ብልፄው የደግነቱ ልክ ለፓርላማ የክብር አባልነት #በቻሪቲ። #በምደባ አገር ምድሩን አንበሸበሸ። ኢትዮጵያም የአማራ ህዝብም ሚስ ያደረጓቸው ጨዋ፤ ጭምት፤ አስተዋይ ሰብዕና።
ኢትዮጵያም የአማራ ህዝብም ሚስ ያደረጓቸው ጨዋ፤ ጭምት፤ አስተዋይ ሰብዕና።
#አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
#ምዕራፍ ፲፱።
https://www.youtube.com/watch?v=I_7EVUEbSqE
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ያልቀናቸው ዶክተር አበባው ደሳለው ውጤቱ ያልጠበቁት መሆኑን ተናግረዋል | Abebaw Desalew | Ethiopia Inisder
ብልፄው ለውስጦቹ የፓርላማ ወንበር #ቻሪቲ በ7ኛው ምርጫ ገፋ አድርጎ አንበሽብሿቸዋል። መጠራቅቁ ከተቻለ። ወጥ ሃሳብ። ወጥ ፍላጎት። የሁሉ እሽታ እና ይሁንታ በገፍ ……… የማያጓጓ የማይስብ ይሆናል። በድርጅታዊ ሥራ ሞጋች ተሁኖ ሊወጣ ይችል ይሆናል። ያለፍጥረቱ ያለልኩ የተሰፋ እጀ ጠበባ ወይንም ጥብቆ ይሆናል። እራስን የሚያጸናው የራስ ጥረት ብቻ ነው። በሙሉ ጥገኝነት እና ጥገና እራስን ለማግኜትም፤ ሆነ ለመሆን ጋዳ ይሆናል።
#ዕፍታ።
ለሰከነ፤ ምራቁን ለዋጠ፤ ጥድፊያን ሃራም ለሚል ሰብዕና የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፎርማት የሚመች አይመስለኝም። ምክንያቱም ሴራ ገብ፤ ኢጎ - ገብ ስለሆነ። የ6ኛው አገራዊ ምርጫ ተካሂዷል። ተጫኝ ሁነቶች የተደራጄ ቀውስ ግብዓቶች የፍርሃት፤ የስጋት፤ የጭንቀት ጫና ነበር። ከዘንድሮ ግን የተሻለ የነበረ ይመስለኛል። የ7ኛው አገራዊ ምርጫ #ምደባ ነው።
ብልፄው ሁሉንም ተቆጣጥሮ በሥሩ ያስተዳደረበት እና ቦታወችን አቅዶ የደለደለበት ሁኔታ ነው የታየው። ውጤት ለመንገር መዝግየቱም ለዚያ ነው። ፌስታውን ተመልክቻለሁኝ። ይህ አይጠቅምም። እራስን መሸንገል ስለሚሆን። ዕውነትን ሳይሸሹ በዕውነት ልክ እራስን አርሞ ወደ ትክክለኛው ኃላፊነት እና ተጠያቂነት መግባት የተገባ ይመስለኛል። ዕውነት ቅርፊት አይደለም እና።
ስኬት ቀጣይነቱ በዕውነት፤ በፋክት አቅም ስለሆነ። በሻሻ ላይ ምርጫ ተካሄዷል። ጠቅላይ ሚሩ አሸነፋ ያስኬዳል። ሰቲት ሁመራ ላይ ብልጽግና ካለምንም ድርጅታዊ ሥራ 100% አሸነፈ ያሳምነኛል። ሌላ ቦታ ግን ምደባ ነው። በተለይ ከብልጽግና ውጪ ላሉ ፓርቲወች የተሰጠው ቦታ። ፖለቲካ ብልህነት ያዘልቀዋል። ብልጠት ግን። እእ። ምንም ድርጅታዊ ሥራ ሳያስፈልገው እኮ ብልፄው 50+ የማግኜት ዕድል ነበረው። ሁኔታወችን ስከታተል ስለነበር። ጽፌበትም ነበር። ምርጫውን "ፍትኃዊ፤ ነፃ፤ እኩላዊ" ቢያደርገው። ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ አይታሰብም። ታዛቢወች ዴሞክራሲ ሲሉ እደነግጣለሁኝ። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ገዢው ጠበንጃ ነው።
