እግዚኦ!

እንኳን ደህና መጡልኝ።
ስለምን ብፁዕ ወቅዱስ
አባታችን ይሳደዳሉ?
„በክፉዎች ምክር ያልሄደ፤ በሃጢያተኞች ምክር ያልቆመ፤
 በዋዘኞች ወንበር አልተቀመጠ፤ እሱ የተመሰገነ ነው።“
መዝሙር ፩ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
 04.03.2019
 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን።

·       መነሻ።

Ethiopia: ጥብቅ መረጃ - የአቡነ ማቲያስና የዶ/ አብይ አህመድ ምስጢራዊ ስብሰባ | ""አዲስ አበባን ለቅቄ እሄዳለሁ" አቡነ ማቲያስ

·       መግቢያ።

ውዶቼ እንዴት ሰነበታችሁ። በቅድሚያ እንኳን ለጥቁሮች የድል ቀንዲል ለሆነው ለ123 የዓድዋ ድል በሰላም አደረሰን። ኦነግ ደግሞ ሚኒሶታ ላይ በዚኽው ቀን በታቀደ ሁኔታ ፍላጎቱን አስፈጽሟል። 

በሌላ በኩል በባዕት ያሉት ደግሞ የኦነግ አክሮባቲስቶች ነገሩ ሁሉ ግልብጥብጥ አድርገው እነ አደናግሬ አዲስ ጎፈር ለብሰው ብቅ ብለዋል። እነሱንም እንኳን ለዚህ ቀን አበቃቸው። ሥማችን እንደንቀይር ተደረግን ከማለት ጀምሮ በበታችነት ለዘማናት ሲማስኑ ከባጁበት አረንቋ ወጥተው በቅጽበት ደግሞ የአድዋ ድል ታዳሚነታቸው ታይቷል። ከምን እንደተፈጠሩ ራሱ እስኪገርመን ድረስ።

በሌላ በኩል ዛሬ አብይ ፆም ለቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን ገብቷል። ፆም የፈተና ወቅት ነው። ፈተና በራሱ ጊዜ ሲመጣ መልካም ነው እና ብፁዕ ወቅዱስ ሊቀ - ሊቃውንት አባቶቻችን የቀደመውን ጽናታቸውን አስቀጥለው ቅድስት ቤተ ክርስትያናችን ልዕልና ያስከብሩ ዘንድ ልዑል እግዚአብሄር ብርታቱን እና ጥንካሬውን ይስጥልን። አሜን!

ይህ አብይ ፆም ያን ጉማም የሱባኤ ዘመን ተገፎ ብፁዕን ቅዱሳን አባቶቻችን በቅድስት አገር ኢትዮጵያ በባዕታቸው ሆነው ፆመ ወቅቱን በአኃቲነት በሱባኤ፤ በስግደት፤ በፆም፤ በምህላ የሚያሳልፉበት ስለሆነ ታላቅ ወቅት ነው። በዘመናት መካከል በሁለት ፓትርያርክ ቡራኬ ነው ይህ ፆም የሚከወነው። ስውሩን ፓትርያርክ ሳያካትት። ሌላ የታሪክ ምዕራፍ። ሌላ የፈቃደ እግዚአብሄር ይሁንታ።

·       ሀዘን።

አምና ይሄን ሰሞን የገሃዳዊ የመንፈሳዊ ሁነቶች ወጀብ በግራ በቀኝ እያለጋን መልሱን ሱባኤው አህዱ ብሎ ሲያብት በህማማት አዳምጠን ነበር። ዘንድሮ ገና ሱባኤው ዋዜማ ላይ እያለን ሌላ አስደንጋጭ ዜና ከዘሃበሻ አዳመጥኩኝ። ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ሰላማቸው እንደታወከ እና ጠበቂ እንዳጡ የሚገልጽ መርዶ ነበር። እግዚኦ!

እኔ ሆን ተብሎ የሚከወን አድርጌ ነው እማዬው። ጫና በመፍጠረ ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አባታችን አገር ለማሳደድ የሚደረግ እንደሆን ነው እማሰበው። 

ያን ያህል የድምጻችን ይሰማ ለተከታታይ አመታት ለእምነት ነፃነት ሲተጋ ኮሽ ሳይል ለጥ ብሎ የከረመ የሥም ብቻ የቤተ ክርስትያን ተቆርቋሪ ዛሬ ምን አስነሳው? ስንት ግፍ እና መከራ ቤተክርስትያናችን 27 ዓመት ሙሉ አሳልፋለች - ምነው ያን ጊዜ ኮሽ አላለም? በታሪክ እንደ ህወሃት ዘመን ብጹዕን አባቶቻችን አልተሰደዱም፤ አልተሳደዱ ምነው የት ነበር ይህ ኃይል? ፈጣሪ ከነሰራዊቱ ወርዶ ያን ያህል በምድረ ኢትዮጵያ ማዕቱን ሲፈጽም እኮ ማህበረ ምዕመኑ ቻለኝ ብሎ በመተኛቱ ነበር። የሰማይ ነጎድጓድ ፍርዱን የበዬነው።
   
