ሽሽትና መሸትሸት። በመከሰም ላይ ስላለው ዛሬ።

እንኳን ደህና መጡልኝ
    ሽሽትና 
 መሸትሸት።
„አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል?
በተቀደሰው ተራራህ ማን ይኖራል?“
መዝሙር ፲፬ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።

ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? አራት ዓመት ሙሉ ሞትን  በዕለታዊነት ስትመገብ የባጀችው አላዛሯ ኢትዮጵያ በኬክ እና በድግስ፤ በፈረሰኛ ጉግስ እና በዲስኩር ዳንኪራ ስትሽሞነሞን ሰነበተች። እንግዲህ ይህን ስል 23 ዐመቱን የት ጥለሽው አትበሉኝ … ያ ይቀመጥ ከቅርቡ ብንነሳ እንኳን ለማለት ነው …

አያድርግብኝ እንጂ እኔ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ብሆን ኖሮ የለውጥ ዓመት የማክበርበት ጊዜ አሁን ባልነበረ፤ ከሽሽት ላይ ተሁኖ፤ መሸትሽት ካለው ድንግዝ ተሁኖ አውደ ዓምት የለምና። በቂ እኮ ነበር ወደ ንግሥና ሲመጡ የሆነው ሥርዓት …

ባለፈው አንድ ዓመት በሀገሪቱ ውስጥ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ የተሰሩ ስራዎችና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ ያተኮረ መድረክ OBN መጋቢት 132011

https://www.youtube.com/watch?v=Wn3YcmL8FGk

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ አንደኛ ዓመት የመዘከሪያ ፕሮግራም ላይ የደረጉት ንግግር

Published on Apr 2, 2019

https://www.youtube.com/watch?v=lTSFGQMVWfk

#etv ህፃን ያኔት በሚሊንየም አዳራሽ

Published on Apr 2, 2019

https://www.youtube.com/watch?v=UOwF2Y5cK6k

#etv 29ኛው የኦዲፒ ምስረታ ማጠቃለያ ዝግጅት ተከናወነ፡፡

Published on Apr 6, 2019

Best information addis ababa - ODP ዛሬም ልደቱን አክብሮ ካልጨረሰ ተአምር ነው አቤ ተኩቻው ዋዛና ቁምነገር

Published on Apr 6, 2019

·       ማጣጠሚያ በእንቆቆ።

 

ከላይ የተቀመጡት መቀናጫዎች እነዚህ ሊንኮች ከዚህ ጋር ነው መጣጠም ያለባቸው ለማን ፈንጠዝያ የማን የሞት ድግስ ስለመሆኑ ህሊና ይፈተልበታል ወይንም ይጋመድበታልወይንም ይጋደምበታል … መደቡ ተተገኜ ነው ታዲያ

 

https://www.youtube.com/watch?v=r0DdB3qc7jw

Ethiopia: ሰበር ዜና - / አምባቸው መኮንን በከሚሴና ሰሜን ሸዋ ጉዳይ ተናገሩ

Published on Apr 7, 2019


·       ሞትና ኬክ!

 

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ስልጣን ከያዙ ጀምሮ ድግስ ነው በዲታዋ አገር  በኢትዮጵያ። ሙስናን አብዝቶ ለተጠዬፈ ነፍስ የድግስ ሙስና ተገልበጦ በለኝ እያለ ነው። ዓመቱን ሙሉ ድግስ አይሰለችም? አይገለማም? ቋቅ እያለኝ ነው።

ሞት ላይ ያለ መንግሥት አንድ ጊዜ የዲስኩር፤ ሌላ ጊዜ የፎቶ ግራፍ ሌላ ጊዜ የሚዲያ ዲስኮ ከማካሄድ ታቅቦ በመፍረስ ላይ ያለውን መኖር ጥቁር ለብሶ ትቢያ ተንተርሶ አመዷን ነስንሶ እግዚኦ ማረኝ የሚልበት ወቅት ነበር እንደ ልደታ ማርያሙ እዮር ቁጣ ምልክት … ማ  … ቢሆን ኖሮ …

የOMN እና የአቶ በቀለ ገርባ ኢትዮጵያን ለማፈረስ አዲስ የባቢሎን ግንብ ትልም ህጋዊ አውቅና አግኝቶ ይለፍ ከማስጠት በህግ ጠይቆ ፍርድ ቤት መገተር ነበር ነፍስ ያለው መንግሥት ኢትዮጵያ ቢኖር። ይህ ተረግጦ ነው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ርዋናዳ ላይ ዕንባ ለማዋጣት የተጓዙት … „የራሷ ሲያርባት የሰው …“

#etv 

Published on Apr 7, 2019

 

የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ችግሮችን ከኃይል ይልቅ በውይይት መፍታት 

እንደሚገባ ማሳያ መሆኑን / / ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡

 

ለመሆኑ የጌዲኦን ዕንባ? የቡራዩን ጎለጎታ፤ የሻሸመኔውን ቀራንዮ አዝለው? አሽኮኮ አድርገው እንዴት እና አንዴት ሆኖ ይሆን ህሊናቸው ለዚህ ቀን የታደመው?


ማህል አገር ቤት በማፍረስ፤ አዲስ ላይ ዘመናዊ የሆነ የዲስክርምኔሽን የብወዛ ምህንድስና በመቀመር፤ ዳር አገር በአጥፍተህ ጥፋት የተደራጀ የተቀነባበረ ተግባር ሲከውን የኢትዮጵያ መንግሥት ጁቢተር ላይ ፎቁን ሠርቶ ተደላድሎ ኬክ ያዛል። 

ከመሰከረም ጀምሮ መንፈሱ እርጋታ አጥቶ ፍዳውን በሚከፈለው የመዲናዋ የስቅለት መባጀት ላይ ሆኖ የሩዋንዳን  ነገር ለመታደም መታሰቡ ራሱ ማህጸንን ይቀዳል … ምክንያቱም ደጅ ላይ ያለ ዶፍ መከራ አለና …

መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (/)
·               የመከራ መባቻ።

የሰሞናቱ አገር አይብቃኝ የተደራራቢ ድል አከባባር ማለት የ ኦህዴድ የምስረታ ባዕል፤ የ ኦህዴድ የቤተመንግሥት ቅብዕ እና የከምሴ እና የሽዋ መናጥ  የኦነግ ታጣቂ ከጉለሌለው ኮማንድ ፖስት ተነጥያለሁ ማለቱ እና የጠ/ሚር አብይ አህመድ የርዋንዳ ቀዳሚ አስተዛዛኝነት ጉዞ የኢትዮጵያ ችግር…

የብሄር ንድፈ ሃሳብ ችግር ስለመሆኑ የተሰጠው መግለጫ ሲደምር ሲካተት በአንድም በሌላም ሊበቀሉት የፈለጉት ወገን በመበቀል ከሃላፊነት ሽሽት ላይ ያለ ራስን የጣሰ የታማኝነት ሽሽት መሸትሸት አዲስ ኪኖ ነው ለእኔ የሚገባኝ።

ሰሞኑን ብአዴን ላይ የለውጥ ዓይነታ ተቋዳሽ እንደሆነ ሁሉ አንድ የኬክ ቆረሳ ድርሻ ደርሶት ኩፈሳ ቢጤ ነበር … የተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚዎችን አክሎ … ኦሮምያ ላይ ይህቺ ቀልድ አትሞከረም? 

