የአማራ ህዝብ ከቶ ወደ #ማርስ ይምጠቅላችሁን?????? ሞፈር ቀንበርን ለምን #ታነዱታላችሁ??? የአማራን #ገበሬ ለምን #በድሮን ታነዱታላችሁ? መሬቷንስ ለምን #በቦንብ መርዝ ታነዟታላችሁ? "የቤትህ ቅናት በላኝ።"

 

የአማራ ህዝብ ከቶ ወደ #ማርስ ይምጠቅላችሁን??????
ሞፈር ቀንበርን ለምን #ታነዱታላችሁ???
የአማራን #ገበሬ ለምን #በድሮን ታነዱታላችሁ?
መሬቷንስ ለምን #በቦንብ መርዝ ታነዟታላችሁ? 
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
እህል አልባ መኖር አለን?
ዘር አልባ የሰው ልጅ ይቀጥላልን?
ውኃስ አልባ መተንፈስ ይቻል ይሆን? 
 
የኦነግ ጠረን የተላበሰው የኦህዴድ ወራሽ ብልጽግና የአማራ መሬት ይመረዝ ዘንድ ተግቶ እዬሰራ ነው። ለትውልድ እንዳይደርስ አርቆ በማሰብ ጠፍ የማድረግ ብቻ ሳይሆን በተመረዘ መሬት የሚበቅል አዝዕርት ለትውልድ የአካል አፈጣጠር እክል ይሆናል።
#ገበሬን በቦንም? 
 
ገበሬን በአውሮፕላን #መጨፍጨፍ? ምን ይባል። 
 
በአማራ ህዝብ ተገድሎም፤ ተዘርፎም፤ ተገሎም፤ ታስሮም፤ ተሰውሮም፤፦በገፍ በዬተገኘበት ተጨፍጭፎም የተረፈው በራህብ ያልቅ ዘንድ የጠቅላይ ሚር አብይ መንግሥት ተግቶ እዬሠራበት ይገኛል። የምርት ሰዓት፤ የእርሻ ወቅት ጠብቆ ይቀጣል ያሳዳል። ሲያሻውም ሰብሉን መስክ ላይ የዶግ አመድ ያስደርጋል። የአገር ልጅነቱን ፍቆ የውጭ ወራሪ ነው የሚመስለው። መሃከነ። 
 
የሚገርመኝ አብረው የሚሠሩት የአማራ ግዑዛን ናቸው። ህሊና የሚባል ያልሠራላቸው #ገደላገደሎች። እኔ የገበሬ አደራጅ ነበርኩኝ። በአንድ ወቅት የኢትዮጵያን መሪ በአካል አግኝቼ ነበር። እናም መልሼ ላላገኝሽ እችላለሁ እና ምን ላድርግልሽ ሲሉ በትህትና ጠየቁኝ። ጎበዝ ተማሪ ነኝ። ውጭ አገር ለትምህርት ላኩኝ አላልኩም። ወይንም አዲስ አበባ የተሻለ ሥራ ይሰጠኝ አላልኩም። ወይንም እዚህ ሥራ ይሰጠኝ አላልኩም።
 
የጠዬቅኩት ገበሬ መንደር ሄጄ ገበሬ ማደራጀት ነው እምፈልገው አልኩኝ። እኔ የጎንደር ከተማ ልጅ ነኝ። ቤተሰቦቼም ባላባቶች ስለሆኑ ገጠሩን አያውቁትም። የገበሬ ንጽህና፤ የገበሬ ጤናማ ጠረን፤ የገበሬ የአነጋገር ለዛ፤ የገበሬን የአኗኗር ጥዑም ቃና፤ የገበሬን ዕውነተኛ ቅንነት #መተንፈስ ፈለግሁ። የፈለግሁት ተሰጠኝ - ኖርኩበትም።
 
ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል አደራጅቻለሁኝ። የሙያ ሰወችንም። ግን እንደ ፃዕዳው ገበሬ ተፈጥሮ የሚመስጠኝ #የምቀናበትም ህይወት የለም። ገበሬው ንጽህናው በመላው ኢትዮጵያ ተመሳሳይ ነው ብዬ አምናለሁኝ። ምክንያቱም በሥራ መላው በጌምድር እና ስሜንን፦ እንዲሁም አርሲ ክፍለ አገር የጢቾ አወራጃ የአምኛ፤ የሴሩ፤ የጠናን ገበሬወች፤ በልምድ ልውውጥ የጎጃምን፤ የሽዋን፤ በራሴ ፈቃድ በጉብኝት የአቶ በቀለ ሞላውን የጋሞ ጎፋን አካባቢ አዬሁ። ያዬሁት #ፃዕዳ ተፈጥሮን ብቻ ነው።
 
