የአማራ ተጋድሎ አንበሶች ድላቸው ያለው በብአዴን ውስጥ ነው።
ገዱ ገድ ወይንስ መንገድ?
„አንተ ታካች ወደ ገብረ ጉንዳን
ሂድ
መንገዳዋን ተለምክተህ ጠቢብ ሁን።“
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፮ ቁጥር፮)
ከሥርጉተ ©ሥላሴ
13.07.2018
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)
ቁም ነገር
ይሄ የለውጥ አብዮት ቢቀለበስ የመጀመሪያ ተጠቂዎች የቄሮ እንበሶች እና የአማራ የማንነት የህልውና ታግድሎ አንበሶች ናቸው። ይህን ከልብ ማድመጥ ያሰፈልጋል። ለዚህ አብዮት ቄሮ እና የአማራ ታገድሎ ወታደሩ፤ የደህንነት ሰራተኛው መሆን ይኖርባቸው። ገዱና እና ለማ ኢህአዴግን አፍርሱ የነበረው ዘመቻ እኮ ታጋድሎዎቹ ተቀብረው፤ ታሪኩም ድሉም ለሌላ ሥጦታነት እንዲቀርብ የታሰበ ነበር። ስለዚህ እንደ ጎንደሮች "ልብ ያለው ሸብ ነው!"
- · ውሃ ቀጠነ።
በሰሞኑ በብአዴን ጉባኤ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተናገሩት ላይ ትርምስ ተፈጥሯል። የተደገፈውን መንገድ
ውሃ በቀጣነ ቁጥር እዬቀጣህ እና እዬቀጠቀጥክ አይሆንም። አሁን እኮ የእነ ገዱ መንፈስ ተጋድሎ ላይ ነው። መከራ ውስጥ ነው። እያንዳንዷ
ደቂቃ ውጪ ግቢ ነብስ ነው።
ወያኔ ሃርነት ትግራይ አይደለም በፊትም ዛሬም እያመሰ ያለው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ሎሌ
ለመሆን የፈቀደው አማራ፤ አፋር፤ ሲዳማ፤ ሆዳሙ ፤ ከምባታ፤ ሆ ኢትዮ ሱማሊያ ሃድያ፤ ጉምዝ ነው ወዘተ ወዘተ ጠላትማ ጠላት ነው ይታወቃል ውሎውም አድርሻውም። በወዳጅ
ሥም የተጠጋው ነው ለጥቃት ለሽንፍት የሚዳርገው።
ብአዴን እኮ አሁንም እነ ሳጅን አለምነህ መኮነን ተሸክሞ ነው ያለው። ይቻለዋል ቦታውን ማስለቀቅ፤
ምክንያቱም ህዝብ ለሰከንድ እሳቸውን ማዬት እንደማይፈቀድ አሳምሮ ያውቀዋል። ስለዚህ እነኝህን የተሸከመ ብአዴን ችግሮቹ አልቃዋል
ማለት አይቻልም።
ምን ትግራይ ያስኬዳል የነሳጅን በረከት ስምዖን፤ የእነ አዲሱ ለገሰ ግርፎች እነ ሳጅን ከበደ ጫኔ እዛው እያሉለት።
ውጪ አገር እንኳን እነገ አቶ ኤርምያስ ለገሰ ስንት ነው ሲያውኩን የከረሙት። አዲሱን ለውጥ ቀልብሶ የበለሃሰብ ቄጤማ ሆኖ አቅጣጫ
ያለሽ ጉዞ እንዲኖር ያልተሳለ ጉዳይ አልነበረም። እንኳን እዛው ባለቱ ተሰግስገው የሚያምሱት እያሉና፤
- · ካለአቅሙ የተሸከመው የብአዴን አማረነትን ነው።
እርግጥ ነው የአማራ መከራ ብአዴን ነበር። ብአዴን ለአማራ ምኑን እንዳይሆን ሆኖ ነው የተደረጀው።
እራሱ አማራ ሳይሆኑ አማራነትን ተሸከሙ የተባሉት የትግራይ ሆነ የኤርትራ ባላባት ከሚችሉት በላይ ነበር የተሸክሙት። አማራ ስትሆን
ብቻ ነው አማራ መሆን የምትችለው። ከዛ በላይ የብአዴን አይዲወሎጂው የኢህአፓ ነው።
ኢህአፓ ደግሞ ከአማራ ጋር የሚያገናኛው ምንም
እንጥፍጣፊ ነገር የለም። አማራ ጨቋኝ ነው ገዢ ነው ስለዚህ አማራ ገዢ ጨቋኝ ያለሆነበት ሥርዓት እንመሠርታለን ነው የነበረው ትግሉ፤
