#ግን #አንዱ #ሆስፒታል #ለምን #በክቡር፦ #ሰማዕቱ #ዶር. #አንዱአለም #ዳኜ #አይሰየምም????
#ግን #አንዱ #ሆስፒታል #ለምን #በክቡር፦ #ሰማዕቱ #ዶር. #አንዱአለም #ዳኜ #አይሰየምም???? ቅዱስ መንፈስ የረበበት ብሩክ። አንድ መምሪያ ብቻ ሳይሆን አንድ ህልው ሆኖ እዬሠራ ያለ ሆስፒታል ነው በሥሙ መሰዬም ያለበት። ዘገባውን ከማቅረቤ ጋር ግን የግል ዕይታዬነን …
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"




ከእሱ በላይ #ክብር፤ ከእሱ በላይ #ሞገስ፦ ከእሱ በላይ #ማዕረገ- ህይወት ምን አለና! #ቁርጠኛ #ውሳኔ #ይጠይቃል ሃሳቤ። ለምን ከውስጤ ገባ ብዬ ሳስብ ምላሹ ተፈጥሮው ውስጤን አሸንፎ ተደላድሎ የመቀመጥ አቅሙ #አንቱ በመሆኑ ነው። ዜናውን ስሰማ ድንጋጤዬ ከባድ ነበር። በቀጥታ ነውከውስጤ የገባው። መረጃውን ሳልሰማ ማለት ነው። መረጃውን ሳገኝ በዚህ ልክ #ትህትና፤ በዚህ ልክ #ቅንነት፤ በዚህ ልክ #ውስጥነት፤ በዚህ ልክ #አገልጋይነት፤ በዚህ ልክ ለሌሎች መኖር #ድንቅ ሰብዕና ሊመጣ ወይንም ሊገኝ ነው???
አንዱ ሆስፒታል በሥሙ ይሰዬም እና ትንሽ የወል ሃዘናችን የመጽናኛ አቅም ያግኝ። ሌላ ማሰብ እኮ አልተቻለም። ረቂቅ የሆነ የማናውቀው #ስበት አለው ፀጋውም ሁነቱም። የስብሰባው ጭብጥ ፈጣን እና የአንጀት በመሆኑ መልካም ጅምር ነው። ፡ልትመሰገኑም ይገባል።
በሥሙ ወርክሾፖች፤ ሰሚናሮች፤ ፓናል ዲስከሽኖች በቀጣይነት ቢኖሩም መልካም ይመስለኛል። ዝክረ ታሪኩ በፎቶ፤ በመጸሐፍ፤ በመጋዚን በበራሪ ጹሁፍ በተከታታይ ሊሰራበት ይገባል። የዘመን ሥጦታ ፒላር ነውና። የትውልድ ድርሻውን እራሱን ሸልሞ ሰማዕትነት የተቀበለ ጀግና ነውና። ፋውንዴሽን ለማቋቋም ማሰብ፤ የሙያ አጋሮቹ ውጭ የሚኖሩ አጀንዳቸው ሆኑ ትጋቱ እና ሰማዕትነቱን ለዓለም የሙያ አገሮቻቸው እና የሰባዕዊነት ተፈጥሯቸው ከፍ ላሉት ማስተዋወቅ ይገባል።
ውዶች እንዴት ዋላችሁ? መልካም ምሽት።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ሥርጉትሻ06/02/2025
~~~~~~~~~~~~~~+~~~~~~~~~~~~+~~~~~~~~~~~~~~+~~~~~~~~~~~~+~~~~~~~
BDU የባህርዳር ተማሪወች ማህበር የተገኜ ዘገባ።
"ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሰራት ባለባቸው ስራዎች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ
---------------------------------------------
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ከዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አመራር አካላት ጋር የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሰራት ባለባቸው ስራዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያካሄደ ሲሆን በተለይ ቤተሰቦቹ ሊደገፉ በሚችሉባቸውና ሃኪሙ በህይዎት ዘመኑ ያከናወናቸው ልዩ ሙያዊ አስተዋጽኦችን መዘከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡
ዶ/ር አንዱአለም ምንም እንኳን የተሰጠውን ጸጋ ሳይሰስት በመጠቀም ለበርካቶች የዘርፉ ባለሙያዎችና በሙያው ላገለገላቸው በርካታ ህሙማን የቅን አገልጋይነት ተምሳሌት የነበረ እንቁ ባለሙያ ቢሆንም ገና በ37 ዓመቱ የተቀጠፈ በመሆኑ ለህጻናት ልጆቹና ቤተሰቡ ትቶ ያለፈው ቤትም ሆነ ሌላ ንብረት የሌለው መሆኑን፣ የቀረቡለትን በርካታ ዓለምአቀፍ የስራ ቅጥር ግብዣዎች ባለመቀበል ወገኑን ለማገልገል ቆርጦ የነበረ ባለሙያ ከመሆኑም በላይ በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀዶ ጥገና ክፍል የነበረውን ልዩ አበርክቶና የቀዶ ጥገና ክፍሉን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሻሻል እየጣረ የነበረ እና እውን ለማድረግ ጫፍ ላይ ደርሶ ያለፈ መሆኑን፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ የነበረውን ሞያዊ አቅም ተጠቅሞ ራሱን ለተገልጋዮች በቅንነት ሰጥቶ ያለፈ ታላቅ ባለሙያ እንደነበረ የስራ ባልደረቦቹ ፣ተማሪዎቹ እና አገልግሎቱን ያገኙ ደምበኞቹ የሚመሰክሩለት ድንቅ ሃኪም የነበረ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው በጥልቀት ገምግሟል፡።
