የአባ ገዳ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ሚዲያ AMMA „ፊንፊኔ“ ማለትን አህዱ አለ።
እንኳን ደህና መጡልኝ።
የአባ ገዳ አቶ ንጉሡ ጥላሁን
ሚዲያ AMMA
„ፊንፊኔ“ ማለትን
አህዱ አለ።
„አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል?
በተቀደሰው ተራራህስ ምን ይኖራል?“
መዝሙር ፲፬ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
04.03.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
·
መነሻ።
"የት እንግባ?"
ቤታቸው የፈረሰባቸው የለገጣፎ ነዋሪዎች
በብአዴን በዘመነ ህወሃት እንዳሻቸው ሲወራኙበት የነበረው የሳጅን በረከት ዘመን ተጠናቆ አሁን
ለባለተራው ለአባ ገዳ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለጥ ብሎ በመስገድ ላይ ይገኛል። ጥቁሩ ዘመን በአዲስ የባርነት ጥቀርሻማ
ዘመን በተሃድሶ ላይ ይገኛል።
እንሆ የህወሃትን ዓርማ የህወሃትን ዓላም እና ግብ የጣለለትን እራፊ ጨርቅም መለያዬ ነው ብሎ
አደግድጎ በሎሌነት ወደ ተግባር ለመቀዬር ከፍ እና ዝቅ ሲል 27 ዓመት ሙሉ የባጀው ብአዴን አሁን ደግሞ የአማራ የማንነት ተጋድሎን
ድል እና ዕሴት አሳልፎ ለኦነጋውያን በማስረከብ ለአዲሱ ግርባነት ለጥ ብሎ ሰግዶ፤ አደግደግዶ በበታችነት ይማስናል።
አዲሱ የኦዴፓ ካድሬ ጉዳይ አስፈጻሚ እና የኦነግ አንባሳደር አቤቶ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ሆነው ተገኝተዋል።
አጤው በዛ ሰሞን በተርሚናል ምረቃት ላይ ከቤታቸው ተነስተው እስከ አዬር መንገዱ የባዕል ቦታ
ድረስ እንደ ታቦት ታጅበው በቴሌቪዥን በተደገፈ ቅንብር ነበር ጉዟቸውን ታደሙ የተባልነው። ሁለተኛው ይሁኑ አጥቢያው ይሁኑ ሳልሳዊ ይሁን የሳቸው ደረጃ ባይታወቅም።
በዚህ የሰላይነት ተግባራቸውም
አንቱ ሆነው ቁንጮው የጠ/ሚር ሆድ ዕቃ ለመሆን በቅተዋል። ለእኔ ከአቶ አባ ዱላ ገመዳ ቀጥሎ ያለው ቦታ የሳቸው እንደሆነ ነው
የሚገባኝ።
የሐምሌው ዝምታ ሲፍታታ፤ መፈንቅሉም፤ ኩዴታውም፤ በብክል መርዝ ማስወገዱም ሲያጠነጥን የነበረው ቡድን ዋና
መሪ አቶ አባ ዱላ ገመዳ በአርሲኛ ቀለም ነው። የልዕልት ቤቲ የመነሻ መድረሻ እድምታም
በዚህ የተቃኜ ነው።
የሆነ ሆኖ የሊቃውንት አንባ በሆነው በአማራ መንፈስ ላይ በታቀደ ሁኔታ ሌላ መርዝ የያዘ አዲስ
ብርዝ ደግሞ አንቱ ብሏል። የአቤቱ የአቶ ንጉሡ ጥላሁን የግል ሃብት እንደሆነ የሚታይበት የአማራ የብዙሃን የመገናኛ ሚዲያ ከዛ
ክብሩ ዘጭ ብሎ አዲስ አባባን በይፋ እና በአደባባይ „በፊንፊኔ አካባቢ“ ሲል ተደመጠ። አዲስ የጠቀራ የፊደል ገበታ
መለማመጃ መሆኑ ነው።
በጥንካሬው፤ በግርማ ሞገሱ፤ በኢትዮጵያዊ ማንነቱ በአብዛኞቹ ዘንድ ግርማ ሞገስ ያለው ውዳሴ
ሲቸር የባጀው የአማራ የብዙሃን መገናኛ ድርጅት የብአዴን ግርባነትን በአደባባይ በይፋ በሙሉ እንሆ አትሞበታል።
ብአዴን በሚዲያው ይህን ባለበት ቀን ቢሞት ይሻለው ነበር። ለነገሩ ከሎሌነት መቼ ወጥቶ በዬዘመኑ? አቅመ ቢስ!
