"የተከሰስኩት የወከለኝ ሕዝብ ላይ የደረሰውን በደል እና ግፍ በመቃወሜ ነው" - አቶ ዮሐንስ ቧያሌው BBC#የአማራ #እናት #መኖሯም ሆነ #በሥጋ #መለዬቷም #ሰላሙን #እንዲህ #እዬተቀማ #ነው።
#የአማራ #እናት #መኖሯም ሆነ #በሥጋ #መለዬቷም #ሰላሙን #እንዲህ #እዬተቀማ #ነው። መቼ እና መቼ በቃሽ እንደሚላት አምላካችን፦ አላሃችን እሱ ይወቀው። ዳኝነቱን እንጠብቃለን። ዕውነተኛ ርትህ በአውደ ምህረቱ ብቻ ነውና ያለው። ይህን ያህል የአማራ ልጅ በግዞት መጋዝ፥ መፈናቀል፤ መገደል #መፈናፈኛ #አጥቶ ህዝባችን መሰቃዬት። #ድምጹን ሳይሰስት በሙሉ ሰጥቶ ሥልጣን ላይ አስቀምጦ፦ ለኖቤልም ስለአስበቃ። ግፍ ፍሩ ማህበረ - ኦነግ በቀላችሁም #በቃ።
"የተከሰስኩት የወከለኝ ሕዝብ ላይ የደረሰውን በደል እና ግፍ በመቃወሜ ነው" - አቶ ዮሐንስ ቧያሌው
https://www.bbc.com/amharic/articles/cx2m18l8r98o
ዮሐንስ ቧያሌው፣ ክርስትያን ታደለ፣ ካሳ ተሻገር (ዶ/ር) እና ጫኔ ከበደ (ዶ/ር)
"በዐቃቤ ሕግ የሽብር ወንጀል ክስ የቀረበባቸው አማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው ክስ የቀረበባቸው "የወከላቸው ሕዝብ ላይ የደረሰውን በደል እና ግፍ" በመቃወማቸው መሆኑን ተናገሩ።
አቶ ዮሐንስ ይህን ያሉት ሐሙስ ጥር 29/2017 ዓ.ም. በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሕገ መንግሥት እና የሽብር ወንጀል ጉዳዮች ችሎት በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል ነው።
ከእሳቸው በተጨማሪ ሌሎች 15 ተከሳሾችም በዐቃቤ ሕግ ለተመሠረተባቸው ክስ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል። አቶ ዮሐንስን ጨምሮ ችሎት የቀረቡት 16ቱም ተከሳሾች የቀረበባቸውን ወንጀል "አልፈጸምንም" ማለታቸውን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የእምነት ክህደት ቃላቸውን በቅድሚያ የሰጡት አቶ ዮሐንስ "የፍትሕ ሚኒስቴር በእኔ እና በእኔ ስም በሚጠራው መዝገብ ላይ ያቀረበው ክስ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የለውም" ብለዋል፥
አቶ ዮሐንስ አክለውም "ሕግን በመተላለፍ እና ወንጀል በመፈጸማቸው ሳይሆን ንቁ አማራዎች፣ ፖለቲከኞች እና ምሁራን" በመሆናቸው ምክንያት እንደተከሰሱ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የቀረበባቸውን "ወንጀል እና አሉባልታ" እንደማይቀበሉ እንዲሁም ወንጀልም እንዳልፈጸሙ የጠቆሙት አቶ ዮሐንስ፤ "ፍትሕ የለም እንጂ እኔ ነጻ ሰው ነኝ። ፍርድ ቤቱ በነጻ ለቆ ለደረሰብኝ በደል ሁሉ ካሳ ሊያሰጠኝ በቻለ ነበር" ብለዋል።
ሁለተኛ ተከሳሽ የሆኑት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ በበኩላቸው "[የተከሰስኩት] የመንግሥትን ብልሹ አሠራር በማጋለጤ ነው" ሲሉ የቀረበባቸውን ክስ ክደዋል።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካዩ አክለውም በእስር ላይ የሚገኙት "የወንጀል ድርጊትን የሚያቋቁም የሕግ መተላለፍ" ስለፈጸሙ አለመሆኑን ገልጸዋል። አቶ ክርስቲያን ለእስር ተዳረጉት "የገዢውን ፓርቲ እና የመንግሥት አሠራሮችን እንዲሁም የአመራሮችን ብልሹነት እና ዘረፋ በመታገላቸው እና በማጋለጣቸው" መሆኑን በእምነት ክህደት ቃላቸው ላይ ጠቁመዋል።
በምክር ቤቱ በመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነት በነበራቸው ኃላፊነት የሠሩት ሥራ ለእስር እንዳደረጋቸው አቶ ክርስቲያን ጠቁመዋል። አቶ ክርስቲያን በዚህ ኃላፊነታቸው "ተደጋጋሚ የአመራር ብልሹነት" ያሳዩ አካላት ላይ "የወንጀል እና የፍትሐ ብሔር ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ" ክስ እንዲመሠረት ፍትሕ ሚኒስቴርን ማዘዛቸውን አስታውሰዋል።
