በለው! ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር የግንባሩም የጽ/ቤት ሃላፊ ናቸውን? ዳጥ!
ጫን ተደል ሸክም።
„እንሆ አፌን ከፍቻለሁ
አንደቤተም በትናጋዬ ተናግሯል።“
መጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ ፴፫ ቁጥር ፪
ከሥርጉተ© ሥላሴ
ከጭምቷ ሲወዘርላንድ
በ/ሮዋ ዙሪያ ...
· መጀመሪያ ያመለክትኩበት ቀን 01.06.2018 - እርአስ አብይ ሆይ!
· ሁለተኛ ያሳስብኩበት ቀን 08.08.2018 - እርእስ - ቁልፍ
· ለሦስተኛ ጊዜ ማሳሰቢያ ያቀርብኩበት 25.08.2018 እርአስ
- ጫን ተደል ሸከም።
ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ
ደህና ነኝ። ሰሞናቱ ትንሽ ዕንባ ተገስ ስላለ ይመስለኛል ደህንነቴ። እትዬዋ ግን ዛሬ ክፍት ብሏት ጭጭ ብላለች። እጽዋት ግን
ባልሳቸውን ያስነኩታል በዝግታ እና በተደሞ።
v የቅድሚያ።
ኢትዮ ሱማኤልን በዘለቄታ መስመር ለማስያዝ የተወሰደው እርምጃ
እና ሲከወን የሰነበተው ብሄራዊ ተግባር እጅግ አስደስቶኛል። አብሶ የመሪ ለውጡ እና በሰባዕዊ መብት ዙሪያ ሲተጉ የነበሩት ቅን
የአካባቢው ተወላጆች አገር ቤት መግባት ለአዲሱ አማራር ማገር ሊሆኑት እንደሚችሉ ሳስብ ውስጤ ይረጋጋል ይጽናናልም።
በሰብዕዊነት ጉዳይ ላይ ትጉኽ የነበሩት የአቶ ሙስጠፋ ኡመር ወደ አማራር መምጣት፤
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ጀማል ዲሬይ ኸሊፍ አገር መግባት ከአያያዝ
ይፈረዳል ከአነጋገር ይቀደዳል እንዲሉ …. ተስፋን አሰንቆኛል።
በተያያዘ ዜናም በርካት ኢትዮ ሱማሌ ተወላጆች ከጠ/
ሚር አብይ አህመድ ጋር በአዲስ አበባ የተደረገው ውይይትም ተስፋን አበረታቶታል። ያው የሚያስፍልገው የአዕምሮ ዕጥባን በትጋት
መከወኑ ነው፤ ለዚህ ደግሞ አቶ ጀማል ዲሬይ ይሸንፋሉ ብዬ አላስብም፤ ሃላፊነቱን ወስደው የጎበጠውን ያቃኑታል ብዬ አስባለሁኝ።
በሌላ በኩል ጭንቅ የሚለኝ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ተስፋ የነፃ
ምርጫ፤ የነፃ ፕሬስ፤ የነፃ ፍትሃዊ ሥርዓት ግንባት፤ በነፃነት የመተንፈስ፤ በነፃነት የመኖር፤ በነፃነት የመመራመር፤ በነፃነት
የመደራጀት፤ በነፃነት የመሰብስብ፤ በነፃነት ሃሳብን የመግለፅ፤
በነፃነት የማሰብ፤ በነፃነት የመራመድ፤ በነፃነት የመጠበብ፤
በነፃነት የመገናኘት፤ በነፃነት የመሞገት፤ በነፃነት የመፍጠር፤ በነፃነት የመዘመር፤ በነፃነት የማዜም፤ በመነፃነት የመንደፍ፤
በነፃነት የማቀድ፤ በነፃነት የመከወን፤ በነፃነት የመጻፍ መንፈሱ ሁሉ የሚደራጀው የሚመራው ዴሞክራሲን ማዕክል አድርጎ
በተመሰረተው ቢሮ ውስጥ ነው። ለዚህ ቢሮ ሚ/ሯ ደግሞ ወ/ ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር ናቸው።
ይህም ብቻ አይደለም እኔ አሁን ነው የሰማሁት የአውራው ግንባር
