30የተኛ ሸክም ዘመን። በለሽታ ልምሻ አሻራ፤ በአልቦሽ ሌጋሲ ለለሽታም አሸኛኜት ……… ተቀለደ። ነገ ደግሞ ገራገሩ አማራ ያልተዘመረለት ትለን ይሆናል፤ ልታጀግን ስትፎክር ትገኝ ይሆናል፤ መጥኔ ብለናል።

 

30የተኛ ሸክም ዘመን። በለሽታ ልምሻ አሻራ፤ በአልቦሽ ሌጋሲ ለለሽታም አሸኛኜት ……… ተቀለደ።
ነገ ደግሞ ገራገሩ አማራ ያልተዘመረለት ትለን ይሆናል፤ ልታጀግን ስትፎክር ትገኝ ይሆናል፤ መጥኔ ብለናል።
ሲነሪቲ መነቀል ለስሜናዊ ፖለቲከኞች እንጅ ማህበረኦነግን አይመለከትም።
 May be an image of 5 people and phoneMay be an image of 9 people and text
 May be an image of ticket stub and textMay be an image of 5 people, people smiling and textMay be an image of 5 people and textMay be an image of 2 people and textMay be an image of 1 person, child, smiling, tree and textMay be an image of 1 personMay be an image of 1 person and text that says 'STOP VOLENCE the The world Shoul know the brave and the Hero Asmra Her Na me is Asmira Shumye! She escaped from the Oromo Terrorist Group n Ethiopia & spent 3 nights in a jungle hanging on a tree! Sheis he is now a voice for the remaining kidnapped 13 girls and 4 Boy University students.'May be an image of 2 people and childMay be an image of ‎4 people and ‎text that says '‎مه 83% 12:20 PM facebook Yohannes G Yoha 6h 6h የአማራን ትንሣኤ የሚጠብቁ ግፉዓን Tesfa Media 1 Like Comment Send‎'‎‎
አዛውንት የኦነግ ፖለቲከኞች አሁንም ሥልጣን ላይ ናቸው። ስለዚህ መተካካት የሚለው የኮኔፊውዝድ ዕሳቤ የድቡሽት ቤት ይሆናል።
የሆኖ ሆኖ ዘመናቸው በልዝ እንጨት የምመስለው የአቶ ደመቀ መኮነን ሽኝት ወይ አይነድ ወይ አያነድሆኖ የባከነ ዘመን ነው። ለትውልድም አብነት የማይሆን ያልሆነም። 
 
የምዕራፍ ፲፩ ማጠናቀቂያ ወጋወግ።
እግዚአብሄር በአንድም በሌላም
ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም
እንዴት ነን? አቶ ደመቀ መኮነን ሙሉ 30 ዓመት በቅኑ ዬአማራ ህዝብ ውክልና፦ በተደላደለ ኑሮ እና ምቾት ቤተሰባዊ ኃላፊነታቸውን በሚገባ ተወጥተው፤ ለዛ ክብር እና ልዕልና ላበቃቸው ፍፁም ደግ፤ ፍፁም ሰው አማኝ፤ ፍፁም አክባሪ የአማራ ህዝብ ከቀዩ በዬዘመኑ መነቀሉ አልበቃ ብሎ፤ በድሮን ጭፍጨፋ እንዲያልቅ፤ ገዳማውያን በገፍ ሲገደሉ፤ ልጆች በወጡበት ሲቀሩ፤ ህዝብ በስጋት ረመጥ ሲቀቀል፤ በጠኔ ሲርገበገብ፤ እሳቸው ከገበርዲናቸው ጋር ይቆለማመጣሉ።
 
የአማርን ህዝብ በግዞት ይኖር ዘንድ፤ ተተኪ እንዳያፈራ ቀንበጥቹ ለሁለገብ አሳር ሲዳረጉ፤ በድህነት ለመኖር ሰላሙ ሲነጠቅ እዬኖሩ ያልኖሩም ያላኖሩም ሰው ናቸው አቶ ደመቀ መኮነን። ተንሳፋፊም ነው የነበሩት። በእንድም ዬኮሚቴ ሰብሳቢነታቸው ውጤታማ አልነበሩም። የሚገርመው ዛሬ ከአለምንም ኃላፊነት እና ተጠያቂነት በሽልማት ተንሳፋፊነታቸው ባለማህተም ሆኗል። #ሲነሪቲ የሚባል ደመኛ ያላቸው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊም ስልችት ያላቸውን የአቶ ደመቀን ገጽ ጥዋት ማታ ከማዬት #እፎይ ብለዋል። እርካታቸውን ሲያጣጥሙም አድረዋል።
 
