በልጥ መወራረድ? ህም - እም - እህ!

ዕውነትን የሚገልጸው
ዕውነት እራሱ እንጂ
ዓዋጅ አይደለም።
„እያሱም ህዝቡን፤--- እርሱ ቅዱስ አምላክ ነውና፤
እርሱ ቀናተኛ አምላክ ነውና እግዚአብሄርን ማምለክ
አትችሉም፤ መተላላፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም።“
መጽሐፈ እያሱ ወልደ ነዌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፲፱
ከሥርጉተ©ሥላሴ
08.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
ባለወረፋው ቆፍጣናው ጎንደሬ!

  • ·       ልብ ሊሰጠው የሚገባው የዕውነት አደባባያዊ ፍርድ - በልጥ ተወራረደ።

Ethiopia: የኢንጂነር ስመኘው ሞት ዝርዝር የምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ!! [እራሱን አጠፋ?]
ድንቄም ስንታዬን መግለጫ፤ ለኮሜዲነት ይልቅ ይመቻሉ የፖሊስ ኮሚሽነሩ ….

ከአብይ ሌጋሲ የማልጠብቀው እንግዳ ነገር ነበር መግለጫው። የግፍ ችሎት ነበር ፍርዱ። ደመከልብ። ልክ እንደ ፕ/ እምሩ ስዩም። እሳቸውም ተከሳሽ አልነበራቸውም። ችሎቱን ሰጪው ሞት የግፍ ብቻ ነወብ።

የሆነ ሆኖ በቆሞስ ስመኘው በቀል አሟሟት ከጅምሩ ሂደቱ የሰጠኝ ጭብጥ ግብረ ምላሽ ቢኖርም ትንሽ ብጣቂ የሚመስል ተለጣፊ ማሰተባባያ ጠብቄ ነበር ግን በረዶ ለቀቀበት። እግዚኦ! ብላለች ልዩ የመንፈስ፤ የታማኝነት ወዳጁ ሥርጉተ ሥላሴ በዘመነ አብይ።  … ከአብይ ሌጋሲ ታማኝነቱን የሚያሰተጓጉሉ ለጠፎች ቁሮዎች ወይንም ቀዳዳዎችን ማድመጥ አልሻም።

 እርግጥ ነው ፍጽምና አልጠብቅም፤ ግን በዜግነት እኩልነት ላይ ድርድር አላውቅም። ሲሶ እርቦ ዜግነት መሮኛል፤ ተመልሰሽ ያን ከርቤ እና ሃሞት ተጎንጪ ደግሞ ህልፈቴን መራራ ያደርገዋል። ሞትን ፈርቼው አላውቅም፤ ባሰኘው ቀን እንደሚመጣ ስለማውቅ ተሰናድቼ ነው እምጠብቀው። የኖርኩት ጊዜ በቂ ነው። እምኖረውም በትርፍ ጊዜነት ነው። ዓለም ወረተኛ ብቻ ሳትሆን ተቀዳጅም ናት። 
  • ·       እፍታ

እንዴት ናችሁ የኔዎቹ። ደህና ናችሁ ወይ። የቀንበጥን ታዳሚዎች የማዬው እኔ ልክ ቲያትር ሊይ በጽሞና አቅዶ መንፈሱን አደራጅቶ፤ ገንዘቡን አውጥቶ፤ ትኬቱን ገዝቱ፤ በረጅሙ ፈቅዶ ተስልፎ ተራ ወረፋ ጠብቆ አክብሮትን እንደሚገልጸው የጥበብ የልብ ወዳጅ፤ የልብ ፍቅረኛ የልብ ጽናታዊ ነባቢት ነው። ቫዎሌ ናችሁ!

ስለሆነም ክብሬም - ፍቅሬም - ስስቴም ሆነ ናፍቆቴ የዛኑ ያህል ጥልቅ እና ርቁቅ ነው። ሥርጉተ ልዋሽ ብትል አያምርባትም፤ ትከስማለች፤ ስለዚህ ውስጤን ነው እማሳያችሁ፤ ብቻ ላደረጋችሁልኝ የቸርነት ልክ እኔ ሳልሆን የጥበብ አምላክ የልባችሁን ያድርስልኝ። የሎሬቱ ጥበባዊ ታቦትም መንፈሱ አይለያችሁ። እግዚአብሄር ይስጥልኝም።

  • ·       ጉዳይ እና ባለጉዳዩ ዕውነት።

በ80ዎቹ ወደ አጋማሹ ሲጠጋጋ ላይ ከሥነ-ጹሁፍ /ቲያትር ኮርስ በኋዋላ ነበር ሥነ - ግጥምን በተከታታይ መጻፍ የጀመርኩት። አንድ ሥነ - ግጥሜ ነፍሱን ይማርልኝ እና ትውልድ ከቶውንም የማይተካው የጋሼ ወጋዬሁ መታሰቢያ አማተር ክበብ 5ኛ ሙት ዓመቱን ለማክበር ውድድሩን ለኮርሰኞች ሰጥቶ ነበር።

