"በዩኤስ ኤይድ የሚደገፉ የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሀብት እና ገንዘብ እንዳያስተላልፉ ተከለከሉ" BBC

 

በዩኤስ ኤይድ የሚደገፉ የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሀብት እና ገንዘብ እንዳያስተላልፉ ተከለከሉ

https://www.bbc.com/amharic/articles/cx2pwngd20lo

እንዳያስተላልፉ ተከለከሉ

47 ደቂቃዎች በፊት

«የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ እና ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ያለ ባለስልጣኑ "ግልፅ ፈቃድ" ሀብት እና ገንዘብ እንዳያስተላልፉ እንዲሁም እንዳይሸጡ አሳሰበ።

ይህንን ማሳሰቢያ በሚተላለፉ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድም ባለስልጣኑ አስጠንቅቋል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን የመከታተል እና የመቆጣጠር ስልጣን ያለው ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤቱ ይህንን ማሳሰቢያ የሰጠው ማክሰኞ ጥር 27/2017 .. ባወጣው "አስቸኳይ መግለጫ" ነው።

የባለስልጣኑ መግለጫ፤ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅትን የእርዳታ የማቆም ውሳኔ የተመለከተ ነው።

ባለፈው ወር ሥልጣን የያዙት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያሳለፉትን ትዕዛዝ ተከትሎ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት በዓለም ዙሪያ የሚሰጠውን እርዳታ እና ድጋፍ አቁሟል። የትራምፕ አስተዳደር ተቋሙን በሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሥር ለማድረግ ማቀዱም ተገልጿል።

አሜሪካ በአውሮፓውያኑ 2023 በጀት ዓመት ብቻ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለተለያዩ ሀገራት 72 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጋለች።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው ዩኤስ ኤይድ በኢትዮጵያ ግጭት እና የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተሉትን ጉዳት ለመቋቋም .. 2020 አንስቶ 3.6 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቧል።

ተቋሙ፤ የኢትዮጵያን ብሔራዊ የጤና ስርዓት ለማጠናከር በየዓመቱ 154 ሚሊዮን ዶላር ፈሰስ እንደሚያደርግም የመስሪያ ቤቱ መረጃ ይጠቁማል።

በተጨማሪም ድርጅቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ለመደገፍ እና የመገናኛ ብዙሃንን አቅም ለማሳደግ እርዳታ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ዛሬ ባወጣው መግለጫ "በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በኩል የእርዳታ የማቆም ውሳኔ የተወሰነ መሆኑን" መረዳቱን ገልጿል።

ይህንን የተቋሙን እርዳታ የማቆም ውሳኔ "በቅርበት እየተከታተለ" መሆኑን ያስታወቀው ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ፤ "ዝርዝር ሁኔታዎችን መሠረት በማድረግ በቀጣይ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል የሚያከናውን ይሆናል" ብሏል።

ይሁንና ባለሥልጣኑ፤ ከዩኤስ ኤይድ ድጋፍ የሚያገኙ በኢትዮጵያ ሚገኙ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ይህንን ውሳኔ ተከትሎ ባላቸው ሀብት እና ገንዘብ ላይ ለውጥ እንዳያደርጉ የሚገድብ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶቹ ያለ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ "ግልፅ ፈቃድ" ንብረት እንዳያስተላልፉ፣ እንዳያስወግዱ ወይም እንዳይሸጡ አሳስቧል።

"ከመደበኛ የፕሮጀክት ስራዎች ጋር ተያያዥ ከሆኑ ጉዳዮች ውጭ በማናቸውም መልኩ ሃብት እና ገንዘብን ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የተከለከለ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን" ሲልም ተጨማሪ ክልከላዎችን ይፋ አድርጓል።

ባለሥልጣኑ ይህንን ማሳሰቢያ "በመተላለፍ በሚንቀሳቀሱ" የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ "ተገቢውን እርምጃ" እንደሚወስድም በዛሬው መግለጫው አስታውቋል።

ቢቢሲ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ እዚህ ውሳኔ ላይ ስለደረሰበት ምክንያት መረጃ ለማግኘት ያደረጋቸው ጥረቶች አልተሳኩም።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በአባልነት የያዘው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በበኩሉ በጉዳዩ ላይ መግለጫ እንደሚያወጣ ገልጿል።»

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?