ቸር ዜና። "ዐዲስ ቸኮል ቀዶ ሕክምናውን አጠናቆ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል! Tsion Girma Tadesse"

 

ዐዲስ ቸኮል ቀዶ ሕክምናውን አጠናቆ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል! 

Tsion Girma Tadesse

 May be an image of hospital

👉"የአሜሪካ ድምጽ፣ የድሬዳዋ ዘጋቢ ዐዲስ ቸኮል፣ የተደረገለት ቀዶ ሕክምና ተሳክቶ በጥሩ ኹኔታ ላይ ይገኛል።
ዐዲስ ቸኮል፣ ከቀዶ ሕክምናው በኋላ የንግግር እክል ሊያጋጥመው ይችላል በሚል የነበረው ፍርሃት ሙሉ ለሙሉ ተወግዷል። ከቀዶ ሕክምናው በኋላ በተደረገለት ክትትል የንግግር ብቃቱ፣ ቀድሞ ወደ ነበረው ጤናው መመለሱን አረጋገጠዋል።
ሰባት ሰዓት አካባቢ በፈጀ ቀዶ ሕክምናም፣ ዕጢው ሙሉ ለሙሉ ወጥቶለታል። በአኹኑ ሰዓት በሆስፒታሉ ውስጥ በማገገም ላይ ይገኛል።
“እግዚያብሔር ይመስገን ለዚኽ በቅቻለኹ” ያለው ዐዲስ፣ “ እኔን እዚኽ ለማድረስ የተረባረባችኹ በሙሉ እግዚያብሔር ብድራችኹን ይክፈላችኹ። ለእኔ እንደደረሳችኹልኝ። እግዚያብሔር ለእናንተም ይድረስላችኹ” ብሏል።
ዐዲስን ለማሳከም፣ የተረባረበው ሰው በቁጥርና በስም ተለይቶ የሚቀመጥ አይደለም። በኹሉም ነገር ከላይ እስከ ታች የተሳተፈው በሙሉ ድጋፉ ፍሬ አፍርቷልና፣ ኹላችሁንም እግዚያብሔር ይባርካችኹ። በደግ ይመልስላችኹ።
ጓደኞቹ እና የሞያ አጋሮቹ!"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።