የመቀሌ የፖለቲካ ትኩሳት ደግሞ ወደዬት?

በዕለ አሸንዳ በትግራይ።
 ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥
በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም።
 የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልዕከት
ወደ ቆረንቶስ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፲፪

ከሥርጉተ© ሥላሴ
25.08.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።





መቀሌ እንደለመደባት ሞቅ ደመቅ ብላለች። በሁለተኛው ስታዲዮዋ ላይ ደግሞ ሁለተኛውን ባዕሏን እያከበረች ነው። የትግራይ ባልሥልጣናት በሙሉ በተገኙበት በዚሐው ባዕል ላይ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በባህላዊ ቀሚሱ ተውበው ተገኝተዋል። 

በዚህ ባዕል ላይ ከትግራይ ደም ያላቸው ተዋናዮችን እና ታዋቂ ሰዎችም አንደተገኙ መረጃው ይጠቁማል። ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤልም አብያዊ ለመሆን በተሸለ አቀራረብ በሚመሯቸው ወገኖች ማህል ሰላምታ በመለዋወጥ እና በማከበር ቀረቤት እንዳላቸው አንድ ያልተለመደ ነገር ሲሳዩ ተመልክቻለሁኝ።

ይህም መልካም የሆነው ያልተለመደው ነገር በወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥር የወደቁ ነፍሶችን ከእሥር በባዶ 6 ያሉትን ግፉዕና በማስለቀለቅ እና የወረሩትን መሬት በክብር በመመለስ አብነቱን ወደ ስልጣኔ ቢያሻግሩት ምንኛ ይህ ድርጊታቸው ከልባችን በገባ በነበረ።

በዚህ የአሽነድዬ ባዕል ባህላዊ ውዝዋዜውንም ሲያኬዱት ተመልከተናል። ከውስጣቸው ይሁን አይሁን አይታወቅም ብቻ ደስ ብሏቸው ሲወዛወዙ አይቻለሁኝ። በዚህ ዓመት በነበረው የትግራይ ህዝባዊ ኮንፈረንስም ላይ እንዲሁ ልባቸው ጥፍት እሲክል ድርስ ሲጨፍሩ አይቻለሁኝ። ይህ መቼም ሰውኛ ነው።

እንደ ሰውኛ ጭፈራው ደግሞ ሌሎችን የሸር ገመዶችን እና የሴራ ድሮችን ተወት ቢያደርጉት መልካም ነው። ከሴራ፤ ከሸር፤ ከተንኮል ጋር መፋታተትም ሰውኛ ስለሆነ።

በዚህ የአሸንዳ ባዕል ግብዣ የተደረገለት ንጉሥ ጃዋር መሃመድ ነበር፤ እንደ የወያኔ ሃርነት ትግራይ አክቲቢስት አቶ አሉላ ገለጻ ከሆነ። ነገር ግን የተገኙት በወያኔ ሃርነት ትግራይ ፈቃድ ያገኙት ደርባባዋ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ናቸው። መጠራቱም፤ ጠሪ አክብሪ ስለሆነ መገኘቱም መልካም ነው። መጠርጠር የተጋባ ባይሆን አጋጣሚው ቀጣይ ግንኙነቶች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ግድ ይላል። የሚሊዮን ነፍስ ጉዳይ ስለሆነ ... የሚሊዮን ተስፋ ጉዳይ ስለሆነ ... 43 ዓመት የባከነው ትውልድ የተስፋ አንባ ስለሆነ ... 

ወደ ቀደመው ምልስት ሳደርግ ...

ባላፉት ሳምንት አንድ ዓለም አቀፍ የሴቶች ሰላማዊ ጉባኤ አዲስ አበባ ላይ ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ሳይሆኑ የቀድሞዋ ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ነበሩ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት። ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ መክፈታቸው ችግር የለበተም ግን ለእኔ ስጋት ጥሎብኝ ነበር ምን ሆኑ ብዬ። ጽፌያለሁም። ትናንት መቀሌ ላይ ሳያቸው ግን ከእነ ሙሉ ግርማቸው፤ ሞገሳቸው፤ ክብራቸው በተለመደው የማይጠገበው እርጋታቸው ጋር ስለሆነ በውነቱ ደስ ብሎኛል። ትግራይ ላይ መገኘታቸውም ማለፊያ ነው። በስተጀርባው ሌላ ድር ከሌለበትስ። ማዬት ጥሩ ነው ከግድፈት ይታደጋል፤ ሚዛናዊም ያደርጋል።