"#ክቡር"
ይህ የክብር ሥም ለተከበሩ ዶር አበባው ደሳለኝ ልካቸው ነው። ደርባባ እና ደልዳላ ስለሆኑ። የሆነ ሆነ በዶር አበባው ደስአለኝ የፓርላማ እጩነት ስኬት አለማግኜት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስሪት ለወጣቶች፤ ምራቁን ለዋጠ ሰብዕና ምቹ እንዳልሆነ ቢታወቅም፤ በዘርፋ ጥቂትም ቅርጥምጣሚ ዕድል እንደለለ ተገንዝቤያለሁኝ። ኢትዮጵያም እንደ አገር፤ የአማራ ህዝብም እንደ ህዝብ ሚስ ያደረጓቸው ናቸው።
እኔ የኢትዮጵያ የምርጫ ሁኔታ የማልጠብቀውን ነፃ፤ ፍትኃዊ እና ዴሞክራሲ ሳያሟላ መካሄድ የለበትም ብዬ አላምን። ፎርሙላ ነው። ስለዚህ በለመደው መስመር ምርጫው ተካሂዶ ኢትዮጵያ አገሬ መንግሥት አላት፤ ህዝቡም መንግሥት ያለው ህዝብ ይባል ዘንድ ምርጫው መካሄዱም፤ በሰላም እንታገላለን የሚሉትም ይሳተፋ ዘንድ በትህትና አሳስቤያለሁኝ።
ኃይለ ቃልም ጨምሬያለሁኝ በተለይ ለኢህአፓ ዕድላችሁን አታፍስሱ ብዬ። አናርኪዝምን እጅግ በጣም ነው እምፈራው። የመንግሥት መኖር ይህን ስጋቴን ያስቀርልኛል። ለዘመናት የመንግሥት ሥርዓት ውስጥ ለኖረች አገር ለጥያቄ የሚገባ አይደለም።
የሆነ ሆኖ ምንም የማያንሳቸው፤ ብቁ፤ የተማሩ፤ ዲስፕሊናቸው መምህር የሆነ፤ ለስኩን ፖለቲካ ሮልሞዴል ሊሆኑ የሚችሉ ክቡር ዶር አበባው ደስአለው የፓርላማ ውድድራቸው እንዲህ መጨንግፋ ከውስጤ አዝኛለሁኝ። ሃዘኔ የምር ነው።
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ "#ይሁነን ብለን" ያሉት ቃልም #መና መቅረቱን አይቸበታለሁኝ። ለጨዋታ ማሟያ ነበር ማለት ነው። አንድ የአገር መሪ የሚናገረው #ፖሊሲ ሊሆን ይገባል። ቃሉን ጠብቆም ማስፈጸም ይሁን መፈጸም ግዴታው ነበር። የመሪነት ቅርጹ ሳይሆን ይዘቱ የሚለካውም በሚለው ውስጥ የተግባር ሰብሎቹ ተለክተው አብላጫ ሚዛን ሊመቱ ይገባ ነበር።
የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ ብቁ የሆኑ የተሳትፎ ፍላጎታቸውን እንዲህ በመጫን፤ በመሰልሰል ነገን በፈካ ገጽ መጠበቅ አይቻልም። አንድ ብቁ ፖለቲከኛ ከህዝብ የሚያገኜው ድጋፍ እና ፍቅር ሞተሩ ነው። በራስ የመተማመን አቅሙ ምንጩም በጥረቱ ልክ ሲያገኝ ነው።
እኒህ ወጣት ፖለቲከኛ ሃሳባቸውን በፓርላማ ሲያቀርቡም ህግን ሳይተላለፋ በቁጥብነት፤ በሰከነ ለዛ፤ ዕውቀታዊ በሆነ አቅም ነው። ግብረ መልሱ ወጨፎ ነበር። የፓርላማ ቆይታቸውም በእዳሪ ልጅነት በግልምጫ እና በማሸማቀቅ፤ ፊት #በመንሳት በግለትም እንደ ነበር አስተውል ነበር። እኔ ካደመጥኩ ይሁን፤ ካየሁ ከውስጥ ነው የምከታተለው።
