መነቀስ>>>>>> እኛበእኛ።

እንኳን ደህና መጡልኝ።
„ተነሡ፤
መልዕከተኛ ወደ አህዛብ ተልኮ፣
--- ተነሡ፤
በላይዋ በሰልፍ እንነሣ ብሎአል።“
ትንቢተ አብድዩ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፩
መነቀስ>>>>>>   
እኛበእኛ።
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
 06.04.2019
 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።


እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ? መነቀስ ዘመኑን የሚገልጠው ይመስለኛል። 
ዛሬ የረባ ነገር ሳልሰራ ነው የዋልኩት። ዝም ብዬ ስለመነቀስ እኛበእኛ ሳስበው፤ ሳስበው አልገፋ ሲለኝ ነው ወደ ብራናዬ መጣሁት።

ዝም ብዬ ሳስበው ይህ ከጣና ኬኛ ጀምሮ ያለውን ሁነት ፊልም ልስራው ቢባል
 ምን እና ምን ሊሆን እንደሚችልጭብጡ ታሬና ቁንጮ ቁጭ አድርጌ አወያዬሁት። 
እሱ ጥሩ አድማጭ እኔ ደግሞ ተናጋሪ ሆኜ፤  … የዛሬን አያድርገው እንጂ የወጣልኝ ተናጋሪ ነበርኩኝ … ጥሩ አድምጭም ...

የሁሉም ወረርሽ እንዲህ ሊሆን ሁሉም ሊደርሰው ማለቴ ነው ዛሬ ላይ እኔ ሰለባው ነበርኩኝ የመነቀስ … አሳዛኙ ቀጣይነቱ ቢሆን ዛሬ የእኔ የኖርኩበትን ሰቀቀን የሚጋሩ የእውነት አርበኞች የግንባር ሥጋዎች በርከት ብለዋል መታዬታቸው ነው፤ ቀደም ባለው ጊዜ ነጠል ብለው ቢወጡም ሸፋኝ፤ ጋራጅ፤ አለን የሚሉት ጥግ ነበራቸው፤ ዛሬ ግን ያው የእኔ ቢጤ ነው የሆኑት ...ብዬ አስባለሁኝ … ዘመድ ተገኜ እንደማለት ... 

·       እምታን በነፍሰጡር እይታ …

ያጠፋነውን ጊዜ፤ ያበከነውን መንፈስ፤ ሳይባክን የተተረፈረፈበት ሁኔታ፤ ሳይንቦጀቦጅ የተገኘውን የመንፈስ ጥሪት ሚዛናዊ አድርጎ በማቅረብ እና ባለማቅረብ የገጠመን ትልቁ ጋሬጣ ምንድን ነው ይሆን ብዬ አሰብኩት፤ ዘመኑን ሳሳበው ሳወጣ እና ሳወርደው ... መጪው ጊዜ እኔ ከብዶኛል ... 

አሳለሁት፤ አነጋገርኩት፤ አወያዬሁት። ያው እኔ የፌስ ቡክ ታዳሚ ባለመሆኔ በሚያቆስሉ ነገሮች ብዙም አልጎዳም። ቁጥብነቴ ረድቶኛል። ነገረ ፌስ ቡክን የጣመ ነገር ሲገጥመው ሳተናው በብራናው ጋዜጠኛ ሄኖክ አለማዬሁ በልሳኑ ከሚቀርቡት፤ አልፎ አልፎ ቤተሰቦቼ ከሚነግሩኝ ከምቃመሰው ውጪ አልሰማም። አላይም።

ይልቅ ከጥገናዊ ለውጡ መንፈስ ወዲህ የኢትዮጵያን የመንግሥት ሚዲያ ወግ ደርሶት በመደበኛ ከመጋቢት 24/2010 ቀን ጀምሮ እከታተላለሁኝ። የውጮችን እንዲሁ እከታተላለሁኝ ለመንፈሴ ቅርብ የሆነውን ለይቼ። አብሶ ሙግት ያለበትን ነው እኔ እምወደው። ወጥ ሃሳብ አልወድም።

