#ትልቅ #ሰው #አይሞትም።

 

"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 
 
በተከታታይ በወል የሚሰጥ የታሪክ ትምህርት ላይ አስተምረውኛል። የተከበሩ ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ፤ ዴሌቦ ያን ጊዜ በኢትዮጵያዊነት ላይ ጠንከር ያሉ ጉልበታም አመክንዮችን በፋክት እያዋዙ ነበር ያሰተማሩኝ። በዘመነ ህወሃት መራሹ ኢህአዴግም ይሰጡ የነበሩትን ማብራሪያወችን አዳምጥ ነበር። #ማድመጥመልካም ነገር ነው። ከስማ በለው ዳኝነት ያወጣል።
 
ካልተሳሳትኩኝ በአምስተርዳሙ ኢሳት ከልጅ ፋሲል ጋርም ቆይታ ነበራቸው። ጹሁፍም የፃፍኩበት ይመስለኛል። ህወሃት ከመንበሩ ሲለቅም አቤቱ ፋና ሚዲያ በመኖሪያ ቤታቸው ተገኝቶ የዘገበውንም ያዳመጥኩ ይመስለኛል። ይመስለኛል በዛ። መረጃው ስለሚበዛ ከተሳሳትኩ ይቅርታ ከወዲሁ እገልፃለሁኝ። 
 
የሆነ ሆኖ የታሪክ ትምህርት ኢትዮጵያ ላይ ፈተናው ብዙ ነው። ችግሩ ወዘተረፈ ነው። የችግሩምየፈተናውም ብዛት ቋሚሥርዓት የመፍጠር አቅም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድርጅቶች መፍጠር ባለመቻላቸው ነው። ሰሞኑን አንድ ኦራተር ወጣት በአሜሪካ ለከንቲባነት ያደረገውን ጥረት አሳክቷል። የኒወርክ ከተማ #ከንቲባ ዞህራን ማምዳኒ 35 ዓመት ሳይደፍኑ ተመርጠዋል። የወጣቱ ፓለቲከኚ ጥረት ስኬትን ሃይማኖታቸው #እስልምና መሆኑ ወይንም የትውልድ አገራቸው ከአፍሪካዊቷ #ኡጋንዳ እና ከህንድ ቤተሰብ መገኘታቸው መሻታቸውን አላገደውም። ሁለት ጊዜ ባለ ዕድሉ ክቡር ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፤ ይሁኑ ክቡር ዶናል ትራንፕ አስግሮም ቢሆን ለምኞታቸው ዕውንነት ማዕቀብ ያልጣለው የተደራጄ #ህያው #ተቋም መኖሩ ነው።
 
ለምን??? አሜሪካ ቋሚ ሥርዓትን የገነባች አገር በመሆኗ። ተቋም መኖሩ ብቻ ሳይሆን ተቋሙ ህልውናው ትንፋሹን የማስቀጠል አቅሙ አንቱ በመሆኑ ነው። ስለሚተነፍስ ትንፋሽን ይለግሳል።
 
ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ ትውልዱ በብዙ የደከሙ፤ የተጉ ሙሁራንን፤ የለፋ የጥበብ ሰወችን ሲያጣ #በጎ #ነገሮችን ብቻ አስቦ መራራ ስንብቱን ቢያስተናግድ ምኞቴ ነው። በሌላ በኩል #ለነፃነት የሚተጋ መንፈስ #ለራሱ ነፃነት የመስጠት አቅም ሊኖረው ይገባል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። ይህ ከሆነ #ለሌሎችም ነፃነት የመስጠት አቅም #ማመንጨት ስለሚቻል። 
 
በሚያምኑበት ዘርፍ ለአመኑበት የታሪክ አቅም፤ ለየዘመኑ በሚመች መልክ እራሳቸውን #ሞድሬት በማድረግ ፕሮፌሰሩ ተግተዋል ሊቀ ሊቃውንቱ ሳይንቲስትም ነበሩ ለዘርፋ። #አልተሰደዱም። በባዕታቸው ኖሩ። በባዕታቸውም ለብትን አፈር ይበቃሉ። #ሰፊነት ቢሰጠንም አቅማችን ስለመቻሉ የእያንዳዳችን ሰብዕና ይወስነዋል። 
 
እግዚአብሄር አምላክ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር። አሜን።
ለቤተሰብ፤ #ለኢትዮጵያም፤ ለተማሪወቻቸው መጽናናትንእመኛለሁኝ።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
10/11/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።