#የኮፒራይቱ የይገባኛል ፉክክሩ ተጧጡፏል። ዕልፍኘ - #ትራንፒዝም እንዳሻ የሚወጣበት የሚገባበት አይደለም።
«ለቁጣ የዘገየ ፍቅሩም የበዛ ነው።» ( መዝሙር ፻፫፤ ፰)
#ምዕራፍ ፲፰።
«አሜሪካ በህወሓት መሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ ማዕቀብ ጣለች» ዘገባው የቢቢሲ ነበር።
መቼም ለማህበረ ህውኃት አካልን ሳይሆን መንፈስን #መቅኖ አልቦሽ የሚያደርግ ውሳኔ ነው። ሰሟናቱ የነሃሴ ዝናብ ጨቀጨቅ ሳይመጣ የህወሃትን የተንጠራራ መሻት እሳት ውስጥ የገባ #ፕላስቲክ የሚያደርግም ነው። #ኩፍትርትር።
የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ ፖለቲከኞች ዕውቅና ይሰጡት ዘንድ ትሁታዊ ማሳሰቢያ የምሰጠውም ለዚህ ነው። በዘመነ ኢሠፓ የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬ አንድ ሳብጀክት ነበር። አቅምህን ማቀድ፤ ወደ ተግባር ለመቀዬር #ቀያሹ የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ መረዳት ሲቻል ነው።
ይህ ዘመን ቋሚ ባህሬ #ስለሌለው ተለዋዋጩን ባህሬውን በመከታተል እራስን ማጣጣም Update ማድረግን ግድ ይሆናል። ዲታ ተሆነ፤ ደኃ። በሌላ በኩል #ትራንፒዝምን ማንበብ፤ መተርጎም እና ማመሳጠርም ከባድ ነው። የዘመኑን ባህሬ አውቆ ለመሰናዳት #አቃች ሁነቶች አሉበት። ግን ዝንባሌውን በስሱ መገመት ይቻላል። ከፖለቲካዊ አቅም ይልቅ #ቢዝነሳዊ ባህሪው፤ አትራፊ ቅያሶች ለዘመኑ የፖለቲካ ባህሬ መሃንዲስ እንደሆኑ ማስተዋል ይቻላል።
አንድ ምሳሌ ባነሳ …… ፋርስን ስታስቡ በዚህን ያህል አቅም ዓውራ ሆና ለመውጣት ዳጥማ ዳገቱን ተቋቁማ እዚህ ትደርሳለች ብሎ መገመት አይቻልም ነበር። አሁን እኮ የአህጉርነት አቅም ብቻ ሳይሆን ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ካላቸው አገሮች ጋር #መሳ ለመሳ የሚያቆም ሁነት ላይ ነው ያለው።
የቅድመ ድርድር እጩነት፤ ይሁን የድርድር #የሙሽርነት ሰነዱ በተመደ ይጽደቅልኝ ስትል፤ ሶብዬት ህብረት ጎርባቾቢዝም የሾለከበትን ብልህነት ኢራኖች ዘውድ ደፍተውለታል። በነገሮች ሁሉ የመሪወቻቸውን መራራ ስንብት ችለው አደብን ምራን ያሉበት መንገድም በቅጽበታዊ ዕሳቤ በርካታ የመስዋዕትነት ሂደትን በሚያመነጩ ፖለቲከኞች ላይም ቋሚ ካሪክለም ነድፋለች።
በውስጥ አቅም መተማመን፤ ተስፋን ተስፋ በማስቆረጥ ሳይሆን ተጨማሪ ተስፋን አጎልብቶ #በመቀለብ አቅም እንዴት እንደሚመራም የሐዋርያት ተግባር በዚህ የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬ አስገዳጅነት አይተናል። እርግጥ ነው አገረ እስራኤልን በሃሳብ ከመሞገት ይልቅ ዘለፋው፤ ትርፍ ንግግሩ አቃሎ ማዬቱንም ከሃይማኖት አንፃርም ባልወድላቸውም በአብዛኛው የስክነት ጎዳናቸው የኢራኖችን ግን ይገርመኛል።
