እንደምን የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ዲያሪክተር ዶር ቢኒያም አሥራት #ከኃላፊነታቸው ይነሳሉ? (ዘገባው የዋዜማ ነው።) ይድረስ ለኢትዮጵያ ጤና ሚር ለክብርት ዶር. #መቅደስ ዳባ።
ክብርት ሆይ!



አሳዛኝ ዜና ሰማሁኝ። መረጃ ያገኜሁበትን ፔጅ ከሥር ለጥፌያለሁኝ። በመከራችን ሁሉ በአንድነት ሊያቆመን የማይችለው በታኝ ጉዳይ ይህን መሰል #የጓጎለ ውሳኔ ነው። እንደምን የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ዲያሪክተር ዶር ቢኒያም አሥራት #ከኃላፊነታቸው ይነሳሉ? በዚህ ወቅት? በዚህ ጊዜ? ሳይለንት ማጆሪቲው ሆድ እንዲብሰው የኢትዮጵያ ቢሮክራሲ ሞጥሮ እየሰራበት ነው።
የጤና ሚር አይደለም ለሰው ልጅ ለኢትዮጵያ ሃኪሟ ሊሆን ይገባዋል፤ በድርጊቱ፤ በሞራሉ፤ በኤቲክሱ አብነታዊ ተግባር መፈጸም ከቻለ። ግን እየተሳነው ነው። አዌርኔሱ ሌላ የአፍሪካ አገሮች ያላገኙት እጅግ ፈጣን ውስጣዊ እርምጃ WHO እንዲያገኝ አድርጎታል። አትኩሮቱ የተቋሙ ልዩ ሥጦታ ነው። ይህን ዕድሉን በክብር ማስቀጠል ሲገባ የኢትዮጵያ ጤና ሚር #ማፍሰስ የእርግማን ነው። አቶ ጎዳና ያዕቆብ የሚሉት ነበራቸው ቢያንስ አስተካክለው ቢሳሳቱ ይሉታል የብልጽግናን እርምጃ። በዚህ ወቅት ህዝብ የሚያስከፋ ተግባር እንደምን ይፈጸማል? ማንን ለማስደሰት? ማንንስ ለመጥቀም???
ለዛው ጥሪውም፤ አፈጣጠሩም፤ ተልዕኮውም ለሰብዕዊነት፤ ለተፈጥሯዊነት ለሆነው የጤና ተቋማት እንዲህ ያለ ያልሰከነ #ትርምስ፤ #ለመግደፍ መባተል ምን ይባል? እጅግ አዝኛለሁኝ። የተከበሩ የጂንካ ሆስፒታል ዴያሪክተር ሞታቸው ይፈለግ ነበርን? ለምን በህይወት ተረፋ ነውን? ትጋታቸው፤ ፍጥነታቸው ውስጣችን አግኝቶ መረባረባችን ዶር ቢንያም አሥራትን #ሊያስመሰግናቸው፤ ሊያሸልማቸው ሲገባ እንደምን ከኃላፊነታቸው ያስነሳቸዋል??? አለመታደል ነው።
የኢትዮጵያ ቢሮክራሲ ከህዝብ ጋር የሚያገናኜውን ጤናማ ሊንክ ፈቅዶ እየበጣጠሰ እንደዚህ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህዝብ ሆድ እና ጀርባ ሆኖ ዘመናት እንደታመሙ ይሄዳሉ፤ አዲሱ ዘመንም ራድን ሰንቆ እየቆዘመ፤ እያዘገመ ይመጣል ሽኝቱም እንደ አነባ ደብዝዞ ይሆናል። በዚህ ማህል ትውልዱ የተስፋ መጠጊያ አጥቶ እንደ ባተለ #እፎይታ እርቆት ይሻላል በሚለው ሁሉ እየሞከረ ማገዶ ሆኖ እንደ አዘነ መራራ ስንብት ይሆናል። አንድ ተቋም፤ አንድ ንጹህ ህሊና ያለው ዘመን ከዘመን አጣን። ለምን ክፋት፤ ክፋነት፤ ጭካኔ፤ ሸር በርክቶ ምርቃታችን ስለተነሳ። ለዚህ ነው እኔ ሁልጊዜ…………