የሆነ ሆኖ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ምን ታይቶት እንደጋበዛቸው አላውቅም። በዚህ ባዕል ላይ ሞዴል ፍርያት የማነ እና ሌሎችም አርቲስቶች ተገኝተዋል። ተዋናይት ሰላም ተስፋዬ እና ተዋናይት ሩታ መንግሥትአብም… አክሎ። 

ተዋናይት ፍርያት የማነ እና ደርባባዋ ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የቀሃ፤ የአንገርብ፤ የፈጭፋጭት ወንዘኛ ናቸው።

ስለዚህ ምን ተፈልጎ እንዲህ የቀረበ ግንኙነት እንዲፈጥሩ እንደታሰብ መገመት ብዙም ባይቻልም በወንዘኛ ቋንቋ አንድ መስመር የታሰብ እንዳለ አስባለሁኝ። እንዲህ አይነት ግነኙነቶች ከጠነከሩ ሊያመጡ የሚችሉ ስጋቶች መጠነ ሰፊ ናቸው።

የትግራይ እና የኤርትራ አንስቶች በጣም ብልሆች ናቸው። አጋጣሚዎችን አያሳልፉም። እኔ እራሴ ሥራ ላይ በነበርኩበት ጊዜ የቅርቦቼ የትግራይ ልጆች ነበሩ። የትላላቅ ባለስልጣነት የትዳር አጋራቾም ከነዚህ ከሁለቱ አያልፍም ነበር።

አሁንም ባለው የነፃነት ነፍስ ውስጥ ይሄ አምክንዮ እንዳለ ይታያል። ይህን ተልዕኮዊ ተግባር አማራው፤ ጉራጌው፤ ከንባታው፤ ሲዳማው ወዘተ አይከውነውም፤ በፍጹም አናስበውም። እነሱ ግን ከሃሳቡ በላይ ናቸው። ብልህም ናቸው።

እንደ እኔ ከወያኔ ተፈጥሯዊ ባህሪ ስነሳ ይሄ ግብዣ ዝም ብሎ የተጠመደ ነው ብዬ አላስብም። ቤተ መንግሥት በትዳር ካልተቻለ በጓደኝነት፤ በአብሮ አደግነት፤ በጋብቻ ዝምድና ወዘተ መጥመድ የተለመደ የፖለቲካ ስልት ነው …. ስለሆነም በግራው ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአበሄር በቀኙ የታጋሩ ነፍስ ጎንደር ተውልዳ ያደገችው ወ/ት ፍርያት የማነ አንዲገናኙ የተደረገበት ሚስጢር በተደሞ ሊታይ የገባዋል። እንዲህ በልሙጡ ወይንም በዝርጉ ሊኬድበት አይገባም። 

በዚህ ባዕል ላይ የቀድሞው የራዕያችን ንጉሥ የሚሏቸው የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወይንም ልጆች አልተገኙም። የሙት ዓመቱም ሲከበር እንዲሁ። ነገር ግን አንድም የዶር አብይ ፎቶ ይዘው ለመውጣት ያላደፈረው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ለምን ስልት እና ዘዴ ቀዳማዊ እመቤትን ለመጋበዝ እንዳሰበ በግርድፉ ሊኬድበት አይገባም።

እነሱ ሳያቅዱ፤ የማያተረፋቸውን መስመርን እንዲህ ደፈረው አያደርጉትም። ለዬትኛው ፖቲካዊ ሴራ ማካካሻ፤ ለዬትኛው ሴራዊ ማግለያ፤ ለዬትኛው ቀጣይ ተንኮላዊ ስልት እና ስትራቴጂ፤ ምን ዓይነት ሚስጢራዊ ውስጥን ለማግኘት እንደታሰበ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቅ። ይህን በቀደሙት ቀዳማይ እመቤትም ካለፈኝ በስተቀር ዜና አላደመጥኩኝም ነበር። ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ትግራይ የተጋበዙበትን ዜና አላስታውስም።

ይሄ የትኛውም ክልል ላይ ቢሆን ምንም አይደንቅም። ትግራይ ላይ ግን ፖለቲካዊ ትርፍ የያዘ ስለመሆኑ ለአፍታም ቸል ሊባል አይገባም። ጎንደር ላይ ተገኝተው ነበር ደርባባዋ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ባባዕታቸው፤ ግን ከዛች ትንታግ ወጣት ወ/ሪትንግሥት ይርጋ ጋር እንዲገናኙ አልተደረገም። አልተፈቀደም። ጠ/ ሚር አብይ አህመድም ጎንደር ሄደው  ነበር ከኮ/ ደመቀ ዘውዴ ጋር እንዲገናኙ አልተደረገም። አልተፈቀደም።  

