እነ አያልቅበት ብአዴኖች ደግሞ ምን እያሉን ነው?

እንኳን ደህና መጡልኝ።
እነ አያልቅበት?

„የሞት ጣር ያዘኝ“
መዝሙር ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፬
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
 04.03.2019
 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
                                               አሁን ደግሞ ከመጋቢት 24. ቀን 2010 ጀምሮ
                                                  በኦህዴድ ሎሌነት አዲስ መጸሐፍ ይጻፍለታል 
                                                     ሰኔል ላይ ለሽ ብሎ ለተኛው ብአዴን።
መነሻ።

"ለአማራ ሕዝብ ባሪያ እንሆናለን።" አዴፓ


·       ናግሮ አናጋሪ ነው ብአዴን …

ድንቄም! ብለናል ብአዴን ለአማራ ህዝብ ባሪያ እሆናለሁ የሚለውን ተረት ተረት። ለኦነጋውያን ባሪያ እንሆናለን ቢባባል ያምራል። ኦዴፓ // ኦህዴድ ለውጥ ከታባለበት ቀን ጀምሮ የኦሮሞ ሙሁራንን፤ የኦሮሞ ጸሐፍትን፤ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን፤ የኦሮሞ ብለጎሮችን፤ የኦሮሞ የሲቢክስ ድርጅቶችን፤ የኦሮሞ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችን፤ የኦሮሞን አክቲቢስቶችን አቅም ያላቸውንም የሌላቸውንም፤ በአገር ውስጥ እና በውጪ በትጋት፤ ባልተቋረጠ ትትርና በዶር ለማ መገርሳ የቅድሚያ ቅድሚያ ተስጥቶት ሲሳረበት ባጅቷል። ብአዴን ደግሞ የፌድራል መንግሥቱን ጫና ተሸክሞ ግርባነቱን ሲከውን ከራርሟል።

ይህም ብቻ አይደለም የኦሮሞ አክቲቢስቶች፤ የኦሮሞ ጸሐፍት፤ የኦሮሞ ደም ያላቸው ሁሉ በተገኘው የሃላፊነት ቦታ ሁሉ በክብር በልዕልና ቦታ ሲሰጣቸው አያሆይ ብአዴን የሚሰጠውን ትእዛዝ ለጥ ብሎ ሰግዶ ይቀበልና የፌድራሉን እንግዶች በመቀበል እና በመሸኘት የወርቅ ካባ ሲገዛ እና ሲሸልም ነው የባጀው።

ሌላው ቀርቶ በአዲስ አመት ዋዜማ በሚሊዬነም አዳራሽ አንድም የአማራ ድርጅት ዕውቅና ሳይሰጠው እንደዛ የአማራ ሊሂቃን በይፋ እና በአደባባይ ሲገለሉ ጸጥ ረጭ ነበር ያለው አመዱ ቡን ብሎ አይዋ ብአዴን እንግዳ ዶሮ መስሎ ... እንጉልች... 

ከሰሞናቱ የተቃዋሚ/ የተፎካካሪ/ የተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች ጉባኤ ላይ ገላጭ ሆነው የቀረቡት እነማን እንደሆኑ እንኳን ማስተዋል የተሰናው ብአዴን ሊከሰትለት አልቻለም። አብን እራሱ ጭላጭ ሆኖ በር ጠበቂ ሲሆን ሰፊውን አማራ እወክላለሁ የሚለው ብአዴን የተተኮሰበት ሚዲቋ ነው የሆነው። እንቅልፍ!

እንደገና ብአዴን ከእነ አቦ ሌንጮ ለታ ፤ ከእነ ዶር አረጋይ በርሄ የልምድ ተመክሮ ተማር መባሉ ምን ያህል እንደተናቀ አያስተውለውም። መረጋገጫ¡

የብአዴን ርእሰ መሰተዳደር ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ተቀምጠው አቶ ንገሡ ጥላሁን ኤርትራ ድረስ ሄደው አዴሃን ሲያደራድሩ የትኛው ፕላኔት ላይ ይሆን የነበረው አይዋ ለሽይበሉ ብአዴን? ለውጡ እንዳይቀለብስ ይሆን? ለውጡ እኮ ከሀምሌ 19ቀን እኩለ ሌሊት ጀምሮ ተቀልብሶ ነው ቆሞስ ኢንጂነር ስመኛው በቀለ ግብር የሆኑት። በዚህችም ትንፍሽ አይልም አይዋ ብአዴን … በጎኑ ይሁን በደረቱ ለሽ ብሏለኝ … ሁለት ዕንቁዎችን አስከሬን ተሸክሞ ድርጭት ... ግራቀኝ ይላል ..

