ልጥፎች

ለአቶ አዲሱ አረጋ ማስተባበያ ጉልበታም ምላሽ።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ለአማርኛው ደግሞ አስተርጓሚ  አንሻም። ትንሽ እስኪ ደብቁኝ በሉ! ለቅጥፈት ድፍረት አያዋጣም   እና! „አቤቱ በአንተ ታምኛለሁ እና ጠብቀኝ።“ መዝሙር ፲፭ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  04.03.2019  ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ምነው ዛሬ ነፍስ ምርጥ ኦሮሞነት ሆነሳ? እያለቀስኩኝ! ይድረስ ለአቶ አዲሱ አረጋ እንደ ተለመደው ዛሬም ተመልሼ መጣሁኝ፤ ቅጥፈት መሸፈኛ ኮባ ስሌለው። የትርጉም ግድፈት የለበትም። ናዚያዊ ጉዞው ወንጀል መሆኑም እወቁ … ለውጡ መቀልበሱንም ሀምሌ ላይ የጻፍኳቸውን ማንበብ ነው። ከቀልቦሾቹ አንዱ እርሰዎ መሆነዎትን ዛሬ ሳይሆን ትናንት ተናግሬያለሁኝ።   የስሜን አሜሪካ ጉዞ ሞት ነበር ድግሱ እና ስምምነቱ፤ ያ አለመሆኑ ሲታወቅ እገታ ነበር ። ይህን በአንክሮ በተደሞ በሚገባ ጽፌዋለሁኝ። ዶር አብይ አህመድ እሰረኛ ስለመሆናቸው እኔ አሳምሬ አውቃለሁኝ። የሚደንቀው ምንም እንዳልተፈጠረ ወጥተው የሞገቱት ደግሞ ዕውቁ ተዋዳጅ ሊሂቅ "አክ ወሬ" በሚል ፕ/ አለማርያም ነበሩ። ትልቅ የታሪክ ግድፈት ነበር። ቢያንስ ሊሆን ይችላል ብሎ መጠርጠር ከአንድ የፖለቲካ ሊቀ ሊቃውንት የሚጠበቅ ነበር።  ወደ ቀደመው ምለስት ሳደርግ እሳቸውን ሸኝቶ በለማው የ አብይ ልሁቅ መንፈስ መንፈስ ልታስቀምጡ ያሰባችሁት ሌላ መንፈስ ነበር፤ በፈጣሪ እርዳታ ያ ሳይሳካ መቅረቱን ስታውቁ፤ እገታውን አዬን፤ እሰረኛ ነበሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድ። ከዚያ አና ብላችሁ ዓላማችሁን ተያያዛችሁት፤ በቀልና ጩቤ … በግርዶሽ … አቶ አዲዱ እርሰዎ ሲጀመርም ብጣቂ ኢትዮጵያዊ ስሜት የለወትም።  በሽንገላ ኮሶ ነው የእርሰው ቃለ ምህዳን ማደ

