አዲስ #ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱ ተደመጠ። የህክምና ባለሙያወችም በጅንካ ከተማ ሰማዕትነትን ተቀበሉ።
አፋጣኝ እርምጃም፤ አፋጣኝ ጥንቃቄም ማድረግ የሚገባ ይመስለኛል። በተለይ በአዋሳኝ ባሉ ከተሞች እና በመሃል አዲስ አበባም በሽታው የመዛመት ዕድል ሊኖረው ስለሚችል መረጃውን ሼር በማድረግ መተባበር ይገባል። የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር የሰጠው መግለጫ አያይዤዋለሁኝ። ይህን የጤና መስሪያ ቤት ያወጣው ቅድመ መከላከል አስመልክቶ የተሰጡትን መመሪያወች በድርጊት ላይ ማዋል አገር ቤት የሚገኙ ወገኖቻችን እንደ ህይወት #መርኃቸው ሊወስዱት ይገባል።
ከዚህ በተጨማሪም ጉዞወችን #መከርከም እና፤ በወል በሚሠሩ አስገዳች የሥራ ባህሪያት ላይ ጥንቃቄ ማድረግ፤ የጋራ ጉዞ እና የተለያዩ የማህበራዊ ኑሮ መስተጋብሮችን ክስተቱ መልክ እስኪይዝ፤ ወይንም በቁጥጥር ሥር እስኪውል ድረስ ከፈጣሪ በታች የተቻለውን ሁሉ ማድረግ ያስፈልጋል። #ማስክ መጠቀም እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ይመስለኝ።
በተረፈ ምንጊዜም ለሰብዓዊነት ግንባራቸውን አጥፈው ለማያውቁት የህክምና ባለሙያወች፤ እራሳቸውን ለሚማግዱት ለኢትዮጵያ የጤና ባለሙያወች፤ የጤና አገልግሎት ሠራተኞች ሁሉ ክብር መስጠት ይገባል። እራሳቸውን አስቀድመው ሌላውን ለማትረፍ #ሰማዕትነት ለተቀበሉት የጤና ባለሙያወች፤ እንዲሁም በበሽታው ለተቀዘፋ ወገኖቻችን ነፍሳቸውን ፈጣሪ በገነት ያኑር አሜን። ለቤተሰብም መጽናናት ይስጥልን አምላካችን አሜን።
ፈጣሪን የምናስከፋበት መንገድ በረከተ። ልብ ይስጠን አሜን።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
12/11/2025
ፈጣሪ ሆይ! ምህረትህ ይቅረብላት ለኢትዮጵያ። አሜን።
ቸር አስበን ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።


አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