ሌላው ቀርቶ በቆሞስ ኢንጀነር ስመኛው በቀለ በሳቸው ቀብር ሥርዓት አድናቂዎቻቸው አፈር ለማልበስ በመዲናዋ ፍትህ ሲነፈጉ፤ ሲደበደቡ የት ነበር አይዋ ለሽይበሉ?

ለመሆኑ ቆሞስ ጌታቸው ተስፋዬን ህይወት ማነው ያጠፋው? ተከድኖ ይንተክተክ። የደመ ከልብ አርበኞች ነፍስ ለአቤቱ ለልሙጡ ብአዴን ምኑ ነው? የቆሞስ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አባት ሸንቦቂት ላይ በምን ሁኔታ ላይ እያሉ ነው አገር ምድሩን እነሱ ካባ እና ተክሊል ሲደፉ የባጁት? ለመሆኑ ነፍሳቸው አለን ብአዴኖች? ለደላው የሚኪና ትዕይንት ሲያሳዩ ... 

በምን ሂሳብ እና ቀምር ይሆን አቶ አሰማህኝ አስረስ የብአዴን አንደበት ሆነው የተሾሙት? መልስ አላቸውን?ስለምን ይሆን ብአዴን ተወካይ አልባ የሰሜን አሜሪካ የጠ/ሚር ጉዞ የተደራጀው? አለን ከዚህ አይሉንም ነበር? ለነገሩ ኦዴፓ ብአዴንን ቢጠዬፈው ይገባዋል? ለራሱ ክብር ልጥ ሲገምድ ስለሚውል ወይንም ቹቻ … ሲያርስ … ላንቁሶ!

ስለምን ይሆን የአንባሳደር ካሳ ተ/ብርሃን ቦታ ለአንባሳደር ፍጹም አረጋ የተሰጠው? አማራ የአሜሪካ አንባሳደር መሆን አቅቶት ነውን? ሊቀ ሊቃውንት አማራ አጥቶ?
ለመሆኑ  ነፍሱ አለችን የብአዴን? ስለምን ይሆን ግዞተኛው ሚ/ር ዶር አንባቸው መኮነን የጠ/ሚር ቢሮ የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው እሳቸው  እያሉ የአሜሪካ ባለሙሉስልጣን አንባሳደር ሆነው የተሾሙት አንባሳደር ፍጹም አረጋ በዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ላይ በድርብ ዕውቅና ሲገኙ የብአዴኑ ቀንዲል ዶር አንባቸው መኮነን ሳይገኙ እንዲቀሩ የተደረጉት? ይህ ይጎረብጠዋል ወይንስ ይሰነጥረዋል ወይንስ ሞዝበልድ ሆነለትን ጥቃትራቱ ብአዴን?

ስለምን ይሆን የጀርመን ጉዞ በኦዴፓ ሥ/አ/ ኮሜቴ አባላት ብቻ  እንዲሆን የተደረገው? የሚነሱት የሚሾሙት ሁለቱም የጠ/ሚር ቢሮ የጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ እና አቶ ሺመለስ አብዲሳ እንዲገኙ የተደረጉት በዬትኛው ቀመር ነው ብአዴን ሰው ጠፍቶ ወይንስ  የአቶ አባ ዱላ ገመዳ ፈቃድ ሳይሆን ቀርቶ?

