የኦቦ ንጉሡ ጥላሁን ትናጋ ግድነት - በኦቦነት ግንድነት።

እንኳን ደህና መጡልኝ።

የኦቦ ንጉሡ ጥላሁን
ትናጋ ግነት -
በኦቦነት ግድነት።
ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፣
 የወይራ ሥራ ቢጓል እርሾችም መብልን ባይሰጡ
በጎችም ከበረት ቢጠፉ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ
 እኔ ግን እግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤
በመዳህኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።
ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ ቁጥር ፲፰

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
06.03.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።



                                                 የለውጡ ቅልበሳ ማህበርተኝነት  በአጋፋሪ!

እንዴት ናችሁ አዱኛዎቼ። ግርም አለኝ ዛሬ። ኦቦ ንጉሡ ጥላሁን አዲስ ሥም ስለምን እንዳልወጣላቸው በኦሮሞ ትውፊት ግር እያለኝ ነው። ግንድ ስለሆኑላቸው ለኦነጋዊነት ለዛውም ለጃዋርውያን ሜንጫነት። የጃዋርውያኑ የንስሃ አባት አቦ ንጉሡ ጥላሁን ሰሞናቱ ግድ አላቸው እና አንድ ነገር ትናጋቸው እዬተንገዳገደ ፈጸመ።

መራራውን፤ ጎምዛዛውን ሥም ጠሩት … እሬት እሬት እያላቸው፤ ቅፍፍ ቅፍፍ እያላቸው፤ ጭምድድ ጭምድድ እያደረጋቸው …. ምን ይደረግ አባ ገዳ ንጉሡ ጥላሁን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከተሾሞ ልክ በ11ኛ ወራቸው እንሆ በሥማቸው ሲጠሩ ሰማሁኝ። ዳቦ መቆረስ ነበረበት፤ እውነት ቀኑን እኔ ባገኘው እራሱ ቀለበት አስርለት ነበር። አሳንጋላውን ተገደው ሲጎነጩ ማዬት በእጅጉ ይናፍቀኝ ነበር።

እና … እናም ግርም አለኝ ግርም አለኝ። አቦ ንጉሡ ጥላሁን ኢትዮጵያን  „በአገሪቱ“ ዶር አብይ አህመድን ደግሞ „በጠ/ሚሩ“ ነበር ሸብልለው ሲጠሩ የተደመጡት። እሱን ከመሼ ነው እንጂ የሳቸው ቀልብ በጠ/ሚር አብይ ጉዳይ ዘው ብሎ አያውቅም።


ከጠ/ሚር አብይ ጎን መቆም፤ አብሮ ፎቶ መነሳትም በእጅጉ የሚጠሉት አቦ ንጉሡ ጥላሁን ባለፈው ተርሚናል ላይ የመፍንቀለ መንፈስ ባዕላቸውን አዬር መንገድ ላይ በኬክ ቆረሳ ሲያከብሩ ከአለቃቸው አቶ አባ ዱላ ገመዳ ጋር ከርፈፍ ብለው ታዬተው ነበር በጭንቅ እና በመከራ። ከሰሞናቱ ደግሞ እንዲህ ወደ ደቡብ ጉብኝት ነበር ከዛም ከስተሆላ ላይ ገርበብ ብለው ታይተዋል እሱንም በጣር …

#EBC የአድዋ ድል በአል የሁሉም አፍሪካውያን ኩራት መሆኑን የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ተናገሩ፡፡




ከጠ/ሚር አብይ አህመድ ጋር መታዬት እንደ መርግ፤ እንደ ክፉ ዕጣ ፈንታ የሚቀፋቸውን ያህል ሥማቸውን ለመጥራትም ያን ያህል የሶቆቃ ጥሪ ነበር የሚሆንባቸው ዛሬ ጠ/ሚሩ በሥማቸው ሲጠሩ ሰማሁኝ ጃዋርውያኑ ኦቦ ንጉሡ ጥላሁን። ታሪካዊ ቀን ስለሆነ ሊንኩ ይኸውና።

Ethiopia: መረጃ - / አብይ ይህን 5 ቀን ምን እያደረጉ ነው? | ጎንደር...


የኦቦ ንጉሱ ጥላሁን የዶር አብይን ሥም መጥራት ይህ ለእኔ ሠበር ዜና ነው። ያው እዬጨነቃቸውም ቢሆን በታች ሆነው ያው እዬጎረጎሩና እዬሰረሰሩ የተፈጠሩበትን ተልዕኮ መፈጸም ግድ ይላቸዋል። ተልዕኦኳቸው በ ኢትዮጵያ ላይ የ ኦሮምን ኢንፓዬር አደላድለው መጫን ነው። ያው ትንሽ እንዳይርቃቸው ግን መንጠራራት ግን ግድ ይላቻዋል። 

አንገጠው ትንሽ ለማዬት ቢገደዱም አስረንሃል ጠ/ሚር የሚለውን ድርሳን በመድገም መሆኑ ግን መዘንጋት የለበትም። እንዳሹት ነው ያን ብጡል የሚሊዮን ተቀባይነት አፈር ድሜ ያስጋጡት። አርበኛ ናቸው ለ ኦነግ ጀዋርውያን ... ክርስትናንንም ደህና አድርገው ነው የደለቁት .. የፈጫጩት ... 

