን አሳምኖ አስፈርሞ፤ ተመዝግቦ ሥራ መጀመር ከዬት ያመጣዋል። እንዴት ብሎ አይችለውም። 

ከራሱ ውስጥ አባላትን ያወጣል፤ ሌላ ፓርቲ ተመሰረተ ብሎ ያውጃል ከዛ ጥምረት ምንትሶ ቅብጥርሶ የጮሌዎች የሥም ንግድ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ተዋህደ ይባላል በአዲስ ሥም። የአዲሱም የነባሩም ሊቀመንበር አንድ ሰው ይሆናል። 

ከ97 ጀምሮ በዬጊዜው የኢትዮጵያን ፖለቲካ እምስ የሚያደርገው የእሱ መንፈስ ነው። ሰማያዊ ሲያምስ እና ሲያተራምስ የባጀውም በዚኸው መንገድ ነው። እንደ አበደ ወይፈን ሲቀበዘበዝ የውጪ አደራዳሪ ሲያሰኘው የነበረው ይሄው ነው መላው። ብራስልስ ላይ የቀረው ቀይ ምንጣፍ ተዚህ መጥቶ ደግሞ እኔ ላደክድክ ብሎ። እኔ ለሰማያዊ ፓርቲ አልደከምኩለትም፤ አልፎ አልፎ ጥቃት ሲሰነዘርበት ብቻ ለምን ከማለት ውጪ እሱ እንደ ፍጥርጠሩ። ቅጭጭ አይለኝም።

ነገር ግን የአማር ብሄራዊ ንቅናቄ በአማራ ሥም ለዳግም ሞት እና ጥቃት እንደ ገና ለእርድ ጎንደር እንዲሰናዳ ግን በፍጹም አልፈቅድም። አብን ለዛሬው በግንቦት 7 ፕሮዎች ተጨብጭቦለታል። በሚዲያውም ሰፊ ሽፋን አግኝቷል። የአማራ ጀግኖቻችን ሲፈቱ ኩርፊያ ላይ ነበር የተነበረው መላ የግንቦት 7 ፕሮዎች። በሥማቸው እንደ ማያዣ ሲነገድ ስለተኖረ። የአብን ጭብጨባ ይቀጥላል ብሎ አያስበው … ጎንደር መሬት ላይ … ጨዋታው ያን ጊዜ ነው።

ለአማራ ከኦህዴድ የበለጠ ሁነኛ ንጹህ ድርጅት የለውም። ከአብይ መንፈስ በላይ መሪ አማራ መጠበቅ የለበትም። ለዚህ ደግሞ ቀን ከሌት ይሠራበታል። አብን ወልቆ ነው የሚቀረው። ምክንያቱም አያያዙ አላማረኝም እና … እራሱ ጉባኤው የለበሰው ልብስ ተናጋሪ ነው ቀጣዩ የአማራ ዕጣ ለሎሌነት እንዳሰናዳው፤ ወይ ለወጪት ለቅላቂነት። … ለራስ ተሰማ ናደው ሌጋሲ እንዳሳጨው አሳምረን እናውቃለን …

ለነገሩ እኮ 2 ዓመት ተተኝቶ ከርሞ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ እናም አሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲታወጅ ነው እኮ ታሰረ፤ ታገተ የሚል ዜና የነበረው? እስከዛ ድርስ የማንን ጎፈሬ ያበጥር ነበር አቤቶ አብን? ስለምን ያነ ወቅት ተፈለገ? ይህን ከልብ ሆኖ መመርምር ያስፈልጋል። 

የዶር አብይ አህመድ መምጣት ለሰማያዊ መርዶው ነው፤ ለአማራ ደስ ሊያሰኘው ሲጋባ ስለምን እንቅፋት አማራ መሬት ላይ ተፈለገ? የቀረበት ቀረብኝ ብሎ ይፍጨርጨር ከቻለው ያን ቅዱስ ዕጹብ ድንቅ መንፈስ፤ አማራ ግን የቀረበት የለም። ምን ቀርቶበት። ምን ቀርቶብን። ክብሩ ጎልቶ፤ ተጋድሎ መስክሮ ነው የወጣው። አይደለም ለእትዮጵያ ለዛሬው የኤርትራ ህዝብ ሰናይ እኮ የአማራ ተጋድሎ ያስገኘው እረዴት ነው … 