የዝናብ ውኃ ታውቃላችሁ? እንደዛ። ንፁህ። ፃዕዳ። ቅዱስ። ብሩክ። ገር። የዋህ። ሰውኛ። ምሩቅ። ሳቂተኛ። ግልጽ። ይህ የማህበረሰብ ክፍል ለ33 ዓመታት #የፖለቲካ #ውክልና አልባ ተገሎ ግን ሲገደል ኖረ። የአሁኑ ደግሞ ከፋ። በአውሮፕላን ቀረጥ ከፍሎ የሚያስተዳድረው መንግሥት ጨፈጨፈው። መቆሚያ መቀመጫ አሳጣው። ከቶ የአማራ ገበሬ ወደ ማርስ? ወደ ጁቢተር፦ ወደ ኡራኖስ ይምጠቅላችሁ ይሆን? እራፊ ቀዬ አሳጣችሁት። በጭካኔ አዋከባችሁት። በግፍ አጣደፋችሁት።
 
መሬትም #ነደደች። አዬሩም ከሰለ። ጭንቀትም ኦክስጅን ሆነ። ሞፈር ቀንበርም በግፍ #አረረ። ይህ ሥርዓት አማላክን // አላህን ነው እዬታገለ የሚገኘው። እንደምን ንፁህ ቅዱስ ገበሬ #በድሮን ይጨፈጨፋል? እንዴት ልባቸው ቻለ? በእሱ ምርት ታድጎ፤ ተጎልምሶ፤ ለሥልጣንም ተበቅቶ። እንደምን እንዲህ ይደረጋል? ግራጫ የመከነባት አገረ ኢትዮጵያ መጥኔ ላንች። 
 
ዓለም #ዝም አለ ይባላል። ምን ይደረግ ተሰላፊው #ተወዳሹ በረከተ። በሌለበት ባልነበረበት ውዳሴው ደራ። ቃለ ምልልሱም ተጧጧፈ በ2023 ግንቦትን ይዞ የነበረው የደራ ወግ አስታውሱት። እንሆ ዝም ሲባል ዝም ሆነ። የሆነ ሆኖ መንግሥት የህዝብ አገልጋይ እንጂ የህዝብ ቁንጮ ሊሆን አይገባም። መንግሥት እኮ የህዝብ ሰረባንት ነው። ይህ በህግ ጥሰት ገበሬን በድሮን መጨፍጨፍ ጉዳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊቆም ይገባል። በጣም የኦነግ መራሽ አስተዳደር ተቀናጣ። ሰርክ በመታበይ ጎርፍ ያጎርፋል። ሲከር ይበጠሳል፤ ሲሞላም ይፈሳል። 
 
የገረመኝ "ልበ ሰፊነታችን፤ ታጋሽነታችን አብቅቷል" ሲሉ መልካቸውም ልሳናቸውም ሻለቃ መላኩ ተፈራ የሚመስሉ የግርባው ብአዴን ላንቃ ዶር መንገሻ ፈንታ የሚባሉ ሲናገሩ ሰማሁኝ። አስቸኳይ አዋጅ አውጆ በመላ ኢትዮጵያ ለአማራ ህዝብ ብቻ ከዓመት በላይ ከ50 በላይ በድሮን ሲጨፈጭፍ፤ ሲያስር፤ ሲያግት፦ ሲቢሊያን ከቤት አውጥቶ ሲረሽን፤ አማራዊ መንፈስን በጽኑ በዘመቻ ሲያዋክብ የባጄ ሥርዓት ታገስኩኝ ትዕግሥቴ አለቀ ለበጣ ነው። ማፈሪያነትም ነው። ፋክክር አያስፈልግም ለጭካኔ። መንግሥት ነን ካላችሁ። ተሸላችሁ፤ በልጣችሁ መገኜት ነው ለሚዛናዊነትም የሚመቸው።
 
ውጊያው ከፋኝ ካለ ፋኖ ጋር ነው። እሱን መፋለም ሲያቅት በቀሉን፤ ቁጫኑን በንፁኃን አርሶአደር ላይ ማድረግ ያንገሸግሻል። ኦህዴድ እኮ መመሥረቻ ቀዬው #በለሳ#ላሊበላ እና #አርማጭሆ ስለመሆኑ አቶ አባዱላ ገመዳ ነግረውናል። ያን የክፋ ጊዜ መጠጊያ ነው ዛሬ ቀን ሲቀና ማት እዬዘነበበት የሚገኜው። ያን ያህል ወጣቶች በሬቻ ሲጨፈጨፋ እኔን የቀደመኝ፤ አቤቱታውንም ያሳካ አልነበርም። የኦሮሞ ፖለቲካ አቅል፤ አደብ አቅም ቢሰራለት ምላሹ እንዲህ ቅጣት፤ እንዲህ የአማራን መንፈስ መፈናፈኛ ነስቶ መቀቀል ባልሆነ ነበር።
 