ይህ ተገልብጦ አማራ መሬት ላይ ትንሽ ብናኝ የዘር ፍረፋሪ የአያት ቅድመ አያት እዬተቆጣጠረ ለማጠጋጋት ቢሞከርም ሸክሙን አልታቸለውም
ብአዴን።
አማራም፤ ኦሮሞም፤ አፋርም፤ ከንባታም፤ ሃድያም፤ ጉምዝም፤ ትግሬም ስትሆን የሚኖርህ የራስህ ከዘርህ
ግንድ ግድ ሆኖ የሚኖርህ መለያ ንጥረ ነገር አለ። ስለዚህ ያ ንጥረ ነገር ሳይኖር ትግሬውን አማራ ሁን፤ ከንባታውን አማራ ሁን፤
ኤርትራውን አማራ ሁን ብትለው አይሆንም። አንድ ሲደምር አንድ ሁለት እንጂ ሦስት አይሆንም።
ስለዚህ ከአማሠራረቱ ራሱ ብአዴን የተፋለሰ
ነው። ዓራማውም መለያ ባድንዴራውም የነፈሰበት ነው። እራሱ አውሮፕላን ማረፊያው ግንቦት 20 ነው የሚባለው። አማራን ለማጥፈት የተዘጋጀ
ፖለሲ ይዘህ ግንቦት 20 ዝክረ ቋሚ ቅርስ ማድረግ መቼም እብደት መሆን አለበት።
የድርጅቱ አርማ የጎመ ቢጫ ሊሞት የታቀረበ መንፈስ ልዝ አይሉት ልዝ፤ እንጨት አይሉት እንጨት የተለመጠ
አገዳ ነው የሚስለው ያው በቁምህ የሞትክ ነህ ነው። ስለዚህ ሥር ነቀል ለውጥ የአወቃቅር ብቻ ሳይሆን የመርህም፤ የ አይዲዎሎጂም
ግድ ይለዋል ብአዴን አማራን እመራለሁ ካለ መቀጠልም ከፈለገ። አሁን ያለውን የአብይን መንፈስ በፀና መሰረት
ለማስቀጠል ብአዴን ላይ የተሟል ተግባር መከወን ይኖርበታል። አደራጃጀቱ የተደራጀበት ፖሊሲ አማራን እያጠፋ ለመቀጠል ነውና።
- · ጣር።
ብአዴን እንደሚያውቅ ሌሎች በህብረ ብሄረሰብ የተደራጁትም ቢሆን ሌላ ቦታ ተንበርክኮ የሚዛቅ ምንም
የመንፈስ ፍርፋሪ ስለማይግኝ አትኩሮታቸው አማራ መሬት ላይ ነው። ይህን የገዱ መንፈስ አጀንዳው ሊሆን ይገባል። አጀንዳው ሊሆን
ይገባል ሲባል ህዝቡን ከሚያስቆጣው ነገር መቆጠብ ያስፈልጋል። አማራሩ ከታች እስከ ላይ ሰቆቃ የበዛበት፤ የተሰላቸ እና እራሱን
ተሸክሞ ለመንቀሳቀስ የማይችል የበደነ ስለመሆኑ በወሎም፤ በባህርዳርም፤ በአዲስ ዘመንም፤ በደብረታቦርም የተካሄዱ ውይይቶችን አዳምጫለሁኝ።
የአቶ ገዱም ይሁን የዶር አንባቸው መኮነን የጊዜ ስጡን ተማጽኖ ፍጥነት፤ ቅልጥፍና፤ ጥራት እስከ አላመጣ ድረስ መንፈስ ዘራፊዎች
አሁን አስፍስፈው ስለሚጠብቁ ለእነሱ ሲሳይ ነው የሚኮነው።
ይህ ደግሞ አገራዊ ብልጹግ ራዩን ያደብዝዘዋል። የአብይ መንፈስ ለመቀጠል
የብአዴን ድምጽ የግድ ያስፍልገዋል፤ ያን ለማምጣት ደግሞ የትካዜ ነገሩን ብአዴን አቆሞ አመራሩን በፍጥነት የሚያስተካክለበትን እርምጃ
መውሰድ፤ የታሠሩ ወገኖችን ከእስር መልቀቅ፤ ከህዝብ ጋር ቀረቦ መነጋገር ህዝብ የፈቀዳቸውን፤ የወደዳቸውን ማክብር ይጠበቅበታል።
ኦህዴድ ላይ ምንግዜም ንጹህ ኦሮሞዎች ስለሆኑ ሃላፊነቱን ለመሸከም የመጀመሪያውን ደረጃ ግማድ የለባቸውም።
ኦሮሞ ስለሆኑ ኦሮማዊ ንጥረ ነገሩ አለ። ስለዚህ ቢያጠፉም ቢያለሙም በዚያ ማዕቀፍ ውስጥ ነው። አማራ መሬት ላይ ግን ይሄ አለነበረም።
ዕድሉም አልነበረም።
በቀጥታ በወያኔ ሃርነት ትግራይ መንፈስ ነበር የሚመራው። ባንዴራ ተብዬው እራሱ ሊቀጠል የሚገባው እኮ ነው።
ወይ ደግሞ ተጥቅልሎ ለታሪክ ደብቁኝ ሊል የሚገባው።
አማራ የደረሰበትን በደል ይህን አይደለም እኛ የውጪ አገር መንግሥታት በአንድም
