ዘቢቤ የነባቢቴ ቃናዬ!
ዘቢቤ *** „የወርቅ እንኮይ በብር ፃህል ላይ የጊዜው ቃል እንዲሁ“ (ምሳሌ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፭ ቁጥር ፲፩) ከሥርጉተ ሥላሴ 14.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ሽው አልሽኝ ... ሽው፣ ከአፈሬ ጋር ትዝ አልሽኝ ... ትዝ፣ ከመዝሙሬ ጋር። አንች ወ/ሮ እሜቴ የብሩህ ራዕይ ጉልላቴ የወልዮሽ ማዕዶቴ። የእኔ ወዳጄ፣ እንዳት-ወጭብኝ ከእጄ ልማጸንሽ ይሆን ጀግንነትን ሰድጄ?! ዘ ተስፋዬ ነሽ ፍጹም ገዴ ቢ የመልካም ዜማ ነዶዬ ቤ ተፈጥሮዬ ነሽ ልዩ ዘወዴ። መሸብያዬ የዓምዴ የምህረት ዝናር ዬዓውዴ የህልውናዬ ቀና መንገዴ። ሽው አልሽኝ ... ሽው፣ ከመንደሬ ጋር ትዝ አልሽኝ ... ትዝ፣ ከመዝሙሬ ጋር። የምንጊዜም ልዕልቴ የጫጉላ ጊዜ ስስቴ የዕድሜ ልክ ክታብ ህብስቴ ፍቅረ ዕድምታ መስታውቴ። ዘ ቢ የአዝምራ ማሳ ማዕዶቴ ቤ ሙቀተ-ማህጸን የዕትብቴ ወላንሳዬ የእኔነቴ ተቋሜ።