1) በሚሆነው ሁሉ አብረን #እንፈር የምለው።
2) ኢትዮጵያ የከበደችን #ለሁላችን ነው የምለውም። በኢትዮጵያ ዙሪያ በእንግሊዘኛ የሰጡትን መግለጫ፤ ከትናንት በስቲያ የዘውዲቱ ሆስፒታል የዕደሳት ሁነት አስመልክቶ ክብርት ሚኒስተሯ ያደረጉትን ንግግር አዳምጨዋለሁኝ። ለኢትዮጵያ ክብር ያን ያህል ውስጥነት ካለ፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ የጤና አያያዝ መሻሻል ይህን ያህል ጥረት ካለ፤ እንደነዚህ ካሉ #ግብታዊ እርምጃወች ስለምን የጤና ሚር አይታቀብም? እኛን ከማስከፋት መቆጠብ ተሳነው? እኛን በንግግሩ ብቻ ሳይሆን በተግባሩ ውስጣችን ለማሳመን ስለምን አይተጋም? ለእኔ ኦድ ነው።
#እና።
የዶር ቢኒያም አሥራት ከኃላፊነት መነሳት ውስጤን ከፍቶታል። የጤና ሚር ይቅርታ ጠይቆ እሳቸው በፈለጉበት የኃላፊነት ቦታ ይመደቡ ዘንድ ፈቃዳቸውን ይጠይቅ ዘንድ በትህትና አቤቱታ አቀርባለሁኝ። ብልህነት ነው ስኬት። ግዴለሽነት + በቀል ለትውልድ፤ ለአደራ፤ ለሰብዓዊነት፤ ለተፈጥሯዊነት የመሆን አቅሙ #ዱካ ነው። መረጃው ከሥር ተያይዟል።
ግንእኔ ሥርጉተ©ሥላሴ ሙሉ ዕድሜየን የኢትዮጵያ ፖለቲካ #ከገበርዲን እና #ከሱፍ ካልወጣ የድምጽ አልባወቹ የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ #አይታበስም ብየ የሞገትኩበት አመክንዮ #ፈሶ ነው የቀረ። ሴት የፖለቲካ ሊቃናት ለእናትነት ጸጋቸው አብነት ሲሆኖ እንደናፈቀኝ 8 ዓመት እንደ ዋዛ ነጎደ። ፋሽን አያለሁኝ። መዋብ ጥሩ ነው። ግን ለእናትነት #አንከርነት እየዋለለ።
ዛሬ በብዙ ቦታወች የሴት የፖለቲካ ሊቃናት ኃላፊነት ተሰጥቷል። በሚገርም ሁኔታ። ለእስልምና ዕምነትም ተካታይ አንስቶች በብልጫ ስለመሆኑም አያለሁኝ። ህብራዊነቱ ጥሩ ነው። የተደከመበት የእናቶች መከፋትን ስለመቅረፍ ፋይዳው ግን ……??? ቦታው ካለድካም ስላገኙት የኢትዮጵያ ሴት የፖለቲካ ሊቃናት ምን ያህል እንደ ተደከመበት አያውቁትም። ህወሃትን ፈቅዶ ከመንበሩ እንዲነሳ ያደረገው አንዱ ጉልበታም ሙግት ይሄው ነበር።
እንዲያውም አንድ ጊዜ የኢትዮጵያ እናቶች ያመሰግኑኃል ብለው ጠቅላይ ሚር አብይን ያመሰገኑበት ሴሪሞኒ አይቻለሁኝ። ከቤቴ ሁኜ እስቅ ነበር። እሳቸው ጠቅላይ ሚር ይሆኑ ዘንድ ይሁንታ ያገኙበት አንዱ ሚስጢር የኢትዮጵያ ሴት ሊቃናት የፖለቲካ ውክልና ተሰርቶበት ነው የተገኜው። በሴት ሊቃናት ዙሪያ ቅንጣት ጥረት የዶር አብይ አህመድ የለም። አስበውትም አያውቁም። ይህ ዘርፍ ባለቤት አልባ ነው የነበረው። በተፎካካሪወችም ዘንድ ፋይዳ አለው ተብሎ አይታሰብም ነበር። ግን ብዙ በጣም ብዙ የህሊና አቅም ፈሰበታል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ውክልና በሴቶች ዘርፍ ተመጣጣኝነቱ፤ ስኬቱ ከወንዝ ዳር የታፈሰ #አሽዋ አልነበረም።