የተከበሩ ዶር አበባው ደስአለኝ "#የተከበሩ" ብዬ ልጠራቸው የሚያስችል ሰብዕና ያላቸው ጠንቃቃ፤ ርጉ የነገ ኢትዮጵያ ሙሉ ተስፋ ሊሆኑ የሚችሉ ፖለቲከኛ ናቸው። አብን ለኢትዮጵያ አበረከተ ብዬ የማስበው የዲስፕሊን ልክ በዶር አበባው ደስአለው ልክ መሆኑን አምንበታለሁኝ።
በዚህ ሂደት ብልፄው እንደ አተረፈ ሊቆጥረው ይችላል። በገዘፈ ሁኔታ የአቅሙን ስስነት እና ፍራቻ አይቻለሁኝ። ለነገሩ በሃሳብ ሙግቱ ላይም ብልፄው ቁንጮ ሚኒስትሮች አቅርቦ መመጣጠን ያለመቻል ሁነትን አስተውል ነበር። ያለ የሌለ ኃይሉን ነበር ለሃሳብ ፋክክሩ ብልፄው ያቀርብ የነበረው። ይሄ ለምርጫው ሂደት የነበረውን ዲስፕሊን ያሳየኝ ነበር። ተወካዮቹ ግን በተሠራ ቢጋር ልክ ወጥ መልስ ይሰጡ ስለነበር ሞናትነስ ነበር። ተፈጥሯዊ አቅማቸው የፓርቲያቸው ትዕዛዝ እንደ አገደው አይ ነበር።
ሌላው ለውድድር ለተሰለፋት የፖለቲካ ድርጅቶች ያልተፈቀደው፤ ለብልጽግና ብቻ የክት ልጅ ስለሆነ፤ ብልፄው የስለት ልጅ ስለሆነ ፈረሱም በሠረገላ፤ ሜዳውም ተብሎለት #በኢትዮጵያ በጀትም ለብልፄ ብቻ ሰፊ መስክ ተፈጥሮ በማስ ህዝብ ሲያንቀሳቅስ ነበር። ለተፎካካሪወቹ ደግሞ ብጣቂ ዕድል ሳይሰጥ #ከርችሞ ነበር። ይህን መመዘን የቻለው ተፎካካሪወች በምርጫው ሂደት በመሳተፋቸው ነው። ባይሳተፋ የብልፄውን ትሬኪ ፊልም ማየት አንችልም ነበር።
#ህም።
አብን በሚመለከት እስከ 6ኛው ምርጫ ትጋት ነበረው። የሚያጓጉ፤ የሚስቡ ነበሩ። ተወዳጅነቱም ግሎባል ነበር። ከዛስ? ያን የህዝብ ፍቅር የደፋውን ፖለቲካዊ ቀመር ውስጥ በጥልቀት መግባት አልሻም።
ብዙወቹ አብን አደጋ ላይ የጣለው የተሰጠውን የሥልጣን ችሮታ መቀበሉ ይላሉ። ይህ አብን በመንግሥታዊ አስተዳደር ልምድ ለማግኜት ቢጠቅመው እንጂ የሚጎዳው አልነበረም። ይታገል የነበረው እኮ ለፖለቲካ ስልጣን ነው። አባ ቸርዬ ብልፄው የፓርቲዬን ማንነት ለመገንባት ስሚንቶ አቀባይ ያስፈልገኛል ብሎ ሲመርጥ መቼም ቢገርም እንጂ የሚያሰቅቅ አልነበረም።
በ7ኛው የህዝብ ምርጫ ብቃቱ ግን ለእኔ #የሌለ ንቅናቄ ነው። ጥርት ያለው፤ ጥንቅቅ ያለው ዕውነት ይህ ነው። ከላይ ተንጠልጥሎ ያለ፤ መሠረቱ የተኒደ ተቋም #በመጠመን፤ #በመቀለት፤ #በአውጫጭኝ፤ በብልዔው ለራሱ ሲል ባደረገው ሰፊ ልግሥና የተገኜ ወንበር ሊያሸማቅቅ ሲገባ #የዴሞክራሲ መለኪያ ተደርጎ ሲወሰድ ብርቅየዋ ሳቄ መጥታ ነበር። #ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ???? ሰማይ ደጅ ያለ የኤዶም ገነት ነው። እሱ ቀርቶ በድህነት ለመኖር የዜጎች ወጥቶ የመግባት ነፃነት ህልም ባልሆነ።