ስለምን ይሁን ትናንት ሚኒሶታ ላይ ዶር ለማ መገርሳ ቆንሲላ ጽ/ቤቱን መርቀው እንዲከፍቱ የተደረገው? በምን አግባብ? በምንስ አግባብ ነው ለመከላከያ 7ኛ ባዕል ዶር ለማ መገርሳ ተናጋሪ ሆነው የተገኙት? እሳቸው የኦዴፓ መሪ ናቸው? ኦነግን ኤርትራ ሄደው ያደራደሩ እሳቸው ናቸው? አዴሃን ደግሞ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ከላይ እንደጠቀስኩት በመሃል የወለሌ ገበታ ላይ የሚገኘው አቋም የለሽ ብአዴን እነቀሩ፤ ስንዴውን አስረከበው እነሱ ገላባውን ተሸከመው … 

መጀመሪያ ብአዴን ራሱን  ከኦህዴድ / ኦዴፓ ባርነት ነጻ ያውጣ?
ስለምን ይሆን የአማራ የብዙሃን ሚዲያ አዲስ አባባን በይፋ „ፊንፊኔ“ ብሎ እንዲዘግብ የሚደረገው? የትኛው ፕላኔት ላይ ይሆን ብአዴን ያለው? 

"የት እንግባ?" ቤታቸው የፈረሰባቸው የለገጣፎ ነዋሪዎች


ለመሆኑ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከተመረጡ ጊዜ ጀምሮ የትኛውን የአማራ ሊሂቅ ነው ሥም ሲጠሩ ተጠምደው የሚያውቁት? ኢትዮ አፍሪካውያኑን ፕ/ ማሞ ሙጬን እንኳን ሥም አልደፈሩም? አይደፍሩምም።

በምን ይለያል ጋዜጠኛ አክቲቢስት እና ጸሐፊ ሙሉቀን ተስፋው እና አክቲቢስት ጃዋር ማህመድ? ለሁለቱ የተደረገው አቀባበል በፌድራል ደረጃ እንዴት ነበር? የት ነው ያለው ብአዴን? ደም አለውን ብአዴን? ወንዶቹ እነ ለማ መገርሳማ የልባቸውን በሚፈልጉት ልክ ግልብጥብጥ አድረገው እዬከወኑ ነው። ወንዳታ!

ያ ሁሉ ሸር ጉድ እና እነ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በቀባባል ላይ በኦነግ አርማ በተንቆጠቆጠው ሚሊዬነም አዳራሽ ሲገኙ ብአዴን ምን አለ? ምን ወሰነ? ምን ተናገረ? ለመሆኑ ብአዴን ኢትዮጵያዊ ነውን ወይንስ ኦነጋውያን ጃዋርውያን?


ብአዴን ባልረጋው እና ባልሰከነው የግዛት ክልሉ ለማን አምኖ ነው ሰጥቶ ነው ሽርሽሽር ልቅምቅም ብሎ ወደ አሜሪካ የሄደው? ለአማራ ህዝብ አስቦ? እኛም ፊትም የተረሳን ነን አሁንም በድርብ እዬተረገጥን ነው።

እስኪ ስሜን አሜሪካ ሽርሽር የተገኘው ትርፍ እና የ90 ሺህ ህዝብ መፈናቀል በምን ሂሳብ ሊያወራረድ ይችላል? ዶር ደብረ ጽዮን እኮ ሽርሽር አላማራቸውም? አካባቢያቸውን ነው እያጠናከሩ የሚገኙት።

እራሳቸውን ስላስከበሩ እሰከ ከተማቸው ድረስ እዬተሄደ ባዕላቸው ይከበርላቸዋል። ጠያቂ ጋዜጣኛም ሲኖር ከሥፍራቸው ሄዶ ነው የሚያነጋግራቸው፤ የአሽንዳዬ ባዕል ቀዳማዊት እመቤት ነበሩ፤ የአደዋ ባዕልም ክብርት ፕሬዚዳንቷ ነበሩ። ማን ይደፍራቸዋል እነሱን። ወንዳታ!

ለዛውም ለአብይ መንፈስ ቢሆን ምንም አልነበረም ለአቶ አባ ዱላ መፍንቀል መንፈስ፤  ለአቶ ንጉሡ ጥላሁን ጃዋርውያን አጤነት ይህን ያህል ማረጥረጥ? ይህን ያህል ማረግረግ ለተቀለበሰ ለውጥ? ምን አግኝቶ ብአዴን ምንስ ሊቀርበት? ስለምን ኮራ አይልም ብአዴን? በምርኮኛ መንፈስ እዬተመራ ስለመሆኑ አይረዳውም? ባርነቱ ለምርኮኛ መሆኑ አይገባውም? መቼ ነው ሰው መሆን የሚችለው ብአዴን?