በሌላም አሳምረው ያውቁታል። እርግጥ ነው ከወያኔ ሃርነት ጋር አማራ እዬገዛ ነው የሚል መንፈስ ጎልቶ ወጥቶ ነበር ያ አሁን መስመር እንዲይዝ ተደርጓል። ልኩንም ሊይዝ ተገዷል። ለነገሩ ለራሱም ትንሽ
ቁጥቋጦ የሙጥኝ እያለም ነው።
- · ግን ብአዴነን ከኦህዴድ ጋር ለማነጻጸር ይከብዳል።
አሁን ያለው መንፈስ የለውጥ መንፈስ ነው። በዚህ የለውጥ መንፈስ ብአዴን ለመጠቀም ያለው የተግባር
ፍጥነት እና የቅንጀት ሁኔታ የኤሊ ነው። ዳታ አብዝቷል። ይሄ ትክክል ነው።
ኦህዴድ በሺህ የሚቆጠሩ አማራሮችን አውርዶ፤ አሸጋሽጎ
ሥልጣናቸውን ቀንሶ፤ አባሮ እንቅፋት የሚፈጥሩበትን ከማዕከል ጀምሮ ነቃቅሎ ራሱን አጥርቶ እዬተጎዘ ነው። ብአዴን ደግሞ ከነሙጃው
ሙጃውን እንደ ተሸከመ ነው። ኦህዴድ የሰላ መስመር በመዘርጋት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥረለትን የተሃድሶ
ሰሚናር ሁሉ ለአዲሱ አማራር እንደ ሰጠ አዳምጫለሁኝ።
ኦህዴድ ከ750 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እያሉበት ግን ከ40ሺህ
በላይ እስረኞችን ፈቷል። ይህ እንግዲህ በአምስት ሲሰላ ወደ ሁለት መቶ ሺህ ነፍስ አርፏል ማለት ነው መሬት ላይ። በርቀት ደግሞ
እኛንም ፈውሶናል።
ሌላው ዝናሩን ጢስ ሲያጠጣ የባጀው አንዱ የኦንግ ክንፍም ሰተት ብሎ ገብቶ እያወከው ነው ያለው። ከ
ውጪ ወደ አገር የገቤት ሰላማዊዎቹ፤ መሬት ላይ የነበሩትም ቢሆኑ ቀናው እገዛ ሲያደርጉለት አላዬሁም፤ ኦህዴድ በውጥረት ውስጥ ነው፤
ይህም ሆኖ እያንዳንዷን ሰከንድ እዬተጠቀመባት ነው። ብአዴን ደግሞ ሲያኖሩት ሲያስቀምጡት እንዳለ ነው ያለው።
አዲሱ ካቢኔ ምን
ያህል አቅም አለው ለሚለው በተለመደው አኳሆን ያው አሁንም ቅድም አቶ ንጉሱ ጥላሁን ነው እየወጡ መግለጫ እዬሰጡ ነው ያሉት። ራሱ
ሥራ ሰጥቶ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ መድረክ በመፍጠር ረገድ አዲሱ ካቢኔ በራሱ ዝግ ውስጥ እንደ ተከረቸመበት ነው ያለው። ትናንትም ዛሬም አቶ ንጉሱ ናቸው …
መንፈሳቸው ጤናማ ነው ቢባልም
ኦህዴድን ያህል የማብቃት እና አዲስ አማራር የማብቀል ተግባር ብአዴን ውስጥ አለ ለማለት አይቻልም። በ100 ቀን ውስጥ አንድ ጠ/
ሚር ምን ሠራ ብለን ብአዴን ላይ ስናይ ምንም ነው። ኦህዴድም ላይ የተከወኑ ግዙፍ የተግባር መስኮች አሉ።
ሦስት ስብሰባዎችን አንድ የካቢኔ ምርጫ ለተጎዱ ካሳ ነገር አይተናል ከዛ ውጪ ምንም ነው። ኦህዴድ
ዘንድ ስንሄድ ዕድሉን ሳያዛንፍ በጥድፊያ እዬተጠቀመበት ነው። በሁሉም ዘርፍ። ስለዚህ የአማራ ልጆች ብአዴን በሚሰጣቸው መግለጫዎች
ሆድ የሚበሳቸው ከዚህ አንፃር ነው።
አማራ ተስፋው በአብይ መንፈስ ላይ ቢሆንም መሬት ላይ ያለው ዕውነት ግን ምንም ነው። እንዲያውም
ይህን እምቅ አቅም ለመቀማት ያሰፈሰፉ እንደ ሰማያዊ እንደ አብን ያሉ ድርጅቶች ተኮለኩለዋል። በስተጀርባ ደግሞ የፕ/ መስፍን ወልደማርያም
መንፈስ አድፍጦ ለተጨማሪ መናጆነት እና ሎሌነት አማራውን ለማስደረግ እዬጠበቀ ነው።
- · ብልህነት ለአማራ ተጋድሎ ዕውነተኛ አንበሶቼ!