አብን እንደ ተቋም ውነቱ ለብልፄው ያደረገለት አንዳች ነገር የለም። ያን የመሰለ የሚሊዮን ግሎባል የህዝብ ፍቅር መምራት ተስኖት፤ በግል ኢጎ ይሁን በስንፍና፤ በሌሎች ገፊ ምክንያቶች የልምድ የተመክሮ የደም ማነስ ችግር፤ የማድመጥ አቅም ስስነት፤ በትግል ውስጥ ያልነበረ ሰብዕና የውስጥ ኮንፊደንስ እና ደረጃው መጋጨት፤ ከሰማይ የወረደ የሥልጣን ርከን ከፍታ የፖለቲካ ማንነት ቀውስ የፈጠረበት ይመስለኛል።
ሌላው "ከጎዳና ወደ ፓርላማ" የህዝቡ አህታዊ ስኬትን እንኳን በቅጡ ማኔጅ ለማድረግ አብን አልቻለም። ይልቁንም የፌድራሉ መንግሥት ተጠያቂነት እና ኃላፊነት ዘው እያለ የሰፋ ቅራኔ ውስጥ ገብቷል፤ የራሱን የቤት ሥራ መስራት ባለመቻሉ በአብን አገኜዋለሁ ያለውን የአማራ ህዝብ ዕውነት ብልጽግና አለመሳካቱን አይቷል።
አብን ሳይፈጠር የብልጽግና መሥራቹ ጠቅላዩ እኮ ካለምንም መሥፈርት ሙሉ ይሁንታ በአማራ ህዝብ ተሰጥቶ ነበር። ይህ እኮ ቅርብ ጊዜ ነው። ለአማራ ህዝብ ግን ፊት ሰጥቶ፤ ጥያቄውን አክብሮ ደረጃ በደረጃ መልስ ከመስጠት ይልክ ወከባው ጠነከረ። እና የአማራ ሊቃናት #ጫካን ይሁን ያሉበት ምክንያት ያን አብን የአማራ ህዝብን ጥያቄ የማስመለስ አቅሙ #ሽባ ስለነበር ነው።
ምን አልባት ብልፄው አብን የልቤ ያለውም ሁለመናው ማስረከቡ ይመስለኛል። ግዴታውን ረስቶታል። በተስፈኞቹ ዘንድ ሃዘኑ ጥልቅ ነው። "ሁሉን ቢንገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል" ይላሉ ጎንደሬወች። ሚስጢር ተደፍቶ ትንፋሽ ውጪ ነፍስ፤ ግቢ ይሆናል።
የአማራ ህዝብ ጥያቄን አንሳፎ ያከሸፈ ተቋም ውለታ ፈፃሚነቱ ለማን እንደሆን ይታወቃል። የአማራ ህዝብ ትግል በህግ በተደነገገ፤ ታቅዶ የተገለለ፤ ታቅዶ ዲስክርምኔሽን የሚፈጸምበት፤ ታቅዶ ከህዝብ ቁጥር መቀነስ ፕላን ጋር ተፈፃሚ እንዲሆን ተደርጓል። ከበዓቱ በገፍ ተነቅሏል። በሃይማኖቱ ቁልጭ ያለ አሉታዊ ዴሞግራፊ ተሰርቶበታል።
ይህ አሰቃቂ ገጠመኝ ለአማራ ህዝብ ሊሆን አይገባም ነበር። ጭራሽ ወደ አራት ዓመት ድምፃቸው ያልተሰሙ የአብን ሰብዕናወች ምርጫ ዋዜማ ብቅ ብለው አብን ወክለው የፓርላማ ወንበር ተገሪነት ቢያሳፍር እንጂ አስከባሪ ነበር። "የተውሶ ይሄዳል ተመልሶ" ይሆናል። አቅምህ አቅምህን ይመግባል።
የራስህ የአቅም ጥሪት ያደራጅኃል - ይመራሃል። "ክቡር" የሚል ሥምም ለጠፍ ይሆናል። የብድር ዱቄት ብቄተ ቢስ ነው። አይበረክትም። ለአማራ ህዝብ ውክል ነኝ የሚለው አብን የብልጽግና የፓርላማ ወንበር #ቻሪቲ ውስጥ ታዳሚ መሆን ይሸበሽባል። ልኩ ስላልሆነ። በግል ሥም ቢሆን ምርጫየ ነበር።
አያድርግብኝ እንጂ እኔ ብሆን በግል ነበር እምወዳደረው። ለእሱም ምን ያደረኩት፤ የሠራሁት ያሳካሁት አለ ብዬ ምላሽ ከኖረኝ ነው። ኢትዮጵያ ታላቅ ፍልስፍና አላት ይሉኝታ የሚባል። ይህን ማመሳጠር ሲያቅት?