ለነገሩ የጽዋ ማህበር ነን ብሏል እኮ¡ ሥልጣን አንፈልገም ብሏል። መሳቂያ! ለምን አይፈርስም? ደግሞ የሚገርመው የአማራ ሊሂቃን አልረዳነም ይላል? እስኪ ለፈላስማው ዶር ዳኛቸው አሰፋ እና ለረ/ ፕ አባባው አያሌው ምን አስደረገ? የአማራ ብሄርተኝነትን እንዲያርግቡ ከማስደረግ በስተቀር፤ ለነገሩ አሁን ኦሮምኛ የፌድራል ቋንቋ እንዲሆን እዬተሰራበት ነው ተብሏል ለዚህ ዶር/ ዳኛቸው አሰፋ ታጭተው ይሆናል። ይህን እዬሠሩ ይሆናል … ለዚህ ለዚህ ነው የአማራ ሊሂቃን ለብአዴን የሚስፈልገው … በ27 ዓመት አንዲት ነፍስ ያላት የአማራ ሊሂቅ ማውጣት አልተቻለም …  

በቀጣይ ኦሮምኛ የፌድራል ቋንቋው ይሁን ብሎ ላይ እና ታች ያረግርግ እንደ ለመደበት ብአዴን። ብዙ ሰው በዶር ለማ መገርሳ እያዘነ ነው። የተፈጠሩበትን ነው እዬሠሩ የሚገኙት። የኦሮሞ መሪ ናቸው እያንዳንዷን ሰከንድ የኦሮሞን የመግዛት አቅም እያሳደጉ ይገኛሉ። ብአዴንን የመሰለ ባሪያ ሎሌ ሲገኝ አይደለም ቀን ሌት ቢተጉ አይፈረድባቸውም። ጥገት የዘመን ... 

ይህቺ ጊዜ አትገኘም፤ እንዲያ ሲል ደግሞ ከህወሃት ጋር በጎን ድርድር አድርገው ቂጡ የወለቀ ዋንጫ አድርገው ቁጭ ያደርጉታል ብአዴንን  … አሁን ስትራቴጂክ ወዳጅ ሲዳመኛ ሆኗል። ኤርትራን ነው ቁልፋቸው አድርገዋል ብልሆቹ የዋዛ!

ልባቸው ሰፊ፤ መንገዳቸው ረቂቅ፤ በብቁ የተሰናዱ ዓላማቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ የተሰጣቸውም ናቸው ኦዴፓዎች … አማራ አርማጭሆ፤ ላሊበላ፤ በለሳ ኦህዴድን አገዘ በሙሉ አቅሙ፤ አብረው ከህወሃት ጋር እስኪባቀቸው ደልቁት አማራን በማተቢስነት፤ ሲያልቅ አያምር ሆነ ከህወሃት ጋር ገጭ ገው ሲመጣ ደግሞ ቢከፋኝ ብመለስ ብለው አማራ ነፍሳችን አሉ፤ እኛም ጅሎች ዘመን የማያስተመርን እናት ኢትዮጵያ ሲባል ወለል አልንላቸው፤ አሁን ደግሞ እንደልማዱ ኦህዴድ አማራን በፎርፌ ገፍትሮ ከሲዳማ ጋር ፍቅር በፍቅር ሆኗል … የአባ ዱላ ገመዳ ድርጅት  …

ገና ክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜል ይወዳደራሉ ተብለው ከሦስት ክልሉ እዬተሸነሸነ ነው ራሱ ደቡብ። ያ ሁለተኛው የምርጫ ሂደት እኮ ለጥቂት ነው ላጥ ሊል ሥልጣኑ ያመለጠው፤ ስለሆነም በስልት የደቡብ መንፈሱ ወጥነቱ ታውኳል። ሲዳማን ከጎኑ አስልፏል ኦዴፓ።