የፕ/ ኢሳያስ ካቢኔም ይሄ ይጠፋዋል ብዬ አላስብም። ተጠግተውት የነበረው መንፈስ ሲሮጡ የታጠቁት እንደነበር ይረዱታል ብዬም አስባለሁኝ። ለዚህ ነው በመጀመሪያው ግብዣ ፋሲል ከነማ ያቀረበውን የወዳጅነት ግጥሚያ ኤርትራ በፍቅር እና በቅንነት የተቀበለው።

ብቻውን የኦሮሞ ንቅናቄ ካለ አማራ ተጋድሎ፤ ብቻውን የለማ መንፈስ ካለ ገዱ መንፈስ ህልም ነው። ይህ ሁሉ ፋሲካ አማራ መሬት ላይ „ያ የኦሮሞ ደም ደሜ ነው“ ያለውን መርህ የመንፈስ ውጤት ነው። ደም የተከፈለበት። የትኛው ክልል እና ህዝብ ነው „የኦሮሞ የጋንቤላው ደም ደሜ ነው፤ ድምጻችን ይሰማስ“ ብሎ የተነሳው። የሞተለትስ፤ የታሰረለትስ። 

ተጋድሎዎችን ወንጅሎ ካሾለከው ቅስሙን እንኩት አድርጎ ከሰበረው፤ ምኞቱን ውሃ የበላው ቅል ካደረገው ከሞላ አስገዶም መንፈስ ጋር ከከተመ ከግንቦት 7 ድርጅት ጋር አብሮ ውህደት ይቀፋል? ያቅለሸልሻል፤ ያስታውካልም … አብን ይህን ካደረገው።

 ቀና ብሎ ለመሄድም ሞራሉ ከዬት ይመጣል … የእኔ ነው  የአማራ የህልውና ተጋድሎውን በVOA እና በESAT በሚዲያው አስፎከረ ግንቦት 7 በቃ ባዶ ሆኖ ቀረ፤ ከዛ ደግሞ ያለውን አለ … አሁን ያ የእኔም ድምጽ ነው እያለን ሰማያዊ። 

እና የአማራ ተጋድሎ የትግራይ እህትና ወንድሞችን አፈናቅሏልን? ያልተጋባ ድርጊት ፈጽሟባቸዋልን? ይሄን ነው መመርመር የሚገባው። ሎሌነትን የናፈቀው የአማራ ብሄራዊ ድርጅት ራሱን ከእነ አማራሩ አስነጥፎ እንደ ፍጥርጥሩ መሆን ይችላል፤ 

አማራን ጎንደርን ግን አይችልም። ጎንደር በኤልኮፈትር እንዲጨፈጨፍ እና የአውሮፓው ህብረት ተጽዕኖ አሳድሮ ግንቦት 7 ለሥልጣን ለማብቃት ነበር ህልሙ፤ ግን ተዚህ ላይ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ልብ ገዝቶ መለበጫ የሆነ ድራማ አልፈጸመም እንደ ጅሉ ደርግ አልተጃጃለም እንደ ሃውዚን …

የሚገርመኝ የዛሬ 43 ዓመት የሆነውን፤ የዛሬ 27 ዓመት እንደሆነው ያን ኮፒ አድርጎ ነበረ ግንቦት 7 ሲንቀሳቀስ የነበረው። አዲስ ሃሳብ አፍልቆ መንቀሳቀስ ስለማይችል በውራጅ ሃሳብ ብቻ ነው የሚነዳው።

 … 7 ሚሊዮን ካድሬ በ7 ሚሊዮን ዓመት ገድዬ ስልጣን እይዛለሁ። ለዛውም እኮ ተገደለ የሚባለው ጎንደሬ አማራ ነው።
  … የማይሆን ነበር … አሁን ጭዋታው ፈረስ ዳቦው ተቆረስ ሆነ።

ጠፈፍ ብለው ሳይነካኩ ከኖሩት ድርጅቶች ጋር እኩል ወንበር ይዞ በአዲሱ ግንቦት ሰማያዊ ሥያሜው ወይም ሀማሌያዊ ሠማያዊ ያው አትደፈርም ያቺ የሊቀመንበርነት ቦታ ሰማያዊ ወደ ምክትል ለስም ብቻ ሊቀመንበርነት ዝቅ ይል እና ጸሐፊነቱ እና ሊቀመንበርነቱን ድርጅት ዘርፍ እና ውጪ ጉዳይን ለግንቦት 7 ይረከብ እና በአዲሱ የሚዲያ ሠርግና መልስ ይታያል … ጉሮ ወሻባዬ ደግሞ አዲስ ድራማ ... 