በወልቃይት ጠገዴ፤ በራያ ህዝብ የመምረጥ መብቱን ማስከበር ይህችን እንኳን በኋላ የተፈጠረው #ሥምረት ፓርቲ ሲያስፈጽም አብን ተንጋሎ ይተክዝ ወይንም ይፍነሸነሽ ነበር። የወልቃይት - የጠገዴ - የጠለምት - የአዳርቃይ - የአዲረመጥ የራያ ጉዳይ የትም ተወርውሮ ያልታገለው ሲዳማ በክብር፤ በሞገስ ፍላጎቱ ሲፈጸም ባዶነትን ኃላፊነት ላይ ለተቀመጡ የአብን አካላት ይልካል።እንደ አማራ ቅብዓው ቢኖር ኖሮ።
ብልፄው ህወሃትን በሚመለከት አንደበቱ አብን ነው። በአብን አቋም ህዝቡ ይማገድለታል። የህወሃት ብስጭት እና የውድምት ቅያሴ አብን በማይመለከተው የፖለቲካ ዞን ላይ ስለነበረ ነው። በአብን ምክንያት የታሰሩ፤ የተንገላቱ፤ የተሰው አባል እና አካላትም ዋጋቸው ታሳቢ ሆኖ አላይም። አብን በተፈጠረበት አመክንዮ ውስጥ አይደለም።
ከብልፄው ጋር 5/6/7/8/9/10 አካላቱ ቢጠቃለሉ የተሻለ ነው። የአማራ ህዝብ ግን ያን ገድላዊ አቅሙን እና ተደማጭነቱን ለክህደት አያስረክብም። የተደራጀህበትን ዓላማ ስቶ ተፈላጊነት፤ ተከባሪነት፤ ተደማጭነት ከፋንታዚ አያልፍም።
አብን ትንፋሽ ቢኖረው እኮ ይህን ሁሉ ተዘርዝሮም፤ ተሰልቶም የማይዘለቅ መከራ የአማራ ህዝብ ባልደረሰበት ነበር። ምን ያህል ፐርሰንት የአማራ ህዝብ በዚህ ንቅናቄ አለ ቢባል ግብረ መልሱ ያሸማቅቃል። ብዙ የተደከመለት፤ ብዙ ተስፋ የተደረገበት የአቅም ቁንጮ የነበረ ንቅናቄ ዛሬ አዲስ አበባም ሳይፈቀድለት፤ ክልሉ ላይም ለጠኔው ችሮታ ከብልፄ ማግኜቱ #አለ ህልው ነው ሊያሰኜው ፈጽሞ አይችልም።
አለ ከተባለ ህንፃው እና የቢሮክራሲው ሠራተኞቹ ይሆናል። አብን እና የአማራ ህዝብ መራራ ስንብት ፈጽመዋል። ሹመኞቹ ፓርላማ ገቡ አልገቡ ለአማራ ህዝብ ሳይሆን ለራሳቸው ለብዕና አንድ ታይትል ጨምረዋል። "ክቡር" የአማራ ህዝብ በአብን #ተክዷል። በዚህ መልክ የአብን ታሪክ ሲጠናቀቅ ማዬትም መስማትም አሳዛኙ የዘመኑ ትራጀዲ ነው።
#ተጫኝ።
ሌላው የፋኖ መራራ ማስጠንቀቂያ በመራጩ ህዝብ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ ዕውነት ነው። እኔ በምርጫው የአማራ ህዝብ አለመሳተፉ ቢጎዳው እንጂ አትራፊ አይደለም። የፖለቲካ ውክልናችን ሳሳ የሚል ዕድምታ አለ በአማራ ህዝብ ዘንድ። ጠቀመም አልጠቀመም ዕድሉ ሲገኝ ደግሞ በር መዝጋት የፖለቲካ ብልህነት አይደለም። ይህ ሂደት የበለጠ የሚጎዳው የአማራ ህዝብን ነው።
ትግራይ የተጠቀመው ካለ ቆጥራችሁ ልታስረዱኝ ትችላላችሁ። የኦሮሞ ሊቃናት ተደራጄ በሚባለው ሁሉ ይሳተፋሉ። በደርግ፤ በህወሃት፤ በብልጽግናም ዘመን። በተገኙበት ቦታ ሁሉ ደግሞ የውስጣቸውን ያሳካሉ። ብልህነት ነው።
ሁሉንም የፖለቲካ ትርፍ ትተን ቢያንስ የፓርላማ ተወካይ ሲኮን መንግስታዊ አደረጃጀት፤ አመራር በተግባር መማር ይቻላል። በሌላ በኩል ቢያንስ 5 ሰው የአኗኗር ደረጃው ይሻሻላል። የምርጫ ጣቢያወችም አነሰም በዛም በፖለቲካ ውክልና አብሰንት አይሆኑም።