አቶ ደመቀ መኮነን የረጉ ናቸው። ጭምትም ይባላሉ። ርጋታም ጭምትነት ሲበዛ ግን #ፍዝ ወይ #ቦዝ ይሆናል። ህወሃትን አሽኮኮ አድርገው ሲያረገርጉ ብዙ በጣም ጥፋቶች ደርሰዋል። እሳቸው ለቢዝነስ ሰወች ትንሳኤ ናቸው ቢባልም ለሰፊው የአማራ ህዝብ ግን አለቅት ናቸው። አማራ ወኪል አለው ከመባል ውጪ የፈዬዱት አንድም የርትህ መስመር የለሚ። የኢትዮጵያ እስር ቤቶች ትናንትም ዛሬም ቲፍ ያሉት በአማር ነው።
 
በዘመነ ህወሃት የሰሩት ሽምቅ ሸምቀቆ አልበቃቸውም አቶ ደመቀ መኮነን። ለኦነግ መንገዱን አስልተው፤ ሁለመናቸውን ሆድ ዕቃቸውን ሳይቀር አስረከቡ። አብረዋቸው የባተሉትንም ጓዶቻቸውንም እስከ ወላጆቻቸው ድረስ በሰማዕትነት ሸኝተው በከረባት፤ በገበርዲን፤ በልዩ ፕሮቶኮል ጥበቃ ሲዘናከቱ ባጅተው አሁንም ወደ ተደላደለ ኑሯቸው አማትረዋል። ለአማራ ህዝብ ዕድል ከርቻሚ ብረት መዝጊያ ሆነው ለማህበረ ህወሃትም፤ ለማህበረ ኦነግም አገልግለዋል። ወቀሳ እንዳይቀርብባቸው መስጥረው በያዙት ብልጥነት ዝምተኛ ተብለው ኑረዋል። አንድ ቀን #ሳይፀፀቱ፤ አንድ ቀን በገፍ ሞት ከተፈረደበት ህዝብ ድንኳን ተገኝተው አይዟችሁ ብለው #ሳያጽናኑ፦ ከአንደበታቸው #አይዟችሁ ሳይወጣ በፍሰኃ፤ በሐሴት አለቃቸው ያሻቸውን ይፈጽሙ ዘንድ ድር እና ማግ ሆነው ሲያገለግሉ ኖረዋል።
 
ለዚህ የእርግማን ዘመን እሳቸው እራሳቸው ተጨማሪ እርግማን ናቸው። ሙሉ ስድስት ዓመት ቹቻ፤ ሰኔል፤ ካቴና፤ ዕገታ፤ መስቃ፤ መፈናቀል፤ ማህበራዊ ድህነት ሲዘንብበት ለባጀው በክልሉም፦ ከክልሉ ውጪም ለሚኖረው የአማራ ህዝብ አንዲት ሰዓት ከጎኑ ሳይቆሙ መሰንበቱ በስንብት በሽልማት ተወራረደ።
 
#አሻራ የአቶ ደመቀ ማፊ፤ 
 
#ሌጋሲ የአቶ ደመቀ {}የሚባል ሳይኖር መኖራቸው በአልቦሽ እንሆተጠናቀቀ። መኖራቸው ዘሃ ግራው #ሽሽት ነው።
ኃላፊነትን በመሸሽ በራሳቸው ዬመኖር ዛብያ ሲሽከረከሩ በቅኔዊ ንግግር "ቁመና፤ የላስታ አለት" በሚሉ አስመሳይ ጌጥማ ቃላት መኖራቸውን #ሲደልሉት፤ እና ሲያስደልሉት ኖረዋል። 
 