ዕውነተኞቹ 20ሺህ የተጋድሎው አንበሶች ስራሳችሁ ራሳችሁ መሆን ይገባችሁዋል። በዚህም የገዱ መንፈስ ሥራ መሥራት አለበት። ሌት ተቀን መባተል አለበት። አሁን የከረባትም፤
የገበርዲንም ጊዜ በፍጹም አይደለም። አመራር አካሉን በሙሉ መለወጥ አለበት።
ጥፋቱ የእኔ ነው ብሎ ካመነ ብአዴን ህዝብን ያማራሩ
አማራሮችን አባሮ የአማራ ተጋድሎው አባል የሆኑ አንበሶችን ወደ ድርጅቱ ማምጣት ግድ ይለዋል። የተገድሎው አንበሶችም ውጪ ሆነው
ከማጣወር አዲስ ጉልቻ ለማሟሟቅ ከመባከን፤ በሞቀው ቤት ገብተው እራሱን ብአዴን ታግለው ማጥራት ይኖርባቸዋል። ይህ ብልህነት ነው።
ለዚህ የትግራይ ልጆች ልባሞች ናቸው። ከተራ ማህብርተኝነት እንኳን ዘው አያሉም ካለመንፈሳቸው። ድርጅታቸውን
ገትረው 27 ዓመት ሙሉ የጉደለውን እዬሞሉ፤ የተዛናፈውን እያስተካካሉ፤ የተጎዳውን እዬጠገኑ፤ ክፍተተቱን እዬደፈኑ ፊት ለፊት ወጥተው
እዬሞገቱ ነው ለዚህ ሁሉ ዘመን ያበቁት እንጂ ወያኔ ሃርነት ምን ነበረው ጫካ እያለ እኮ የምናውቀው ድርጅት ነው …
ስለሆነም ይህን ለወጥ ያመጣው የ አማራ ትውለድ የበይ ተመለካች እንዳይሆን ከፈለገ፤ አብይ መንፈሴ ነው ካለ፤ አብይ በሚመራው
ብአዴን ውስጥ ገብቶ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ከቃል ያለፈ ተነሳሽነት ያስፈልጋዋል፤ ትግሬ
መራኝ የሚለውን ስሞታ ከማሰማት ያ ዘመን ስለለፈ ደፍሮ ይግባ፤ ደፍሮም „ይደመር“ ከዛም የድርሻውን ለአዲሱ ለውጥ ያበርክት። የብአዴ ዓውድ የታጋድሎው አንበሶች ማጥለቅለቅ አለበት።
በተጋድሎው መንፈስ ላይ ነውና ነፍሱ የቀጠለቸው የብአዴን።
ይህ ዕድል ዕድላቸው ነው ለተጋድሎው አንበሶች የእነሱ የደም ዋጋ ነው፤ የከፈሉትን መስዋእትነት ህጋዊ
ጥበቃ እና አውቅና እንዲያግኝ የገዱን መንፈስ ለመደገፍ ቆርጠው መነሳት አለባቸው። ማማት፤ ማሰጣት አቁመው በማዕዱ እኩል ተሳታፊ
ለመሆን አባል መሆን ይኖርባቸዋል።
… ያን አስፈሪ ግርማ ሞገሳቸውን ይዘው ግብተው ጨዋነታቸውን፤ ብቃታቸውን ለአብይ መንፈስ ያላቸውን
አክብሮት ውስጡ ሆነው ይትጉ። አቅም አላቸው የነጠረ ያን ልድላቸው ዘላቂነት ያውሉት። ሌላ ድርጅት ጋር ቢጠቃለሉ ታሪኩ ለሌላ ሰው
የታሪክ ግንባታ ነው ሎሌ የሚሆኑት። ብአዴን ላይ ከሆነ ዘሃውም ፈትሎም ራሱ የአማራ ይህልውና ተጋድሎ ነው የሚሆነው። የለውጡ አውራ
የአማራ የህልውና ተጋድሎ ነውና!
እጅግ የማናውቃቸው ስውር መንፈሶች አሰፍስፈው ነው ያሉት። ሁሉም ጥረቱ ደግሞ አማራን በመቅበር ነው።
ለዚህ ደግሞ አማራ ልባም ሆኖ ውሃ በቀጠነ ቁጥር ስሞታ ከማቀጠጣል፤ የገዱን ምንፈስ አጥር ቅጥር ሆኖ ገብቶ አግዞ፤ የገዱ መንፈስ
የአማራ ሁለንትና መንፈስ መንገድ ቀያሽ መሃንዲስ እንዲሆን ማገዝ ግድ ይላል … ገዱ ብቻውን ነው። ይህን ሃቅ መቀበል የግድ ነው።
ምነው እኔ በኖርኩለት ሌት እና ቀን ብዬ አግዘው በነበረ … ምክንያቱም አብይ የሰማይ ስጦታ ነው፤
አላዛሯ ኢትዮጵያ በአብይ መንፈስ ዘልቃ አፍሪካን እንድተመራ እፈልጋላሁኝ።
ይህ ጉዳይ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዓርማ እንድትሆን፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ችግር መፍቻ መሠረት እንድትሆን ህልም ያለው ዜጋ የአብይን
መንፈስ በቅሎ እንዲጸድቅ ተግቶ መሥራት አለበት።
ይህ ደግሞ ዳር ቆሞ ሳይሆን የብአዴን አባል ሆኖ ነው። ፈቅዶ እና ወዶ።
ደስ ብሎት በሐሴት መንፈሱን
ሰብስቦ ከታጋደሎው ውጤት ጋር አብሮ ቆሞ፤ አብሮነቱን በተግባር ማረጋገጥ ሲኖርበት ነው። አይዞህ የገዱ መንፈስ እኛ እያለንልህ