ኦቦ ሌንጮ ለታማ በተባባሪ ሊቀመንበርነታቸው ፍንክች ሳይሉ በሙያ በልብ ፍንክት አድርገው የሆነውን አድርገዋል። መቀላቀል፤ መዋህድ፤ መጣመር፤ መቀዬጥ፤ መዋጥ መፍረስ አሻም ያለ መገለል አስከመቼ? የዚህ ድራማ ሎሌኔት የሚፈለገው ደግሞ አማራ ነው። 

አቤቱ አብን በል ተዘጋጅ ለሎሌነት … ወይንም ምንጣፍ ለማንጠፍ … ተዘስ አይታለፍም … ቀድመህ ከሰማያዊ ጋር ተዋህደሃል እኮ … ጉባኤህ ያው ነው የነበረው …. አካልህም እንዲሁ ነው ስርክራኪ እና አተላ አንጣላይ ነው የሆነው። ዛሬ እኔ አውነቱን ፍርጥ አድርጌ ስነግርህ ይመርሃል ግን ዕውነቱ ደርሶ ደመር ከምትቀጥር ዛሬ እርምህን አውጣ

የኔዎቹ ዛሬ ላይመስለን ይችላል ነገ ግን የሚሆን ይሄው ነው። ስለዚህ መናገር ያስፈልጋል። ግንቦት 7 ማህብራዊ መሠረቱን እንደሚያሳጣው በሰሞና አማራ ታገድሎ በስፋት ጽፌ ነበር። የሆነውም ይሄው ነው። ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

ለአማራ የግንቦት 7 መንገድ አትራፊው አይደለም። በውስጡም የለንም። ብዙ የተከደኑ የተመሰጠሩ የተወሳስቡ ስውር ጉዳዮች አሉበት። ግርድና - አለቅላቂነት - አንጣፊነት - ዘበኝነት ላሰኘው ከልካይ የለበትም፤ ክብር እና ልእልና ራስን አውቆ መኖር ለኖረበት ሰብዕና ግን ግጥሙ አይደለም። ስለዚህ አማራ አቅምም - ጊዜም - መዋለ መንፈስን ማባከን የለበትም። እኔም የመጨረሻዬ ነው የዛሬ ጹሑፍ በግንቦት 7። ደክሜበታለሁኝ ግን ወስጡ የጭቃ እሾኽ የሆነ ድርጅት ነው። 

እሱን አምኜ ስለባከንኩት ጊዜ ግን አይቆረቁረኝም። ስለምን? ቅንነት ከጸጸት ስለሚታደግ። ከእኛ ራስ ቢወርድ ግን ምርጫዬ ነው። ቢተወን በዬዘመኑ ግብር እንድንከፍል ባያሰገድደን ...የሚፈለገውን ደቡብን ማዕከል ያደረገ መንግሥቱን ከቻለ ይሞክረው ...  

ለአማራ የአብይ አሜኑ ቅዱስ መንፈስ ሜሮናዊ መንፈስ ዕዮራዊ ነው፤ አትራፊውም ጸጋውም እሱ ብቻ ነው። ኦህዴድ ጭንቅላት ብቻ ሳይሆን ዕዕምሮም አለው። ብልህ ድርጅት ነው። ሰውኛ ተፈጥሮኛ ነው። አማራን ከልቡ ከውስጡ ያስጠጋ በታሪክ ድርጅት ቢኖር ኦህዴድ ነው። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ አሁንም ለማውያን ነኝ።

·       ሞና።
የስሜን አሜሪካ የስፖርት ፌስቲባልን ምክንያት በማደረግ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ለመገኘት ፈቀዱ ተባለ። ለእኛ ቢመጡም ቢቀሩም ለበጎው የሆነው መንገድ ያሳከላቸው አለን። እኛ የምንፈልገው ጤናቸውን ብቻ ነው። በቅናት ቀን እና ሌት የሚበጠበጥ አውሌያ ስላላ ከእሱ እንዲጋርድልን ነው። 