ለባርነቱ ለሎሌነቱ ለግርባነቱ ደግሞ ብአዴን አለለት። ብአዴን የትም አይሄድም ካኖሩት የሚገኝ ትክልድንጋይ፤ እራሱን አዋርዶ ሰፊውን የአማራ ህዝብ እያስጠቀቀጠ ይገኛል።
ብሄርተኝነት የአማራ ጎላ አለ እባካችሁ በልክ አድርጉት ብለው ሊሂቃኑን የተማጸኑት ጠ/ሚር አብይ አህመድ እነሱ ደግሞ ዴሞግራፊ ለመለወጥ ሌት እና ቀን ይባትላሉ። የኦሮሞ ቆንሲሊ ጽ/ቤት በአሜሪካ እስከመክፈትም ደረሰዋል። ከዚህ በላይ ባርነት ከዚህ በላይ ሎሌነት ምን ይምጣ? ይህ ደግሞ ክብር ተብሎ ሊወደስ ይሆን ለብአዴን? ኢትዮጵያዊነት እራሱ ውስጡ እዬታመመ ነው … ፈዋሽ ይሻል … አካሄዱ አላምር እያለ ነው …

Ethiopia: Reyot - ርዕዮት የአዲስ አበባንና ዙርያዋን የህዝብ ተዋጽኦ Demography ለመለወጥ እየተሰራ መሆኑን አቶ ለማ መገርሳ አምነዋል፡፡ …


ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከተመረጡ ጀምሮ ሌላ ሥራ የለም የአማራ ሊሂቃን ኢትዮጵያዊነትህን አትልቀቅ በማለት ሰፊ ማዋለ ንዋይ አስፈስሰው ሥራ ፈት ተግባር  ሲከውኑ በሳቸው በሚመሩት ድርጅት ግን አንዲትም ቀን ስለ ኢትዮጵያዊነት ሊሂቃኑ ተስብስበው አይታወቅም። እንዲያውም የነፍጠኛውን ከተማ ዲሞግራፊ በመለወጥ ዘመነ የኦሮሞ ኢንፓዬርነት አና ብሎ ጎልቶ በሁሉም መስክ እዬተደመጠ ነው … የሚገኘው።

አማራ በባዕቱ መቀመጫ አጥቶ 90 ሺህ አማራ ተፈናቅሎ አለን ለማለት ብአዴን አይቻልም። ፈጽሞ ሬሳነት ነው። በሬሳነት ላይ ተሆኖ፤ ሙት መሬት ላይ ተሁኖ አሁን ደግሞ ፉከራ ጀርባን መላላጥ ብቻ ነው ትርፉ። በምን አቅም ሁሉንም ቦታ እኮ አሳልፎ ሰጥቶ ፍርፋሪ ልቅምቃሚ፤ ቅንጥብጣቢ ለመኝ ነው ብአዴን የሆነው። 

…  አሻም ይበል እና እስኪ ያሳይ … የተሰጠውን ሁሉ አቤት ወዴት እያለ ሲያስተናግድ ነው የባጀው … ጀግናው ዶር ለማ መገርሳ ደግሞ ለኦሮሞ ልዕልና ሌት እና ቀን ይባትላሉ የቀራቸው ማሳ ፈጽሞ የለም …

ብአዴን የአቶ ንጉሱ ባሬያ እንጂ የአማራ ህዝብ ባሪያ አይደለም። ብአዴን የምርኮኛው የስውሩ መንግሥት መሪ የአቶ አባ ዱላ ገመዳ ሎሌ እንጂ የአማራ ህዝብ ሎሌ አይደለም፤ ብአዴን ከአቶ ሌንጮ ለታ ነው ልቅምቃሚ ለማኝ ነው የሆነው። ማፈሪያ! … ጊዜም ዘመንም የማያስተምረው … አስጠቂ …

ክምታደርገው ይልቅ የምትናረው ብዙ ርቀት ይጓዛል (ይኄይስ አእምሮ)
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሰራተኞች በደረሰባቸው የዘር መድሎ ተማረው መፍትሄ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ነው (ከተቋሙ የተላከና ጠቃሚ ስለሆነ በትዕግስት ይነበብ)

እስኪ በጉሙሩክ መስሪያ ቤት አቤት የሚሉትን? በአዬር መንገድ ያንት ያለህ የሚሉትን? በለገጣፎ ለገዳዲ መጤ ስደተኛ የሚባሉትን ወገኖቹን አለሁ ይበላቸው? መቼ አለና ነውና አለሁ የሚለው ብአዴን? ፈሪ!