በዓሉ በብሄራዊ ቲያትር ያው አንጋፈዎቹ ባለጸጋ የጥበብ ዘውዶች በሚገኙበት ነበር የሚከበረው። እና እኔም ተወዳደሩክኝ እና ሥነ - ግጥሜ አሸነፈ „እሱ ማነው?“ የሚል ነበር። ከታተሙት የግጥም መድብሎች ውስጥም አንዱ ነው።

በብሄራዊ ቲያትር ለመጀመሪያ ጊዜ ሥነ - ግጥሜን ያቀርብኩት ያን ግዜ ነበር። እንግዲህ የመግጠም አውሌያ ጋር ቁርኝቱ በትጋት የቀጠለው ከዚህ በኋዋላ ነበር። በዛ ዘመን እግጥመቻው የነበሩ አጫጫር እና ግልጽ የሆኑ እውነት እና የራሱ የዕውነት ባጉዳይነት ነበር።

በእጄ የነበሩት ከእኔ ጋር ክልትምትም ሲሉ የኖሩትን ግጥሞች ከአዲሱቹ ጋር ምንም ለውጥ ሳላድርጋባቸው ለህትምት በቅተዋል። ዛሬም ዕለቱ በዕውነት ዙረያ እንድል ጠራኝ እና እስኪ ትንሽ ልበል አልኩኝ። ደግሞም ይገባል።

ያን ጊዜ የቤት ቆጠራም የሐተታ ብሄራዊ ውድድር ነበር በዛም ተወዳድሬ ሦስተኛ ወጥቼ ብር ተሸልሜያለሁኝ።

ይህም ብቻ ሳይሆን በፍቅር ደብዳቤም እንዲሁ ተወዳድሪ አሸናፊ ሆኜ ነበር። ብሄራዊ መዝመሩን ለመቀዬር ሃሳብም ስለነበር ለዛም ተወዳድሬ ነበር ሥንኞችም አብረውኝ አሉ። አገር ባለቅ ኖሮ በዘርፉ በተለይ ከፖለቲካ ውጪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብተጋ የተሻለ የመድረክ ዕድሉ ነበረኝ።

እዚህ ሲዊዝ እንደሆነ እስር ነው ካቴና፤ ካቴናው ደግሞ በእጥፍ ድርብ ነው። ብታሳታሙትም ያው የስቶር ሲሳይ ነው … አሁን አገር ሲገቡ ደግሞ እንዴት ሊያሠሩ እንደሚችሉ ጉልበተኞች ልምምድ ይሰጧችኋዋል …  ዕውነት ተፈርታ የነፃነት ታጋይነት ቧልት ነው ተረት ተረት። 

ብጣቂ የነፃነት ጠረን አልጠብቅም ከእንሱ ...መጀመሪያ ከዚህ ለስደተኛ እህታቸው ነፃነት በሰጡኝ ... ስለሆነም ይህ የግጥግጦሽ የድንኳን ርብርቦሽ አይሞቀኝም። እንዲያውም ብርድ ብርድ ይለኛል። ይህ መጓጓዣው ኢትዮጵያዊነት ቢሆንም ቅርጽ ነው የተለበጠ ... ዲኮር ... ብሄራዊ ሰንደቁም እንዲሁ። ሲሆኑት ሲኖሩበት ሰው ነህ ብለው ወገንህን ስትቀበል ነው የነፃነት ታገድሎ መሪነት ማህለቁ ...  

ቃና የለሽ።

አትቀመሽ መራራ ነሽ
አተጠጭም ጎምዛዛ ነጭ
አትዋጭም ይለኛ ነሽ
ዕውነት ደፋር ካለገኘሽ
ቃና የለሽ ትሆኛለሽ ሽ ሽ ሽ ሽ ሽ ሽ ሽ ሽ ሽ ሽ ሽ ሽ ሽ …..

ይህ ያን ጊዜ አዲስ አበባ ድልገብያ ገብርኤል አካባቢ ስኖር በነበርኩበት ወቅት ከተጻፈው አንዱ ግጥም ነው። እርእሱን የሰዬመችልኝ የመምህርት እናቴም ታላቅ እህቴም ነው።

ዕውነት ባጉዳይ ነው። የዕውነት ባለጉዳይነት የዘመን ጣሪያ፤ የቀለም ዘለበት፤ የሥርዓት ፍርቀት፤ የደንበር ኩንታሮት የለበትም። ዕውነት ጥዱ ክስተት ነው። ጥድ በረዶም አይፈሬ ነው ዕውነትም በቋያው፤ በበርሃው በስኪሞስ ቢሆንም ያው ራሱን ሆኖ ነው እንደ ተፈጠሮው ደንግሎ ይገኛል።