አቅም አቅም የሚሰጥህ በአቅምህ ልክ አቅደህ ስትነሳ፤ ያለህን የህዝብ ሃብት እንካ ብላ፤ እንካ አሞራ ሳትል ጥሩ፤ ብቁ ክህሎት ዘለቅ አቅምን የመምራት አቅም ሲኖርኽ ነው። "በመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ አዲስ ኃይል ሆኜ እወጣለሁ" ብሎ ያለመው ህወሃት እና ተስፋው እንዲህ የነኮተው አንድም የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ አለመረዳት ሲሆን ሁለትም የአቅምን ልኬታ ያለማወቅ ነው። በሌላ በኩል ሳይለንት ማጆሪቲው ስለህወሃት ያለውን #የቴርሞሜትር የሙቀት ደረጃ አጢኖት ስለማያውቅም ነው።
እኔ እንደሚገባኝ በህወሃት ላይ የተያዘው የአሜሪካ አቋም መራራነቱ #የቢዛ ጉዳይ ብቻ አለመሆኑ ሌላው ለህወሃት የተጋረጠበት አደጋ ነው። ህወሃት በማስተዋል እራሱን አርሞ እንዲጓዝ ቅን እና ቀና አስተያዬቶችን ማድመጥ አልፈቀደም። ሥልጣን ወይም ሞትን በእልህ በሌለው የበላይነት አቅም አቀደ እንሆ አልቦሽ ሆነ። ታላቋን አሜሪካን ማጣት ለህወሃት የጭንቅላት ካንሰር ነው።
"በዚህ የውሳኔ ሂደት እያንዳንዱን የህወሃትን የህግ #ትልልፍ አሳውቀናል ለዚህ ነው ከዚህ ቆራጥ ውሳኔ የአሜሪካ መንግሥት የደረሰው" የሚል ድምጽ ሰምቻለሁኝ። ያ ከሆነ በ2023 ሰኔ መጀመሪያ ወር ጀምሮ ነጩ ቤተ - መንግሥት ስለህወሃት አውራ ዜናነት፤ "ምዕራብ ትግራይን" እርግፍ አድርጎ ሲተው የዛን ጊዜ የህወሃት አንበሎች ይህን #ወለምታ ለመጠገን ስለምን አልሞከሩም። ስለምንስ አልቻሉም? ለዛውም በባይደኒዝም ዘመን።
በሌላ በኩል የተከበሩ አንባሳደር ማይክ ሃመር ነገረ ህወሃት መደበኛ ተግባራቸው በነበረበት ጊዜ ነው እንዲህ ያለ እርምጃ የተወሰደው። ተገፋው ባለው የአማራ ህዝብ የሊቃናት ጉባኤ ላይ ሲጣደፋም የት ይሆን የነበሩት? የተከበሩ አንባሳደር ማይክ ሃመር ኤክስ አካውንታቸው ላይ ግንቦት 2023 ማለቂያ ላይ የፃፋትን ደግመው #አልኮለሙትም ነበር።
የሆነ ሆኖ የህወሃት የትናንት አንበሎች፤ ጥረቱ አስቀድመው ቢነግሩን፤ የዛሬ የህወሃት ሞጋቾች ጥሩ ይሆን ነበር። ሌላው "የድላችን ዕለት ማክበር የልፋታችን ውጤት ነው።" የሚሉ ሰብዕናወችን አዳምጫለሁኝ። ይህ ከሆነ ነገረ ግብጽን በሚመለከት ያለውን ሁነት ለማስከን #በነካ እጃችሁ እንላለን።
ለሁሉም እምገልጸው እውነት ----- ሠው ሰራሽ ያልሆኑ ድንገተኛ የመዳን ምርቃት አቃጁም፤ ፈፃሚውም ፈጣሪ እግዚአብሄር ነው እና ክብሩን ለባለቤቱ መስጠት ይገባል።
በሌላ በኩል ብልፄ ዲል ያለ ድል እና ዕድል ገጥሞታለኝ። ይህን ዕድል ሲያገኝ ምን #ሰጥቶ ይሆን የሚል ጥያቄም ተከታይ ይሆናል። ምርጫና ሂደቱ ብላችሁ ውሽክ እንዳታደርጉኝ። ህወሃት 100% አሸነፈ በታላላቅ የዓለም መሪወች እና ልምድ ጠቸብ አንባሳደሮቼ ተገልጦ ነበር። ነገር ግን አቤቱ ኢህአዴግ ፌስታ እና ፌስታው #ወዙ ርፍ ሳይል የገጠመው ይታወቃል።