አንቦ የነፃነት አንባነቱ ዕውቅና አግኝቶ ብሄራዊ እንቅስቃሴ እዬተደረገ ነው። አንቦ ይጋባዋል። ጎንደርስ?  ጎንደር 90 ሺህ ህዝብ ተፈናቅሎ ፍዳውን ያያል፤ ዳንሻ ልጆቹን ቀልሃ ይባላቸዋል …

የሚገርመው አንድ ዓመት ሙሉ የግንጫ አብዮት ተጋድሎ ሲደረግ እኮ የትም አይደርስም ተብሎ ህወሃት የተፈጠረበትን ሲከውን የሐምሌ 5ቱ የጎንደር የአማራ ይህልውና የማንነት አብዮት ህዝባዊ ሞገድ ሲነሳ ግን አሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነው የታወጀው። እነ ፕ/ መራራ ጉዲና ተፈተው ሺዎች አቀባbል ሲያደርጉ ስጋት አልነበረም፤ ኮ/ደመቀ ዘውዱ ሊፈቱ የዋዜማው ግን ሁለተኛው አሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ።ተፈሪነት እና የማድረግ አቅም የት ላይ እንዳለ በለቅኔዎች የዕድምታ ባለሞያዎች ያፍታቱታል። 

ካለ አማራ ተጋድሎ አንዲት ስንዝር የህወሃት ስልጣን አይገፋም ነበር? ነገር ግን አሁንም ያ ቦታ በድርብ ቂም በቀል እዬተከተከ ይገኛል። ብአዴን አለሁ የሚለው በዚህ በዘበጠ ተሸናፊቱ ሥር ሆኖ ነው … አማራ ድጋሚ የቆረጠ ዕለት ኢትዮጵያ ያበቃላታል። ምክንያቱም የትናንቱ ግፍ ላይበቃ አሁንም በአዲስ ጉልበተኛ አማራነት እዬተፈጨ ስለሆነ።
ለነገሩ ም/ጠ/ ሚር አቶ ደመቀ መኮነን አንቦ ተገኝተው „ቄሮ ጀግና“ ሲሉ ጎንደር አልተገኙም ነበር። 

የራሳቸውን ታሪክ ፈሩት ''' ሸሹት፤ ዕውቅና ለመስጠትም ነፈጉት፤ ስለዚህም በብአዴን ጉባኤ እሳቸውን ለማስወገድ የአቶ አባዱላ ገመዳ ቡድን እነ አቶ ንጉሡ ጥላሁን አሰልፎ በጽኑ ተግተው ሠሩ፤ እኛ ግን ማተበኛ ነን እና ከጎናቸው ተሰለፍን። አማራነት እንዲህ ነው። አሁንም እሳቸው ሳይሆኑ አማካሪ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው … የተሻለ ክብር በ ኦዴፓ የተሰጣቸው ... 

ስለምን? የመነሻ መደረሻቸውን የአማራ ተጋድሎን ዕውቅና ለመስጠት፤ ለማሰጠት ትትርናቸው የአቶ ደመቀ መኮነን ልል ስለሆነ። ራሳችን ለማስከበር ሰነፍ ስለሆኑ። ኦዴፓዎች በአቶ ንጉሡ ጥላሁን ምርኩዝነት እና ሊንክነት በብልጥ ፓለቲካ ሥልጣን ያዙ እኛም አቅማችን ሁሉ ገብረንበታል፤ አሁን አማራን እዬጠቀጠቁ የልባቸውን ሲያደርሱ አሁንም በለውጥ ስም ለጥሰጥ ብሎ መገዛትን አለብን እያሉ እነ አያልቅበት ዶር አንባቸው መኮነን ይሰብኩናል።

ለውጡ የተቀለበሰው ሐምሌ 19ቀን 2010 ዓ/ም ነው። ዕውነቱ ይሄው ነው። በይፋ አይነገረም። ስለምን? ምዕራብውያን ፊታቸውን ስለሚያዞሩ፤ ጠ/ሚር አብይ አህመድን ከፊት አሰልፎ የአቶ አባዱላ አርሲኛ ኢትዮጵውያንን እዬገላበው ነው … ይህ የሚታዬው አይዋ ምርጫ ሲመጣ ነው … የላዩ ታች የታቹ ላይ ሲሆን፤ ለዚህ እኮ ነው ከሶሞነቱ ጠ/ሚር አብይ አህመድ መቼ እንደሆን ባላውቀውም ስልጣን እለቃለሁኝ ያሉት። ያው ቂነኛ ነው። 