ዕውነትነቱ የትም ቢሆን ያው ዕውነት ነው። ቀይ ቀለም አውሮፓ ላይ፤ አስያ ለይ፤ አትላንቲክ ላይ፤ አፍሪካ ላይ፤ አሜሪካ ላይ በቀለሙ ያው ቀይ ነው። የቀይ ቀይነት ያው ቀይነት ነው። በቃ። ጠረኑ፤ ወዙ፤ ሳቢነቱ ያው እንደ ተፈጥሮው ነው።

ልብ የሰው ልብ፤ የዶሮ ልብ፤ የከብት ልብ፤ የወፍ ልብ፤ የፈረስ ልብ ወዘተ ያው መጠኑ ይለያይ እንጂ ያው ልብ ነው አገልግሎቱም፤ ተመሳሳይ ነው: ስለምን? ዕውነት ስለሆነ።

የሰው ልብ ነጭ ዳማ ቡኒ አፍሪካዊ፤ አስያዊ፤ አረባዊ፤ ህንዳዊ፤ ብራዚላዊ፤ ካናዳዊ፤ ሲዊዛዊያዊ እሰራኤላዊ ይሁን ሰብዕናው ያው በቀለምም በተግባርም ተመሳሳይ ነው። ስለምን? የልብ የቅርጽ እና የይዘት ተልዕኮው አንድ አይነትነቱ በሚሰጠው አገልግሎት እኩልነት ይገለጻል። ሲታመም እንዲሁ። ስለምን? ዕውነት ሰልሆነ።

የደም ቀለም አንድ አይነት ነው። የእስንሰሳም ይሁን የሰው ደማዊ ፍሰት ሲገጥም ተመሳሳይ ነው። ስለምን? ዕውነት ስለሆነ።

እነዚህ ከላይ ያነሳኋዋቸው ማመሳካሪያዎች ቦታም፤ ዘርም፤ ዘመንም፤ ሥርዓትም ቢፈራራረቅባቸው ያው ዕውነታዊ ተፈጥሯቸውን የሚሰርዝ ምንም ነገር የለውም።
ለእኔ ለውጥ ማለት ዕውነትን መድፈር ማለት ነው።

ዕውነትን ለመድፈር የግድ የፖለቲካ ድርጅት አባል መሆን አይጠይቅም። የግድ አህጉር፤ የአገር መመሰሰል አያስፈልገውም። ሰው መሆን በቻ በቂ ነው። ሰው መሆን በቂ ሲሆን ብቻ ነው ዕውነትን ደፋር የሚያገኘው። ከሁሉ በላይ ዕውነት ህሊናን ይጠይቃል። ዳኛው የሰብዕናው ህሊናው ጥንዘላ ወይንም እሸትነት ... 

ብዙ ሰው ሺ ሚሊዮን ጊዜ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሴራ ሸር ምንትሶ ቅብጥርሶ ሲል አዳምጣለሁኝ አነበላሁኝ። አሁን እኮ ለውጥ ላይ ነው ያላችው እምቤት ኢትዮጵያ። ለውጥ ማለት ደግሞ ባዬነው መልክ የተከሰተ ማለት ነው።

አሁን አውራው ፓርቲ ኦህዴድ ነው። ቀደም ሲል የወያኔ ሃርነት ትግራይ አምላኪዎች አውራው ፓርቲ ኢህአዴግ ነው ይሉ ነበር። ጥፋቱ - ሃጢያቱ - ተጠያቂነቱ የጋራ ነው ለማለት። እንደዛ ከላይ አስከታች ድረስ በተጋሩ ጌትነት እና ዘመናይነት በተገዛ አገር ላይ ያን ሲሉ ቧልት ነበር። 

ዛሬም ተመሳሳዩ እዬታዬ ነው። ጥፋት ሲሆን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ልማት ሲሆን የዶር ለማ መገርሳ እና የዶር አብይ አህመድ እንደ ግለሰብ እንደ ድርጅትም የኦህዴድ። "ተንቅን እዚህ አድርሰናል" ብለዋል አቦ ለማ መገርሳ እራሳቸው። ስለዚህ ግደፈት ሲመጣም የእኛ ነው ማለት ይጠበቅባቸዋል። ፍትህ እንዲህ በጠራራ ጸሐይ አቤት ያንት ያለህ ሲል።፡

አሁን የአውራው ፓርቲ ሚናን እና ድርሻ ያለው ኦህዴድ ላይ ነው። ተቆጣጥሮ መልክ ማስያዝ ያለበት ራሱ ነው። ማዕከላዊ መንግሥታዊ ሥልጣን ሲባል ከዚህ እና ከዚያ ማዶ ሊባል አይገባምና። ኢትዮጵያ ማለት ሁሉንም አቃፊ ከሆነ። ሁለንም መሪ ከተሆነ። በስተቀር አቅሙ ወርደ ጠባብ ሆኗል ማለት ነው።  