ኦሮምያ ሪፕብሊክ ምስረታን ስንጥቅ ስለምትፈጠር … ደቡብ ላይ ደግሞ ቀደም ሲል አቶ ሌንጮ ለታ ሲዳማን ነጠል አድርገው በኩሸኝ ቱማታ ተቃኝተውበታል። አሁን ፕ/ መራራ ጉዲና ደበብ ላይ በምንኛ ይሆን እንደለሆን አላውቅም ተሰይመው አይቻለሁኝ … መቱ ላይ ደግሞ ዶር/ ዲማ ነግዎ ከሁለቱ ጠ/ሚርት ጋር እድምታ አድርገዋል። ሠርጋና መልስ በዓይነት ዕንባ ደግሞ በቡፌ… እኛ እንዲህ ነን። ፍኖተ ካርታው ይኸው ነው ... 

/ ዶክተር አብይ አህመድ ከመቱ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል

Published on Apr 4, 2019

ሰበር ዜና - የኦነግ ጦር ከግንባሩ ተነጠለ | Ethiopia

Published on Apr 6, 2019

https://www.youtube.com/watch?v=3JKHRSFx180&t=2s

/ መራራ ጉዲና በጥያቄ ያፋተጧቸው የደቡብ ወጣቶች እናተ እራሱ የዘር ፖለቲካ እያራመደቹ ነው

Published on Apr 5, 2019


·       ማያያዣ መላሾ።


በለውጡ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ኢትዮጵያዊ ቅርፅ እንዲኖራቸው ተደርጓል- መንግስት

Published on Apr 5, 2019

ይህ መላሾ ደግሞ የአንድነት ሃይል ነን ለሚሉት ለገቡላቸው ቃል ቃልአባይነታቸውን የሚሸፍን የጋሬጣ ግላጭ መንገድ ነው። ጋሬጣ ያልኩት መንፈሱን አይደለም። እነሱ ዲል ባለ የዞግኛ ልዕልና 29ኛ ዓመታቸውን አገር ምድሩ አይብቃን እያሉ በኬክ በሰገር በቅሎ በፌስታ በግጥም ታንጎውን እያስነኩት፤

ኢትዮጵያዊነትን ተሸከም የተባለው አማራ ላይ አሸልበኝን ኦርኬስተር ከፍተው እነሱ ግን የዞግ አቦላቸውን እያስኬዱት ስለመሆኑ „ልብ ያለው ሸብ“ እንላልን እንደ ልባሞቹ ጎንደሬዎች።

መቱ ላይ ዶር ዲማ ነግዖ ይዞ ከመሄድ ፕ/ ብርሃኑ ነጋን አጋራቸውን፤ ውስጣቸውን ህሊናቸውን፤ ልባቸውን የገጠሙላቸውን ባለውለታቸውን ይዘው ቢሄዱ ይመከር ነበር።
የአማራን ብሄርተኝነት ለመሰበር ቀኝ ክንዳቸው ስለሆኑ ወይንም „የፌኳ“ አብረነን እንዘጭን ትንሽ ቀባ ቀባ ለማድረግ  … ቢሞክሩ ባያምርባቸውም አያሳጣም ነበር። እራሳቸውን እያጠናከሩ ሌላውን ስለመናድ ተግባራቸው እንዲህ በግለጫ አና አይልም ነበር። የዜግነት ፖለቲካ አድብ ገዝቶ ኦሮምያ ምድር አይፈለገም ስብከትም፤ 
ዲስኩርም አይደረግበትም።   

ለነገሩ አሁን ደግሞ አዲሱን የዘፍጥረትን ድርመስት ለማስተባበል በቄዋም አዲስ ዜማ ይዘው ብቅ እንዲሉ ተደርጓል። ጨዋታው የሥነ - ልቦና ነው። እንዲህ ዓይነት ውሎጉዞ የሌለው መንገድ ኢትዮጵያ በታሪኳ ገጥሟት አያውቅም። ኢትዮጵያ ቃሬዛ ላይ ናት።  ለእኔ ሁለመናው ያስፈራኛል። 

Ethiopia: “ኢትዮጵያዊነቴን ከኦሮሞነቴ ልነጥለው አልችልም!!” አቶ በቀለ ገርባ ጋር የተደረገ ልዩ ቃለ ምልልስ
Published on Apr 7, 2019

ማላጋጥ ማፈራገጥ ስለእውነት። ውሸት ነው ስለሚሉት ነገር ይህ አላዬሁም አለሰማነም መቼም አይሉም።

የሆነ ሆኖ እኛ የለንበትም ስለሚሉት ጉዳይ እራሳቸው ደግሞ እንዲህ ይገልጡታል።

Ethiopia: ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማሳካት ቀን ከሌት እየሰሩ መሆኑን አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ በአንደበታቸው አረጋግጠዋል፡፡


Published on Mar 9, 2019

/ ታከለ ኡማ ስለዴሞግራፊ ከመታወቂያና ሌሎች ጉዳዮች መልስ ሰጡ | Takele Uma Give an answer to Eskender Nega

Published on Apr 6, 2019


መታበይ፤ ውሸት፤ ራስን አስከብዶ ማቅረብ ምን የቀረ ሙርቅርቅ ነገር አለና …? ... ትዝ ይላችሁ ይሆን የመሰከረም 5ቱ የ ኦነግ የመስቀል አደባባይ አቀባበል አቶ በቀለ ገርባአዬር ላይ ነበር የሚራመዱት ... ቄንጠኛው አዬርም ከመጣህልኝ ብሎ ሰፈፍ ሰፈፍ አደረጋቸው ...ምድርን ግን አረገረገች...  

ወደ ቀደመው ምልስት ሲደረግ …  የባዕሉ አከበባርም ዲል ብሎ ሲከበር አዬን … የ ኦህዴድ ምሰረታ የሚኒሊክ ቤተመንግሥት አልጋ ውርስነት ... አዲስ አበባ ላይ … ጥንድ ተግባርን አራውጦ እዬከወኑ፤ ሌላውን ሰላሙን በማወክ መቅኖ በመሳጣት ተጠምዶ ኢትዮጵያዊነት በማስፈራራት ላይ ተግቶ እዬሰሩ … ምን አለ ፈጣሪ ቢፈራ እንላለን … ልጅ ስለማያወጣ … እንደወጡም ስለሚያስቀር …

·       „የአክ ወሬ“ ትጥቅ አስፈቺነት።

ያ ጥቁሩ „የአክ ወሬ“ ጥላሽት ጊዜውን እዬጠበቀ እንዲህ እያዋዛ የዕንባ ጽዋችን እድናነሳ ስለመዳረጉ ከጹሑፌ ጋር የባጁ ቅን ወገኖቼ ያውቁታል። አንድ ቀውስ ሲነሳ፤ አንድ ቀውስ ሊመጣ ሲል ዋዜማ ላይ ሲሆን ጠ/ሚር አብይ አህመድ አይኖሩም አገር ውስጥ።

