የኔታወቼ ማህበረ ቅንነት ክብረቶቼ እንኳን አደረሰን።

 

ኔታወቼ ማህበረ ቅንነት ክብረቶቼ እንኳን አደረሰን። 
 ሰዋስው | የገና በዓል እና ጾም
 
 
መድረስ አልቀረብንም እንሆ ለብርኃነ ልደቱ ደረስን። ተመስገን ሲያንስበት። ሰማዕቶቻችን እያሰብን፤ የፈቃድ ዘብ አደሮቻችን እያስታወስን አቅማችን በክብር እዬለገሰን ክብሩን በክብር እናክብር።
 
አብረን ለመዝለቅ ቅንነት በትህትና ያስፈልጋል። ግልጽነት በፍፁም ታማኝነት ይሻል፤ ሰዋዊነት በተፈጥሯዊነት ይጠይቃል። ወዶ ገብነታዊ ዲስፕሊን ልንለው እንችላለን።
 
ከዕንባ ጋር መቆም ውስጥን ይጎዳል፤ ጤናን ያጓድላል። ከቤተሰብም ሊለይ ይችላል። ብቸኝነትን ሊሸልም ይችላል። መኖርን ማኖር ባልፈቅድነው ልክ የቤተሰቦቻችን ጊዜ ይሻማልና። ቻሌንጁ ከባድ ነው። 
 
በሌላ በኩል ደግሞ የምንታገለውን ጭካኔ እና ጥላቻ በአድማ ተነስተው መኖራችን ያዋክቡታል። መታመንን የሸጡ ሰብዕናወች አደጋምይደንቃሉ። ግን አለን። ትርታችን በሱ ቸርነት ቀጥሏል። ተመስገን።
 
ስንብታችን ቢታቀድም የፈጣሪን ጥሪ ሳያሸንፍ እንሆ ልደትንም አዬን። ለዛውም የምድር እና የሰማዩን ንጉሠ ክርስትስ። ምስጋና ለአማኑኤል።
 
አለሁኝ። አወን አለሁኝ። የነጮችን አዲስዓመትም፤ የውስጤን ማተባዊ ብርኃነ ልደትንም አዶናይ አሳዬኝ። አለሁኝ! ኑሩልኝ ከእኔ ጋር የዘለቃችሁ ውስጦቼ ጽናቶቼ። እንኳን አደረሳችሁ። አሜን።
 
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ"
ሥርጉትሻ 24/06/01

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።