ያተረፋት ልጆቻቸውን በተረጋጋ ቤተሰባዊ አስተዳደር ማስተማር እና ለቁምነገር ማብቃት፤ በትዳራቸው መዝለቃቸው ብቻ ነው። ይህንን የባይወለጂ መምህርነታቸውን ገፍተውበት ቢሆኑ እንኳን የማያጡት ዕድል ነበር። #ቅባቸውን አባክነው #ያመከኑ ሰው ናቸው። ፈቅደው ያደረጉት ስለሆነም ሊታዘንላቸው አይገባም። 
 
አቶ ደመቀ መኮነን በሙያቸው ቢበረቱ ሳይንቲስት የመሆኑም ዕድል ሁሉ ነበራቸው። እንደ ባይወሎጂ ተማሪነቴ ባይወሎጂ ተፈጥሯዊነትን የሚያስክድ አለመሆኑን አውቃለሁኝ። ባይወሎጂስት ከአረመኔወች ጋር አብሮ፤ ለጨካኞች ጥላ ከለለ ሆኖ ሙያን ግዞተኛ ማድረግ ምድራዊም ሰማያዊም ሐጢያት ይመስለኛል። ብዙ በጣም ብዙ በወንጀል የሚያስጠይቅ እኛ የማናውቃቸው ክስተቶችም ይኖሩ ይሆናል። ጓዶቻቸው በባዕታቸው ተጨፍጭፈው ሲገደሉ እሳቸው ዋሽንግተን አቶገዱ አውሮፓ ነበሩ። የአቤል ዕንባ ምንጊዜም ይጮኃል። ደጉ አማራ አሁን ደግሞ ይህን አሉ፤ ያን አሉ እያለ ያጀግንም ይሆናል። አለቃቸውጅል፤ ጅላጅል፤ ጅልአንፎ የሚሉትን ማስተዋል የነሳውን ለበዳይ ጋሬነትንም ነው።
 
#ከቶ ………
በዚህ ሁሉ የመገፋት፤ የመጨነቅ፤ መኖርን የመዘረፍ ዘመን በአማራ ህዝብ ተወክሎ በቦታው አለመገኜት መታመኑን ማቃጠል፤ ኃላፊነቱን መሰባበር ለህሊና እረፍት ይሰጥ ይሆን???
 
በክፋም በደጉም ቢያንስ የፓርክ ፕሮጀክተር በመሆን ከሳቸው በታች የነበሩት ጠሚ አብይ አህመድ አሊ አለኝ የሚሉት አላቸው። ሳይንስ እና ቴክኖሎጂም ሚር ሳሉ የተሻለ ሰባዕዊነትም ነበራቸው። እዛም መጠሪያ አላቸው። ባለ ኖቤል ተሸላሚም ናቸው። አቶ ደመቀ ግን ሰምቼው እማውቀው መጠሪያ የለም። አንጋችነት ብቻ። አልቦሽ። ዘመን መቁጠር። ኃላፊነት እና ተጠያቂነትን ቁሞቀር ያደረጉ፤ ለትውልድ የሚሆን ቆራጣ አብነት የሌላቸው ሽሽትን የሙጥኝ ብለው የኖሩ ብልጥ ሰው ናቸው። እንኳንስ ከቅርብ ላለ ለእኛ ለሩቆችም የሰባዕዊ መብት ጥሰቱ፤ እና የተፈጥሯዊነት እርግጫው ወላፈኑ፤ ወጨፎው ረፍት ነስቶን ይኽው ዘመን ተዘመን እንባትላለን።
 