ሊለው ይገባል የአማራ የህልውና ተጋድሎ መንፈስ። ብዙ ረቂቅ መንፈሳዊ
ትርፎች አሉ በዚህ የተጋድሎ መንፈስ።
ትንሽ ማስፋት አርቆ ነገን ማሰብ ያስፍልጋል። ቂምን፤ ቁርሾን፤ ጥላቻን ማራቅ አስወግዶ ቅንነትን ትህትናን
አዛኝነትን ማብሰል ያስፈልጋል። ቄሮ እኮ አሁንም ኦህዴድን እዬደገፈ እንዳለ የሰሞኑን የዶር ለማ መግርሳ ንግግር አዳምጫለሁኝ።
የሚያስደስተው አማራ መሬት ላይ ውጥረት የለበትም ብአዴን እንደ ኦህዴድ ግን የወጣቱን መንፈስ የሚበትኑ ነገሮች ስላለ የተጋድሎው
አንበሶች „የሽግግር መንግሥት“ ህልም ቢሳካ የተጋድሎው ታሪክ ይቀበራል የተቃጠለ ካርቦን ነው የሚሆነው።
በተጋድሎው ተረማምደው ነው አሁን ሌላ ቅዬሳ ያለው። ይህን ድሉን፤ ታሪኩን፤ ትውፊቱን ማስጠብቅ ያለበት
ደግሞ የተጋድሎው አንበሶች ናቸው። አብን ቢሆን የተጋድሎው መንፈስ የለበትም። በፍጹም። እስከዛሬ የት ነበረ? አጃቢነቱ ለሌላ ታሪክ
ነው … „ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቁመው ማውረድ“ እንዳይችግር ድሉንም ዕድሉንም አማራ አሳልፎ መስጠት የለበትም። ለውጡ የራሱ ነው።
ለለውጡ ዘብ መቆም ያለበት እራሱ አማራ ነው። አማራ የቤት
ሥራውን ለነገ ትወልድ መሥራት የሚችለው ዳር ቆሞ ሳይሆን ታሪክ በሰራበት ገድሉ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ሲሆን ነው። ያ ደግሞ የ አብይ
መንፈስ የ እኔ፤ የገዱ መንፈስ የእኔ የለማ መንፈስ የእኔ የራሴ ብሎ ቆርጦ እና ወስኖ ሳያወላውል የማዕዱ ዕድምተኛ ለመሆን ሲፈቅድ
ብቻ ይሆናል።
- · ተጠያቂነት።
ሌላው ተጠያቂነትን በመወሰድ ረገድ ይህ የገዱ መንፈስ ብቻ አይደለም የአብይም የለማም የአንባቸውም
የንጉሡም መንፈስ ይሄው ነው አቋማቸው። ያጠፋነው እኛ ነን ነው የሚሉት።
እኛ ነው ተጠያቂ የምንሆነው ነው የሚሉት። እኛ ተዋርደናል
ነው የሚሉት። እስኪ ፈልጉ በቅንጅት ለጠፋው ነፍስ ሁሉ፤ ተበትኖ ለቀረው ሥነ - ልቦና ሁሉ፤ በሌላውም በዘመን ደርግም፤ በኢህአፓም፤
በኦንግም እኛ አጥፍተናል፤ ተጠያቂ ነን የሚል ህብረት፤ ጥምረት በሉት ተናጠላዊ ድርጅት ፈልጉ።
ማንኛውም 43 ዓመት የተገበረው
ትውልድ፤ የባከነው መንፈስ ሁሉ እንደ ተበተነ ነው የቀረው፤ ይቅርታ ጠያቂም አመስጋኝም የለውም።
ይቅርታ አድርጉልን የሚል አንድ ቀንጣ ነፍስ ጥሩልኝ። ለዬዘመኑ የሰው ግብር አይታክቴ የኢትዮጵያ እናቶች ያቀርባሉ
ግን ሃላፊነትን፤ ተጠያቂነትን የሚወስድ የለም። ለዛውም ወድቀንም
ተንኮታኩተንም የሞተው ሙቷል እኛ አክተሮች ደግሞ በህይወት አለን ሹሙን ሸልሙንም ነው።
አሁንም አክተሮች አሉ ማገዶዎች ግን አለቀዋል።
አክተሮች አሁንም ሥልጣን ካላገኝን ጦርነቱ ይቀጥላል ባዮች ናቸው።
በቃ ለማን እና ለምንም ነው ያ ሁሉ ግብር ለዛውም የሰው ግብር የተገበረው፤ የመንፈስ ጥሪቱስ፤ የተጎዳው ሥነ - ልቦናስ?
ዕድሜውስ ባክኖ የቀረው? በቃ ወድመት ለዛውም የትውልድ። ጠያቂ የለ
ተጠያቂም የለም።
በቃ … አሁን ኢህአዴግ ጥፋቱን ወደ ሌላ ቢያለክከው ዙሮ ተመልሶ ያው ታሪክ ነው የሚደገመው። በዛ ላይ ጥላቻው
እኮ እስኪ ሁላችንም እራሳችን እንመርምረው፤ የማንጠላው ምን ነገር አለና ቀድሞ ነገር? የማንተቸው ምን ነገር አለ? የማንብጠለጥለው
ምን ነገር አለ? የማንቀረድደው ምን ነገር አለ? ሁሉም ጥላቻን ሴብ አድርጎ ለትውልድ ነፃነት፤ ለዴሞክራሲ፤ ለእርቅና ሰላም ሲል
ነው የሚደመጠው … ይህን አዲሱ መንፈስ ማበረታት ወይንስ ይህን ሰብሮ መወጣት የቱ ይሁን ምርጫው?
