የችሎት ህልፈት...
እስከ ህልፈት
ያልቀጠለ የዜግነት ክብር …
የችሎት ህልፈቱ።
„የሰጎን ክንፍ በደስታ ይንቀሳቀሳል፤
ነገር ግን ክንፍና ላባዋ ጭምተኛ ነውን?“
መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፲፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ 08.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
የችሎት
ህልፈቱ መውደቅ ብልሃቱ
የችሎት
ንቅዘቱ በዕብለት መፈታቱ
የችሎት
ጭላጩ ዕውነት መደፋቱ
የችሎት
ራህቡ ሚዛን ማጣፋቱ
የችሎት
ጥማቱ ጠያቂ ማጣቱ።
- · ሥጦታ ርትህ ለጠማት ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ይሁንልኝ።
መኖርን ያከበረ ዘመን ይናፍቀኛል።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