በአውሮፓ #ህብረት በጀርመነኛ እና በእንግሊዘኛ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ስለ አማራ፤ የቀረበ መግለጫ #በዋርካው ሊቀ ሊቃውንት የቀረበ ነው።
“A remark on the systematic persecution of Orthodox and Amhara.”
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ። "
ክቡር ልዑል አስፋውወሰን አሥራተ ካሳ ናቸው አቅራቢው። ባለመታደል ሆነ እንጂ በመጀመሪያ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ወደ ሥልጣን ሲመጡ #በአወንታዊ በአክብሮት ከተቀበሏቸው ሊቀ - ሊቃውንት ውስጥ አንዱ ነበሩ። በወቅቱ #ጽፌበታለሁኝ። ብሎጌ ላይ ይገኛል። ቆጥቤ፤ መስጥሬ የያዝኳቸው ናቸው። #ኢትዮጵያና #ኢትዮጵያዊነትን በሚመለከት #ዋርካ ናቸው። ጥግም መከታም ናቸው። ትውልዱ እናቱን #ውስጡ እንዲያደርግ ጥረት ያደርጋሉ።
ክቡርነታቸው መሆናቸውን እራሱ ልለያቸው አልቻልኩም። በድምፃቸው ነው የለየኋቸው። በጣም ተለውጠዋል። #ጀርመንኛቸው #የማይጠገብ ነው #አክሰንቱ የአፃፃፍ አወቃቀሩ፤ ቃናው ሳቢ ነው። ለመረዳት ግን ሥነ - ጹሁፋዊ ስለሆነ እጅግ ከባድ ነው። በጀርመንኛ መጽሐፍም አላቸው። ጀርመኖች ሰው ማክበር ባህላቸው ስለሆነ #ልቀታቸውን በታላቅ ትህትና ያስተናግዱታል።
ቁጥቧ እምዬ #ሲዊዘርላንድም ታከብራቸዋለች። ጋብዛም ፕረዘንቴሽናቸውን #ታጣጥማለች። በብዙ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ በክብር እንግድነት ተገኝተው የመክፈቻ #ንግግር ያደርጋሉ።የራሳቸውም #ተቋም ነበራቸው። ዓለም ዓቀፍ የኢትዮጵያ #ወዳጆች የሚገኙበት። ለሰማዕታት ቤተሰቦች መጽናናትን ይለግሳል።
በዘንድሮ ምርጫ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የፖለቲካ ውክልናዋ በአማራ ክልል ብቻ ነው። ይህም ተቀንቶበት አሉታዊ ዴሞግራፊ በሰፊው ተሰርቶበታል። ውስጤ በጣም ነው ያዘነው። አንድ ዓይን ቢኖራት እሱንም በዘነዘና ይላሉ ጎንደሬወች ባለቅኔ ናቸውና።
*** #ዴሞግራፊን እኔ በሁለት እከፍለዋለሁኝ። አሉታዊ እና አወንታዊ ብዬ። በተፈጥሮ ይሁን በሰው ሰራሽ አደጋ የሚገጥመውን ፈተና ለመቋቋም የሚካሄደውን የቦታ ሽግሽግ #አወንታዊ ስለው፤ ታቅዶ ለተሰወረ የማግለል፤ የመሰረዝ፤ የመለሞጥ አንዱን አግንኖ ሌላውን #ለመጫን የሚወሰደውን #አሉታዊ #ዴሞግራፊ እለዋለሁኝ።
የመንፈስ #ነቀላ እና #ተከላም ይኖራል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ #ተዋህዶም ይሁን በአማራ ላይ ያለው የማፈናቀል ሂደት በዚህ አካተዋለሁኝ። #አይጠቅምም። ፈጽሞ #አይጠቅም። ከፈጣሪ ጋር #ታግሎ ያሸነፈ የለምና።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ቸር ያሰማን። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
18/06/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