ነገር ግን ከንጉሥ ጃዋር መሃመድ ጋር ሁለቱም እንዲገኙ ተደረገ ወጣት ንግሥት ይርጋ እና ኮ/ ደመቀ ዘውዱ። አሁን ደግሞ ወጣት ፍርያት የማነ እና ቀዳማዊ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው መቀሌ ላይ እንዲገናኙ ተደረገ። ለዚህ ቁልፍ ብልህነት ይጠይቃል።

የሆነ ሆኖ ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። እና ቀጣይ ግንኙነቶች በሚመለከት ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል ባይ ነኝ። ከጥንቃቄ ትርፍ እንጂ ኪሳራ የለም እና። ሁኔታዎችን ከፖለቲካ አንጻር ከሆነ ቅንነት ብቻውን የሂደቶችን ውስጠት ሊያስገኝ አይችልም። ስልታዊ ሂደቶችን ከደህንነት ጋር በውል ሊተኮርባቸው ይገባል። 

በተለያዬ ሁኔታ ለምን? ስለምን? እንዴት? መቼ? ወዬት ብሎ መጠዬቅ ግድ ይላል። እኔ እንደውጭው ሳያቸው ቀዳማዊ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በእምነት ጉዳይ ያተኮሩ ስለሆነ ገር ናቸው ብዬ አስባለሁኝ። እንደዚህ ዓይነት የፖለቲካ አኒትሪጎች ላይገቧቸው ቢችልም ግን ለትዳራቸው ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ዓይን ሲሉ ጠንቃቃ መሆን ያለባቸው መሆኑን በአጽህኖት፤ በተደሞ ማስገንዘብ እወዳለሁኝ።

ለምሳሌ ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤል ቅዱስ ወብፁዑ አባታችን አቡነ መሪቀርዮስን ሊጎበኙ ስሄድ ደስ ብሎኝ ሁሉ አንድ ራሱን የቻለ ወግ ጽፌ ነበር። ይህን ግን በፍጹም ከጥርጣሬ ውጪ ላዬው አልችልም … ትንሽ ገፋ አድርጎ ማሰብ ብቻ ሳይሆን ትንሽ ገፋ አድርጎ መመራመርም ያስፈልገዋል። ፖለቲካዊ ስልጣን የዳማ ጨዋታ ስላልሆነ … የ100 ዓመት ህልም እንዲህ ሩብ ላይ ሲቀር ብዙ ነገር በርቀት ማሰብ ይገባል …

ይህን ማለቴ ግን በነበረው የወልዮሽ ፌሳታ አብሮ ታገሪነቱ፤ የሁለቱ አብሮ ፎቶ መነሳት፤ አብሮ ለተወሰነ ጊዜ በቅንነት መነጋገር ሰውኛ ነው። እኔ ከዚህ የዘለለ ቀጣይ ግንኙነት ከኖረ ግን ብዙ የማይቻሉ ችግሮችን ወላጅ ነው የሚሆነው … በዚህ ላዩ እሳት፤ ጎኑ እሳት ምድሩ እሳት በሆነው አብያዊ አመራር የሚረዳው ቁጥብነት ብቻ ነው። መቆጠብ ነፍስን ማሰንበት ብቻ ሳይሆን አያባካንም፤ ሰላምም ይሰጣል። እኔ ሰላሜን እማስጠብቀው በመገደሜ ነው።

ይህን መንገድ ባልመርጠው ድሮ ገና አለቆቼ ይፈሩት እንደነበረው በቀንበጤ ከስሜ እቀር ነበር። ጠንቃቃነት ከምንም እና ከማንም በላይ ጥቃትን ያወጣል። ሁሉንም ነገር በመወስን፤ በደንበር፤ በደረበቡ ማድረግ ህይወትን ማሰነበቱ ብቻ ሳይሆን ከህሊና ጋርም ያዘልቃል። ከማንም እና ከምንም በላይ ደርባባዋ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እንደ አባት አደሩ ትሩፋትና ትውፊት ጠንቃቃ መሆን አለባቸው ብዬ አስባለሁኝ። የ አብይ ነፍስ ከ እግዚአበሄር በታች ጥቃቄ ሊያደርጉለት የሚገባው ከሚስትነት ጋር ብቻ ሳይሆን በፖለቲካዊ እሳቤም መሆን አለበት። ዘብርሃነ ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ እኮ የዘመን አውራ ነበሩ ብልህነታቸው ... 

ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም።
ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥
በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

የኔዎቹ የነፍስ ጉዳይ ስለሆነ የቻላችሁ ሸር አድርጉልኝ።
ውዶቼ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ሰንበት።

Ethiopia: በአሸንዳ በአል ላይ የተገኙት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ እና ተወዳጇ ፍርያት



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።