ከሩቅ ይጠራኛል / ግጥም
ከሩቅ ይጠራኛል።
„በውኑ ጥብብ አትጮኽምን?“
ምሳሌ ምዕራፍ ፰ ቁጥር፩
ከሥርጉተ ሥላሴ
02.09.2018
ከገዳማዊቷ ሲወዚዬ።
መምረር ይመረኛል፤ ልዋጥህም ብለው እንብዬው ይለኛል።
ጎምዝዞ ይዞኛል፤ ልፈትነው ስልም አይሆንም ይለኛል።
ደማኖም ታጥቆኛል፤ ልቀቀኝም ስለው ልሽሽ - ልሰልቅሽ እንዲህም ይለኛል።
ይለኛል ይለኛል፤ መንሹን አስልፎ ክንደኛ ብሎኛል።
ተረከዝ ተጎርዶ ራመድ ክዶኛል፤
መክዳቱ ክዳቱ ክዳኑ ጥፎኛል።
በትርፈኛ ዘይቤ ዜማ ቀንጥቦኛል፤
ፈር ተገብ ስለሆንኩ ዓይነት ቀንድቦኛል።
ይሆናል አይሆንም „አይም“ ያምርብኛል
„እሺ“ ቢቀርበት እንቆቆ ልኮኛል።
ለእሷ ከሆነማ፤ ንጋትና ዕውነት ከሩቅ ይጠረኛል
ለሚዛንም ቀኑ ናፍቆቱ ይዞኛል፤
ሸው እንዲያው ሽው እሱን ያሰኘኛል
የእኩልነት ማዶት ሁሌም ይርበኛል።
ተጣፈ አሁን 19.58።
ስለምን ተጣፈ? ስለግራሞት ብቻ …
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