… ቃለ የገቡ ይመስለኛል ትውልድን ለማዳን
የፈለገ ዓይነት መከራ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ይፍጠር ዛሬም እንደ ትናንቱ ግን ሃላፊነቱን እኛ መወስድ አለብን ብለው ተመካክረዋል።
ወስነዋል። ምክንያቱም ረመጡ የታመቀው ቋያ ከፈነዳ የሚተርፍ የትግራይ ልጅ የለም። መሪነት ማለት ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገንም ማዬት ይገባል።
በዚህ ውስጥ ንጹሃንም ይኖራሉ። በሥነ - ልቦናው የበላይነት ቢኖርም ድጋፉ በዬፌርማታው
የተኖረበት የታዬ ቢሆንም፤ ተጠቃሚነቱም ከላይ እስከታች እስከ አንገት ማሰሪያ ድረስ ቢሆንም፤ ግን ደግሞ ለሴራ ተበባሪ የማይሆኑ ፍጥረቶች አሉ የትግራይ ልጆች። ይህን መቼም
አሊ አይባልም። ልዑል እግዚአብሄር ለአንድ ሰው ሲል ምህረት ይሰጣል።
በመሪ አንደበት ያ ቢገለጽ ልክ ባህርዳር ስተዲዬም „የሽግግር
መንግሥት፤ በተቀደደ ቦይ መፍሰስ“ የሚል ዕሳቤ ዓይነት ይሆንና ዘር ይነቀላል። በመጥፎ መንገድ ተሂዶ ወይንም ያን መጥፎ አሰቃቂ
ድርጊት ፈጽሞ የመንፈስ እረፍት አይገኝም። በፍጹም።
ስለዚህ ነገሮችን ገፍተን ባቀጣጠልነው ቁጥር ይቃጠላል፤ ትርፉ አመድ ነው። እኛ ውሃ ለመሆን ስንፈቅድ መራረውን
ነገር እንደ ጣፋጭ በመወስድ ይሆናል። አሁን የወያኔ ሃርንት ትግራይ እንኳን ብአዴን እራሱን ለምመራትም አልቸለም፤
ያልቻለው ዛሬ አይደለም።
ከአማራ ተጋድሎ በኋዋላ አልቻለም፤ ሁሉም ነገር ከቊጥጥሩ ውጪ ነው የሆነው። ያን ጊዜ ነው መዋቅሩ የተተረተረው።
ደመንፍሱን ነበር። ከዚህ በኋዋላ በዚህ ዓምት ትግራይ ላይ በተካሄደው ኮንፈንስ ብአዴንም ኦህዴድም አለተገኙም ነበር። የወያኔ ሃርነት
ትግራይ ማዛዝ ቢችሉ ያን ጊዜ ይችሉ ነበር።
ወያኔዎች ማዘዝ ቢችሉ የሚችሉበት የድምጽ ሥርዓት እኮ አይናቸው ጉድ አሳይቷቸዋል። የብአዴን ድምጽ
ሙሉው ወጥ በሆነ አቋም የብአዴን ተወዳዳሪው አቶ ደመቀ መኮነን እራሳቸውን አግለው ድምጽ እንዳይከፋፈል እርምጃ አይወስድም ነበር።
ስለዚህ አሁን ብአዴን በራሳቸው ውስጥ ናቸው ያሉት። ስለዚህ ለጥፋቱ ከእንግዲህ እኛን ጠይቁን ነው የሚሉት … ወያኔ ሃርነት ትግራይም
ቢፈጽመው በእኛ ድክመት የሆነ ነው።
ዛሬ ሁላችንም ራሳችን ለማስተዳደር ሥልጣኑ በመዳፋችን ነው ያለው ነው የሚሉት፤ ደግሞም ዕውነት
ነው፤ ኦህዴድ ላይ በመወሰድ ላይ ያሉትን እርምጃዎች ስናይ ዕውነቱ ይሄው ነው። የጠ/ ሚር ቢሮም ጉዳይ ስትመለከቱት ይሄው ነው፤
ከወያኔ ሃርነት ፈቃድ እና ቁጥጥር ውጪ የሆኑ መልካም ነገሮችን ነው እያዬን ያለነው። ለዛውም የለመለሙ፤ ሚሊዮኖች የሚመሰጡባቸው። እኛ ብቻ ሳንሆን ውጮችም ሳይቀሩ በጣም
እዬተደነቁ ነው።
ወያኔ ሃርነት ትግራይ በኦህዴድ ላይ
ዛሬ አቅም የለውም። በፍጹም። በብአዴን ላይም እንዲሁ፤ ብአዴን ሊከፍል፤ ሰላሙን ሊያውክ የሚችለው በተለመደው በነሳጅን አለምነህ
መኮነን ነው። እንደ ቀደመው ጊዜ በቀጭን ትእዛዝ ግን የሚሆን አይደለም።
ለምሳሌ የአርበኛ ጎቤ ሰማዕትነት ቀን ቅልጥ ብሎ ነበር በተኮስ ባዕቱ፤ ለዛውም አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
ነበር። ግን ምንም አላወከውም ባህሉን ብአዴን። ሰሞኑን የአማራ ቴሌቪዥን በእስረኞች ጉዳይ ላይ የነበረው ቆይታ፤ የአብን ምሥረታ፤
የጎንደር የትናንቱ የሀምሌ 5 ክብረ በዓል ሂደት፤ የሰሞኑ የአቶ በረከት ጉዳይ እና ሰው ሳይጎዳ ቁጣውን ለማስናገድ ያደረጉት ጥረት፤
የባህርዳሩ የድጋፍ ሰልፍ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ነፃነት ታምር ነው።