ስለዚህም በመልካሙ ነገር ላይ ሆ! ተብሎ  ኦህዴድ እንደሚደገፈው እንደዚህ ዕውነትን ለመድፈር ዳር ዳር ሲል ደግሞ ተጠያቂው ኦህዴድ ነው ብለን ደፍረን መውጣት አለብን። አሁንም ኤንም ቢንም እንዳይከፋው ከሆነ ጨዋታው ዕውነት በጠራራ ጸሐይ ቀራንዮ እንደዋለች አስባለሁኝ እኔ በግሌ።

አትንካኝ አልነካህም በዜጋ ደም ላይ ከሆነ ጨዋታው ሰውነት ተፈጥሯዊነት - ሩህሩህነት - ደግነት - ተስፋነት ጥያቄ ውስጥ ይገባሉ። የተፎካካሪ ይባሉ ተቀናቃኞች እኮ አልተመቸነም ሲሉ ነው የሚደራጁት፤ ቢመቻቸው ተጥቅልለው ፓርቲያቸውን አፍርስው እንደኛ ፓርቲ አልቦሽ ይሆኑ ነበር። በቃ ተርታ ዜጋ። 

እንሱ ስለራሳቸው ማንፌስቶ ይተጋሉ። ስለ ዕውነት አይደለም የሚታገሉት። ዕውነት የሚባለው ነገር ለእነሱ እስከ ጠቀመ ድረስ ብቻ ነው። ወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ ብሄራዊ ጀግና ናት። ወ/ሪት ጫልቱ ታከለም ብሄራዊ ጀግና ናት። ወ/ሪት ንግሥት ይርጋም ብሄራዊ ጀግና ናት። እማዋይ በእስር ዘመኗ ያን ጊዜ የግንቦት 7 ጀግና አልነበረችም። ስተፈታም ጀግናው አልነበረችም ለኢሳትም፤ ለግንቦት 7ትም ለፕሮ ድህረ ገፆችም፤ አባል ለመሆን ስትፈቅድ ነው ጀግናቸው የምትሆንው። 

አርበኛ ሜሮን አለማዬሁ ብሄራዊ ጀግና ናት አሁን እሷ የግንቦት 7 ጀግና ብቻ ናት ለሌላው ጀግናዬ አይደለችም፤ ነገር ግን ለእኔም የግንቦት 7 ሆነች አለሆነች ነፃነት አስገኛለሁ ብላ በርሃ የተቃጠለች አንበሳ ሴት ናትና ስለዚህ ለእኔም ጀግናዬ ናት። ለሌላው ላትሆን ትችላለች።

ዕውነት የሚሆነው ነገር ለእኛ እስከተመቼ ድረስ ነው። ከዛ ባሻገር ዕውነት አይደለም። ዕውነት የሆነው ድንግሉ ጉዳይ። ራያ የትግራይ አልነበረም። ምንአልባት በኦሮሞ ታሪክ ውስጥ ኤርትራ እና ትግራይ ላይ ኦሮሞ አለኝ የሚለው መንፈስ የለውም። በጋብቻ ከሚዛመደው ውጭ።

ነገር ግን አሁን ትግራይ ላይም ኦሮሞ አለ ተብሎ በምሳሌነት በጠ/ ሚር አብይ አንደበት ተነግሯል። ይህን አንሞግተውም። ጋዜጠኞች እዛው ፊት ለፊት ተቀምጠው አልሞገቷቸውም። ራያ ዜጋ አይደለማ? መብቱ መጣስ አለበት። ራያ ውስጥ ኦሮሞ የለም እያልኩ አይደለም። ውህድ ነው ራያ። 

ቀድሞ ነገር ይህን ለጫዋታ ሟሟያ እንኳን ሊቀርብ የማይችል ማስረጃ በምን ሁኔታ እዛ ላይ እንደተሰነቀረ ራሱ እጅግ ይገርማል። ልክ መቀሌ ላይ ስለ ጎንደር ተነስቶ የተሰጠው መልስ መሰል የታሪክ፤ የጂኦግራፊ የትውፊት ግድፈት ነበር።

ሙሴነቱ ነጥሮ እንዲወጣ አብነቱ የዓለም ወጥ ቋንቋ እንዲሆን ከፈለግን መሰል ግድፈቶችን ነቅስን መተቸት መጥረብ ይገባናል። ምክንያቱም እኔ ከፍሪካም ያለፈ ሃላፊነትን ይወጣሉ ብዬ ዶር አብይ አህመድን ስለማምናቸው። ለተባባሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊነት የሚበቃ ክህሎት ስብዕና አላቸው። ነገር ግን ግድፈት ሲፈጥሩ አሸሼ ገዳሜ አብረን እያልን አይደለም። ይህ ግድፈት ነው ማለት ይጠበቅብናል። 