ያን ቅን ጥያቄ ያን ማን አባቱ እስኪ ያደርጋትል የስሜን አሜሪካ የስፖርት ዝግጅት ብሎ በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን አዝማችነት ተቃውሞው ቀጠለ። ኮሜቴው ከሁለት ተክፍሎ የወሰነውን ወሰነ። አሁን ደግሞ ያን ያዩ ቅን ኢትዮጵውያን ድልድይ እንሆናለን ብለው እንቅስቃሴ ጀመሩ። ሙሉውን አዳምጫለሁኝ። መልካም ነው። 

አሁንም ይህን በሚመለከት ግንቦት 7 ካድሬዎች እስከ ሚዲያው ዲሲ ላይ አሰማርቶ ይታመሳሉ። ሌላው ፓርቲ፤ ሚዲያ ጸጥ ብሎ ይመለከታል። ተፎካካሪዎች ፓርቲዎችም ሄደን እንታገላለን ያሉት አገር ገቡ፤ የቀሩትም ሁሉንም በተደሞ ጣልቃ ሳይገቡ እዬተከታተሉ ነው። አይሞቃቸው አይቀዝቅዛቸው። ለገቡትም አብሮ ሰው ልኳል አቤቶ ባላውራው መንፈስ። ደጅ ጥናት ቢጤ። ስመጣ ከፍ ባለ መስተንግዶ ተቀበሉኝ ዓይነት። ከዛም አለሁበት ለማለት። ረብሻው ብጥበጣው ደግሞ በተለያዬ ስልት ቀጥሏል።

የሚገርመው ያለፈው ዘመን አልበቃ ብሎ በዚህ የይቅርታ እና የምህረት ዘመን አሁንም ግንቦት 7 ከነሠራዊቱ ያምሳል፤ ያተራምሳል ዲሲ ላይ። መቼ ነው ይሄ ድርጅት ውሃ በቀጠነ ቁጥር ህውከት፤ ብጥብጥ፤ ሃሳብ መከፍል እንደ ሥልጣኔ ይዞ የሚቀጥለው እስከ መቼ ነው? ቀድሞስ ድርጁ እረኛ ስላልነበረው ቢያንስ አሁን ህሊናቸው አሉ ለንደን ላይ። 

ይሄ ገመና ተይዞ ነው አሁን ደግሞ አገር ቤት የሚገባው። … ማነኮር - መበጥበጥ - ሰላም መንሳት ማደናቀፍ፤ እነሱ ካለመሩት እነሱ ካለስተዳደሩት ወይ በእንሱ ሹፌር ካልተነዳ ይሄው ነው። ቢችሉት እማ ከ8 ዓመት በላይ እኮ አውራ ፓርቲ ሆነው ተጨብጭቦላቸዋል እኮ።

ዛሬ  … አንጋፋዎቹ የፖለቲካ ድርጅቶች እንኳን ጥሞና ውስጥ ነው ያሉት። መጥኔ ለአዲሱ የለውጥ መንፈስ ይህን ዕዳ መሬት ላይ ተሸከም መባሉ አይቀርም። እንደ አቶ ዳውድ ኢብሳ ደግሞ እንደ ኦነግ ትንሽ ፉከራ ሚጤ አሰምቶ ዘራፍን አስጭሆ ኩላሊት ነኝ ማለት ነው። በቦሌ ገብቶ ጫካውን ሞከር አደርጎ የተኮስ አቁም ስምምምነት ምንትሶ ቅብጥርሶ በነጭ ድርድር ያሰኘናል፤ ለዛም ግጥሜ ፖርቱጋል ነው ይበል እንደ ጡት ልጁ እንደ ሰማያዊ ፓርቲ …


እንዲህ ዓይነት የፖለቲካ መስመር 100 ሚሊዮን ህዝብ እንዴት ተብሎ ነው የሚመራው … በጥቃቅኑ የሰው ስሜት፤ ፍላጎት እንቅስቃሴ እዬገባህ መርዝ እዬነሰነስክ፤ መሰባበሰብን፤ መተማማንን እዬፈራህ፤ ለይቅርታ ልቦናህ ተደፍኖ … ሎቱ ስብሃት … መሸነፍን መቀበልን እንዴት ያቅታል? 

የኔዎቹ ኑሩልኝ!
„አማራነት ይከበር!“

የአማራን ክብር ለሚያስደፍሩ አንተኛላቸውም!

መሸቢያ ጊዜ።





አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።