የሆነ ሆኖ በፈጣሪ መልካም ፈቃድ በጠ/ሚር አብይ አህመድ ትትርና፤ በግራ ቀኙ በብፁዕ ቅዱሳን አባቶቻችን ይሁንታ እንሆ ዛሬ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አንድ በሆነችበት ወቅት ሌላ ትርምስ ይፈጠር ዘንድ ተተግቶ እዬተሠራበት ነው። የጂጅጋው ሰምዕትነት ተቀጥላነት መሆኑ ነው።

የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የብጹዕ ወቅዱሳን አባቶቻችን አንድነት፤ ህብረት ውህደት የፈጣሪ ኪናዊነት ስለመሆኑ አምነን ሌት እና ቀን ፈጣሪያችን ልዑል እግዚአብሄርን በምናመሰግንበት በአሁኑ ጊዜ በሃይማኖት የለሹ የመንፈስ ኩዴታ ፈጻሚው ቡድን የሚመሩ ግለሰቦች ህውከት በመፍጠር ቤተክርስትያናችን ከሁለት ለመተርትር በመትጋት ላይ ይገኛሉ። ማህከነ!

ለዚህም ነው እጅግ ደም ዕንባ በሚያስለቅስ ሁኔታ በተጠናከረ ስውር ድጋፍ የሚንቀሰቃሱ ጸረ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ  ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሰላም እያወኩ የሚገኙት። ድፈረቱ ራሱ የሚገርም ነው። ከጽ/ቤታቸው ሁሉ እዬተገባ ነው ማስጠንቀቂያ የሚሰጣቸው። አንድ ነገር ቢሆኑ ማነው ተጠያቂው? በግፍ ቢገድሏቸውስ?! አካላቸውን ቢያጎድላቸወስ?

ይህ የሚፈለገበት ምክንያት ሥልጣኔን በፈቃዴ እለቃለሁ ሲሉ የተዘጋጁ ሌላ የሰውር መንግሥቱ ፓትርያርክ ስላሉ እሳቸውን አምጥተው ፕትርክና ለመስጠት ሆን ተብሎ ታቅዶ እዬተከወነ ነው የሚገኘው። ሰው ልብ አላለውም እንጂ ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ አያሉ እሳቸው በጥምቀት ባህሩ ላይ ቡራኬ ሲሰጡ ሌላ ተደራቢ በቴሌኢ
ቪዥን ደግሞ እኮ በኦሮምኛ ቡራኬ ሲሰጥ አዳምጠናል። ጉዞው ወደዬት እንደሆን አዬተመለከትን ነው። 

ስለዚህም ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከመቼመው በጠነከረ አኳኋን ይህ በሃይማኖታችን ላይ የመጣውን ኩዴታ በጽኑ በመቃወም ከዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጎን መቆም ይኖርብናል። ክርስትና የሚነጥረው በፈተና ወቅት ነውና።

ብጹዕነታቸውም ቢሆኑም አገር በሠራዊት ብዛት እንደማይድን አምነውና ተቀበለው የቤተክርስትያናችን አንድነት ለማስጠበቅ ያሳዩንትን ንዑድ ቅንነት በጽናት በመቀመመ ተጋድሏቸውን ከሚሊዮኑ ምዕመን ልጆቻቸው ጋር ሆነው በድል ለመወጣት መትጋት ይኖርባቸዋል - በትህትና። መረበሽ - አለመረጋጋት አይኖርባቸውም። በሌላ በኩል ሁላችንም ከጎናቸው ልንሆን ይገባል - ሳናመናታ። እንደገና ቅደስት ኦርቶዶክ ተዋህዶ በፖለቲካ ፍላጎት ልትጠለፍ አፋፍ ላይ ናትና። 

ስለሆነም ብጹዕ አባታችን አቡነ ማትያስ በከፋቸው ጊዜዬ አይዘዎት ልንላቸው ይገባል። ሰላም በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይገኝም። ሰላም የሚገኘው በሁለት ወገን ይሁንታ ነው። የሳቸው ጥልቅ ቅኔያዊ ቅንነት ነው ቅደስት ቤተክርስትያናችን አንድ ያደረጋት። 

ይህ ውለታቸው፤ ይህን ሰማዕትነታቸው መቼውንም ቢሆን እኛ ብቻ ሳንሆን የዓለም 5ቱ አብያተ ቤተክርስትያናት የማይረሱት ነው የሚሆነው። ታላቅ ተጋድሎ ነው የፈጸሙት። ተሳክቶላቸዋልም። የተሰካላቸው ስለመሆኑ የጎረበጣቸው ናቸው ዛሬ ሌላ አቲካራ ፈጥረው በጫና ታሪካቸውን ጥቅርሻ ለማልበስ እዬተጉ የሚገኙት።