ይሄ በራሳቸው ውስጥ ስለመሆኑ ለማንም እንደማይገዙ እያሳዩ ያሉበት የነጠረ ሃቅ ነው። ከዚህ ባላፈ
ስለላፈው ድክምት አሁንም የራሳቸው ነው፤ እንደ ባለፈው ጊዜ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ምንትሶ ቅብጥርሶ የሚሉት ነገር አይኖርም።
ለቀደመው እንደ ግንባር ማህብረተኝነታችን አብረን ተጠያቂ ስለሆን በይፋ ይቅርታ አድርጉልን ብለው ጠይቃዋል።
ስለዚህ ሃላፊነት ሲሰጥ
በሌላው ላይ እያላከኩ መሸሽ ራሱ የተባላ ዕቁብ ሆኗል። በግልም በጋራም ለጠፋው ጥፋት ተጠያቂ እኛ ነን ማለት የ አመራር ብልህነት
ብቃት ነው። ይልቅ ይህ ሁሉ እዬተደረገለት የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማስታወል ሊፈጥረልት አለመቻሉ ምን ያህል ለትግራይ ነገ ጭንቅ
እንደሌለው በሚገባ ተረድቻለሁኝ። 700 ሺህ ህዝብ ተፈናቅሎ እኛ ነን። በኤልኮፍተር በተደገፈ ውጊያ ተካሂዶ የእኛ ድክመት ነው
ይህ ታምረኛ ዘመን ጉዳኛ ነው።
- · በውስጥ ለመኖር መፍቀድ።
በሌላ በኩል በብሮድ ካስት ስብሰባ ላይ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ያዬ ለዛውም በዛን ጊዜ በውስጣቸው ያለውን
በራስ መተማመን ስሜት ልቅና መዬት ይቻላል። አሁን ከላይም አድማጭ እናት አላቸው። የኢትዮጵያ ህዝብም የጀርባ አጥንት ለመሆን ዝግጁ
ነው።
ስለዚህ በፈለገው የሴራ መንፈስ ውስጥ ሴራው የእነሱን የአመራር አቅም ጥሶ መሬት ቢረግጥ ድክመቱ የእነሱ ነው። ለምሳሌ ያ
ትዕይንት ባህርዳር የሆነ ነገር ተፈጥሮ ቢሆን፤ በእነሱ እንዝህላልነት ነው ለጥቃት የሚጋለጡት የነበረው። ምክንያቱም አሁን ሥልጣን በእጃቸው አለና።
ከብአዴኖች የጸጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ክትትል ከእነሱ ዘሎ
አቅም አንሷቸው ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተጠያቂ ሊሆን ከቶውንም አይችልም። በዛ ስብሰባ ላይ እኮ „ሽግግር
መንግሥትን ጥያቄ“ አስተናግደዋል እኮ፤
እኔ እራሴ በጣም ነበር የደነገጥኩት። ልክ አቶ ዳውድ ኢብሳ እንደ ከፈቱት ጦርነት፤ የሥነ - ልቦና
ጦርነት ነው የተከፈተው ባህርዳር ላይ፤ በተለያዬ ሁኔታ የሚጻፉ ጹሑፎችም የሚዋኩ ናቸው። ብአዴን ሊታገዝ ይገባዋል ነው የምለው
እኔ።
ብአዴን የምናግዘው ለኢትዮጵያ ብቻ አይደለም አፍሪካ ድምጽን
በድምጽ የመሻር አቅሟ ዕውን እንዲሆን የአብይ ካቢኔ መንፈስ እንዲቀጥል ማድረግ ሲቻል ብቻ ነው። እገዛ ማድረግ ይገባል የምለው
ይህ መንፈስ አፍሪካዊ ክንዱ ፈርጥሞ በሁሉም መስክ ማርከሻ፤ ጥቃት የሚወጣ ብቁ - ንቁ - ብልህ - ጥበበኛ - ዲፕሎማት - ሰውኛና
ተፈጥሮኛ ስለሆነም ጭምር ነው።
የአብይን መንፈስ ማገዝ ማለት ለዓለም ሰላም ማገዝ ማለት ነው። ዛሬ ዓለም ሰላም ነው የሚፈለገው።
እኔ ወድጄ ነው የእጅ ስልክ የሌለኝ። የቤቴ ስልክ አጠገቡ ከሌለሁ አልሰማውም እጅግ ዝቅተኛ ነው ድምጹ። ብሰማውም አላነሳውም።
የስልክ ጮኽቱን እሱን የመስማት አቅም እንኳን የለኝም። ስለምን? ሰላም ስለምፈልግ።
እና የሰላም ንጹህ መንፈስን ለማምጣት የጥላቻ
ግድግዳዎችን ለመናድ መድፈር ግድ ይላል። አሁን አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ምን ለማግኘት ነው ከወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚለጠፉት? ምንስ
ቀረብኝ ብለው? መታሰር፤ ግልምጫ፤ መንጓጠጥ መሳደድ? በፍጹም አይደለም። ብልህነት ነው። ሃላፊነትን ሸር የማድረግ አዲስ መንገድ
ነው።