1) ይህም አንድ በብልህነት ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ሲሆን፤
2) ሁለትም የታሪክ ተሳታፊነትም ተመስጥሮ የሚገኝ አመክንዮ ነው።
ሌላው ለመራጩ ህዝብ ከፍተኛ ችግር የነበረው እኔንም ሲያቅለሸልሸኝ የቆየው የትብብሩ በአንድ ጊዜ ሁለት ዛፍ መውጣትን እንደ መርኽ የወሰደበት ጉዳይ የትብብሩን እጩ ተወዳዳሪወችን ዋጋ አስከፍሎታል።
ትብብሩ በምርጫው ሂደት የተስረከረከ ፍላጎት ነበረው። ህዝቡ ተሰቃይቷል። ወይ የለንም አይሉም፤ ወይ አለን አይሉም። ሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ አላችሁ ብሎ ሲያስብ "#እያጤን ነው።" የላችሁም ብሎ ሲያስብ ደግሞ የሃሳብ ፋክክሩ ላይ ብቅ ይላሉ። ለእኔ ሊገባኝ ይችላል። ብቻ በግርድፋ ሳቀርበው ለተወሰነ ቀን ቁርጠኛ ውሳኔ ለመድረስ አለመቻል ሰፊ ተጽዕኖ አሳድሯል በተወዳዳሪወች ላይ። ይህን ዶር አበባው አልተናገሩትም። ሊገልጹት ግን ይገባ ነበር።ማዕድ ቀርቦ፤ እጅ ታጥቦ፤ ጉረሱ እንጂ ሲባል ………
አሁንም "የእናጤነዋለን" ፖለቲካ ቀጥሏል። ተወዳድሮ፤ ተፎካክሮ፤ በሂደቱ በሙሉ አቅም ተንቀሳቅሶ የመረጠን ህዝብ፤ በዚህ ዙሪያ የተደከመበትን ሂደት ወደ ኋላ ተንቀሳቀስ ተብሏል? ስም የለሽ ገጠመኝ። ነው። ምርጫው ላይ እራሳቸውን ማግደው ለትብብሩ ድምጽ የሰጡትን ሁሉ አድራሻ ቢስ ማድረግ አይጠቅምም።
በልጅነቴ በጣም አኩራፊ ነበርኩኝ። አልበላም ዋነኛው የኩርፊያዬ ማስፈጸሚያ ነበር። እናቴ እቭየ ሆዴ "ላም እረኛ ቢያኮርፍ ምሳው እራቱ" ይሆናል ትል ነበር። ለፓርላማ ሁለት እጩ ነው ብልፄ ለትብብር የፈቀደው። ያ ሁለት ወንበር የሚፈጥረው ተጽዕኖ አስሉት።
ተጎጂው ሆነ ተጠቃሚውንም መርምሩት። በውስጥ ሆኖ መታገል እና ውጭ ሆኖ አቤት ማለት እኩል አድማጭ አያገኙም። የፓርላማ አካል መሆን ማዕረግ ነው። ሞገስ ነው። ምደባም ቢሆን።
ተመራጭ ጥርት ያለ አቋም፤ ያልተወላወለ ውሳኔ ይዞ መግባት ሲገባ በተለዋዋጭ አቋም የህዝብን ህሊና ማዋለል ቃሉን ባልጠቅሰው ይሻላል ስለሚጎዳ ውስጥን። ተሰቃዬ ህዝባችን። ሌላው በሚታለመው ልክ ፖለቲካዊ አቅም ይጠይቃል። ሙሉ አቅም። ሙሉ ልምድ ወደ ተመክሮ ሊያድግ የሚችል ገጠመኝ ያስፈልጋል።
ምኞት ሊኖር ይችላል። የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬ ሊደመጥ ይገባል። ማን አቅም እንዳለው እና እንደሌለው፤ ማን ዲስፕሊን እንዳለው እና እንደ ሌለው ሳይለንት ማጆሪቲው ያውቀዋል። ምኞትን ለማሳካት የሳይለንት ማጆሪቲው ሙሉ ፈቃድ ማግኜት ይጠይቃል። ችሎቱ ሰበር ያለው ከጭምቱ ማህበረሰብ ነውና። መራጩ ህዝብ የሚያጽናና ጥግ ማግኜት አልቻለም። ይህን ያክል መንፈሱን ማዋለል ለምን አስፈለገ? "ወይ ባልዘፈንሽ፤ ከዘፈንሽ ባላሳፈርሽ" ህዝቡ የያንዳንዱ መግለጫ ስንኝ ተፈታኝ እንዲሆን ለምን ያስፈልጋል?