እሳቸውን እራሱ ዶር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ያመጣው አንዱ ጉልበታም አመክንዮ ይህ ነው። ዶር አብይ አህመድ እራሳቸው ያውቁታል። በብልጠትም ነው የከወኑት። ለዛ ነው 50% ካቢኔያቸውን #በሴት ሊቃናት ያስጌጡት። ይህም ሆኖ ተሿሚ፤ ተሸላሚ ሴት የብልጽግና የፖለቲካ ሊቃናት ተስፋየን ጥግ እንዲያገኝ ሲያደርጉ አላዬሁም። ተከታታይነት ያለው በትጋት የሚከወን ተግባር ነበር ጥበቃዬ። ነቀል ተከል ጉዳይ በከንቲባ ጽ/ ቤት አያለሁኝ። በዚህ ውስጥ ተፈናቃይ የሴቶች ዕንባ ደግሞ አለ። ያ ነው ለእኔ ውስጥ የሚቀርበው። አጽናኝ ሊያጣ አይገባም ነበር።
ቋሚ የሆነ ከከፋቸው የኢትዮጵያ እናቶች ጎን ተሰልፈው ሲያጽናኑ የኢትዮጵያ ሴት ሊቃናት ሹመኞች #አላየሁም፤ አልሰማሁም። እንዲህ ስንጽፍም አያዳምጡንም። #አርጀንቲናዊቷ ውዷ ኢቪታ ፔሩን ( ህይዋን ፔሩን) የአገሯን ሴቶችን በሚመለከት ቋሚ አሻራዋ የማህበረሰብ ሥር - ነቀል ለውጥ አምጥቷል። ከጎዳና ህይወት ወጥታ ቀዳማዊ #እመቤት ስትሆን በህግ ነው የውስጧን መሻት ያዋዋለችው። ሴቶችን ከዕንባ ማውጣት አያቅትም። ልቦና ላለው ብልህነት። የእኛ የፖለቲካ ሴት ሊቃናት ግን ቦታውን ይዘው --- #ተሳናቸው።
የእኔ ውዶች ማህበረ ቅንነት እንዴት አደራችሁልኝ? አይዞን። #በሰፊ ልቦና፤ በተከታታይ በሚሰራ ሰላማዊ የብዕር ትጋት ጸሎትም ለቀኑ ቀን ሲሰጠው የመፍትሄው ምርቃት ከእዮር ይመጣል። አትጠራጠሩት። #ዝምታ ከትጋት በላይ የስኬት ዓውደምህረት ነው።
የጤና ሚር ጥሩ ሰብዓዊ አማካሪ የሚያስፈልገው ይመስለኛል። የዶር ቢኒያም አስራት ጉዳይ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ ፈጣን ቢሆን ምርጫየ ነው። ሲከር ይበጠሳል፤ ሲሞላም ይፈሳል። ብጣቂ ሥልጣን ቀርቶ ሙገሳ የማንፈልግ ኢትዮጵያዊ ዜጎችን ማድመጥ በሚመለከት የኢትዮጵያ ቢሮክራሲ ሊለመን አይገባም። "ላም እረኛ ምን አለን% አድምጡ" ሥርዓቱ መቀጠሉ እኮ ነው ትንፋሻችሁ? አይደለምን???
ክብረቶቼ እንዴት ናችሁልኝ። አይዟችሁ! አይዞን! ሰፊነት ብቻ ከእኛ ይፈለጋል።
ቸር አስበን፤ ቸርእንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17/11/2025
#ሰውኛነት አይፈራ!