በዚህ ዙሪያ ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸውም ድርሻ አለባቸው። ለሰው ልጅ ፍቅሩን እምትገልጥለጥ የሚከፋበትን ስትነግረው ጭምር ነው። የተሻለ ስብዕና ያመጣል እና። ለዚህ ነው እኔ „አይ ኖ ልዩ አቅም አለው ብዬ የጻፍኩት። እሺ እሺ እኮ ነው መሪዎቻቸውን ሙልጭ አድርጎ ወደ አልሆነው አቅጣጫ የሚመራብን። በዚህ ብዙ ከስረናል። ወደፊትም እንዳንከስር ስጋት አለብኝ። 


 ዶር ደብረጽዮን ገ/ሚኬኤል ሲናገሩት ብቻ ነው እኛ የምንሞግተው። ዶር ደብረጽዮን ትግራይም ኦሮሞ ራያ ላይ አለ ቢሉ አገር ይቃጠል ነበር። እነሱ ይህን አይደፍሩትም ምክንያቱም ስርቆት ወረራ እውነት አንድ አለመሆናቸውን ባይቀበሉትም፤ ያውቁታል። 

ዕውነት ባለጉዳይነቱ እንደ ተርጎሚው እንደ ተጠቃሚው ነው። ስለዚህ የእውነት ዘመን ሜርኩሪ ላይ ብቻ ነው ያለው። ፍርድና ዳኝነትም እንዲዚሁ። የኢትዮጵያ መንግሥት አርበኛ አንዱአለም አራጌ እና ኦቦ ሌንጮ ለታን እንዴት ያያቸዋል? ኦቦ በቀለ ገርባንና አቶ አንዷለም አራጌን እንዴት እዬያዘቸው ነው ሌላው የዕውነት በላ ልበልሃ ጉዳይ ነው።  
  • ·       እኩል ቃሉ ወይንስ ምግባሩ ከባዱ?

 በመጀመሪያ ነገር ሁሉም ባለሙያ ለአገሩ እኩል ቢሆንም የተለዩ ደግሞ አሉ። ለእኔ በግሌ በመሪ ደረጃ ዶር አብይ አህመድን እማይበት፤ እምሰፍርበት መንገዴ የራሴ ስለሆነ በመሪ ደረጃ ብቃታቸውን ተጠራጥሬው አላውቅም።

እንዳሳቸው ደግሞ እንዲያውም ፖለቲካ ሳይንስ ሙሁር ሊቀ ሊቃውንት መርጌታ የሆኑ ኢትዮጵያ ሃብት አላት። በብሄራዊ ደረጃ ሁሉንም በማቀፍ በመሪ ደረጃ ሲመጣ ግን ለእኔ ዶር አብይ አህመድ ይብልጡብኛል። 

ዕውቀት መኖሩ ብቻ ሳይሆን ዕውቁቱን ለመግለጽ፤ የውስጡን ገብያ ላይ በማቅረብ ሸማችን በገፍ የማግኘት፤ ያለውን ሥራ ላይ ለማዋል ያለው አቅም ስልት እና ስትራቴጅ ነው ጉዳዩ የመሪነት። 

እጣቶቻችን አንድ ዓይነት አይደሉም ይለያያሉ። የጣቶቻችን አግልግሎታቸው በግል የተለያዬ ነው። በጋራ ደግሞ መኖርን ፈጣሪ ጠበብቶች ናቸው። አዎና! እጣቶች የጥብብ ሐዋርያ ናቸው።

መክሊት የሚባል አለ፤ ጸጋ የሚባል አለ። ስኬት የሚባል አለ። ተለይቶ መፈጠር የሚባል አለ። ሁሉም መሃንዲስ አንድ አይደለም። ለቆሞስ ኢንጂነር ስመኘው የኢትዮጵያ መንግሥት የሰጠው ዕውቅና በመንፈስ ደረጃ፤ በሥነ - ልቦና ደረጃ ተራ ማህንዲስ አድርጎ ነው። „ወላድ በድባብ ትሂድ“ አይነት … ማንም ሰው ኮፒ የለውም!

ልክ እንደ ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን እንደ ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ 4ኛው ፓትርያክ 30ኛ የሲመት ባዕል ሲከበር እጅግ ታች ወርዶ „እንዳያም ጥራው እንዳይበላም ግፋው“ ተብሎ እንደ ተከበረው አይነት ነው ሞቱ የተለመደ ነው ሌላም ሰው ይተካዋል አይነት ነው። በ እግዚአብሄርም ሞት አለ ግን ትክ የለሾች ደግሞ አሉ። ሦስት የኤልትሪክ ማምንጫ ሃይልነት ከመገንባት ሌላ ምን ብርሃንነት ኖረና ደግሞ? 