አሁን አገር ቤት ወያኔ አገር መግዛት ሲጀመር በነበረው መልክ የግል ሚዲያዎች ፈክተዋል ይዘልቃል ብየ ግን አላስብም። አሁን ሞገደኛውን ኢሳት እራሱ አደጋ ውስጥ እንዳለ ይሰማኛል። ምርጫ ከመምጣቱ በፊት አቅሙን የሚፈታተኑ ነገሮች ብቅ እያሉበት ነው። አብሶ የዲሲው ጠንካራ እና ጉልበታም፤ ለመሞገትም የሚመች ነበር። አሁን ላይ መነቀስ እኛበእኛ እዬገጠመው ነው። 

በጥንካሬ እና በፅናት ይህን የፈተና ጊዜ ለመወጣት የተቀማው ነገር እንዳለ ግን ይሰማኛል። ከመጋቢት እስከ ሀምሌ መግቢያ በነበረው ጊዜ የተሰባሰበው መንፈስም በለመደበት ሁኔታ እዬተበተነ ነው። ድግምቱም አዚሙም ስለምንመቸው አይለቀንም። መሪዎችም አይማሩም አፍሰው መልቀም ለምዶባቸዋል።

አሁን ሌላ አዲስ ጥረት ጀመረዋል። ሲላቸው በብስጭት፤ ሲላቸው በመፈረጅ፤ ሲላቸው በማነቁኖቅ፤ ሲላቸው በማስፈራራት፤ ሲላቸው ለክስ በመሰናዳት፤ ሲላቸው በጅምላ በመዛት፤ ሲላቸው ጡንቻቸውን በመጎነጥ፤ ሲላቸው ደግሞ አውራ ደጋፊ አላቸው የተባሉትን ተጽኦኖ ፈጣሪዎችን ተርትር እንደ ዳንቴል በማድረግ …  ተክለ ሰውነት እርቃን ለማስቀረት ምህንድስናው ጦፏል … ግን እኛ ምን ነን?

አይዋ ዕውነትም እንደለመደበት በግራ ቀኝ ወጀብ እዬተላጋ ነው። ውጭ አገር ባሉት ጋዜጠኞች ብዙም ችግር አይኖርም። ቢያንስ ጥንቃቄ ካላቸው የመኖር ዋስትናቸው አይታወክም፤ ከምግብ ብክለትም ከምንትሶ ተጠንቅቀው በቁጥብ መስመር ለመኖር ከፈቀዱ፤ አገር ቤት ባሉት ግን ይከብዳል። የተቀማነው ረቂቅ ነገር አለና።

ረቂቅ ነገር ፈውስ ነበር። የትም እንሁን የትም ሙቀት ነበረው። ረቂቅ ነገር በረከት ነበር፤ ረቂቅ ነገር ረድኤት ነበር፤ ረቂቅ ነገር የነገ ማገርና ዋልታ ነበር። ረቂቅ ነገር እኛው ውስጥ ሳናውቀው፤ ሳናፈቅድልትም አንድ መንፈስ ፈጥሮ አንድ የማይበጠስ ውል አበጅቶ ያሰተሳሰረን ነበር። 

አሁን ተቦድሷል። እግዜር ይይለት  ለአይዋ መንትሶ …  ይሄ ነው ዛሬን በሃዘን ዝም አሰኝቶ ያስቀመጠኝ። ጨንቆኛል። የእውነት ጨንቆኛል። የተቀማነው በሀብትም፤ 
በመኖርም፤ በፍትጊያው ልክ የምንመጥነው አይደለም። 

በምንም መስፈርት እና በምንም ሁኔታ ትክ ልናቀርብለት፤ ልንዋሰው ለአፍታ የማንችል ነገር ግን አንድ ላይ አምጥቶን ሳናበው ሳናልመው ስሜታችን የሚገዛ ነገር ውህደት ላይ የነበርን ይስለኛል። ብቻ ህልም ህልም የሚመስል ነገር ነበር።

