ነፍስ ይማር። አሜን!

ነፍስ ይማር።
አሜን!
„ከምድር ስተገኘህ ወደ መጣህበት መሬት እስከትመለስ ድረስ
 … እንጀራህን በፊትህ ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ ዐፈር ትመለሳለህ“

ዘፍጥረት ፫ ቁጥር ፱
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
19.12.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

                                                        

          
ዛሬ ኢትዮጵያ ብሄራዊ የሃዘን ቀን ነው። ይህ ብሄራዊ የሀዘን ቀን የታወጀበት ምክንያት ደግሞ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በስጋ ከእናት ምድራቸው በመለየታቸው ምክንያት ነው።

ሟቹ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህድ ቤተክርስትያን ወደ አንድ መምጣቷ ከስደሰታቸው የኢትዮጵውያ የፖለቲካ ሊሂቃን አንዱ ናቸው።

እርቁን በንጹህ ህሊናቸው፤ በንዑድ መንፈስ ተቀብለውታል። ብጹዕን ቅዱስ ሊቀና ጳጳሳትን ጨምሮ 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትርያርክን ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቀሪዮስንም ከቦታው ድርስ ተገኝተው ጠይቀዋል። እንኳን ደህና መጣችሁም በለዋል።

የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን የአቡነ መርቀሪዮስ ባዕለ ስመትም በብሄራዊ ደረጃ መከበር እንዳለበት ቃለ ምህዳን ሰጥተዋል። በባዕሉ ላይም በአካል ተገኝተዋል። 
  
ብጹዐኑ ሊቀ ቤተክርስትያናት ከስደት ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በሚመለከት ከቀደሙት የኢትዮጵያ ፖለቲካ መሪዎች በፍጹም በተለዬ ሁኔታ ብሥራተ ዜናውን በዬምሥራች መቀበላቸው ይህን እንዲያሳቸው እግዚአብሄር ዕድሉን መሰጠቱ ቅንነታቸውን ያሳያል።

በሌላ በኩል በኢትዮ ኤርትራ ጉዳይም ሰላም ሰፍኖ ለማዬት ጉጉትም፤ የተለዬ ናፍቆት እንደ ነበራቸው የተለያዩ ዜናዎችን ስከታትል ኖሬያለሁኝ። ይህንም ያዩ ዘንድ ፈጣሪ ፈቅዶ እንሆ የኢትዮ ኤርትራ ሰላምም በጥሩ ሁኔታ መገኘቱን ማዬት ችለዋል። ሁለቱንም የተመኙትን መልካም እና ደግ ነገሮች ልዑል እግዚአብሄር እንዲዩ ካደረገ በኋዋላ ወደ ራሱ መንግሥት ጠርቷቸዋል።

ለሃይማኖታቸው የነበራቸው ቀናይነት እና ለሰላም የነበራቸው ናፍቆት ጉልህ መሆኑን ባለፉት 7 ወራት ባሳዩት ቅንነት ማዬት ችያለሁን እኔ በግሌ።

ስለሆነም የቀንበጥ ብሎግ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እዬተመኘ ነፍሳቸውን በጽረ አርያም ልዑል እግዚአብሄር ያስቀመጥ ዘንድ ፈጣሪውን ይለምናል።



                                  ነፍስ ይማር! አሜን!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።