ወይ ቀድሞ ወይ ቀጥሎ ደግሞ እሳት ይነሳል … ይህን በተደጋጋሚ ጽፌያለሁኝ። ስለምን? ወንበሩ ባዶ ስለሆነ። እሳቸው ሥልጣን ከመያዛቸው ጀምሮ ምልክቶች እዮራዊ ነበሩ … እሳት ያልነካው መቀሌ ብቻ ነው … የመሬት መናጥ ግን ገጥሞታል … 

አሁን እኔ ያሳዝኑኛል አቤቱታ የሚያቀርቡ ሰዎች፤ እኔ መጀመሪያ ላይ እንደተጃጃልኩት ማለት ነው። የመፍትሄ ጉዳይ የሚያነሱ ሰዎችም ያንኑ መንፈስ አምነው ሲሆን ደግሞ ያሳዝኑኛል። ወንበሩ መቼ አለ እና ቀድሞ ነገር።

አሁን የኢትዮጵያ የደህንነት ችግር መግለጫ እና የጉለሌለው መንግሥት ኮማንድ ፖስት ከሠራዊቱ መነጠሉ እኮ ሌላ ምንም ነገር የለውም። አቶ ዳውድ ኢብሳን ተጠያቂ ላለማድረግ፤ ኦዴፓን ተጠያቂ ላለማድረግ እርምጃ አልወሰደም እንዳይባል ለማድረግ የሚደረግ ጥረት ነው። 

ምክንያቱሙም አራጊ ፈጣሪዎቹ እነሱው ናቸው እሱበእሱ። ድሬድዋ ላይም መሰሉ ይከሰት እና ጂጂጋ ደግሞ ትናጣላች ጠበቁት … በዚህ ውስጥ የአቶ ንጉሡ ጥላሁንን መንፈስም ቀርብ አድርጋችሁ መርምሩት … ስለምን እሳቸው ወደ ጠ/ሚር ቢሮ እንዲገቡ እንደተፈለገ …

·       ት ላይ ያለችው ኢትዮጵያ ናት፤ የተጎዳቸውም እሷ።

የስሜን ፖለቲካ ለመናድ ከሥር ነው የተጀመረው የለማ ምህንድስና ክህሎት። ፍልስፍናው ይኸው ነው። ሞት ላይ ያለችው ኢትዮጵያ ናት። እኔ እንዲያውም ከዚህ ቀደምም አንስቼዋለሁኝ የተባበሩት መንግሥስታት ጽ/ቤት የሰላም አስከባሪ ሃይል ቀድሞ ካልገባ ማን እና ምን እንደሚሆን ስለማይታወቅ እልቂቱ የከፋ ነው የሚሆነው …

ሌላው የማይገባኝ አሁን ከኦዴፓ ችግሩን አሻግሮ ወደ ህወሃት ለመውሰድ የሚደረገው ጥረት ነው … የአዲሱ የኦሮማማ ልማታዊ ካድሬ የአቶ ስዩም ተሾመ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር የነበረው ቃለ ምልልስ ጭብጡ ያ ነበር። ፊት ለፊት የተቀመጠ ቋያ እያለ።\/ የጥያቄው ጭብጥ ህወሃት ተኮር ነበር … አቅጣጫ ለማስቀዬስ። አውራው ችግር ያለው ኦዴፓ ውስጥ ነው። ወይ አልተገለጠ ወይ አልተገለበጠ ድንብልብ።

ለቀደመው ቢሆን ህወሃት፤ ሻብያ ኦነግ ናቸው ሃዲዱን አቶ ተስፋዬ ሳጥናኤል ጋር አብረው ተባብረው ሰሩት፤ ያ የተቀበረ ቦንብ አሁን ደግሞ ለባለተራው አስርክቦ ሥልጣኑን የተረከበው ሃይል የቀደመ ትልሙን እዬፈጸመ ነው … ምን ኦነጋዊ ያልሆነ መንፈስ አለና ቀድሞ ነገር  … አገሩ አልበቃቸው ብሎ እኮ መርቅነዋል። እንጃ           
ኡራኑስም ኬኛ            ! 
           ሜርዩኩሪ ኬኛ! 
                  ሳተርን ኬኛ … 
                   የኬኛ ማኛ 
አስተኛ               
የአስመተኛ           ሁነኛ 
የጉሮሮ አጥንት የመኖርኛ     
                 አብሮኛ መከረኛ
            መጋኛ        
አዬሩን ናጠው                
                       ሊውጠው
በግምኛ ልሲለጥቀው ..........።

በደርግ ጊዜ እንዳለም አይቆጠርም ነበር። ያው ፈንጂዋን እያጠመደ አርባጉጉ አካባቢ ትንሽ አለሁ ከማለት ውጪ። 

አሁን ህዝብ ባመጣው ለውጥ እሱ ባላባት ሆኖ ቁጭ አለ። ስለመፈጠሩም እኮ ዕድሜ ለግንቦት 7 ይበል። ላይ አውጥቶ አንጠለጠለው - ከፎሰው። 

ኦነግ በቀደመው ጊዜ ድርጅቱ አቅም ቢኖረው እኮ ከህወሃት ጋር ተፎካክሮ መጥኖ መጓዝ ይችል ነበር። አቅም የለውም፤ አቅም አልነበረውም። አሁንም የለውም። 

ይልቅ አሁን አቅም እንዲያገኝ ያደረገው ጥገናዊ ለውጡ ሞተር ከእጅ ስለገባ ነው። 
በእኛ የመንፈስ ሃብት እሱ ዙፋኑን ተረከበ … ለማወይአብይ ተብሎ ራስተሸጠ ተለወጠ እንዳወጣም ተቸበቸበ … በስል ተግበቶ መፈራሰስ ሆነተሆነ … እግዚኦታስ ተዚህ ላይ ነው። አሁን እሱን እንደግፍ ነው ጉንጭ አልፋው መወራጨት፤ መጥኒ እንላላን ለግንቦታውያኑ ... በዬዘመኑ በመዳጥ ላይ ያለ ማዳዳጥ ጤናቸው ስለሆነ ... 

ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ በዬትኛውም ሁኔታ ያሉ የኦሮሞ ሊሂቃንን ማሰባሰብ መደበኛ ተግባራቸው ነበር። ይህንን በተደጋጋሚ ጽፌዋለሁኝ። ፍላጎታቸውን ለማሳካት ጫና የሚፈጠር ሃይል በታቀደ ሁኔታ ለመፍጠር ታተሩ። አቅሙን በጥረታቸው ፈጠሩት። ያለው እውነት ይኽው ነው። ሊከሰስ፤ ሊወቀስም፤ ሊወነጀልም ከተገባ ይህ ምህንድስና ብቻ ነው እንጂ አሁን ላይ ወደ ህወሃት ማሳበብ የተገባ አደለም።

ሁሉንም የኦሮሞ ሚዲያዎች ብታዮዋቸው አንድ አፍታን ጨምሮ የሚያላክኩቱ ወደ ህወሃት ነው፤ እነሱ ድል በመዳፋችን በእጃችን ገባ ብለው ሀገሩን ባልስ እያስዳነሱ በሌላ በኩል ተጠያቂነት ሲመጣ ደግሞ የእኛ ወገን አይደለም ህወሃት የሸረበው ነው ይላሉ። ስለዚህ ህወሃት ይህን ያህል አቅም ከኖረው ሥልጣኑን ለሚችል ማስረክብ ነው በቃ። የልባችን የሚባሉት ሊሂቅም አብረው ናቸው።

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) 29 ዓመት የምስረታ በዓል ማጠቃለያ

Published on Apr 6, 2019

·       አቅም ማለት … በምን ይገለጥ?

