ትግራይ ሳትለግም።

ልዕልተይ ትግራይ ከፈለገች 
ፍቅራዊነት አይሳናትም። 
ለግማ ነው እንጂ።

„ሕይወት ከእግዚአብሄር የሚገኝ ሲሆን 
ድርጎውን ከንጉሥ ይቀበላል።“
መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፩  
ከሥርጉተ© ሥላሴ
25.08.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።

እኛ የምናውቃት ትግራይ እንዲህ በሰንደቅዓላማዋ፤ በሃይማኖቷ የማትደራደረውን 
ዕንቁዋን ነው!
የህዝቡን የኑሮ ደረጃም የህፃናቱ የለበሱትን አልባሳትንም እንዲሁ ማስተዋል ይቻላል። 


ዛሬ ስለልዕት ትግራይ ትንሽ ልበል። ትግራይ የታሪክ ማህደራዊ ባዕት ናት። ትግራይ በቀደመው ጊዜ በነፃነት ዙሪያ የተምሳሌት ባዕት ናት። ትግራይ በቀደመው ዘመን የሰው አደራ የሚገኝበት ባድማ ናት። ትግራይ በቀደመው ዘመን የሃይማኖት ጽናት ጽላታዊ ተምሳሌት መንደር ናት። ዛሬስ ያ ዕሴታዊ ትሩፋት እና ትውፊት ሃዲዱ? ስለምትሉት እኔ ሳይሆን ራሳችሁን ትጠይቁ ዘንድ በትህትና አሳስባለሁኝ።

ያው የእኔ ሞቶ ለድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች ስለሆነ ትግራይም በዚህ ትታደማለች። ስለሆነም ስለነገ የትግራይ ህፃናት ስላልተወለዱት እጅግ ይጨንቀኛል። ሴቶቹ የነገም እናቶች፤ ሚስቶች እናሱው ናቸው እና። በተወሰነ ደረጃ የረገበ ነገር ያለ ቢመስልም ትግራውያን ግን አሁንም እንዳደቡ እንደሆነ ይደመጣል። 

የሚዋጣቸውን የሚያውቁት እነሱ ስለሆኑ ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው ስለሆነ ይታለፍ አመክንዮው። በሌላ በኩል ግን "ለተራበው ትቼ ለጠገበው የማዘን ግዴታ" ስሌለብኝ ሹመኞችን መሳፍንታትን ግን እስኪባቀቸው በሰላ ብዕሬ ሰወቃቸው ባጅቻለሁኝ።

የሆነ ሆነ በ27 ዓመቱ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት በደረሰው ህዝባዊ በደል ትግራይ በፀጥታ በዝምት ላይ ነበረች። የወገኖቿን የእትብቶቿን ዕንባን ለመጋራት አልደፈረችም። ባላፉት ሦስት ዓመታት በነበረው እጅግ ጭካኔ የተሞላበት የሰብ ዘር የግፍ ክምርም ዝምታዋን ጥሳ ወጥታ ተው ማለትን አልደፈረችም። ግራጫ ነጠፈባት፤ የሃይማኖት አባቶች መከኑባት።

ልዕልት ትግራይ „ችግራችን ድህነት ነው ድህነትን አብረን እንመክት“ ከማለት ውስጪ ህዝባዊ፤ ብሄራዊ በሆኑ የህዝብ በደሎች ላይ ድመፆዋን አለሰማችም። በዚህ በአራት ወራቱም አዲስ የለውጥ ሂደትም ያዬነው አይተናል። የአሉላ አባነጋ እስቴዲዮም ስሙ ደስ ብሎኛል የታዬው ትርኢት የሰማዕታት ቀን መታሰቢያ ለሁለተኛ ጊዜ በአንድ ፈረቃ ሩብ ዓመት ላይ እንዳከበረች አመላካች ነበር።

ትግራይ በኛ ውስጥ እንጂ እኛ በእሷ ውስጥ እኛ የሌለን ስለመሆናችን ዝምታዋ አውጆልናል። ጎንደር ስትነድ እንኳን ትግራይ አላውቅሽም ነበር ያለችው፤ የአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባን ችግርም ከመጤፍ አልቆጠረቸውም ነበር ልዕልተይ ትግራይ። ምንድ ነው ሲባል ትግራይ ታፍና ይባላል። እንዴት ነው ነገሩ ሲባል ትግራይ አይፈቀድላትም ይደመጣል።