የብአዴን መከራም ከዚህ ጋር ነው የሚታዬው። ከሳጅን በረከት ወደ ኦቦ ንጉሱ። ለብአዴን ናዳ ናቸው እኒህ ሰው። የብአዴን ሁለመና ውልቅልቁን አስወጥተው ለአዲስ ባርነት ለመዳረግ ፍጹም የሆነ ትልዕኮ የተሰጣቸው። በብአዴን ስብሰባ ላይ ኦዴፓም ኦነግም ቲም ጃወርም አለፍ ሲልም ባህር ማዶም ያለ መንፈስ አብሮ በልብ ወኪሉ አማካኝነት እንደሚሰበሰብ ብአዴን ልብ ሊለው ይገባል። ሊንክ ናቸው እሳቸው። 

መሰብሰብ ብቻ ሳይሆን ኦዴፓ/ ኦነግ/ ቲም ሜጫ ጃዋር በሚፈለገው አቅጣጫ ቡድን በማደራጀት አቅጣጫውም ይቀዬሳል። ብአዴንን ኦዴፓ አያምነውም። ግንኙነቱ የግብር ይውጣ ስለመሆኑ ዘመን ጥሩ ነው ሚሰጢሩን ገማናውን አደባባይ አና ብሎ እያዬነው። መሳሪያው ደግሞ አቦ ንግሡ ጥላሁን ናቸው። 

በክህደታቸው ልክ ነው ብአዴን ውስጡን እዬተሸረሸረ ያለው። የቆሞስ ጌታቸው ተስፋዬ ሰማዕትነትም ይኸው ነው ዕድምታው። አንበሴ ቢኖሩ ይህን መሰል እንቆቅልሽ አይኖርም ነበር። ያ ነፍስ ቆቅ የነበር መሆኑ አሁን ነው የተከሰተው።    

ይህ የጭቃ ሾኽ ድርብ እና ምድር ገማና ብአዴን ግርባው አይግባው አይታወቀውም … እያለቀ ስለመሆኑ።  ያልታደለው ብአዴን፤ አመድ አፋሹ ብአዴን አሁን በድርብ በሳንጃ በውጋት በግራ በቀኝ ተሰቀዞ ተይዟል። መፈናፈኛ አጥቷል። መቀሌ እና አዳማ ጦራቸውን ስለው ቆልምመው የፋሲካ ዶሮ ለማድረግ በሽታሽቶ እዬወቁት ነው። የኦሮማራ ዘመን ምእራፍ መከደን እንዲህ በእንቆቆ። ያሳዝናል ... 


እሱን መቅጣት የሁሉም ፍላጎት ነው ግን በስልት እና በጥበብ። ኦዴፓ/ ኦነግ/ ቲም ጃዋር በስልት ነው፤ ህወሃት ግን በ አደባባይ ነው። ብአዴን ገና ነው መከራው አላለቀም። እነ አቶ መላኩ ፈንታ ተገፍተው በራሱ የውክልና ሥያሜ እነሆ በቀጥታ በኦቦ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በስል እዬታረደ ነው … የአማራ የህልውና ተጋድሎም ለዚህ ለጃውርውያን ተልዕኮ ተሸልሟል …  
                                          የአቶ ንጉሡ ክህደት መሰረት።

ሌላው በኢትዮጵያ አንድነትም እንዲህ አይነት ጣምራ ተልዕኮ ያዘሉ ግራጫማ ሰብዕናዎች እጅግ አስጊ ናቸው። አሁን ደግሞ ባለሟል ሆነዋል ለመካከለኛው አፍሪካ ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ። ይህ ሰብዕና አንድ ጊዜም ገልጨዋለሁን ለፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂም የልቤ የሚባል ነው። ግራጫማ ሰብዕና ክፍላቸው ናውና።

አሁን የሆነው የኢትዮጵያ ሆድ ዕቃው መዳፋቸው ላይ ጉብ አለ ለኦቦ ንጉሡ ጥላሁን። የኢጎ ገብያተኛ ናቸው እሳቸው። የኦነግ ሥምምነት ዶር ለማ መገርሳ ወደ ኤርትራ ሲያቀኑ ለአማራው ድርጅት ለአዴሃን ለግርባው ብአዴን ግን ውክል አካሉ አዳራዳሪው  ከዶር ገዱ አንዳርጋቸው አባ ገዳ ንጉሡ ጥላሁን ነበር በሰውሩ መንግሥት ፈቃድ የተሰጠው። ቀጣዩ የገዱን ቦታ ለመስጠት የታሰበው ለሳቸው ነው፤ የ አቶ ደመቀ መኮነን ከሥልጣን ለማስለቀቅ የነበረው ጫናም ሚስጢሩ ይሐው ነው። አቶ ንጉሡ ኤርትራ በሄዱበት ያን ጊዜ በጊዜያዊ በቤተ መንግሥት እስር ቤት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ነበሩ።