የአማራ ገበሬ የእምነት #ተቋማቱ፤ ማሳው፥ መኖሩ፥ ተስፋው በበቀል ፋስ አሳሩን እያዬ ነው። በተለይ የቅኔው ጎጃም ገበሬ በእጅጉ ተጎድቷል። ምክንያቱም ሰፊው ምርት የሚቀርበው እዛ ስለሆነ እርሻን በማስተጓጎል አማራን ራህብም እንዲፈጀው ነው ትልሙ። በጎንደር በወሎ፤ በሽዋም መጠኑ ይለያይ እንጂ ማት ነው እዬወረደ የሚገኜው። 
 
ሊቅ የተባለ፤ ሊሂቅ የተባለ መፈጠሩን እስኪጠላ ድረስ በቀዩ ፍዳውን እያዬ ነው። ጠቅሚር አብይ ተፈጥሮ ለአማራ ብቻ ነጥላ ኦክስጅን ላይ ማዕቀብ ብትጥል ይሻሉ። ጥላቻቸው፤ ንቀታቸው፤ ማሳደዳቸው ዲካ የለውም። ብዙ በጥሞና ታዘብኳቸው። ፀፀት ምህረት የሚባል አልሠራላቸውም። ለአማራ ገበሬ የእሳቸው ሪዞልት ምኑ ይሆን????
 
ለዚህ እግዚአብሄርን አላህን #አሻቅቦ ለሚዋጋ ሥርዓት የእግዚአብሄር ቁጣ ቢመጣ ሊፈረድ ነውን? የጠሚር አብይ ሹመት ዋዜማ የመሬት መራድ መቀሌ አካባቢ፤ የአዲሱ ፕሬዚዳንት የአንባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ #እሳቸው #ያልሰሙት ሹመት ዋዜማ ላይም የመሬት መራድ ምልክት በብዙ ከተሞች ተስተዋለ። ረፋድ ላይ ባልደረቦቻቸውን ሰብስበው እያነጋገሩ እያሉ እንደ ጉልት ገብያ ዕቃ ተጠርተው አንብብ የተባሉት አሉ።
 ይገርማል። 
 
እንዲህ ባለ የተዝረከረከ ከምለው የተዝለገለገ ሥርዓት ውስጥ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት የሚሰማው ትውልድ እንደምን ማብቀል ይቻላል? መርግ የሆነ ልቅ ዘመን።
ስለሆነም #በመታበይ ሠረገላ ላይ የሚገኙ የማህበረ ኦነግ ርስት ወራሾች ብልጽግናወች ቢያስቡበት መልካም ይሆናል። 
 
የተያዘ የተረዘዘውን ሁሉ #አጥቅቼ #እጫናለሁ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሚሆን አይደለም። ያ በ16ኛው መቶ ክ/ ዘመን ተነነ። በሰው አቅም ባይሆን የኢትዮጵያ አምላክ ይህን የጎሼ፤ ያጎፈረ፤ ያጎረፈም ዘመን ይዳኜዋል። ፈጣሪ አለ። የበቀል አምላክ ይበቀላልና። 
 
በእሳር ውስጥ ለሚኖር ቀን የለበሳትን ራፊ ሌትም የሚለብስ፤ ለራሱ ኑሮ የማያውቅ #ስመጥር#ደግ እና ቸር ገራገር ገበሬ ይህን ያህል ማት??? ይህን ያህል የቦንብ ናዳ??? ይህን ያህል የበቀል ፋስ????? #ጨካኞች።
 
ፍትህ ለአማራ ገበሬወች።
ፍትህ - ለሞፈር ቀንበር።
ፍትህ - ለመሬት።
ፍትህ - ለተፈጥሮ። 
 
"አገርን እግዚአብሄርካልጠበቀ፤ ሠራዊቱ በከንቱ ይደክማል።"
 
የእኔ ክብሮች ኑሩልኝ። መሸቢያ ውሎ እና አዳር። አሜን።
ቸር አስበን ቸር እንሁን።
ቅን አስበን ቀና እንሁን።
በቀለኞችን እንጠዬፍ። አደራ። 
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/10/2024
 
#የአማራ ገበሬን አትግደሉ።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።