 ሌላውም ተፈቅዶለት አልነበረም ከአንድ ጊዜ እስከ ሁለት ጊዜ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀበት። ሌላው ተፈቅዶለት አለነበረም በወር ውስጥ 50 ሺህ ልጆቹን በቃኝ ግፍ ሲል ለካቴና የዳረገው። ሌላው ተፈቅዶለት አለነበረም ልጆቹ በ አጋዚ ሲታረዱ የነበረው፤ ብቻ ልዕልት ትግራይ አልፈቀደችም ነበር ቢባል ያስኬዳል።

ስተፈቅደማ ቅደመ ሁኔታ፤ የሊሂቃኑ ትርክት፤ የህጉ ድንጋጌ፤ የሚዲያው አርቲ ቡርቲ ሳይገድባት የቀደመውን የአባት አደሩን "ትምክህተኛ ጀብደኛ ነፍጠኛ" የተባለለትን ብሄራዊ ሰንድቅ ዓለማውን ልሙጡን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን የድል መባቻ፤ የድል ማስከኛ፤ ሰንድቅዓላማዋን እያውለበለበች፤ እንደ አባት አደሩ የቤተ እግዚአበሄርን ጃንጥላውን ዘርገታ በመንፈሷ ታቦቷን ተሸክማ መረብን ተሻጋራ ወገኖቿን አገኝኝታ ተቃቅፋ፤ ተሳስማ፤ የልቧን አውግታ፤ ከትከት ብላ ከልቧ ፈክታ ስቃ ተሳስቃ፤ የተገኘውን አብራ ተቋድሳ  ለአዲሱ  ዓመት በወልዮሽ እንደ ጥንቱ እንደ ጥዋቱ እንዳ አባት አደሩ አበባዮሆሽን በወል ልትል ወስና ቀን ቀጥራ ወስና ተመለሰች። የጎመን ምቸት … ልትል …

ልዕልተይ ትግራይ ፈንጂው ከመንገድ ያስቀረኛል ሳትል፤ ካቴናው ይጠብቃኛል ሳትል፤ የጥጋበኛ መሪዎቿ ቅጣቱ ይጫነኛል ሳትል ወፍ ጭጭ ከማለቱ ቀድማ፤ በጥዋቱ ማልዳ ተንስታ የልቧን ከውና፤ የልቧን አድርሳ ተስፋዋን በህሊናዋ ቆጣጣራ ተመለሰች። 

ትግራይ ከፈለገች ሁሉንም ትችላለች። እስካሁንም አለመፈለጓ፤ አለማመኗ ብቻ ነው ነጥሎ ደሴት አድርጎ ያስቀመጣት እንጂ ስትፈልግማ አዲስ ጀግንነት አዲስ ምዕራፍ በፈቃዷ እንሆ ከፈተች። 

የታላቋ ትግራይ የጀርመን ድምጽ የአማርኛው ክፍለ ጊዜ ልዩ ዘጋቢ አቶ ሙሉጌታ አፅብሃ እንደዘገቡት … ያው የአማሪካኑም ድምጽ ልዩ ዘጋቢ አለው ትግራይ ላይ። ሃያሏ ትግራይ እንዲህ በፖለቲካ ሥነ - ልቦናዊ የበላይነት አቅም ሁሉንም ሰጥ ለጥ አድርጋ ስትጋዛ፤ እንዳሻት ስትነዳ ባጀች … የገጠሩ ህዝብ ነዋሪ የልጆች መንፈስ ደግሞ እንደሚታዬው ነው። የዘመኑ ተጠቃሚዎች እና በሥም ንግድ ያለው ነገር ለማገናዘብ ጥሩ ስልዕል ነው የሄ ... የራማ ነዋሪዎች ምስለ ፎቶ ...
  • ምርኩዝ። 

ያለፍቃድ የኤርትራን ድንበር አቋርጠው የገቡት የትግራይ ተወላጆች

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
ቅኖቹ ክብረቶቼ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።