ብልፄም አቅዶ ቁጥር #ደልድሎ በሰራው ዳንቴል 100% አሸንፏል። መቼም ሌላው የቁጥር ስሌት እንዲህ የሚሳካለት ከሆነ በነካ እጅህ ኢኮኖሚውንም፤ ፍትሁንም፤ የመኖር ዋስትናውንም ዳኝልን የሚል ትሁታዊ ጥያቄ አለኝ።
ስለዚህም ማህበረ ብልፄ፤ ቤተ - ብልጼወችም ድልን ቀስ አድርጋችሁ ያዙት እንደ ማለት ነው። ስለደስታ የምለው ቋሚ አባባል አለ። ይህን የፃፍኩት መቀሌን ተቆጣጠርናት #ርችት ላይ ለነበሩ ሁሉ ነበር። እኔ ጦርነቱን አይገባም ባይ ነበርኩኝ። የግራቀኙን ጉዳት ከመዘገብ ውጪ የጦርነት ፈን አልነበርኩም። አልሆንምም። ደስታን በልክ ስለመያዝ እንዲህም እላለሁኝ።
1) አዲስ ተጨማሪ ደስታ ሲመጣ #መደርደሪያ እንዳታጡ፤
2) ደስታው ሲሟሟ ተስፋ ቆራጭ ሆናችሁ ለሥነ - ልቦና #ህመም እንዳትጋለጡ።
3) የሰፋ ፈንጠዝያ የላይኛውን አስከፍቶ ምርቃት #እንዳያስነሳ ………
በግልም ይሁን በተቋምም አንድ ሰው ለሚያገኜው ምድራዊ ፍስኃ ማኔጅመንት እንደሚያስፈልገው አበክሬ እጽፋለሁኝ። አሁንም የምለው ይህ ነው። #ትራንፒዝም ተገማች አይደለም። በብዙ ጥንቃቄ፤ ዘለግ ባለ ማስተዋል፤ በሰከነ እርምጃ ሊያዝ የሚገባው የፖለቲካ ሲስተም ነው --- ትራንፒዝም።
አይደለም ለኢትዮጵያ ለአውሮፓ ህብረት በወል፤ ለአውሮፓ አገራት በግል፤ ለእስያም የዲታ አገራት ሳይቀር አብሮ ለመጓዝ ይሁን አግልሎ ለማዬት የማይቻል ሁነት ነው ያለው። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም እምለውም ለዚህም ነው።
በየትኛውም በጎ ዕንባ አባሽ ዜና ውስጥ የፈጣሪ እጅ አለበት እና ፈጣሪያችን አምላካችን፤ አላሃችን በሰጠን ብቻ ሳይሆን ባላሳካነውም ገጠመኝ መምህራችን ነው እና ልናመሰግነው ይገባል። ስኬቱም የእኔ - ተእኔ ከማለት ያትንግርት ፈጣሪ እና ፈፃሚ እሱ ነውና፤ የእሱን ታምራት ከውስጥ ተቀብሎ ማስከን ያፈልጋል ከመ--- ፎካከር።
በዘመነ ህወሃት አራጊ ፈጣሪ ሳለ፤ እንዲህ በንጉሦች ንጉሥ አጤ ሚኒሊክ ቤተመንግሥት ራህብተኛ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም። ህወሃት እንዲህ ዝቅ ብሎ ይፈጠራል ብሎ ያሰበ፤ ያቀደ፤ ለስኬት ያበቃ ተቋም የለም። አልነበረም። "ጊዜ ለእግዚአብሄር ሆነነ" እና አማኑኤል በፈቃዱ እራሱም ህወሃት ተወዳድሮ በሁለት ድምጽ ብቻ ላይ መወሰኑ፤ እራሱም ድምጽ ሰጥቶ መንበሩን ፈቅዶ ህወሃት ለቀቀ። ይህ የጀንበር ዳንቴል አልነበረም።
ወደ ፊትም ለየትኛውም የስኬት ዓውድ ፈቃደ እግዚአብሄር ስለመሆኑ አምኖ መቀበል እንጂ የሰብዕና ግንባታ ላይ መተኮሩ አያዋጣም። #ምርቃት ስለሚያስነሳ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
20/06/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