አቅም በድግስ ብዛት? ቅቡልነት በዲስኩር ንረት? ተወዳጅነት በመፈናቀል በማፋናቅል? በስጋት የሚመሩትን ህዝብ በዘመቻ ያለረፍት በመናጥ ጅግንነት? ከቶ አቅም አለን የሚባለው ነገር በምን ይሰፈር? እንዴትስ ይዘርዘር? እንዴትስ ይለካ? ከቀዬው የተፈናቀለው ነፍስ ብቻ ሳይሆን ተስፋ ያደረገው ነፍስ ሁሉ ከባዕቱ ተፈናቅሏል። ፈልሷል። ህመም ሃዘን ዕንባ ስኬት? 

እኔ እማዬው መንጠባጠብ ነው የሚታዬው። ማቀናጀት፤ ማደራጀት፤ ማስተዳደር አልተቻለም፤ አሁን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን የደህነት ስጋት ስለገጠመን ነው የሚያወጣ ቅላጼ ምት ነበረውን?ስንት ነገር ይፈፈራ ስንት ነገር ይሸሽ? ስንት ቀዳዳስ ይጣፍ?

በጫና ብዛት የኦሮሞን ሪፕብሊክ ለመመሰረት የተያዘው ትልም በአንድም በሌላም ሲፈነዳዳ እንደ ወተቴ ነው አደባባይ ወጥተው ደግሞ የታቦት ይቀረጽልን ዜማ ነው ሲቃኙት የምናዳምጠው። 

እውነት ሲነገር ደግሞ እንከሳለን ማስፈራሪያ ነው የሚደመጠው …  ከምድር ተነስተው ጣሪያ ላይ የተንጠለጠሉት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሰሞኑን ያሰሙት የተንጠራራ ንግግር፤ መስዋዕት የከፈሉትን ጀግኖች አቃላይ ንግግር ወዳጃቸውን አቶ ጀዋር መሃመድን ማከሉን ባሊህ ሳይሉ ነበር …

መቼም ሰሞኑን ንዴት አድማጭ ሆነናል … ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ አልሰከርኩም፤ አላበድኩም ሲሉ ጦርነት እንገጥማለን ደግሞ ጠ/ሚሩ ነገርውናል … ሆድ መባስ ነውን? የተስፋ መራቆት ነውን? መባባት ነውን? ወፊቱ ትጠዬቅ … በሰጭኝ ሆነ የሦስቱ የሲኦል መንገዶች… ባንድ ... መንገዱ ኦሮሞንም አያድንም። 

የኦዴፓ የመስቀል አደባባይ የፈረስ ጉግስ ትርኢት አዬር ላይ የተንሳፋፈ መባቻ ይሁን መሰንበቻ? ማሳሳቻ ይሁን መመካቻ? ቅጥንብሩ የጠፋው ውሎ ጉዞ የሌለው፤ ማጣፊያ ያጠረው ዝክንትል ነው … ዲሪቶ ነገር ነው - ለእኔ።

ሥራ የሚሰራው እኮ መዳፍ እና ህሊና እንጂ እግር አይደለም፤ ይልቅ የጠ/ሚር ቢሮ አንድ የቱሪስት ጽ/ቤት ቢከፍት የሚሻል ይመስለኛል፤ የውነት ያተርፈዋል … እንደ ቱሪስት የሚያደርገው ውቃቤ - አውሌያ ይባል ቆሌ ይባል አድባሩ ቢሮውን ስለተጫጫነው፤ 

… መሄድ ነው መሄድ ነው መብረር ነው መብረር ነው እንደጊዜ አንድ በጀርመንኛ ግጥም ነበረኝ ስለ ሰዓት … መብረር እንደ አሞራ፤ መፍሰስ እንደ ወንዝ የሚል እርሱ ተጓዡ ይላል እና ባለቅኔውን ጠ/ሚር ዛሬ አንድ ሥም ልሸልማቸው ተጓዡ ጠ/ሚር ብዬ ሲደመር ማለት ነው ባለቅኔ + ተጓዥ= ? ረስቼው ሰባኪም + ለማኝም= የወጣልኝ ለማኝ ነኝ ያሉት እሳቸው ናቸው …

ሰባኪነታቸውን ግን ያዬነው መመሰከር ግድ ይላል … „ቃል ይተክላል ቃል ይነቅላል፤ ኢትዮጵያ የፈረሰቸውም የበቀለችውም በቃል ነው“ ብለውናል እና ይልቅ በዋ የባቢሎን ግንቡን በመንፈስ ለቁቤ ትውልድ ሲያንጹ ግን ዝም አይገባም? ነቃቀሉን እኮ? ያልፈረሰ መንፈስ የለም? ለነጮችም ሹክ ቢባሉ ጉዲሰዲ ሳይሉ አይቀሩም። ሌለኛው የጫት ፕሮፌስር ደግሞ „ኢትዮጲስኛ“ ይሁንልን አማርኛ ቋኝቋ ሲሉስ? አቤት ዘንድሮ ሙጃውን ያላበቀለ ማሳ ከተገኜ መቼም ዕድለኛ ነው … 

·       ብ ካለ …  

ልብ ያላቸው ውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵውያን አዲስ መንገድ ነድፈው አማራጭ የሆነ ሃሳብ በማፍለቅ ገደል አፋፍ ላይ ያለችውን አገራችን ኢትዮጵያን ሊያተርፏት ይገባል። ግን ንክኪ ባይኖር ያ ተሴራ … 

ጊዜው እያለቀ ነው። እኔ መፍራት ከጀመረኝ ቆይቷል። በአንድ ወቅት ፕ/ ዳንኤል ተፈራ እና አቶ ያሬድ ጥበቡ በ2017 ይመስለኛል ከቪኦኤ ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ „መቋሚያ“ በሚል ጹሑፍ ጽፌዋለሁኝ። አቶ ያሬድ ጥበቡ "ተጋምደናል፤ ስጋት የለብኝም" ብለው ሲሞግቱ እኔ ደግሞ እንቅልፍ አልባ ነኝ ብዬ ሞግቼ ጽፌ ነበር።

ዛሬ እነ አቶ በቀለ ገርባ ኢትዮጵያን ለመግደል በይፋ እና በአደባባይ የሞት አዋጅ ባወጁ ማግስት አዲስ አባባ ዩንቨርስቲ ላይ የቀወሰ አዲስ ማንፌስቷቸውን ለማስተማር ፕሮግራም ሲዘጋጅላቸው ምን ማለት እንደሆን ያልገባው ጋዜጠኛ፤ ይህን ማገናዘብ የተሳነው አክቲቢስት፤ ይህን መረዳት ያልቻለ የፖለቲካ ሊሂቅ በመፈጠር ውስጥ ያለ የጠፋ ህሊና ነው ለእኔ።