የኢህአዴግ የጽ/ቤት ሃላፊም እኒሁ ሴት ናቸው። እሳቸው ደግሞ ጉዞችን ትክክል አይደለም፤ ወደ ቀደመው የጭካኔ፤ የፋሽስታዊ
ሥርዓት፤ የናዚዝም ዶክተሪን እንመለስ ባይ ናቸው።
እንዴት ይህን ሁለት ታላላቅ አካላት በሳቸው እጅ ሥር
እንዲወድቅ እንደ ተፈለገ ግልጽ ባይሆንልኝም እሳቸውን ተሸክሞ ስለዴሞክራሲ አፈጻጸም መመስከር ቀርቶ ሃሳቡን ማሰብ የማይቻል
መሆኑን ቀድሞውንም ተናግሬያለሁኝ አሁንም በዛው አቋሜ እጸናለሁኝ።
ምክንያቱም የአሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ ነውና። ጽ/ቤት ሃላፊ ማለት
እኮ ሊቀመንበር ማለት ነው። አስኳሉ ያለው ከዚህ መዋቅር ውስጥ ነው። ዴሞክራሲዊ የሆነውን ሸግግር እኔ እመራዋለሁ የሚለው
ኢህዲግ የዴሞክራሲ መደወሪያው ሰቁንም ራሱ እኒህ ሴት በሚ/ር ማዕረግ እንዲይዙት አድርጎ ነው።
ይሄ ቧልት ነው ለእኔ። መቼም የአማራ ተጋድሎ እና የኦሮሞ
ንቅናቄ ለዚህ ከነበረ ትግሉ ከንቱ ነበር ማለት ነው። የእውነት ከንቱ። ይሄ ሲታሰብ የማግስት ተስፋ እንደ ጤዛ ነው የሚታዬኝ
ለእኔ።
እርግጥ ነው የጠ/ ሚር አብይ አህመድን ቅንነት በሚመለከት እኔ
ሥርጉተ ሥላሴ አስተርጓሚ አልሻም። የድል አጥቢያ አርበኞች ይጭነቃቸው። ነገር ግን ይህ ብቻውን ወደ ታሰበው ያመራል ለሚለው
ግን አይመስለኝም።
ስለመን? ባለው ሰባራ ስለሆነ። ካለግድግዳ ቤት አይቆምም።
ግድግዳ የሌለው ተስፋ የሁሉም ማዕዶት መሆን አይችለም። ለዚህ ነው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ለተወሰነ ጊዜ ሲሰወሩ ህዝቡ ራድ
በራድ የሚሆነው።
ራሱ የሃይማኖት ተቋማት እኮ ከዚህ መዋቅር ጋር በመንፈስ
ይገናኛል። በነፃነት ማመን፤ በነፃነት ያመኑትን ማድረግ፤ በነፃነት ቤተ እምነትን፤ የማደራጀት፤ የመመራት፤ የመገንባት ወዘተ …
ይህ ዘርፍ የማይነካው አንዳችም ነገር የለም። ኢትዮጵያ ይህን
ያህል የሰው ድረቀት አለባትን ለዚህ ሁለት ትላልቅ አንኳር የነፍስ ጉዳይ እኒህን ሴት ሚ/ር አድራጋ የምትሾመው? የኢህአዴግ
ጽ/ቤት ሃላፊ አድርጋ የምትሾመው? ዋናውን አንጎል ሥፍራ በጣምራነት አስረው እኮ የያዙ ሴት ናቸው።
"የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑትን ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሔርን ስለጉዳዩ ቢቢሲ ጠይቋቸው" … ዋናው
ፍሬ ዜናው ሳይሆን የግንባሩ የጽ/ቤት ሃላፊነቱ ብቻ ነው ለጭብጤ የሚረዳው፤ ሌላው አይስፈልገውም ለጹሁፌ።
እኒህ ሁለት ወሳኝ የሃላፊነት ቦታዎች በዴሞክራሲያዊ አብዮት ስታሊንዝም መማራት? ህም! ወ/ሮ ፈትለወረቅ ገ/ እግዚአብሄር በሚኒስተር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ
ማስተባባሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ መሆን፤ ለላው ዳጥ እና ምጥ ደግሞ የኢህአዴግ የጽ/ ሃላፊነት?