ብጹዕነታቸውም ምንም መሸሽ፤ ምንም ሥልጣን መልቀቅ፤ ምንም መደናገጥ ሳይኖር በመሰቀል ሃይል ጸንተው በርትተው ሥልጣነ ጵጵስናቸውን ሳያስደፍሩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። ይህን የሚያስደረግው ቡድን ማን እንደሆነ ይታወቃል።

ማህበረ ማዕመኑም ይህ የሴራ ፈትል ከዬት፤ የማን እንደሆነ ልብ ልንለው ይገባል። የፈጣሪ ስም በፓርላማ ሲነሳ ከትከት ብሎ የሳቀው የጸላዬ ሰናይ መንፈስ ነው፤ ስለሆነም ማህበረ ምዕመናን ቤተክርስትያናችን ለበለሃሰብ አሳለፍው እንዳይሰጡ በብርቱ ተጋድሎ ማድረግ ይኖርባቸዋል - ይኖርብናል። ክርስትና የሚለካው በመከፋት ውስጥ ድል አድርጎ ሐሤትን ለሃይማኖቱ ሲያጎናጽፍ ብቻ ነው። 

ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን ፈተና ላይ ናቸው ብጹዕ አባታችን አቡነ ማትያስ፤ ይህን ፈተና ረቶ ለድል ለመብቃት ሱባኤ ወቅት መሆኑ በራሱ ሚስጢር አለበት፤ በዚህ ሚስጢር ትርጓሜ የፈተና መቋጫ ከጥንካሬ ይገኛል። ጸሎት ሃይላችን ነው። ጸሎት ከቀስት እናመልጥበት ዘንድ የተሰጠን የቡራኬ አዕማዳችን ነው። እንበርታ!

ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስም ቢሆኑ በዘመናቸው አንድ ያደረጓትን ቤተክርስትያን እንዳትናወጽ የቤተክርስትያኗ አለት መሆን ይኖርባቸዋል እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ። ይህን ልዩ ታሪካዊ ዘመን ጥሰው ወደ ትግራይ ከሄዱ ግን በውነቱ አገር እንዳፈረሱ ነው እኔ እምቆጥረው። የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እንጂ ይህን ከፈጸሙ ቅድስናቸውን ሰማዕትነታቸውን ሁሉ ነው በራሳቸው ፈቅደው ነው የሚቀዱት። የክብር ተክሊላቸውንም ነው ትቢያ ነው የሚያለብሱት። ብዙ ነገር ነው የሚናደው።

ብጹዕን ቅዱሳን ሊቀነ ጳጳሳትም የዚህ ሴራ ተደራቢ አጋዥ ሳይሆኑ በጸሎት በመትጋት ትብትቡን - ጥልፍልፉን - ጥምልልምሉን ባለጣምራ ፈተና ድል በማድረግ ለብጹዕ ወቅዱስ አባታችን ለአቡነ ማትያስ ድርና ማግ በመሆን ከጎናቸው ሊሰለፉ ይገባል - በትህትና። 

ማህበረ ምዕመኑም ልዑል እግዚአብሄር የሰጠንን የምርቃት ዘመን እንዳናጣ በምንችለው ሁሉ መታገት ይኖርብናል። ለቅድስት ኦርቶዶክ ተዋህዶ ትልቅ ሞት ነው ቤተክርስትያናችን ለሳቸው ጥበቃ ማድረግ ተስኗት አሳቸው እንደገና ተሰዳጅ ሲሆኑ። ለጠ/ሚር አብይ አህመድም ታላቅ ሽንፈት ይሆናል። የለፉበት፤ የደከሙበት ውሃ የበላው ቅል ይሆናል። 

አገር መናዷ የሚረጋገጥበት ዕለት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አዲስ አባባን የለቀቁ ዕለት ይሆናል። ይህቺ ዕለት ለጠ/ሚር አብይ አህመድ ወንበር ባዶነት የሚረጋገጥበት ይሆናል። ቦታውን አቶ አባ ዱላ ገመዳ የሚመሩት ስለመሆኑ የሚረጋገጥበት ይሆናል። የስውሩ መንግሥት መሪ እሳቸው አቶ አባ ዱላ ገመዳ ናቸው፤ ምክትላቸው ደግሞ አባ ገዳ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው፤ አማካሪያቸው ሀጂ አባ ገዳ ጃዋር መሃመድ ናቸው። የጨለማው ሚስጢር ሲፍታታ ይኸው ነው፤
  
እንሆ … ኢትዮጵያ በዘመኗ በምርኮኛ ወታደር ነው እዬተመራች ያለችው ከሀምሌ 19 ቀን 2010 ጀምሮ። የሆነው ድንብልብሉ ጥፍጥፉ ልሙጡ የሀምሌው ዝምታ ገመና ይኸው ነው። የዛ ዲታው የምልዕት ፍቅር አመክንዮ ኩዴታ ፈጻሚ እና አስፈጻሚ ጠላፊ አቶ አባ ዱላ ገመዳ እና እሳቸው በሥልጣን ዘመናቸው ያደራጁት ቡድን ነው ድል ላይ ያለው …

ወስብሃት ለእግዚአብሄር።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።