በጠራራ ጸሐይ አደባባይ ላይ የተረሸነን አካሉን፤ ጓዴ የሚለውን፤ ፖሊሲውን ለማስፈጸም ፍዳውን ያዬ ተኝቶ አድሮ የማያወቀውን፤ ትዳሩን ብቻ ሳይሆን ራሱንም የራሳ የበረሃውን የተግባር አንበሳ በዛ ደረጃ? ጠቅላላ ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው ድረስ ብትክ የሆነ  የአመክንዮ ጎራዴ ክምሮች ነው የተስተዋለው።

ለእኔ ባይናገረው ይሻለው ነበር የአብይ ካቢኔ ይህን መግለጫ ነው ብሎ ጭድ ከሚከምር። እንደ ተለመደው በደርግ ጊዜ እንደነበረው እንደዛ ትወልድ ከቶም እንደማይተካው እንደ ቅኔው ባዕሉ ግርማ ዝም ማንን ገደለ? በቃ ዝም በቂ ነው።

ዕውነት ለሆነ ነገር ግርዶሽ አይስፈልገውም ወይንም ዓዋጅ። ማን ለማን ስለምን እንዴት የሚለውን እንደተዘረጋ --- በልሙጡ ይሁን በጥፍጥፉ መተው በቃ ዝም። 

ቀብር እኮ ተክልክሏል። በአደባባይ ህዝብ ተደብድቧል። ልጆች እናታችን አገናኙን አቤቱታ አስትመተዋል። መስቀል አደባባይ ላይ የኮልት ተኩስ ድምጽ የሌለው ¡ዝም ብሎ በቃ ገደለው ሽጉጡ? የድሪቶ ብዛት፤ መኖር እራሱ እኮ የአገር የደህንነት ሠራተኛ ያደርጋል።

ግድያው ራሱ እዛ አደባባይ ላይ ተፈጸመን ወይንስ ከሌላ ቦታ ተፈጽሞ እዛ እንዲገኝ ተደረገ? ኢትዮጵያ ድምጽ አልባ ሽጉጥ መስራት ጀመረችን? ፐ ¡ ሰልጥናላች ጃል?

 ቀኝ እጅ ግራ ጆሮግንድን አልሞ ሲመታስ አፈጻጻሙ እና ሂደቱ ዕውነት ከሚበላው ተፈጠሮ ጋር ተዳቀለ ወይንስ ተዋለደ ወይንስ ተጨነገፈ ወይንስ ተመሰቃቀለ? ለመሆኑ አላዛሯ ኢትዮጵያ የፊልም አክተርነት የት ይሆን ሰማዕቱን ኢንጂነር ስመኘውን ያሰለጠናቻቸው? ተጠዬቅ ዘመን? ተጠዬቅ ዕውነት?

ሌላው ሁለተኛው የትርኢቱ መጋራጃ ሲገለጥ ደግሞ ጹሁፍ ፊሪማ ተገኜ ስለሚበላው፤ ቅብጥርሶ ምንጥርሶ አስገድዶ ማስፈርም ይኖራል/ አስመስሎ መፈረምም አለ/// ፎቶ ሾፕ ላይ 6ሰዎችን በአንድ ገጽ ላይ ማውጣት ይቻላል። 

ሌላ ተጽዕኖም ካለም ስጋቱ ሊፈጠረው ይችላል። ህልምም አለ። ከዚህች ምድር ጋር አህል ውሃ ካለቀ በህልም ይነገራል … እኔ ህልሜ ነው የሚመራኝ። ቀጠሮ ኖሮኝ ህልሜ ካልፈቀደ አልሄድም። ስጋት ካለብኝም ቤት ውስጥ ጽፌ ነው የምሄደው። ባልመለስ ብዬ … ይህ ድሪቷም መግለጫ ዘመንን የኋልዮሽ የፊተኞሽ ተነቃነቅ ያስብላል። ዝም ማለት ማንን ገደለ? ምን አለ ዝም ቢባል? 

ምን ይባል ለቆሞስ ስመኘው አሟሟት ቲያትር ሲባል መንግሥት አለን፤ የለም እንበል ከቶ? ዜግነት አለን የለም ምን ይባል ከቶ? ነገስ ተረኛው ማን ነው? ማነው የስጋት ምንጩ? ለዛ ደፈር ጋዜጠኛ ለተመስገን ደስአለኝ ሁልጊዜም እንደሰጋሁለት ነው ያለሁት።

በቀጣይስ ከየትኛው ማህብረስብ የተፈጠረው ነው ስጋት የሚሆነው? ይህ ሲታሰብ ነው ልባችሁን ለሽ አድርጋችሁ አትተኙ፤ ቢሆንስ፤ ቢመጣስ ብላችሁ ትንሽ ራፊ ቦታ ልባችሁ ውስጥ ክፍት ቦታ በሊዝም ይሁን በነፃ ምሪት ይኑር የምለው።

