የነገ መረጃ!

ፍልስፍናዊ አመራር።
   „የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል 
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“
ምሳሌ ምዕራፍ  ፲፮ ቁጥር ፱
ከሥርጉተ© ሥላሴ 
25.08.2018 
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


                                ለዚህ ፎቶ እኔ ትልቅ አክብሮት አለኝ።

ኢትዮጵያ ዕድለኛ የሆነችበት ዘመን ብዬ እማስባው ይህን ዘመን ነው። ለዚህም ነው ከጣና ኬኛ ጀምሮ በትጋት በግል የሚጣሉብኝ ሳንኮችን ሁሉ ተቋቁሜ፤ ጫናዎችን ሁሉ ተጋፍቼ፤ ማስጠንቃቄያዎችን ሁሉ ቸል ብዬ ለዚህ ንጹህ መንፈስ ስሞግት የባጀሁት። ትንፋሼ እሳከለች ድረስም ጉዳዬ የድምጽ አልባዎቹ ኢትዮጵያ እናቶች ዕናባ መግቻም መድህን ነው ብዬ በጽኑ አምናለሁኝ። 

ወይ ዛሬ ወይ ነገ ጋዜጣዊ መግለጫ ይኖራል ተብሏል። በዛም ብዙ የዘበጡ፤ የተስረከረኩ ዘንባለ ዕሳቤዎች ደግሞ መልክ ይይዛሉ ብዬ አስባለሁኝ። እርግጥ ነው ከሰኞ ጀምሮ ደግሞ አቤሽን አካባቢ ጸጥ ረጭ እንደሚልም አንድ መርዶ አለ። ችግሮችን ከሥር ለማድመጥ የፈቀዱት መሪ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ መፍትሄ ያገኙለታል ብዬም አስባለሁኝ።

የሆነ ለእኔ መሪ ማለት ችግር ላይ ጥናት ያደረገ፤ ያን ችግር መፍትሄ ለመስጠት መንገዶችን የተለመ፤ የተለመውን ለመተርጎም ደግሞ ጥበብ ያለው ነው መሪ ማለት ለእኔ። ሌላው እኔ መሪ የምለው በቀደሙ ችግሮች ብቻ ሳይሆነ በገጠመኞች በሚፈጠሩ የገዘፉ አዳዲስ ችግሮችም ሳይደናገጥ፤ ሳይርበተበት፤ በስክነት እና በእርጋት የችግሩን የመነሻ ፌርማታ አጥንቶ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ጥበቡን ከህሊናው የማፍለቅ አቅም ያለው፤ በዚህም ተከታዮቹን አሳምኖ ወደ ድርጊት ለመቀዬር የቆረጠ ማለት ነው።

ይህንም በጂጅጋ በሰው ሰራሽ ችግር የማምረቻ ማከፋፈያ አካባቢ የሆነውን የኢትዮ ሱማሌ የመጀመሪያ የሥራ አህዱ ማድረጉን ብቻ ሳይሆን ያልቆመውን ችግር መፍትሄ ለመስጠት የሰሞናቱ ነፍስ ያላቸው ትጋቶች የአንድን ብልህ መሪ ብቃት ክህሎት ወደ ፍልስፍናዊ ደረጃ ክፍ እንዲያድግ ያደርገዋል።

በዚህ ዙሪያ እኔ እጅግ ብዙ ሥራዎችን ስለሰራሁኝ እነዛን ቅኖቹ ጊዜ ሲኖራችሁ በምልሰት ብትቃኟቸው ፍሬነገሮችን ታገኙባቸዋላችሁ። ዛሬ ይህን የሚያጠናክር ቪዲዮ አገኘሁኝ እና ለጥፍኩላችሁ። ይህን አዳምጣችሁ ስታበቁ ደግሞ በድምጽ አልባው የፍቅራዊነት የቃላት የፖስተር ዝግጅቴ ላይ ያቀናበርኩትን ክፍል አንድ የቪዲዮ ክሊፕ ተመልከቱት። ይሄ እንግዲህ የምዕራፍ አንድ ክንውን ነው። ከሰሜን አሜሪካ መልስ እክሎች እና ሂደቶችን ደግሞ በቀጣዮቹ ጊዜያት አብረን እናያለን።

እራሱ የኤርትራን ችግር ለመፍታት የሄዱበት መንገድን የባድመ ዕድምታ በሥርጉተ ዕይታ ማንበብ ትችላላችሁ። ሊቃናት አፈጻጸም ላይ ሲዳክሩ እሳቸው የጀመሩበት እና ለውጤት የበቁበት ነገር ፍልስፍና ነው ዘመንን የሚያናግር ነው። ባጠቃላይ ሲታይ ውስጣቸውን ለመግለጽ አቅሙ ባይኖረኝም እንደ ሰው ግን በቀደመው የመንፈስ ቀረቤታዬ ተነስቼ የገመገምኳች፤ የሰጣኋዋቸው ምስከርነት፤ ያሰብኳቸው ሂደቶች በሙሉ በሳቸው አንድበት እንዲህ ተቃኝተዋል።

ዶር አብይ አህመድ አስደንጋጭ ትእዛዝ ሲሰጡ በድብቅ የተቀረፀ ቪዲዮ ይፋ ሆነ


ቀጣዩ ሊንክ ደግሞ ምዕራፍ አንድን እኔ በዝምታዬ ውስጥ የሰፈነው ውስጤ የገለጽኩተብ ቪዲዮ ነው ይህ የቪዲዮ ክሊፕን እና ይህ የተቀዳው ድምጽ ውህደቱን እናንተው ለኩት።
ሌላው ሲጨንቀኝም፤ ሲከፋኝም፤ ጥርጣሬ ሲኖረኝም፤ ስደስትም፤ ወስጤን ሳስነብብም በጠቅላላ ማለት እችላለሁ ቀንበጥን የጀመርኩበት መሰረታዊ አምክንዮም ይህን ንጹህ መንፈስ፤ ይህን ቅን መንፈስ ለእኔ ለራሴ ለፍቅራዊነት ፕሮጀክቴ ዋቢ ስለሆነም ጭምር ስለሆነ ሁሉንም የተጻፈበትን ቀን እያዬችሁ ብታነቡት በዚህ ሰብዕ ጭንቅላት ውስጥ ኢትዮጵያን ቁምነገር ከማድረግ ራዕይ ውጪ ሌላ ተለጣፊ መንፈስ እንደሌለ ትረዳላችሁ ብዬ አስባለሁኝ። 

ስለሆነም እኔ በመጻፍ እናንተ ደግሞ በማንበብ ስትችሉም ሸር በማደረግ ያደረግነው ተሳትፎ በውንም ኢትዮጵያን ቁም ነገር ከማድረግ ውስጥነት የመነጬ ስለሆነ ዝቅ ብዬ ላመሰግናችሁ እሻለሁኝ። ተባረኩ ኑሩልኝ። በተለይ ሳተናው ድህረ ገጽ ብዙ ስለረዳኝ እሱንም ከውስጤ፤ ከህሊናዬ ላማሰግነው እሻለሁኝ። ብዙ በጣም ብዙ ረድቶኛል። ይባረክ!
Ethiopia's Prime Minister Abiy Ahmed DR

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

ኑሩልኝ አዱኛዎቼ ማለፊያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።