እህቶቻችን አረብ አገር ላይ ጥቃት ሲፈጸም እኔ ከዛም በፊት ከዛም በኋዋላ ሲዊዘርላንድ እንደዛ አይነት የቁጣ ሰለፍ አይቼ አላውቅም። የሰው ዓይነት ነው የነበረው። እልኹ ቁጭቱ በመጣው ሰው ልክ በቁጥሩ ሳይሆን በእያንዳንዱ ሳታፊ የጸጉሩ ልክ ነበር ማለት ይቻለኛል። ቤቱ የቀረ የማርያም ጠላት ዓይነት ነበር።

ያን አሁን በስል እዬተቀማን፤ የተዘረፍን፤ መንፈሳችን የተወረረ … ከዛ ርሰተ ጉልት እዬተነቀል ነው ያለነው። ክፉ መንፈስ ገብቶብናል። የፈለገ ብንሟገት፤ የፈለገ 
ብንጠዛጠዝ እንዲህ በመንፈስ ግን ተነጣጥለን ቆመን አይቼ አላውቅም ነበር። ፈተና ላይ ነን። ፈተናውን የሚያከብደው የችግሩን ሥር ለማወቅ አቅም ስላነሰን ነው። 

አንዱ በሌለበት ስሌላው የሚቆረቆርበት ቢያንስ  እዬሞገትነው ግን ስለ ህይወቱ የምንጨነቅበት መልካም ጊዜ እንሆ እያመለጠን ነው ከዛ ውስጣዊ ኣኃታዊ 
መንፈስ መራራ ስንብት እንደ ቅንጅት ዘመን እያደረግን ነው ያለነው

ሁሉንም ቅኝት እዩት … ውዶቼ …  ሁሉንም አቅጣጫ ተመልከተቱ ውዶቼ። አንድ 
ሰው አንድ መስታውት ላይ አነጣጥሮ ቀስት ቢልክ፤ ጦሩ በስቶ ሲያልፍ ቀሪው እንዴት እንደሚሰነጣጠቅ እሰቡት እንደዛ ነው አሁን የሆነው … እንደ ጨው ዘር መንፈሳችን 
ብትን ነው ያለው …

በዚህ ማህል ኢትዮጵያን ሊያጠቃ የውጭ አገር ጠላት ቢነሳ ብላችሁ እሰቡት? እሰቡትአንችላለን አገር ለማዳን? አቅም አለን? ለመሆኑ እያንዳንዳችን ከህሊናችን ጋር ነን? ለመሆኑ እያንዳንዳችን ከተሰጠን የመንፈስ ጸጋ ጋር ነን? ለመሆኑ እያንዳንዳችን በተክለ ሰውነታችን ልክ ነን? ለመሆኑ ሁለመናችን የት ላይ ነው ያለው?

ማነው በርባሪያችን? ማነው ጎርጓሪያችን? ማነው ሰርሳሪያችን? እኔ 666 የተቆጣጠረው ይመስላል ያን የወል ሐሤታዊ ጅምር። የሰለበን ይመሰለኛል። እንደ ሆነ ነገር አንዳች ምናምንቴ እዬነዳን ያለ ይመስለኛል … 

ምነው ሐሤታችን እንዲህ ብን አለ ሳይበረክት ገና በማለዳው? ምን መጣብን? ምን ተጫነን? ለዛውም አሁን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብይ ጾም ላይ ነን?