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
//////-/////-/////
"የጂንካ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ለመገናኛ ብዙሀን መረጃ መስጠታቸውን ተከትሎ ከሀላፊነታቸው ተነሱ"
ዋዜማ ራዲዮ
November 17, 2025
"ዋዜማ- የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር በአካባቢው ስለተከሰተው “የሔሞሬጂክ ፊቨር” እንደሆነ በተገመተው ተላላፊ በሽታ ሰዎች መሞታቸውን ገልፀው ለመገናኛ ብዙሀን መረጃ መስጠታቸውን ተከትሎ ከሀላፊነታቸው ተነሱ።
ዋዜማ ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮና ከሆስፒታሉ ምንጮች እንደሰማችው የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ቢንያም አስራት ለአንድ አለማቀፍ ሚዲያ “የሔሞሬጂክ ፊቨር” እንደሆነ በተገመተው በሽታ ሳቢያ ሀኪሞችን ጨምሮ ሰዎች መሞታቸውን ገልፀው መረጃ በመስጠታቸው ከሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ምስጢሩ ሐምደኪ በተጻፈ ደብዳቤ ከሕዳር 5 ቀን 2028 ዓ.ም ከሀላፊነታቸው መነሳታቸው ተነግሯቸዋል።
ዳይሬክተሩ ከሃላፊነት ከመነሳታቸው በፊት ወደ ሆስፒታሉ መጥተው ከታከሙት አራት በሽተኞች አንዱ በህይወት እንዳለ እና የተሻለ የሚባል የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ሁለት የሆስፒታላቸው የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ እስካሁን ስድስት ሰዎች ተመሳሳይ ምልክቶችን በማሳየት ህይወታቸው ማለፉን ለዶቸ ቨለ ራዲዮ በይፋ ገልፀው ነበር።
የበሽታው ክስተትና ምንነት ዓለማቀፍ ትኩረት የሳበ ሲሆን የዓለም የጤና ድርጅትም ከመንግስት ጋር በመቀናጀት አስቸኳይ የመስክ ቡድን ወደ ስፍራው ልኳል።
የጤና ሚኒስቴር እስከአሁን ድረስ ስምንት ሰዎች በበሽታው የተጠረጠሩ መሆኑን ባወጣው መግለጫ ይፋ ያደረገ ሲሆን ስለ ሞቱ ሰዎች ያለው ነገር የለም።
ዶክተር ቢንያም አስራት በበሽታው ሞት መመዝገቡን ይፋ ካደረጉ በኋላ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው እንደሆነ የቅርብ የስራ ባልደረቦቻቸው ነግረውናል።
ዶ/ር ቢንያም በሆስፒታሉ ውስጥ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አስራር በማስተዋወቅና የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከል በማስገንባት ለአገልግሎት ለማብቃት በዝግጅት ላይ እንደነበሩ ባልደረቦቻቸ ይናገራሉ።
ሆስፒታሉን በበላይነት የሚያስተዳድርው የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በጉዳይ ላይ አስተያየት እንዳለው ብንጠይቅም ሀላፊዎቹ ምላሽ መስጠት እንደማይፈልጉ ነግረውናል።
የጤና ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጂንካ ከተማ “ትክክለኛ ምንነቱ ገና በመጣራት ላይ ያለ እና “የሔሞሬጂክ ፊቨር” በሽታ እንደሆነ የተገመተ በሽታ መከሰቱን ሕዳር 3 በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀው ነበር።
የዓለም ጤና ድርጅት፣ የበሽታውን ምንነት ለማወቅ ለሚደረጉ ምርመራዎች እና በሽታውን ለመቆጣጠር ለሚደረጉ ጥረቶች 11 አባላት ያሉት የአስቸኳይ ድጋፍ ሰጪ ቡድን እና የሕክምና መሳሪያዎችን ወደ አካባቢው መላኩን እንዲሁም ለዚሁ ጥረት የሚውል 300 ሺሕ ዶላር መመደቡን አስታውቋል። [ዋዜማ]
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