ለውጡን እንደግፍ፤ ለውጡን እንርዳ አቅሙ ለማን ነው የሚወጣው ብሎ ራስን መጠዬቅ ይገባል? አማራጭ የለንም ዛሬ የሚሉት አማራጭ ሳይኖራቸው ነበር ወይ አውሮፓ ላይ የሸግግር ሰነድ አዘጋጅተው፤ ትንሳኤ እና ብርሃን ነን ይሉ የነበረው? አዬር ላይ ያለው ተስፋ ይኸው ነበር … እኔ አበክሬ ስሞግተው የነበረው።

 የሚገረመው ትንሽ ነፍሱ ትር ትር የምትለውን ሰማያዊ እራሱ አብረው ነው ያፈረሱት። አንድ አይዲኦሎጂ የላቸውም። በተበተነ ሁኔታ አደጋ ላይ ያለችውን አገር ማዳን የሚቻል አይመስለኝም … አቅምን ስትፈትሹ የለንም። ድሮም አልነበረነም። እነሱም ያውቁታል። ለዚህ ነው ዘመን ጠርዘዝ ያለ ቄንጠኛ አጃጅልኝ ክኒን አምርተው በገፍ እያደሉት የሚገኙት። 

"እነሱን እንመን" የሚለውም የሚታመን ብጣቂ ነገር የለም። ቃል ፈሶ በአፍጢሙ ተደፍቶ ኤሉሄ እያለ ነው … ይህን መቀበል ያስፈልጋል፤ ቢመርም፤ ቢጎመዝዝም ቢያንገሸግሽም። አላዛሯን ኢትዮጵያን መልሰው ወደ 16ኛው ክፈለዘመን ወስደው እንደ ጥንቸል ሙከራ ጣቢያ እያደረጓት ነው።

ጠንካራ መከላከያ ቢኖር እኮ ኦነግ ምን አቅም ሲኖረው ነው። አጀንዳ ቢስ የኩሬ ውሃ እኮ ነው። ራሱ ሊሂቃን የሚባሉት እንደዚህ ዘመን ዘነዘናቸው አልወጣም። ግን ኦህዴድ ኦነግን ኢትዮጵያውያን እንዲፈሩት ገኖ እንዲወጣ ድርጅታዊ ሥራ እዬሠሩበት ነው። ቋጠሮው ሚስጢር ይኸው ነው።  

አማራ ክልል ለዚህ መንፈስ የጸጋ ስግደት ይሰገድ ነው የአሁኑ ወረራ … የግራ ቀኝ  ጣምራ የጥቃት ጉዳይ፤ እንዳትረሱ 90ሺህ አማራ ተፈናቅሏል በቀዩ፤ ስሜን ፓርክ ቃጠሎ አለ ለዚህ ይልቅ ህወሃት በተደራቢነት ማዬት ይቻል ይሆናል …

የሆነ ሆኖ ለዚህ ደግሞ ጠ/ሚር አብይ አህመድ አልሰሙም አላዩም … ለዚህም ነው የአገር ደህንነት ስጋት የብሄር ጉዳይ ነው የሚል መግለጫ እንዲወጣ ያስደረጉት … ይህን ጢባ ጢቦሽ ጨዋታ መቀበል ወይንም አለመቀበል የራስነገር ነው።

·       ጉሮሮ አጥንትነት።

ሌላው አቅም እንዳይፈጠር የጉሮሮ አጥንት መሆን፤ ለዚህ ጸጋው ነው ማለት የሚቻልለት ግንቦት 7 ነው። ከዘመነ ቀስተ ዳመና ጀምሮ። ውጭ አገር በነበረው ልኩ አገር ውስጥም ተመሳሳዩን እዬፈጸመ ነው። ወይ እሱ አይችል፤ ወይ ሌላው እንዲያድግ አይፈቅድ ካለ አቅሙ አገራዊ አጅንዳ ተሸክሞ በዬዘመኑ እንዲህ ያምሳል። ያተራምሳል።

እነሱ አቅም ኖሯቸው እንደ አማራጭ ሃይል ተስፋ እንዳይኖርም ይኸው ሜዳ ላይ ተነጥፈው እንደተለመደው የቀንድ ውጊያ … ላይ ይገኛሉ። በዚህ ማህል ነው የእስክንድርን ንቅናቄ ማዬት ማደመጥ ማስተዋል የሚገባን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን እና አቶ አንዱአለም አረጌን እራሱ መንፈሳቸውን ተርትረው ገብተውበታል …

 መከራ የገነባው ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ በጥበብ አህቲነት ነበር። ጽኑ አለትም ነበር እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ። ግን ግንቦት 7 የዞረው ነገር በርክቶ አያውቅም። ይህን ዛሬ ሳይሆን አስቀድሜም ስቸከችከው ነበር። ምን አለ ቢለቁ?!አሁን ለማገዶ የቀረበው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ነው።

ሌላው ቀርቶ በራሳቸው ጋዜኞች እንኳን አገር የገቡት እና ያልገቡት በሃሳብ ልዩነት ላይ እንዳሉ ነው እያዬን ያለነው። ይህን ያስደረገው ማንም ሳይሆን የግንቦት 7 መንፈስ ነው። አሻም ያለው ደግሞ አናናይ፤ አዛርያ እና ሚሳኤል ሆኖ ይቀጥላል …

የኢትዮጵያዊነት አቅሙ የትላይ ነው? ይህን መመርምር ነው። መንፈሱ ኢትዮጵያዊነት የት ላይ ነው ያለው? ያ መንፈስ ተሰቅዞ የተያዘበት የትኛው ላይ ነው፤ ይህን በማስተዋል መመርመር ይገባል …  

የሰው ልጅ ህሊናውን ማሰራት ሲጀመር ዓይኑ ያያል። ዓይን ማዬት ሲጀምር ደግሞ ከእውነት ጋር መገናኘት ይቻላል። ከመራራ ስንብት በፊት እውነትን ለመቀበል መቁረጥ ያስፈልጋል። 

ስለ ነገ ትልም ሳይሆን በመከሰም ላይ ስላለው ዛሬ። ዛሬ ከከሰመ ነገን መፍጠር አይቻልም። የነገ መፈጠሪያ ዛሬ ነውና። እርሾ አልቦሽ ምህንድስናን አምኖ መጪታውን ተታ ብንሸልመው ይገባል …
  
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሥልጣን የላቸውም። ደፈር ያለ እርምጃ ቢወስዱ ኦዴፓ ተሰብስቦ ከሥልጣናቸው ያባራቸዋል። እንደ እኔ ግን ከሥልጣናቸው ቢባረሩ ይሻላቸዋል በሌላ ወንበር አንደበትም ቁመናም እንዲህ በዘነዘናው ለግምገማ ያን የመሰለ ክህሎታቸው አይሆኑ ሆኖ ደቆ ራፊ አልቦሽ ሆኖ ከሚቀር። መራራ ስንብትም ከሚሆን ያው ሥልጣኑን  ለአቶ ለማ መገርሳ በግላጭ አስረክቦ ሾለክ ብልህነት ነበር ... 