ከዛን ጊዜ ጀምሮ ያለው ሂደት በጠላፊዎች መልካም ፈቀድ በተሰጠው የሃላፊነት ልክ ነው እዬተከወነ ያለው። ከዚህች ውልፍት የሚል ካለ ለውጥ በመቀልበስ ተብሎ ካቴና ይጠልቅለታል።

ለነገሩ ዶር አንባቸው መኮነን ግዞት ላይ እንዳሉ ነው እኔ የሚሰማኝ። ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ደግሞ በልጓም። በዚህ ማህል የብአዴን ለአማራ ባሬያ መሆን ህልም ነው በድቡሽት ላይ ቤት እንደመሰራት፤

ተሸናፊ እኮ ነው ብአዴን። 90ሺህ ህዝብ የራሱ ህዝብ በባዕቱ ተፈናቀለ እኮ? ከዚህ በላይ ሽንፈት ምን ይምጣ? ነገ ደግሞ በታጠቀ ሃይል በድርብ ሴራ የሚያገኛትን ያገኛታል። የዚህ ሁሉ የሴራ መቋጠሪያ ግን አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው። ለውጡ አለ ለሚሉት ይሁንላቸው እኔ ግን በህልሜ በሀምሌ 19 ወንበሩ ባዶ ሆኖ ስላዬሁት እማምነው እሱ ነው። እሚታዬውም ይኸው ነው።

የቡራዩ፤ የሻሸመኔ፤ የአዲስ አባባ ጭፍጨፋ እና መፈናቀል ሆን ተብሎ ነው የተከወነው፤ የኦነግም አካኪ ዘራፍ ጫና ለመፍጠር ታቅዶ ተሰውሮ የተከወነ ነው። ዘራፋውም ይሁን ተብሎ። የአሁኑ የጎንደሩም መፈናቀል ሆን ተብሎ የተከወነ ነው። የዚህ ሁሉ ተጠያቂ ደግሞ የታሪክን ሂደት ብል በመሆን እያሰናዱ የሚገኙት አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው።

እሳቸውን ተሸክሞ ብአዴን የትም አይደርሰም እራሱን ከማስደርመስ በስተቀር። የቆሞስ ጌታቸው ተስፋዬ ሞትም ከዚህ አንጻር ነው የሚታዬው … የኢንጂነር ቆሞስ ስመኛው በቀለ ደመ ከልብነትም ከዚህ ጥልቅ ጉዳይ ጋር በውል ስምም ነው … በዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊንት? ? ? ? ይከብዳል፤ ጉድጓድ ነገር ነው …
    
እነ አያልቅበት ብአዴኖች መጀመሪያ እራሳችሁን ከአቶ ንጉሡ ጥላሁን ሎሌነት አውጡ፤ ሚዲያውንም ነፃ አውጡት፤ ከዛ በኋዋላ ስለ ቀሪው ነገር መነጋገር ይቻላል። ለውጡ ደግሞ አለ አትበሉ ተጠልፏል። ጠላፊው ደግሞ የአባ ዱላ ገማዳ በተደራጀ እና በተቀነባበረ ከላይ እስከ ታች ባደራጁት የአርሲ አናብስት ውል ተኮፍሷል።

አርሲ የጢቾ ሴቶችን አውቃቸዋለሁኝ የተግባር ጀግኖች መሆናቸውን እኔ አደራጃቸው አሳምሬ እመሰክርላቸዋለሁኝ። እንደ ጥንድ ነው የሚያጣድፉት ለተልእኳቸውን። ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ የክ/ አገሩን ኮታ ነበር እኛ የምንሸፍነው። ጥቃትም መበለጥም አይወዱም … ዛሬም በማዕካላዊ መንግሥት የሆነው ይኸው ነው …

ልብ ቢሸምት ልብ መግዛት ያለበት ብአዴን መሆን ነበረበት!
ልብ ሲገጠምለት የኖረው ብአዴን አለሁ ባይል ይሻለዋል!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።