#መከወኛ።
ሌላው ዶር አበባው ደስአለው ገፃቸውን ሳየው አሳስቦኛል። ተጎሳቁለዋል። ጫና አለባቸው። በደህንነቶች ተከበዋል። ሰላማቸው ታውኳል፤ ይህ እጅግ በጣም አሳስቦኛል። ብልጽግና ማናቸውንም ጫና እንዲያነሳ በትህትና አሳስበዋለሁኝ።
እኒህ ሰው በግራ በቀኝ ተዋክበዋል። መጠጊያ አጥተዋል። አልዘረፋ - አልሰረቁ። አልዋሹ - አልካዱ። ለምን ይሰቃያሉ? በብቃታቸው እና በልቅናቸው ምክንያት?
ስክነታቸው፤ ደርባባነታቸው ወጣት አይመስሉም። ፈቅጄ የማደምጣቸው የማከብራቸውም ቁጥብ ናቸው። ግርማ ሞገሳቸው ምራቁን የዋጠ ባለ አቅል ነው። ዲስፕሊናቸው ባለ አደብ ነው። በራስ የመተማመን አቅማቸው ኢትዮጵያን በሚገልጽ መልኩ በልክ ነው። ያልተንጠራራ፤ ያልኮሰሰ - ምጥን። ይህ ስጦታ ከሁሉ አይገኝም። ኢትዮጵያ ልትጠብቀው ይገባል።
ቢመረጡ ፓርላማ ይገባሉ ወይ ለሚለው እኮ ምላሽ ሰጥተዋል። ባለማሸነፋቸው ከተበሳጩ አሸንፈው ቢሆን ኖሮ ይገቡ ነበር። የሎጅኩ አቅጣጫ ይህ ነው። ቢገቡ ደግሞ ኢትዮጵያ፤ የአማራ ህዝብ ፓርቲያቸው ይጠቀሙ ነበር። ሁሉም ግን ሚስ አድርገዋል። የኢትዮጵያ ፓርላማ የታረመ አንደበት፤ የሰከነ ፖለቲከኛ ሊናፍቀው ይገባል። የኢትዮጵያ ህዝብም እንዲሁ።
ክቡር ዶር አበባው ደስአለኝ ለተመረጡበት የምርጫ ጣቢያ ህዝብ የሚችሉትን ማድረጋቸውን ጠቁመዋል። እንደ አማራ አብን ስለወከሉ፤ ፓርላማው የኢትዮጵያ ውክልናም ስላለው በውክልና ዘመናቸው ከተመረጡበት የምርጫ ጣቢያ ባሻገር የት የት ሄደው ህዝብን ለማግኜት ጥረት እንዳደረጉ ቢጠቅሱ ጥሩ ነበር።
ውክልናቸው ስለ አብን ስለነበረ የአማራ ክልልን ሙሉውን ጸጥታ የነበረበትን በአካል ተገኝተው ለማየት ያደረጉት ጥረት ካለ ቢነግሩን ጥሩ ነበር። የግድ የፕሮቶኮል ጉዳይ አያስፈልግም። በፓርላማው ዘለግ ያለ የረፍት ጊዜ አማራ ክልልን፤ ኢትዮጵያን የማወቅ ጥረት ማድረግ ለክቡርነታቸው አጠቃላይ ዕውቀት ረጂ ስለሆነ።
ክብረቶቼ እንደምን ዋላችሁልኝ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
25/06/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