አላቸው የበቃ መክሊት ግን አልሆነም። ሊያያዝላቸው አልቻለም … እውነትን በመሸሸት ላይ ያለ መክሊት ምርቃቱ ሙሉ ለሙሉ ሲነሳ ልሙጥነት ግድ ይላል … አቅም ክህሎት ችሎታ ተቀባይነት እያለ ግን እገታው ሊያንቀሳቀስ አልቻለም።

እገታውን ጥሶ ለመውጣት አንድ ነገርን መሳዋት ግድ ይላል … መሳዋትነት ተፈርቶ አገርን የፋሲካ ዶሮ ማድረግ ግን የታሪክ ጠቀራ ነው። ጠ/ሚር አብይ አህመድስ ስንት ቀን ስንቱን አምክንዮ ሸሽተው ይዘልቁታል? ሽሽቱን በመሸኝ ተላምዶ አይሆኑ ሆኖ ከመሸኛኘት በጊዜ የሚሆነውን እንደሚሆን ማድረግ ይገባል …

አሁን እኮ የንግግር ጥበቡ ራሱ እንቆቆ እዬሆነ ነው። ጥሞናል ብሎ በዚህ የተኮለኮሉ ጋዜጠኞች ሆነ ሊሂቃን የማከብረውን ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌናን ይጨምራል፤ የማከብረውን ዲያቆን ዳንኤልን ይጨምራል … በማስተዋል ውስጥ ያሉት ኡስታዞችንም ያካታል እውነትም መፈለግ ማፈላለግ ተግ ብሎ ሂደቶችን አጥንቶ ከቅብ ሁኖች ወጥቶ ቁመናው ሃቅ የሆነ ተፈጥሮውን፤ ከታወከው አዬር ለይቶ መመልከት ይገባል። ለአዬሩን መመርመሪያ መሳሪያ ያስፈልጋል …

Ethiopia -የገቢዎች ሚንስቴር በአንድ ወገን ተይዟል | ክፍል 1

Published on Apr 3, 2019

ዛሬ ሁሉንም ሙያ በአንድ ብሄር ሥር ለማድረግ አቅሙ የለም፤ የሚያጠር አቅም ስላለ … ነገ ግን ሁሉም በታሰበው መልክ ይከወናል … ይህ እንግዲህ በአንድ አመት ውስጥ ነው፤ እኛ ሐሴት አስክሮን ስንደናበር … ለሽ ብለን በፍሰሃ ሰክረን ስለተኛን … ዕድሜ ይነሳውና ስለዛ „አክ ወሬ“ ትርክት … እንጂ፤ ራሳችን ፈርሶ፤ ዛሬም ፈርሶ፤ ማግስትን እናልማለን ለዛውም ዴሚክራሲ? ከትከት እያረሩ ... 

ድንቄም ዴሞክራሲ … የሚገርመው የጊዜ ስጡን አማላይ እና አኖኽላይ ንግግርም ያን ያህል ተደማጭ መሆኑ በራሱ አዚም ይመስለኛል።

በሌለ ወና ምድረ ባዳ መኖር ውስጥ መኖርን መፈለግ እብንነት ነው ያ ዘመን ሰጥ ተፈጥሯዊ ሰዋዊ ቅብዕ የለም ከሐምሌ ጀምሮ። ቀጣዩ ደግሞ የሃይል እርምጃ ነው የሚሆነው። ይህን ጠብቁት።

ስለዚህ ወደ ራስ ተመልሶ አራስነብር በሆነው አዬር ላይ የወልን የመንፈስ ልቅና ክንድ ማንሳት ይገባል። ክንድ ማንሳት ስል ጦርነት ማለቴ አይደለም። የፊኩን ፍልስፍና ለመመርምር አቅም ይኑርን ለማለት ነው። ምስቅልቅሉ ምንጩን ማጥናት ያስፍልጋል።
ቢያንስ አቅምን ሊያፈሱበት የሚገባው ጉዳይ ላይ ማሰብ ያስፈልጋል … አቅም ለማን? አቅም ለምን? አቅም እንዴት? አቅም ወዴት? አቅም ከዬት?

መርመር … እንደ ድርጅት ብአዴን ደህዴንም ልቡን ፈልጎ ማግኘት ያለባቸው ይመስለኛል … ለኦዴፓ ማነው የሚቀረበው?ይህ በሚገባ ጊዜ ተወሰዶ ሊጠና የሚገባው የፊደል ገበታ ነው።

አሁን በአማራ ላይ ነው መቀጣጫው፤ መተንፈሻ ለማሳጣት እዬተደረገ ያለው ስውር ሴራ ነገ ግን የሁሉም ክስለት ነው … ሞትን በተራ ለመቀበል አቅም አዋጥቶ ድንኳን ውስጥ አብሮ ሳልሳ መዳነስ እንደ ሰው የተገባ አይመስለኝም … ሰው እንሁን!

ዳሩን በማወክ፤ ማህሉን ስብጥሩን በመበወዝ፤ ማዕከላዊ መንግስትን በመቆጣጠር ዛሬ ምን? ነገ ምን? ከነገወዲያስ? አሳንጋላው ማን እና እነማን ብሎ ማሰብ ይገባል

የአዬር መንገዱ የተርሚናል ምርቃት፤ የመከላከያ 7 ዓመት ክብረ  በዓል፤ የሚሊኒዬም የንግሥና እንድርቺ እንድርቺ የኦሮማማ እጬጌነት፤ የመሰቀል አደባባይ የፈረስ ጉጉስ ትርኢት የማጀቴ፤ የአጣዬ፤ የካራቆሬ የከምሴ … ቀራንዮ በወጉ መፈተሽ ይገባል …

የአዲስ አበባ የከተማ የ6ሺህ ስብጥር የአጥቂነት ገዢ መሬትን የመቆጣጠር ትልም፤ የአዲስ አባባ የዙሪያው የግማሽ ሚሊዮን ህዝብ የደጀነንት መሰናዶ ሰልፍ  የሁለት ዓመት እራሱን ችሎ የመቆም ምህንድስና ሁሉም መልዕክት አለው …

እነሱ በደመነፍስ አይደለም እዬተንቀሳቀሱ ያሉት፤ እኛ ነው በደመነፍሰ ተጎልተን በለኝ እያልን ያለነው።

የልባቸውን ፈጽመው ወጥተው ሲያሰተባብሉ ወይንም ይቅርታ ሲጠይቁ ወይንም እንዴት ተደፈርኩ ብለው ሲዘባበቱ በዚህ ውስጥ ያለውን እውነት ፈልጎ ለማግኘት አለመጣር የሞት አገር ታዳሚ ከመሆን፤ ከተጠያቂነት የሚያወጣን አይደለም።