አሁን የማንፌስቶ ማህበርተኞች 4ኪሎን በቀይ ምንጣፍ ሲያስቡ ለማ አብይ የሚባሉ ክስተቶች ሲመጡባቸው ሳጅን በረከት ስምዖንን ሆነው ቁጭ አሉ። ስለምን? ሌላ አቅም ያለው ቢፈጠርስ ብለው የተውት ልብ ስላልነበራቸው። እኛ ደግሞ የሚበልጥ ሲመጣ ደስ አለን። ደልድል ብለን አቀባበል አደርግን። መልካምም ተመኘን። ስለምን? ሂደት የኩሬ ውሃ አለመሆኑ ተፈጥሯዊ ስለመሆኑ ስለተቀበልን።  

ብቻ አሁንም በዚህ ጉዳይ የሚተጉ ከኖሩ የተሰወረም ይኖራል …. እራሱን ላጠፋ ነፍስ ምን ቀብር ያስከለክላል፤ ለነገሩ በጥድፊ ቀብር ሁሉ ታልሞ ነበር። ከምርመራ በፊት እንዲሆን ታስቦ እንደማለት። ቀብሩ እንዲራዝም የተደረገው ለለበጣ ምርምራ ታስቦ ነበር። ብቻ ለምንምነት መረጃ ቀጠሮ አስፈላጊ አልነበርም። ነፍሱ  የውሻ  አልነበረም። … አላዛሯ ኢትዮጵያ የአማራ ሊሂቅ ደም ካልፈሰሳለት እንዴት ይነጋል? ምንምነትን ዛሬ ቆሞስ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ተቀብለውታል ነገስ? 

እንደ ዜጋ ለማዬት እንኳን አልተቻለም። ሞቱ ከውስጥ ሊገባ አልተቻለም። የግድ መንግሥት ይዘን አይባልም የክት እና የዘውትር ልጆች ካሉት? ሻሸመኔ ላይ ያ ነፍስ እንደዛ ተዝቅዝቆ ሲሰቀል እዚህ ውጪ የሰብዕዊ መብት ተረገጠ እያለ ሲጎራ የነበረው ሚዲያ እዛ ያለው የለም ጭጭ ነው። 

ዕውነትን ፈርቶ ነፃነት የለም። ዕውነት ተፈርቶ ተስፋ የለም። ዕውነት ተፈርቶ ሰላም የለም። ዕውነት ተፈርቶ ራዕይ የለም። ዕውነት ተፈርቶ ማግሥት የለም። ዕውነት ተፈርቶ የትውልድ መንፈስ ቀረጻ የለም። ችግሩ ይሻላል ብቻ ሳይሆን ምርጥ ያልነው መንፈስ ሲሆን ያቆስላል። ምርጥነቱ በፕሮፖጋንዲስት ተቀስቅሼ ወይንም በገንዘብ ተገዝቼ አልነበረም። እንደ ቋሚ የትህርት ሰነድ አጥነቼው ነው የወሰንኩለት። ሁሉንም መሪ ሆነ ድርጅት ስላጠንሁኝ። 

ብቻ ... ከቤንሻንጉል የሚፈናቀለው ወገን አይደለም? ሌላ ቦታ የሚፈናቀለው ግን ወገን ነው? ከራያ የሚፈናቀለው ወገን አይደለም ሌላ ቦታ የሚፈለናቀለው ግን ወገን ነው? ወልቃይት ላይ ዱላው እንደ በረዶ በወገን ላይ ሲፈስ ባሊህ ባይ የለውም።

ለዚህ ነው እኔ ልቅምቅም ብላችሁ አገር ስትገቡ የሚገርመኝ። እርሾ ያስፈልጋል። አመዛኙ ጥሩ ነገር የሰከነበት ቢሆን የእኛ የፖለቲካ ጥበብ በሴራ የተመረቀ ስለሆነ ጥንቃቄ እና እርጋታን ይጠይቃል። አይደለም የኛው ገና ያረጋው ለውጥ እዚህ ያሉ አውሮፓዊ ነፍሶች በሁሉ ነገር ስለማይረኩ ነው ሰላማዊ ስለፍ ሲያደርጉ እምናያቸው።

በጥገናዊ ለውጥ ውስጥ የሚገኙ ተረፈ ዕሴቶች እንዳሉ ሁሉ በጥገናዊ ለውጥ ውስጥ የሚመጡ ሌላ መከራዎች ቢያንስ ሊኖሩ ይችላሉ ብሎ ሳይስቡ እርሾ አልባ መሆን የተጠበቀው እንዳልተጠበቀ ዝብርቅር ቢል ሰፊ የሆነ የህሊና ንደት እና ተስፋ ቆራጭነት ያመጣሉ። ሽግግር ላይ ማገዶነት ከጥንቃቄ ጉድለትም ጭምር ነው የሚመጣው። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። 
  • ·       ደፋር እርምጃ ለውነትም ለዕብለትም - ግን እንዴት? 

