#ሰንበተ ለአይዟችሁ!

 

#ሰንበተ ለአይዟችሁ!
 
ከቀያችሁ የተነቀላችሁ፣
መጠጊያ ያጣችሁ፣
በግፍ የተደፈራችሁ፣
በበሽታ ላይ ለካቴና የተዳረጋችሁ፣
በዬጫካው፣ በዬስደት ድንኳኑ አራሽ አልባ ዕንባማዎች
ሰቀቀን አይታችሁ መኖርን የሸሻችሁ ምንዱባን፣
በግፍ የታገታችሁ፣ የተሰወራችሁ አሳረኞች፣
መሽቶ እስኪነጋ በጠላት ወታደር የበቀል ፍጥጫ መተንፈሻ ያጣችሁ መከረኞች፣
ቤተሰብ የተበተነባችሁ፣ የእንግልቱ ቤተኞች፣
በማያባራ የእርስበርስ ጦርነት ለተጎዳችሁ፣
በሜዳ ላይ የተበተናችሁ ህፃናት፣ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣
በኢትዮጵያኒዝም ምክንያት ግማድ ተሸካሚዎች፣
ለዕለት ኑሮ፣ ለእራፊ ጨርቅ ያልበቃችሁ የጠኔ ቤተኞች፣ አይዟችሁ!
ኢትዮጵያን የፈጠረ አምላክ መልስ አለው። መልሱ ካሳ ዋጋ አይጠይቅም። ፀሎት እና ምስጋና ብቻ።
በዓለም የጭካኔ ዓይነት ተሞክረው የከሸፋ ጃርታዊ ተግባር ሁሉ እንደ ጥንቸል በምትሞከረው ኢትዮጵያ ተከውኗል። ኢትዮጵያ #የህሊናዋ #ቤተ - #መቅደስ ልጅ ትሻለች።
ይህን ይሰጣት ዘንድ እንፀልይ። ሰው ነን እና እኛም እንደክማለን። ትተነውም እናልፋለን። ፈጣሪ ግን አይተዋትም።
እናታችን አሁንም የምትኖረውም በኪነ - ጥበቡ ነው። ቅን ደግ ሩህሩህ አዛኝ መሆን ብቻ የመዳን መስመር ነው።
የፊቱን የጀርባውን አትዩ። በተሰጣችሁ ልክ ብቻ ሁኑ። ትዕዛዝ አይደለም አስተያዬት እንጂ።
እራስን ከማጣት በላይ አደጋ የለም። እራሳቸውን ያጡ ዓይንም፣ ህሊናም ቢኖራቸውም ግርድ ነው። እነሱን ማዬት አይገባም።
ከእነሱ ጋር መፎካከርም አይገባም። ጠቃሚው በመክሊት ውስጥ እራስን ሳይሸሹ መኖር ነው። ለፍቅር ፍቅር ለመስጠት ስስታም ቆጥቋጣ አትሁኑ። ለግሱ በተሰጣችሁ ልክ። አይከፈልበት።
ቢያንስ መኖርን በጨካኞች ለተቀሙ እንዘን። ተፈጥሯችን አናሰድደው። ፈጣሪ አምላክ በቃችሁ ይበለን። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
24/01/2021.



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።