24.01.2020 ርህራሄ የመከነበት ዘመን።

 

ርህራሄ የመከነበት ዘመን።
 No photo description available.
የአማራ ህዝብ እያዬው ይመስለኛል አብይዝምን። የአማራ ሊሂቃን የተገደሉበትም አመክንዮ ፈጧል። የኢታ ማጆር ሹሙ ምክንያታዊ ግድያ እዬታዬ ነው። በዚህ ሁሉ ሰቆቃ ውስጥ ገዳይን መንፈስ የኢትዮጵያ አዳኝ አድርገህ ትፅፋለህ ትሞግታለህ። ማይክ ላይ ወጥተህ ትፈላሰፋለህ።
 
ይህን ስሰማ እነዚህ ሰዎች መጠቁ ይሆን እላለሁኝ? ሌላው ሊሂቅ ይመጣና እከሌን እመን አታውቀውም፣ እከሌን እመናት አታውቃትም ይልሃል። ሌላው ደግሞ ከአውጊ አደራ ጋር ፎቶ ተነስቶ ጀገንኩ ይልኃል።
እነዛ በበላህሰብ ፍዳቸውን እዬከፈሉ ያሉ ነፍሶች አይመለከታቸውም ለኦነግ ካድሬነት ለተሰለፋ ዘመን ሰጥ ተደማሪ አንደበቶች እና ብዕሮች። ማፈሪያዎች።
የገዳይ መንፈስ አቅም እኮ ጠሚር አብይ አህመድ ናቸው። ትናንት የዴያስፖራ አንበሳ ነኝ ብሎ ሜዳ አይባቃኝ ሲል የነበረው ዛሬ ድርጭት ሆኗል አገር ገብቶ።
አገር ቤት ድርጭት ሆኖ ዘመኑን የሸኜው አገር አይባቃኝ ብሎ እንደጎረምሳ ይዘላል ይፈርጣል። በዚህ ማህል አገር በጨካኞች ታግታ ፍዳዋን ታያለች። ዥንጉርጉር።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ቸር ወሬ ያሰማን አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።