በመሆኑም፡የዶ/ር አንዱአለም ልጆች ለከፍተኛ ትምህርት ሲደርሱ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በነጻ እንዲማሩ፤ ባለቤቱ ከትምህርት ዝግጅት አንጻር በሲቪል ምህንድስና 2ኛ ዲግሪ ያላት እና ጥሩ አቅም ያላት በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል የምትቀጠርበት ሁኔታ እንዲመቻች፤ ዶ/ር እንዱአለም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታሪክ የመጀመሪያውን ቀዶ ጥገና የሰራው እሱ በመሆኑና ክፍሉን እስከ ህልፈቱ ድረስ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የነበረ በመሆኑ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል #የቀዶ #ጥገና #ዋርድ በስሙ ዶ/ር አንዱአለም ዳኘ ቀዶ ጥገና ዋርድ ተብሎ እንዲሰየም፤ የዶ/ር አንዱአለምን የአገልጋይነት ጥግ እንዲሁም ለሙያው የተሰጠ ተምሳሌታዊነቱን በቋሚነት ለመዘከርና #ማስተማሪያ እንዲሆን በጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ #ሃውልት እንዲቆምለት፤ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ School of Medicine ውስጥ በስሙ BDU #Talent Scholarship እንዲቋቋም፤ ለ40ኛ ቀኑ መታሰቢያ የሚደርስ ስለ ዶ/ር አንዱአለም የህይዎት ታሪክ የሚዳስስ መጣጥፍ እንዲዘጋጅ የወሰነ ሲሆን ይህ ውሳኔም ቀድሞ በዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት በኋላም ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ይሁንታን አግኝቶ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡
በሌላ በኩል በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ በኩል የሚሰሩ ዝርዝር ስራዎችን የሚከታተል የስራ ባልደረቦቹን ያቀፈ አንድ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡ በመጨረሻም የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን የግፍ ግድያ አስመልክቶ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እንደ ተቋም ፍትህ አጥብቆ የሚሻ ሲሆን ክስተቱ የአንድ ጊዜ አጋጣሚ ብቻም ሳይሆን ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ያጣውን በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ አቶ አድነው በለጠን ጨምሮ እየተደጋገመ የመጣና ለሕብረተሰቡ አገልጋይ የሆኑ እንቁ ሃኪሞቻችንን ደህንነት እንዲሁም የማሕበረሰቡን የጤና አገልግሎት በእጅጉ እየተፈታተነ ያለ አሳሳቢ ጉዳይ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት በጉዳዩ ላይ ተገቢውን እና ጥልቅ ምርመራ አድርገው በግድያው ላይ እጃቸው ያለበትን አካላት በአፋጣኝ ለህግ እንዲቀርቡ እንዲደረግ እየጠየቀ ይህ ጉዳይ በቋሚነት መፍትሄ በሚያገኝበት መንገድ ላይ ዩኒቨርሲቲው በየደረጃው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ውይይቶችን የሚያደርግ መሆንን ይገልጻል፡፡ "
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