ተዚህ
ላይ አንድ ልባም ነገር አሁን በኢትዮ ሱማሌያም ሆነ በአዲስ አባባ ከንቲባ ሹመትን መርህ የተከተለ አልነበርም፤ የነገረ ዶር
ደብረጽዮንም እንዲሁ ታዲያ እዚህስ መርህን ጣስ አድርጎ ምን አለ ነፍስ ያለው፤ ህሊናዊ፤ ሰብዕዊ የሆነ፤ ነፍሱ በተፈጥሮዊ
መንፈስ የተቀመም ለግራ ቀኙ ቦታ ሰብዕና ቢመደብ።
አሁን ካለው አቋማቸው ጋር ትናንትም እኔ የሚ/ር ሹመቱ
እንደማይመጥን ብቻ ሳይሆን ቢሮው ከማንፌስቶ አምልኮት ውጬ የሆኑ ቅኖች፤ ልምድም፤ እውቀትም፤ ተመክሮም ያላቸው ብቻ እንዲሆን
ያመለከትኩተበት መሰረታዊ ምክንያት እሳቸው ሊለወጡ እንደማይችሉ ስላወቅኩ ነበር። ከድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ነው።
አሁን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ምን
ያህል አቅም እንዳላቸው አላውቅም። እኔ አሁንም በቀደመው ከሰሜን አሜሪካ ጉዞ በፊት በነበረው በሙሉ የሥልጣን አቅም እና
ባላቸው ልዩ ታለንት እዬተንሳቀሱ ነው ብዬ ማመን የሚያስችለኝ አንዳችም ጭብጥ የለም እና።
የሆነ ሆኖ አሁንም አብይ ሆይ! ማመልከቻዬ ውስጥ ባለፈውም ጊዜ
ቆርጬ አቅርቤዋለሁኝ አሁን ሰሚ ቢገኝ ማልከቻዬ ያልተሳሰት እንደ ነበር እና የነገ ተስፋን ቀብሮ ተስፋን ተነስ ብሎ ማዘዝ
እንደማይችል ብቻም ሳይሆን፤ ይሄ ለውጥ … ለውጥ … ለውጥ እምንለው ነገር ይህ መዋቅር ካልተሰተካከለ፤ በዚህ መዋቅር ላይ ሥር
ነቀል የሆነ ለውጥ ካለመጣ ተስፋ ተቀብሮ ይቀራል።
ይህ መዋቅር አደረጃጃቱ በዛው ከቀጠለ „ገድሎ እግዚአብሄር
ይማርህ“ ነው የሚሆነው - ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ።
ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር አሁንም ከጭካኔዊ መንፈሳቸው
አረንቋ ለመውጣት አለመፍቀዳቸውን የግድ ለሦስተኛ ጊዜ ድጋሚ አቀርባለሁኝ። ሰሚ እስኪገኝ ድረስ። የኔ ውዶችም ሳይታክታችሁ ሸር
አድርጉልኝ።
ያለፈው
ለሁለተኛ ጊዜ ሳቀርበው „ቁልፍ““ በሚል ርእስ ነው። በዛሬው ደግሞ „ጫን ተደል ሸከም“ ብያዋለሁኝ።
የኢህአዴግ
አንጎልም እሳቸው ናቸው የጽ/ ቤት ሃላፊ ከሊቀመንበሩ ቀጥሎ ያሉ የሚገኙ ባለ ልዩ ቁልፍ፤ በተጨማሪነት የዲሞክራሲም ህሊና
እሳቸው ናቸው ሚኒስተር ናቸው ለዘርፉ።
ሌላ
ጥያቄ አያስፈልግም አሁን መጀመሪያ ይሄ ይስተካከል መሆን አለበት። ስለሆነም
የቀደመው በቁልፍ ርዕስ ያቀርብኩት ይደገም ብያለሁኝ እስከ ሙሉ ማንነቱ።
አሁን ለሦስተኛ ጊዜ አመልከትበት አንኳር ምክንያቱም እኔ ያልኩትን ነገር በውን ያሳዬ ከራሳቸው ከወ/ሮ ፈትለወርቅ
ገ/ እግዚአብሄር አንደበት፤ ውስጥነት የታቆረው የበቀል ስሜት፤ አረመኒያዊነት የናፈቀው ህሊና ድጋሚ ለነፃነት ይፋዊ የሞት
ዓዋጅ ስለታወጀ። ሰነዱ ይሄውና።
የህወሓት ህልም የሞንጆሪኖ ቅዠት
ይህን ድምጸት
እና የእኔ የቀደመ አቤቱታ ታገናዝቡት ዘንድ ብቻ ሳይሆን ማግስት በተስፋ እንዲዘልቅ ከተፈለገ የሽግግር መንግሥት፤ የተጽዕኖ ፈጣሪዎች
አንድነት መንግሥት፤ የምርጫ ሥርዓት መስተካከል ሳይሆን ይሄ መዋቅር በሥርዓትና በተጠና ሁኔታ እንዲደራጅ መትጋት ነው ያለብን
የሚመስለኝ። ሙሉ ሃሳቡን ለማግኘት ሊንኩ ይሄውና።
የኔዎቹ ውዶቹ ቁልፍን ከዚኸው ብሎግ ታገኙታላችሁ ሊንኩ
ይሄውና።
"ዴሞክራሲ ቃሉ ብቻ ሳይሆን የህሊናው ማሳ ነው እውነትነት።"
ዴሞክራሲ በመፈለግ እና በመፈጸም፤ በማስፈጸም ረገድ
የህሊና ለውጥን ይሻል።
የኔዎቹ ኑሩልኝ መልካም ቀን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