አስደማሚ ታሪክ /ከጸሐፊ መስፍን ማሞ/

ምስል
አስደማሚ ታሪክ “እግዚአብሔርን፤ --- አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ።  መዝሙር” ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፪ መስፍን ማሞ ተሰማ ሠላም ለናንተ ይሁን! ኢትዮጵያ የአውሮፓን አይሁዶች ከሂትለር እልቂት ታድጋለች! (ትርጉም) የኢየሩሳሌም ፖስት (The Jerusalem Post) በ27/1/19 ባስነበበው ዕትሙ ይዞት የወጣው ታሪክ ‘ርዕስ’ ነው - ከላይ የቀረበው። ይዘቱ እንዲህ ይከተላል።  በአውሮፓ በናዚዎች የሚካሄደው ዕልቂት ጡዘት ላይ በደረሰበት ኦገስት 1943 (እኣአ) ኢትዮጵያውያን አይሁዶች (ፈላሻዎች) በመሪዎቻቸው አማካይነት ንጉሠ ነገሥት ሃይለ ሥላሴን በመቅረብ አስደማሚ የሆነ ጉዳይ አቀረቡላቸው። የአውሮፓ አይሁዳውያንን ኢትዮጵያ በስደተኝነት እንድትቀበልና እነሱም በፈላሻዎች መኖሪያ መጠለያ እንዲያገኙ ንጉሡ እንዲረዱ የሚል ነበር ጥያቄያቸው። በዋርሶ (Warsow) የጌቶ (Ghetto) አመፅ ከተካሄደ ሶስት ወር በሁዋላና የናዚዎች ማሰቃያዎች አራቱ የኦሽዊትዝ ማቃጠያዎች (Auschwitz crematoria) በሥራ ላይ ከዋሉ ሁለት ወር በሁዋላ የዛሬው ጄሩሳሌም ፖስት በቀድሞው መጠሪያው ፓልስታይን ፖስት (Palestine Post) ኢትዮጵያ አይሁዳውያን ስደተኞችን መቀበሏን የሚያትት ዘገባ ይዞ ወጣ። ኦገስት 8/1943 የታተመው ይህ ጋዜጣ ሲያብራራ “የአይሁዳውያንን ወደ ኢትዮጵያ የመሰደድ (Jewish Immigration to Abyssinia) አማራጭ በሎንዶን የሚገኙት የኢትዮጵያ ሚኒስትር ከአቶ ሃሪ ጉድማን (Harry Goodman) እና ከእስራኤል የአጉዳቱ ዶ/ር ስፕሪንገር (Dr. Springer of Agudath) ጋር ተወያይተዋል” ብሏል።  “የአውሮፓ አይሁዳውያንን በፈላሻዎች መንደር እንዲጠለሉ ለማድረግ የፈላሻ መ

እነ አያልቅበት ብአዴኖች ደግሞ ምን እያሉን ነው?

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  እነ አያልቅበት ? „የሞት ጣር ያዘኝ“ መዝሙር ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  04.03.2019  ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።                                                 አሁን ደግሞ ከመጋቢት 24. ቀን 2010 ጀምሮ                                                   በኦህዴድ ሎሌነት አዲስ መጸሐፍ ይጻፍለታል ።                                                         ሰኔል ላይ ለሽ ብሎ ለተኛው ብአዴን። መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=LSgTOyi8uCk&t=3s " ለአማራ ሕዝብ ባሪያ እንሆናለን። " አዴፓ ·        ተ ናግሮ አናጋሪ ነው ብአዴን … ድንቄም! ብለናል ብአዴን ለአማራ ህዝብ ባሪያ እሆናለሁ የሚለውን ተረት ተረት። ለኦነጋውያን ባሪያ እንሆናለን ቢባባል ያምራል። ኦዴፓ // ኦህዴድ ለውጥ ከታባለበት ቀን ጀምሮ የኦሮሞ ሙሁራንን፤ የኦሮሞ ጸሐፍትን፤ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን፤ የኦሮሞ ብለጎሮችን፤ የኦሮሞ የሲቢክስ ድርጅቶችን፤ የኦሮሞ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችን፤ የኦሮሞን አክቲቢስቶችን አቅም ያላቸውንም የሌላቸውንም፤ በአገር ውስጥ እና በውጪ በትጋት፤ ባልተቋረጠ ትትርና በዶር ለማ መገርሳ የቅድሚያ ቅድሚያ ተስጥቶት ሲሳረበት ባጅቷል። ብአዴን ደግሞ የፌድራል መንግሥቱን ጫና ተሸክሞ ግርባነቱን ሲከውን ከራርሟል። ይህም ብቻ አይደለም የኦሮሞ አክቲቢስቶች፤ የኦሮሞ ጸሐፍት፤ የኦሮሞ ደም ያላቸው ሁሉ በተገኘው የሃላፊነት ቦታ ሁሉ በክብር በልዕልና ቦታ ሲሰጣቸው አያሆይ ብአዴ