የሆነ ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝብ እኒህን ሰው በጥሞና፤ በማስተዋል፤ በበዛ ተመስጦ ይከታተላቸው ዘንድ ላሳስብ እወዳለሁኝ።

በአቅማቸው፤ በችሎታቸው ላይ እኔ ጥያቄ የለኝም። እንዲያውም ዳግሚያ አባ ኮስትር እኮ ነው እምላቸው። እኔ በልባቸው፤ በህሊናቸው፤ በተልዕኳቸው አሽዋነት ጉዳይ ነው አትኩሮቴ እንጂ በተፈጥሯቸውማ ዳግሚያ ወላጅ አባቴን አበይን ቁርጥ ነው ከማጠራቸው በስተቀር። አባቴ ረጅም ነበር። ከአብይ አንድም የቀረ ነገር የለም ባህካል አበይን ነው የሚመስሉት። ግን ምን ይሆናል ሃሳባቸው ጉድጓድ ነው … ለኢትዮጵያም የመከራ ሌሊት ናቸው።

ኢትዮጵያ ልታጠናቸው የሚገባ ጉዳኛ ፍጥረት ስለሆኑ በአትኩሮት ማዬት ይገባል። በዬዘመኑ ኢትዮጵያ በራሷ በተፈጠሩ ሰላዮች ነው ጥቃት የሚደርስባት። የዚህ ለውጥ ፍዳም ያለው በዚህ በታመቀ ገመና ውስጥ ነው።

ትናንት ፕ/መስፍን ወ/ማርያም ለውጡ የተቀለበሰ ይመስለኛል ሲሉ ተደምጠዋል። ገና ትናንት ነው እኒህ ሊቀ - ሊቃውንት ይህን የሚሉት። እኔማ ሰሚ አጣሁኝ እንጂ የተቀለበሰውም እማ የሐምሌው የጠ/ሚሩ የስሜን አሜሪካ ጉዞ ነበር ሐምሌ 19 ቀን። በህልሜም ወንበሩ ባዶ ሆኖ ነው ያዬሁት። ብዙ ጹሑፍም ጽፌያለሁኝ።

ብዙ ድንብልብል ነገሮች አሉበት። የሰኔው 16 ቀን የድጋፍ ሰልፍና ጦሱ፤  የቆሞስ ስመኛው በቀለ ህልፈት፤ የቆሞስ ጌታቸው ተስፋዬ ሰማዕትነት የዚህ ሁሉ ቅምር ውጤት ነው።

ሌላም የአገር ውስጥ ቀውስ በሽፍት ህወሃት ዛል ሲል ጠላፊው ቡድን ደግሞ ቅንብሩን ይጀምራል። በፈረቃ ነው የሚካሄደው ጥፋቱ ሆነ ንደቱ፤ አንዱ እሳት ሲለኩስ ሌላው ፈንጅ ይቀብራል፤ አንዱ ሲያፈናቅል ሌላው ዘቅዝቆ ይሰቅላል … እንዱ ጦርነት ሲያውጅ ሌላው አፍኖ ይወስዳል … ወይንም ያግታል …

በግራ በቀኝ በጠላፊ እና ሥልጣን ቀረበኝ ባለው ናዚ ባለ ጣማራ ቡድን አገር እየታመሰ የድሃ ነፍስ በግፍ እዬተጨፈጨፈ፤ የድሃ ኑሮ በግሪደር እዬታረሰ ነው ያለው። ድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶችም እንሆ ፍዳቸው ጠንቶ በግሪደር በአራስ ቤት ይታረሳሉ። ልጆችም ሜዳ ላይ ፈሳዋል።

የሰው ልጅ ለማሰብ የተሰጠውን አዕምሮ በቅጡ ስለማይጠቀምበት ነው እንጂ ቢያስብ እና ጉዳዩን ከልቤ ብሎ ቢያው ተወራራሽ ተያያዥ ነገሮችን በማጥናት ከፍሬቸው ከሥራቸው ማዬት ይቻለዋል ነበር። 

ይህን ሲያውቅ ደግሞ ዥንጉርጉር ፍላጎቱን ተግ አድርጎ፤ የተቆለለበትን ኢጎ ደርምሶ ስለሚቆምበት ብትን አፈሩ ያስብ ነበር እንደ ኩርድሾቹ የጨው ዘር ከመሆኑ በፊት … ለነገሩ ሁነናል እኮ አማራ ምን አለሁ ይላል … አሁን ደግሞ ጋሞ እና ጉራጌ ተደረቡ ለመከራው ተብለዋል …  በጃዋርውያን እና እና በ ኦነጋውያን ግን ኦቦ ንጉሡ ጥላሁን ለዬትኛው ሊሆኑ ይሆኑ? እንደዘመኑ ... 

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ፤ መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።