የአልጀርሱ ስምምነት ወደ ተግባር ለመለወጥ የተወሰደው እርምጃ ደፋር ርምጃ ነበር ለውነት። የኢትዮ ሱማሌን ችግር ለመፍታት የምርጫ ህግን ሥርዓትን ወቅትን ሳይከተል የተከወነው የአዲስ ሥልጣን አሰጣጥ ሂደት ደፋር እርምጃ ነው - ለአዎንታዊነት። በቆሞስ ስመኛው ሞት ደግሞ ዕውነትን የተዳፈረ መግለጫ መሰጠቱም ደፋር እርምጃ ነው - ለእብለት ለቅጥፈት ለሚዛን ዝበት ልዕልና። በአንዱ ላይ ጫና በሌላው ላይ ፍሰሃ። ጉራማይሌ … ጥሩ አይደለም ለለውጥ ተስፋ ሆነ አዬር። ድፈረቱ ወጥ ለሆኑ መልካም ነገሮች፤ ለውነት ቢሆን ይሻላል።

መደፈር ያለበት ለአዎንታዊ እና ለዜግነትን አኩልነት ነው። „አንተም አንቺም እኔም ኢትዮጵያዊ ነኝ“ መንፈቅ ሳይሞላው ወገቤን ካለ ጋዳ ነው ገዳዳ። ዜጋን ለማክበር የሚታዬው መልካም ነገረ የእንጂነሩ ነፍስም እንደ ውሻ ነፍስ ማዬት ደማናማ ይሆናል ነገ። ተወደደም ተጠላም ዕውነት ባይበዙም ዘበኞች አሏት። ለነገሩ ወንጀለኞች አይጠዬቁብን የሚል አቤቱታም ተደምጧለኝ እኮ። ይገርም እስተወዲኛው ነው ... 

እኔ በአጽህኖት የአማራ የህልውና ተጋድሎ መቆም የለበትም ብዬ እምሟገተው ለዚህ ነው። በሃሳብ ደረጃ ላልተጸኑስት የአማራ ልጆች ዛሬ ያለው ትውልዱ ሞቶ ዜግነታቸውን ማስከበር አለበት። አማራ ዜጋ ነው ለማለት አሁንም አልተደፍርም እና። 

ኦሮሞው ኦሮሞ ነኝ እያለ ዜጋ ነው። አፋሩ አፋር ነኝ እያለ ዜጋ ነው። አማራው ግን አማራ ነኝ ካለ ዜጋ አይደለም። አይደለሁም አማራም ቢልም ዜጋ አይደለም። ብቻ አማራ እዬሞተ ተሰርዞ ያገልግል ነው ብሂሉ። የቁልቃል እሾህ መከራ …

እኔ ኦህዴድ አማራዊ ምልከታው ከሁሉም የተሻለ እና ተመራጭ ነው እያልኩ ስስብክ ነው የባጀሁት። አሁን ግን እንደማዬው ከሆነ ወቅታዊ ስልት ከመጠቀም ውጪ ውስጣዊነትን ለማግኘት አደከምኝ የሚለው ቃል ብቻ ይመልስልኛል።

መግለጫና ግራጫ።

ጥሩ ነው ሚዛንን የደፈረ የፖሊስ መግለጫው። እኔ የፖሊስ ኮሚሽነሩ ራሳቸው አይመቹኝም። የታመቀ እንኩሮ አለባቸው። ነፃ ሆነህ ና ሳይሆን ታስረህ ና ነው የሚሉት። እራሱ ነፃነት ስለሚባለው ፅነሰ ሃሳብ ት/ ቤት ገብተው መማር አለባቸው ባይ ነኝ። በቴሌቪዥን ሲመጡ መርግ የተጫነኝ ያህል ነው የሚሰማኝ። ይህን ሁሉ ሸክም ተሸክሞ ነገ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ …. ? ? ? >

የሆነ ሆኖ ለቆሞሱ ኢንጂነር "ለተርታው ዜጋ ውለታ ላላበረከተው" ስመኘው በቀለ ሞትም ሆነ የፍርድ አሰጣጥ ተጠያቂ ባልሥልጣኑ ኦህዴድ ነው የሚሆነው። አገር መሪ እሱ ነውና። ሌላው ፈዛዛው ብአዴን ያው እንደ ዘመነ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የሪሞርኬ ተግባሩን ይከውን እንግዳ በመቀበል እና በመሸኝት ሽንጥና ዳሌውን ያሳዬን … ካሰኘውም እስክስታውን ወክ እንዲህ ይበልበት ….

ዕውነት ጠሐይ የወጣላት ዕለት አላዛሯ ኢትዮጵያ ትፈወሳለች።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።





አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።