በምክር ቤት አባልነታቸውም የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች "የፋይናንስ ግልጸኝነት እና ሕጋዊነትን እንዲከተሉ እና እንዲያረጋግጡ" መጠየቃቸውን አቶ ክርስቲያን አውስተዋል። "እነዚህ ጥያቄዎች እንዳልጠይቅ አንዳንድ አመራሮች በግል በኢመደበኛ ሁኔታ ለማግባባት ሞክረዋል" ያሉት አቶ ክርስቲያን በዚህ ሳቢያ ለእስር መዳረጋቸውን ገልጸዋል።
ሦስተኛ ተከሳሹ ሆነው የቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ካሳ ተሻገርም በተመሳሳይ የተከሰሱበትን ወንጀል አለመፈጸማቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።
ዶ/ር ካሳ "እኔ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ነኝ። የወከለኝን ሕዝብ ሰቆቃ እና ስቃይ በምክር ቤት ውስጥ በመናገሬ ነው የተከሰስኩት" ሲሉ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ዐቃቤ ሕግ በዶ/ር ካሳ ላይ ካቀረበባቸው ክሶች መካከል "ታጣቂዎች የሚመሩበት ወታደራዊ ሰነድ አዘጋጅተዋል" የሚለው አንደኛው ነው። ዶ/ር ካሳ ተሻገር "ማኅበራዊ ሳይንስ መምህር ነኝ ይሄ የፈጠራ ክስ ነው። እኔ የወታደራዊ ሳይንስ ትምህርትም ዕውቀትም የለኝም" ሲሉ ማስተባበላቸውን ጠበቃ ሰለሞን ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ሌላኛው ዝርዝር የእምነት ክህደት የሰጡት አምስተኛ ተከሳሽ ዶ/ር ጫኔ ከበደ ናቸው። ዶ/ር ጫኔ "እኔ የኢዜማ ሊቀ መንበር ነኝ። በዚህ ፓርቲ በኩል ሰላምን የምሰብክ ስለሰላም የማወራ እንጂ በሽብር ድርጊት እንዲሳተፉ የፓርቲዬን አባላት የምቀሰቅስ አይደለሁም" ማለታቸውን ጠበቃ ሰለሞን ገልጸዋል።
"ክሱ የቀረበብኝ በኢዜማ ስር ሆኜ በማራምደው ፖለቲካ ሳይሆን በአማራነቴ ምክንያት ነው" ያሉት ዶ/ር ጫኔ፤ "እኔ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት አባል ሆኜ በሰላማዊ መንገድ እየታገልኩ ነው ያለሁት እንጂ የፈጠራ ክሱ ላይ የተገለጸውን የሽብር ድርጊት አልፈጸምኩም" ብለዋል።
ከአራቱ ተከሳሾች በተጨማሪ ችሎት የቀረቡት ሌሎች ተከሳሾችም የቀረባቸውን የወንጀል ክስ አለመፈጸማቸውን ለችሎቱ መግጻቸውን ጠበቃቸው ለቢቢሲ ጠቁመዋል።
በአማራ ክልል የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት የክልል እና የፌደራል ምክር ቤት አባላት እንዲሁም ፖለቲከኞች በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመሠረተባቸው ከ11 ወራት በፊት መጋቢት 18/2016 ዓ.ም. ነበር።
ዐቃቤ ሕግ የወንጀል ሕጉን እና የፀረ ሽብር አዋጁን ጠቅሶ የመሠረተው የክስ የተከፈተው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል በሆኑት በአቶ ዮሐንስ ቧያሌው ስም ነው።
የዐቃቤ ሕግ የክስ ሰነድ ተከሳሾቹ፤ "የፖለቲካ ርዕዮተን በኃይል ለማስፈጸም በማሰብ" ተሰብስበው ስለመደራጀታቸው ያትታል።
ከዚህ በተጨማሪም "[ተከሳሾቹ] የአማራ ርስት ናቸው የሚሏቸውን መሬቶች በወታደራዊ ኃይል ለማስመለስ እና አገርን 'በአማራ እሳቤ ብቻ መገዛት አለባት' ከሚል" ስምምነት ላይ ደርሰዋል" ሲል ይከስሳል።
በዛሬው [ጥር 29/2017] የችሎት ውሎ ተከሳሾች ይህን ክስ ክደው መከራከራቸውን የጠቀሰው ዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎቻችን አቅርቦ ለማሰማት ችሎቱን ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱም በተከሳሾቹ ላይ ቃል የሚሰጡ 21 የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ከመጋቢት 5 አስከ 12/2017 ዓ.ም. ይሰማል።"
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