ወቅቱ ተለዋዋጭ ነው። ተለዋዋጭነቱ ደግሞ ቅብ ነው። በውነቱ ፌካዊ ጉዞን አንግሶ
 መጓዝ እስትም ድረስ? ስለምንስ? አሁን የከምሴውን እና የሸዋውን ጉዳይ ሲታሰብ ይህን ያሰቡት ትግራይ እና አማራ ክልል ላይ ነበር። የሁለቱ የመድፍ መፈታተሽ ከራስ አውርዶ ቄሶች እንዲፈቱት ታስቦ ነበር፤ ለማዘናጊያ አገራዊ፤ ብሄራዊ ሆኖ ግን ከጉዳይ ሳይጣፍ ሁለቱም እንዳደፉጡ ዝም አሉ፤ ዘገዬ … ይህ ሲዘገይ ነው አዲስ በእጃቸው ላይ ባላ ጉዳይ ጦርነቱን አስጀመሩት … ፋታ ሳይሰጡ መጫን ነው ተግባራቸው። ሚዲያውን ደግሞ ለውጡን አደናቃፊዎች ወዘተ ወዘተ እያሉ ያስጮኹታል …

ረጋ ብለው ጉዳያቸውን ይከውናል። የ1ሚሊዮን ህዝብ መፈናቀል ሳይሆን የነበረው ጉዳያቸው ህወሃት ተሸኝቶ በትረ መንግሥት ነበር ሱሳቸው … ዓላማቸውንም ግባቸውንም ጠንቅቀው ያውቁታል፤ አዳሜ ፍኖተ ካርታ ይላል … እነሱማ አላቸው፤ መስጠረው ያያዙት። ኦሮማማ እኮ ነው መርህቸው ይህን አፍሪካዊ መልክ ለመስጠት ነው ጥረቱ። የመስከረሙ ጉባኤ እኮ ሁለመናው መሰናዶው ሙሉ ነው የነበረው።  

… የሆነ ሆኖ የከምሴውም የሽዋውም ትልም መቀሌ እና ባህርዳርን ሳንጃ አማዘው በቅራኔ ካጨቀዩ ማግስት ከድቀት መልስ ነበር ይኼኛውን አደላድለው ለመጀመር ትልማቸው የነበረው … ምህንድስናው በላይ በላይ፤ ጫና በጫና በፍጥነት መከወን ነው ፍላጎቱ … ከዘገዬ ይበላሻል ብለው ስለሚያስቡ።

በዘገዩት ጉዳዮች ላይ በእጅ ባለው ጫና እዬተንቀሳቀሱ በዬማህሉ ደግሞ የይቅርታ ዲስኩር ይመጣል … ይህ ዘፍኖብናል እስኪበቃው ድረስ። አንድ ዓመት ሙሉ … እንደ ሰው እንሆን … ሰውና እንሰሳ የተለያዬበትን ተፈጥሮ ህሊናዊነት በመሆን ውስጥ እናስብለው … ነብይነቱ ቢቀር ሰው ኖርማል ሰው እንሁን እባካችሁን?

ይህን ስል እንጥላቸው፤ እናግላቸው አይደለም፤ እነሱ የተፈጠሩበትን እየተገበሩ ነው፤ እኛም የተፈጠርንበትን ራስን ለማዳን መንገዳችን እንቀይስ፤ በብሰለት፤ በስክነት ለማለት ነው … ቢያንስ ሰው መሆናችን አንድ ያደርገናል። ሰለዚህ ሰውን መጥላት የራስን ተፈጥሮ መጥላት መሆኑን ማወቅ ይገባል። እግዚአብሄር የተጣለው ነው ሰውን የሚጠላ። 

Streamed live on Mar 22, 2019

በለውጡ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ኢትዮጵያዊ ቅርፅ እንዲኖራቸው ተደርጓል- መንግስት

Published on Apr 5, 2019

ኦነግ ላይ እርምጃ ለመውሰድ የማንንም ትእዛዝ አንጠብቅም የአማራ ክልል ለኦነግ የመጨረሻ ያለውን ማስጠንቀቂያ ሰጠ

Published on Apr 7, 2019

/ መራራ ጉዲና በጥያቄ ያፋተጧቸው የደቡብ ወጣቶች እናተ እራሱ የዘር ፖለቲካ እያራመደቹ ነው

/ ዶክተር አብይ አህመድ ከመቱ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል

Published on Apr 4, 2019

የኢትዮጵያ ህዝብ ነገም ቢሆን ሊጠራጠረን አይገባምአቶ ለማ መገርሳ /OBN/

Published on Mar 30, 2019

·       ንዳታችን በመነዳት ስለመሆኑ ማመን ይገባል።

ቅኖቹ የ አገሬ ልጆች... ከላይ በለጠፍኳቸው ሊንኮች ውስጥ ቃለ ምልልሶችን ሆኑ ጹሑፎችን ከስሜት በጸዳ መንፈስ በእኛ ውስጥ እኛ እንዴት ፈቅደን ወደን እንደተዘረፍን ተመልከቱት።

እራሱ ኢሳት እና ግንቦት7 መቅኖ አሳጥተውታል። የእውነት ጀግኖች ናቸው። ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ እውነትም የተጨዋቾች አስልጣኝ፤ አሰማሪም ናቸው … አጥቂውን፤ ተከለካዩን፤ ጎል ጠባቂውን፤ አራጋቢውን፤ ፊሽከኛውን መስኩን፤ መረቡን፤ ኳሱን ማቀባበል ሁሉንም አሳምረው ተቃኝተውታል … እኔ አለ ከሚባለው መሪ ሁሉ እንዲህ በአጭር ጊዜ ፍላጎቱን ያሳካ መሪ አላውቅም።

የአሁኑ ብስጭታቸው ምህንድስናቸው ሳያስቡት እክል ስለገጠመው እንዳይሰተጓጎል ነው፤ እሱንም አስተካክለውታል። … እነለጥ ይበሉም እንደለመደባቸው የጸጋ ስግደቱን እያስነኩላቸው ነው … አሁንስ ከሚሊዬነሙ ንግግር ቀጥሎ ከቶ አልገባችሁንም የሥም ጠ/ሚር እና የህልውና ጠ/ሚር ኦርምይነት እንዳለው  …   

ለዛውም ለጥ ለሽ ተብሎለት እዬተመሰገነ፤ እዬተወደሰ፤ ታቦት ይቀረጽለት እዬተባለ፤ ታመመብን፤ ጠፋብን እዬተባለ … ሚስጢር። ዳጥ ሲል እንኳን ምስጋናው መወደሱ ትናጋን አለስልሶ ከች ሲል መነጠፍ ነው የለመደብን … በቀደመ ስህተት እርማት በማድረግ እረገድ ኮንፒተር ይሻላል ከእኛ ሰው ተብዬ ሰዎች።  

ምን ያህል እዬተናድን እንደሆን የእኔ ብለን ጉዳዩን ወደ ራሳችን አስጠግተን ማዬት ያስፈልጋል።  በዚህ ውስጥ መታዬት ያለበት ኢትዮጵያዊ ብልህነት እና ማስተዋል ደግሞ አለ፤ ይህ የዘመኑ ቅኔ ነው፤ ይህ ቅኔ ደግሞ እንደ አውዳዓመት ሊታይ የሚገባው ነው። 
የአቶ ነአምን ዘለቀ ከግንቦት 7 ራሳቸውን ማግለል። 

የግንቦት 7 ልቡ መነቀል አስደስቶኝ አይደለም፤ እንዲያውም በሁለመናው በጉዳዩ አያያዝ ሁሉ አዝኛለሁኝ። ለነገሩ አገር ውስጥ ከሚዲያ ውጪ ሆነው ነው የከረሙት። ያ ትልቁ የሴራው እንብርት ነው። እስካገለገልክ ድረስ እንጂ ከዛ ወዲህ አሮጌ አካፋ እና ዶማ ያህል እንኳን ክብር የለም … አሁን አዲስ አጃቢዎች ደግሞ አሉ … ሥልጣን ግን ምንድን ነው? በሽታ ነው ቆሌ?