የዚህ ለውጥ አንባ ታላቁ ተጋድሎ የአማራ የህልውና የማንነት አብዮት ሆኖ ሳለ እሱን እንዳወጣ
ሸቅጦ እና መቅጦ እነሆ አሁን ደግሞ ለአዲስ ባርነት በዘበጠ ማንነት አደግድጎ በለኝ ብሏለኝ አይዋ ብአዴን -እንደለመደበት፤ አጋፋሪው ክህደት ፈጻሚው ደግሞ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው።
የአማራ ህዝብ እንዴት ቢናቅ እንዴትስ ቢደፈር ነው የዳዊትን ከተማን፤ የአፍሪካን መዲና የጣይቱን
አበባን በሠፈር ሥያሜ „ፊንፊኔ“ ብሎ ለመጠራት የሚደፈረው? ለመሆኑ ያ ጋዜጠኛ ምንኛ ይሆን? እንዲህ ወደ አሪስኛ ጉዳይ ይኖረው ይሆን
ወይንስ ወደ ጃዋርኛ? ያን ቀን ኢትዮጵያ ተምሳ የተቀበረች እንደሆነ ነበር የተሰማኝ። ያው በሥም ኢትዮጵያ የምትባለው መንፈሷ እዛው
አካባቢ ነውና ፍዳውን የሚያው።
ብአዴን የገዳዩን የህወሃት ድንቡልቡል የሄሮድስ መለስ ዜናዊን ማንፌስቶ ተሸክሞ አማራን ሲያሽጨፈጭፍ
መባጀቱ አልበቃ ብሎ፤ የባህርዳር አወሮፕላን ማረፊያ ግንቦት 20 ሲል የሰዬመውን ዛሬ ደግሞ አቶ አባ ዱላ ገማዳ አውሮፕላን ማረፊያ
ይለው ይሆን? ምርኮኛ ምርኮኛ ጋር ቢወዳጅ ምን ሲገድ? ብአዴንም ምርኮኛ አቶ አባ ዱላ ገመዳም ምርኮኛ።
ለውጡ ተቀለበሰ፤ ለውጡ መንፈሱ ኩዴታ ተካሄደበት ሲባል ብዙ ሰው ግር ይለዋል። የቡድን መሪው
አቶ አባ ዱላ ገመዳ ናቸው። ተባባሪ መሪው ደግሞ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው። ዕውነቱ ይኸው ነው።
በዛ በጠ/ሚር አብይ ልክ ባልተበጀለት ብቃት፤ ክህሎት ትራስነት የተገኘው፤ በመገኘት ላይ ያለው
ቅቡልነት ሁሉ ተጠምዝዞ የሚመራው በምርኮኞው አቶ አባ ዱላ ገመዳ መሪነት ነው። መቼም ይሄ ለህወሃትም ሞቱ ነው።
ልደታቸውን
ደግሞ ቦሌ የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል አውሮፕላን ማረፊያ ኬክ በመቁረስ ተከውኗል። በዕለቱ መሪው አቶ አባ ዱላ ገመዳ እና ምክትሉ
አቶ ንጉሡ ጥላሁን ተገኝተዋል - በፍሰሃ ሥርዓት ንግሱ የተፈጠመው ያን ዕለት ነበር።
ያ ቦታ ከስሜን አሜሪካ መልስ ሐምሌ ላይ ሌላ ጥቁር ቀን ታቅዶ፤ ቹቻ ተርሶ፤ ሰኔል ተዘጋጅቶ፤
ሳጥን ተብጅቶ ቢጠብቅም በብጹዕን አባቶቻችን የመንፈስ ሃይል ትልሙ አምድ ቢለብስም አሁን በእገታ ይሁን በቅድመ ስምምነት በተገለበጠ
ካርቦን አዲሱ ተውኔት በዛ መልክ በታላቅ የኬክ ቆረሰ ሥርዓት ተከውኗል አድመኞቹ አቶ አባ ዱላ ገመዳ እና አቶ ንጉሡ ጥላሁን ግራ ቀኙ በተገኙበት።
ወደ ቀደመው ምልስት ሲሆን „በፊንፊኔ አካባቢ“ ያሉት የአቶ ንጉሱ ጥላሁን ጋዜጠኛ አሁንም ተዛው
ተቦታቸው ይሆኑን? አቶ አሰማኽኝ አስረስም ከህወሃት ቱቦነት ወደ ኦነጋውያን ቱቦነት እንዲህ የአክሮባቱን ትርኢት አሳይተውናል
… መጥኒ ለእነ ለሽ ይበሉ ለብአዲኖች፤ ሎሌነቱም የበታችነቱም ለማይታክታቸው … እነ ላንቁሶ¡
ጥቃትን ተንትርሶ የሚተኛ አማራ ባይፈጠር ይሻለው ነበር።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