ምጠሚ// የውጭ ጉዳይ ሚር እነኝህ የኃላፊነት ቦታወች #ማቆያ እንጂ ጠቅላዩ ጠቅልለው የያዙት ነበር። አሁን ከሆነ ደግሞ የጠቅላይ ሚሩ የውጭ ጉዳይ ልዩ አማካሪነትን ጨምሮ የአቶ ደመቀን ኃላፊነት ዬጠቀለሉት ጮሌው አቶ ሬድዋ ሁሴን ናቸው። አቶ ደመቀ መኮንን ግን ተንሳፈው ባጁ፤ በተንሳፋፊነት ፍፃሜ ተሆነ። ታሪኩ ይኽው ነው። የሚነሳ አንዳችም መልካም ነገር የለም።
ከጨካኞች ተርፋ የመጣችውን ገራገሯን አስምራ ሹምዬን እንኳን መታደግ አልቻሉም አይደለም ሌላውን። የኮሚቴው ሰብሳቢ ሆነው ወላጅ አናጋሪም ነበሩ። ይህ ሁሉ የአማራነት ቤት ንብረት፤ ጥሪት እና አንጡራ ሃብት በበቀል ሲወድም ሰውዬው ኡራኖስ ላይ ነበሩ። አጣዬ እኮ 11 ጊዜ ነው የነደደችው። 
 
አቶ ደመቀ መኮነን በታመቀ ፍላጎት፤ በታፈነ አጀንዳ፤ በድብቅ መሻት የአማራን ህዝብ ገደል ለገደል፤ ከጨለማ ወደ ጨለማ ሲያጓጉዙ ነው የባጁት። በቀላቸው ሆነ ቂማቸው ከምኑ ላይ እንደተነሳ አላውቅም። ሽምቅ በቀለኛ፤ ሽብልቅ ቋሰኛም ይመስሉኛል። ከእናትም እናት የሆኑ የአማራ እናቶች ማህፀናቸው ሙሉ 32 ዓመታት ሉካንዳ ቤት ሆኖ ነው የኖረው። አቶ ደመቀ መኮነን ኖሩም ተሸኙም ለአማራ ህዝብ የሚፈይደው አንዳችም ቁምነገር የለም። የባከነ ዘመን ነውና።
 
ለውጥ መጣ ሲባል #አንቦ ተገኝተው ቄሮን ጀግና ሲሉ አማራ ክልል ላይ ግን አልነበሩም። እንዲያውም በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ያ100 ቀናትጉብኝት ውስጥ በአብዛኛው ቦታ አቶ ደመቀ ተገኝተዋል። አማራ ክልል ግን አልተገኙም። ለምን ብዬ ፁሁፍ በወቅቱ ጽፌያለሁኝ። 
 
ዲያስፖራው በገፍ ሲገባም የአደለው የገጥ ለገጥ ግንኙነት እና የሆቴል እርዳታ አስድርገውለታል። መጓጓዣም እንዲሁ በክብር ትኬት ተጓጉዟል። ከዛ ውጪ አንድም የአማራ ዲያስፖራ ሊቅ በብሄራዊ፤ በአህጉራዊ፤ በዓለማቀፍ ድርጅቶች ቦታ አልተሰጠውም። ልባሙ ቲም ለማ ግን ከውጭ ላስገባቸው ሁሉ ሙሉ ኃላፊነት ያላው ቁልፍ ቦታ በብሄራዊ፤ በአህጉራዊ እና በዓለም ዐቀፍ ደረጃ አሰጥተዋል። ይህ ክስረታዊ ሂደትም የአቶ ደመቀ መኮነን አማራዊ ቃና ያሻግተዋል። እኒህ ሰው እርግጥ አማራ ናቸውን ብለን እንድንጠይቅም ያስገድዳል።
 
የአለም ዲፕሎማሲ ከተማ አዲስ አበባ አይሆኑ ስትሆን ሰውዬው #አብሰንት ናቸው። ደቡብ ሲሸነሸን ሰውዬው ጁቢተር ላይ ናቸው። ኢትዮጵያ መኖርን ለማስተናገድ ጣር ላይ በመሆኗም እሳቸውን አይመለከትም¡ ዛሬ 100 ኪሎሜትር ከርዕሰ መዲናዋ ወደሌላ መጓዝ አይቻለም። በዚህም ሰውዬው አይገዳቸውም። ደንታ አይሰጣቸውም። ተሽሞንሙነው መንጎባለል ብቻ።
 
በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ይህ ሁሉ ማት ሲዘንም፤ የአደባባይ በዓላት እራፊ ባዕት ሲያጡ፤ ሲዋከቡ፤ በአማርኛ ቋንቋ ላይ ይህ ሁሉ አሳር ሲዘንብ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የምፃዕት ሁነት ሲከሰት አብያተ ቤተክርስትያናት ሲነዱ፤ ካህናት ሲገደሉ፤ ቤተመቅደስ ሲደፈር፤ በአብሮነት፤ በታሪክ፤ በትሩፋት ተቋማት ላይ #ዲሞግራፊ አና ሲል እሳቸው ሞድ ሾው ላይ ልባቸው ጥፍት ይላል። ገበርዲን እና ከረባት ዊዝደም ይመስላቸዋል። ሰው ተገድሎ ተዘቅዝቆ የተሰቀለበት ባዕት ውስጥ ምክትል ጠሚር እና የውጭ ጉዳይ ሚር፤ መባል ለእኔ ዱላ ነው። "ቂጥ ገሊቦ እራስ ተከናኒቦ" እንዲሉ።
 
አቶ ደመቀ መኮነን አለባበሳቸውን አሳምረው ሲንጎባለሉ ኢትዮጵያን ያህል ገናና የአፍሪካ አንከርን አገር እዬመሩ ያሉ ይመስላቸዋል። ክንውናቸው #አጓጉል እና #የጓጎለ ስለመሆኑ ትዝ ብሏቸው አያውቁም። ለራሳቸው በጥንቃቄ ኑረው በራሳቸው ዛቢያ ተሽከርክረው #ከተነሱበት መነሻቸው ላይ መዳረሻቸው ሆኗል። አሁን ከቅምጥሉ ማረፊያቸው በሙሉ አገልግሎት ወህ ብለው መኖርን ይቀጣጥሉታል። ምን አልባት ከሱናሜው ከተረፋ። 
 
ጎረቤት ባይስማማ ይለቀቃል፤ አገር ባይመች ይሰደዳል፤ ትዳር ባይቀናም ይፋቱታል። ህሊናንስ? ዕድሜ ዘመናቸው እንዲጨምር ይመኙ ይሆን አቶ ደመቀ መኮነን? ለትዳራቸው እና ለልጆቻቸው ብቻ ነው የኖሩት። አሁንም ለእነሱ ቢኖሩላቸው መልካም ነው። ግን ከሥነ ልቦና በሽታ ነፃ ይሆናሉ ብዬ አላስብም። መሪነት በማይቻልበት ጊዜ የማይቻለው ተጋፍጦ ህዝባዊ አገልግሎት መስጠት እንጂ የአድርባይ ፍልስፍናን እያቆላመጡ ኤንም እንዳይከፋው፤ ቢንም እንዳይከፋው እና መኖሬ እንዳይጎሳቆል ሰይፍላይ አልራመድም ብሎ ከ45 ሚሊዮን በላይ ነው የሚባለው የአማራ ህዝብ ድምጽ ክዶ መኖር የሥልጣን #ዘማዊነት ነው።
 
የህዝብ አገልግሎት እንዲህ ተቀልዶበት፤ እንዲህም ተንጨባርቆ ካለ ተጠያቂነት መሸኜት ወፍ ያውጣው ወይንስ ምን እንበለው ይሆን? ለዚህ የዛገ፤ የሻገተ፤ የማረተ የማጭበርበር እና የማስመሰል የሥልጣን ዘመንስ???? ሥም ይገኝለት ይሆን? አሳቻ ሰብዕና በአሳቻ ዘመን የለሽታ ልምሻ 30 ዓመታትን የተኛ ዘመን ብለውስ???
 
በመጨረሻ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ የአቶ ደመቀ መኮነን ገጽ ማዬት ስልችት ብለወት ስለነበር እንኳን ደስ አለወት! ሌላስ የቀረ በሲነሪቲ የሚበልጠወት የኢህአዴግ ቅርጥምጣሚ ይኖር ይሆን????
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ውዶቼ ምዕራፍ ፲፩ በዚህው ይቋጫል፤ ምዕራፍ ፲፪ ከጥሞና መልስ ይሆናል። ቸር ሁኑልኝ። ቸርእንሰንበት። ቸር እንመኝ። ቅን እንሁን። ተስፋችን አምላካችን ብቻ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
2024/27/01
ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።