ብቻ ወቅትን ገምግሞ አቅምን አላግባብ እንደ አባይ ወንዝ ከማፈስስ ተግ ብሎ ከሁሉም ነገር ራሰን አግልሎ ሱባኤ መግባትን፤ የጥሞና ጊዜ መሻትን የፈጣሪ ጸጋ ስለመሆኑ ማሰብ ይገባል  … ጥሩ እርምጃ ነው የአቶ ነአምን ዘለቀ ውሳኔ።
·       ጠት ወይስ ስጠት?

OBN march 30, 2019

https://www.youtube.com/watch?v=3lS0tv-bmMA

ገፅ ገፅ የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነት እና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር / ብርሃኑ ነጋ ጋር የተደረገ ውይይት፡፡OBN መጋቢት 202011

ይህን ያቀረበ አንድአፍታ

Ethiopia: የግንቦት 7 ጉዳይ - እርገት ወይንስ ሥርገት ? በይታገሱ ዘውዱ

Published on Mar 7, 2019

እንደገና ደግሞ ይህን ይዞ ቀርቧል።

https://www.youtube.com/watch?v=4Fq1eNOcCt4

Ethiopia: [ነፃ ውይይት] "/ አብይ አወደሰኝ ብዬ ስህተቱን በዝምታ የማልፍ ሰው አይደለሁም!" ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር የተደረገ ቆይታ

Published on Apr 4, 2019

 

ሂደቶችን ቁጭ አድርጎ በመፍረስ እና በምስል ያሉ እሳጣ ገባዎችን ውስጣቸውን ገባ ብሎ መመርምር እንደ ሰው ያስፈልጋል። ስጠትም፤ ስጠትም ከሆነ ማለቴ ነው። ይህን የግልቢያ ጉዞ ተግ አድርጎ ማለት ነው።

 

በማን ላይ ዘመቻ እንዳለ፤ ማን እንዲወድቅ እንደተፈለገ፤ ማን ደግሞ ጠንክሮ እንዲወጣ እንደተፈለገ …  ግን ስለምን? ብሎ መጠዬቅ ይገባል። ማነው አድጋ ውስጥ ያለው? 

 

ፈረስ ግልቢያ ያመራው መስቀል አደደባባይ ጎራ ማለት ነው፤ ማስተዋል ያሰኘው ደግሞ የአቶ ነአምን ዘለቀን እርምጃ ውስጥ ዱብ ዱብ ማለት ነው።

 

እባካችሁ ውዶቼ ከግንቦት 7 ጋር አታያይዙት። ምን ኑሮት ግንቦት 7? ምኑስ ተቀንቶበት? ራሱ አጣብቂኝ ውስጥ ነው። አይሆኑ እዬሆነ ስለሆነ።

 

ጉዳዬ አገርን ለማዳን ከራስ መጀመርን እንማርበት ነው። አቅም ለማፍሰስ አቅሙ የራስ ፍላጎት አስፈጻሚ ስለመሆኑ ዲስኩሩን ሳይሆን ዕንባውን ቤቴ ማለት ይገባል። ኢሳትን ያህል ገናና ሚዲያ እንደ አገር ቤቱ ሚዲያ ለፈስፋሳ ወይንም ሰጋጅ አድርጎ ለማውጣት ነው ጥረቱ። ህወሃት አልተሳካለትም ነበር ኦነግ ግን አሳክቶታል። 


ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከጋዜጣዊ መግለጫቸው እንደተራዳሁት ጥሩ ለማኝ እንደሆኑ ነው ነግረውናል፤ እኛም ዋው ብለናል፤ እኔ ደግሞ አንድ ነገር ልከል ጥሩ አንሁለይ እና አማላይ መሆናቸውን ደግሞ አይተናል። ከላይ ሌላም ሥም ጨምሬያለሁኝ ተጓዥ ብዬ። የቀደመው ይሁን የአሁኑ ግን የሽሽት ነው ... ሽኝት ቢሆንስ ብሎ ማሰብም ይገባል? 

 

ማርች 8 አቤቱታ አንስት ሆይ! ጀግኑ እና ኦነግሻን አትርፉልን/ የአቶ ገዱ ሽኝት ማምሻ ላይ ጉሽምታ አማራ ፍጠን ይቅርታውን ሄደህ መቀሌ ላይ እና አንቦ ላይ ካስ አይነት ሽብል/ የአዲስ ወግ የሳንጃ ስለት የፊሻካ አስነፊ መሻት ፉከራ መዲናዋ ላይ ክላሽኮፖ ቀርቶቱ ትዝ አላቸው ነገረ ባድመ መሰል / የጋዜጣዊ መግለጫው የእውነት ሸሽሽት ሸርተቴ ሲቆምስ/  የንግሥና ባዕል የኦሮማማ ትንሳኤ በይቅርታ አፍዝዝ አድንዝዝ ጸበለ ጻዲቅ ርችት ሲደመሩ ግን መናህሪያችን የት ላይ ነው ያሰኛል? 

 

እናላችሁ እኔ አህታችሁ እሳቸውን ካድሬ/ ኢንተርቴዬነር/ ተዋናይ/ ተናጋሪ/ አክቲቢስት/ መሪ/ ሰባኪ/ ወዘተረፈ … ሆኑብኝ።

 

ይሄ ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ ስለሚባሉት ስሜን አሜሪካ ላይ በነበረው ከጠ/ሚር አብይ አህመድ ጋር አንድ ነፍስ ያለው ጥያቂ ሳያቀርቡ በጸጋ ስግደት ለጥ ብለው መሰናበታቸው ያን ቀን ነበር መራራ ስንብቱ … ተስፋየ በልቆ በቅቶታል። ከዛ ... ከዛማ እሽቅድምድም ነበር አገር ቤት ለመግባት ... የጥሞና ግዜ ምንትሶ ቅብጥርሶ የለም፤

 

ስለዚህ አማራጭ ስለሚለው የተስፋ ተጠማኝነት ዱዳ ነኝ። አሁን ሁሉም ከኦነግ ፍላጎት ማዳፍ ውስጥ ነው … ነገ አልቅሶ ወይ አስልቅሶ ይጠብቃል

 

አቤቱ „አክ ወሬም“ ሩጫውን ጨርሶ „አሞራው በረረ ቅሉ ተሰበረን“ አስተቃቅፎ … በሰባራ ስንጥር ታቱ ይበል … ይብቃኝ …

 

ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል!

 

የኔዎቹ ኑሩልኝ።


መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።