ለመሆኑ መቀማታችን አውቀነዋልን? ለመሆኑ እኛበእኛስ መነቃቀሳችንስ ትዝ ብሎናል? ማነው ገዢያችን ህሊናች ወይንስ ሌላ መንፈስ? በቃ ሁለመናው እኮ ቤርሙዳ ትርያንግል ዓይነት እዬሆነ ነው

በመፈረስ ያለ ነፍስ፤ በመፍረስ ላይ ያለ መኖር፤ በመፍረስ ላይ ያለ ማግስት …. በመፍረስ ላይ ያለ ዛሬ፤ በመፍረስ ላይ ያለ ተስፋ በመፍረስ ላይ ያለች አገር ….
ምን እንሁን ምንስ እናደርግ ምንስ አምጠን እንውለድ …. ? ! ? ?
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>> ያደክማል፤

ብቻቸውን ቆመው የሚታዩ የዕውነት ባለሟሎች እዛው ባዕት ላይ አሉን፤ „ላይክስ አይበድል“ ጎንደሬዎች እንደሚሉት…  

መራራውን ጉዞ እንደለመደባቸው ተያይዘውታል ግማዱን አሸንፈው እንዳይወጡም 
የታቆረ ነገር አለ አንዳች የራስጠረን የሆነ ግን የጉሮሮ አጥንት … 
            ግን ምንሆነናል                ?
              እኔ ምን ሆኛለሁኝ?
እርስዎስ ምን ሆነዋል                  ?
                    ሁላችንስ ምን እዬሆን ነው?

እንደገና አሁንም እንደገና እንደገና  … ማን ይማለደን እጬጌው ሂደት ….፧

ስለዚህም የቀደሙ ማዕከላዊ ጹሑፎቼን በድጋሚ አቅርቤያለሁ ከጠቀመ በምልሰት ገምግሙኝ እስኪከዚህ በላይ ዛሬ ለመጻፍ አቅም አጣሁኝ።

አብሶ የጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እና የለመደባቸው የነቃሽ የአቶ ስዩም ተሾመ ዒላማ ግብ አስቤ ምነው ሲሳዩ አንተ የማክበርህ ባትሆንብኝ አልኩኝ። ይህ ቃል የአንተ ባይሆን አልኩኝ።  

መጻፍ አልችል አልኩኝ? ምን ብዬ ልጻፈው? ለዚህ ነው ጥርቅም ያለ ጹሑፍ ለመጻፍ የተገደድኩት። ራሱ ኢንተርኔቴ አልተከፈተም ዛሬ

የሆነ አንዳች ነገር ተጫጫነኝ …  ጠቀራ የሆነ ደመመን ነገር።
ለነገሩ፤ …  እራሱ ልዑል ተስፋም ደመመን ተጫጭኖታል …      .
የፈሩት ይወርሳል የሆነ ይመሰለኛል ... 

ነገ ካገኘሁት አዲስ አበባ እያለሁኝ ሥነ - ጹሑፍ ኮርስ ላይ ጉዑዝ ያናገርኩበት
ጹሑፍ ነበር ስለ አራት እግር ጉዳይ …  እስኪ ፈልጌ እሱንም የጭንቅ ጊዜ 
ለማኝንም እለጠፈዋለሁኝ፤ ....

የመጻፍ አቅሜ ራሱ ፈተናው ውስጥ ነው፤ ያው ብዕሬ እውነትን ፈልጋ እየባከነች ነውባትላለችየራሷ ላይበቃት እኔንም አላስቀምጥ አላስቆም አለችኝ … 

እና /// እናም ክብረቶቼ እኛም እንዳንጠፋፋ አንድ በሉን? ልመና ቢጤ አቤቱታ ቢጤ አቀርብኩኝ … ለቅኖቹ ብቻ … 

·       ቀደምቶቹ እንዲህ ይላሉ …

እጬጌው ሂደት። 08.04.2018

ይህቺ ናት ኢትዮጵያ - ከፈለግናት።  19.04.2018

አይ No“ ልዩ አቅም ነው። 04.03.2018 

አፍንጫህን ላስአቶ ሂደት። March 21, 2014

የለውጥ ሃሳብ።  13.03.2018


ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን 
አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው              !

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።