እኔ አይደለሁም እሱ ነው የሚለው እጣት መጠቋቆምን እያስቀሩት ነው። እነዚህ ሰዎች እኮ ሊጠኑ የሚጋባቸው ጥበቦች ናቸው
… ለገባው …
ውሃ በቀጠነ ብአዴንን አናንሰው። ይልቅ ሊበረቱበት፤ ሊተጉበት፤ ሊያተኩሩበት የሚጋበውን ነገር መጠቆም
ነው መልካሙ እና ዘላቂው የአማራንተ ተጋድሎ ማዝለቅ ማጽደቅም የሚቻለው።
አሁን ከኤርትራ ጋር በመለያዬታችን እንደ ገና ስንገናኝ
ሁላችንም ራሳችን ታዝበናዋል። መጎዳታችን ያወቅነው አሁን ነው። በዘመኑ ግፍ ተስርቷል በዚህ ግፍ ምክንያት ፊታችን አዙረን ትግራይን
አንይሽ ብንል፤ በመንፈስ ብንለያት መለሰን ስንገናኝ ደግሞ የግድ ነው የማናውቅው ስሜት እንደሚፈትነን። ልንማር ይገባል …
ፈታኝ ነው ግን ፈታነውን እኛ ሳናልፍ ሌላው እንዲያልፍ መሞከር ስስታምነት ነው። እኔ እጅግ ራሴን
ነው የታዘብኩት። የኤርትራ ልዑክ አዲስ አባባ ቦሌ ሲገባ ያን የመሰለ ሥም የለሽ ስሜት ለዛውም የማልቆጣጠረው ዕንባ ካለ እኔ ትእዛዝ
ይወርዳል ብዬ አላሰብኩም ነበር በፍጹም።
ደም እትብት ዘር የፈለገ ቢገፋ፤ የፈለገ አልይህ አልስማህ ቢባል፤ የፈለገ መበዳደል ቢኖር
የቁርጡ ግን መቆራረጡን እንችለውም። ይሄው ጉዳችን ዘመን አጋለጠው፤ ያን ቁጭ ብድግ የፕ/ አሳያሳን አፈወርቂን ጉዳይ ተመልከቶ፤
ያን የኤርትራ ወጣቶችን ፍንደቃ ያዬ፤ ያን የኤርትራ እናቶችን ፈገግታ
እና ሰናይ ያዬ ነገ ይህ መከራ እንዲደገምብን በሌላው ወገን ላይ የሚፈቅድ አይሆንም፤ ምንም አይቀርብንም ግን የጎደለን ነገር ነበር።
ለወደፊቱም እንድንጎድል መጣር የለብን። ውሸታችን ነው ጥላቻውም፣ መወቃቀሱም፣ መነቃቀሱም፤ መረጋገሙም እንጂ ውስጣችንማ ተፈትኖ
ታዬ እኮ … እኔ ካለፈው የቦሌ አቀባበል በኋዋላ እኔ እማላዘው፤ ከእኔ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ሌላ ስሜት እንዳለኝ ተረድቻለሁኝ።
- · ክወና።
ስለዚህ ፍቅር ሲባል ሌላው አይቀበለው እኛ ግን እንሁንበት። ምህረት ሲባል ሌላው አይቀበለው እኛ ግን
እንሁንበት። እርቅ ሲባል ሌላው አይቀበለው እኛ ግን እንሁንበት።
መቻቻል ሲባል ሌላው አያድርገው እኛ ግን እንሁንብት።
ስንት ዘመን እንዘን? ስንት ዘመን እንቆዝም? ስንት ዘመንስ ሳቅን ገፍተን
እንኑር? ስንት ዘመንስ እኛን መግራት ተስኖን ትውልድ ይባክን?
አሁን ስለሁሉም ነገር ባለቤት አለው። ኢትዮጵያ ዓራት ዓይናማ መሪ አላት። የማያሳፍር!
አንገት የማያስደፋ! ፈጣሪ ከጠበቀው የሰከነ ጊዜ ሲመጣ ከአሁን እጅግ የተሻሉ አስዳሳች ጊዜዎች ይኖሩናል።
ግን መደማመጥ
- መተሳሰብ - መተጋገዝ ሲኖር ነው …
ይህ ማለት ግደፈቶች ይታለፉ ማለቴ አይደለም ግን አናክረው ነው፤ ወደ ጠቃሚ መንፈስ ለመቀዬር ከራሳችን
እንጀምር ነው፤ አሁን ባለፈው ጊዜ የማከብረው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው „ኢሳይሳ ኢሳያስ ነው“ ማለቱ የሚሰቀጥጥ ጹሁፍ ነበር። ጦርነትን
የሚያነሳሳ ጹሁፍ ነበር።
ጥላቻን የሚጋብዝ ጹሑፍ ነበር። የእሱ ችግር የመብት እና የግዴታውን ጣሪያና ግድግዳ ያለማወቅ ይመስለኛል።
ሁሉ ቢፈቀድም የማይጠቀም ከሆኖ ከዛ ራስን ማራቅ ያስፈልጋል። ለዚህ ነው ሐዋርያው አባት ወንጌላዊ ቅዱስ ጳውሎስ „ሁሉ ተፈቅዶልኛል
ሁሉ ግን አይጠቅምም“ ያለው። እናስተውል።
የኔዎቹ ነገን ደግሞ በሰላም ያሳልፍልን። እኔ ጭንቀታም፤ ፈሪም ነኝ። ዛሬ እንቅልፍ የለም አዲስ እና
አዋሳ በሰላም እሲኪያልፉ ድረስ። የሞት ዘመን ቢያበቃልን ግን ምን አለ?
ፍራቻዬ ቅኖች ጥቂቶች ስለሆኑ ነው።
በተረፈ ኑሩልኝ።
„አማራነት ይከበር!“
መሸቢያ ጊዜ!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