"በአማራ ክልል የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር፤ በከተማይቱ ያሉትን ተፈናቃዮች ማስተናገድ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት አስታወቀ።

#አሳረኛው አማራ።

 
ከአቶ እናት እና አባቴ ዬተገኜ ነው።
"አስመሳይነት እና ከፍሎ አዛኝነት"
"አስመሳዩ አክቲቪዝም የዘነጋቸው፣ ከ26 ሺህ የሚበልጡ የፋሺስቱ የኦሮሚያ አገዛዝ ተፈናቃዮች!"
"በአማራ ክልል የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር፤ በከተማይቱ ያሉትን ተፈናቃዮች ማስተናገድ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት አስታወቀ። ከሁለት ሳምንት ወዲህ ወደ ከተማይቱ የሚገቡ አዲስ ተፈናቃዮችን መቀበልም ሆነ ወደ መጠለያ ማስገባት ማቆሙንም የከተማይቱ አስተዳደር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጿል።
ከአዲስ አበባ 130 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የደብረ ብርሃን ከተማ፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከመንፈቅ ባሉት ጊዜያት በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ አራቱም የወለጋ ዞኖች እንዲሁም ከአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን ስታስተናግድ ቆይታለች።
በአሁኑ ወቅት በከተማይቱ በሚገኙ በስድስት ጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ 26 ሺህ ገደማ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ከከተማይቱ አስተዳደር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
ከምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ሲቡ ሲሪ ወረዳ ተፈናቅለው ለአንድ ዓመት ያህል በከተማይቱ ተጠልለው የሚገኙት አቶ አህመድ መሐመድ፤ ባለፉት 15 ቀናት ወደ ደብረ ብርሃን የመጡ ተፈናቃዮች መጠለያ ሳያገኙ መቅረታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
የከተማይቱ ኃላፊዎች “ህዝቡ ሲጨምር አንመዘግብም ብለዋል” ሲሉም ባለፉት ሁለት ሳምንታት ካሉበት መጠለያ ጣቢያ ሆነው የታዘቡትን አስረድተዋል።
አቶ አህመድ ከተፈናቀሉበት ምስራቅ ወለጋ ዞን፤ ጉቡ ሰዮ ወረዳ የመጡት አቶ አስናቀ ጋሻው ይህንኑ አረጋግጠዋል። በግብርና ስራ ይተዳደሩ የነበሩት አቶ አስናቀ፤ በጸጥታ ችግር ምክንያት የመኖሪያ ቀያቸውን ለቅቀው ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ ከመጡ ሁለተኛ ሳምንት ገደማ ቢያስቆጥሩም መጠለያ ማግኘት አለመቻላቸውን ገልጸዋል።
ከሶስት ልጆቻቸው እና ባለቤታቸው ጋር “በረንዳ” ላይ እያደሩ መሆኑን የሚናገሩት አቶ አስናቀ፤ “ወደ መጠለያ ሄደን ‘እኛ አንመዝግበም፤ እዚህ ሞልቷል’ አሉን” ሲሉ በመጠለያ ጣቢያ ካሉ ኃላፊዎች ያገኙትን ምላሽ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስረድተዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የካቲት 7፤ 2015 በመጠለያ ጣቢያዎች በር ላይ በለጠፈው ማስታወቂያ፤ ከነባር ተፈናቃዮች ውጭ አዲስ ተፈናቃዮችን እንደማያስተናግድ እና እንደማይቀበል አስታውቋል። የከተማ አስተዳደሩ ተፈናቃዮችን መቀበል ያቆመው፤ “በመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች፤ በቋሚነት ወሩን የጠበቀ የምግብ አቅርቦት ባለመኖሩ” መሆኑን በመግለጫው ላይ ጠቁሟል።
ይኽ በእንዲል እንዳለ፤ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በተፈናቃዮች ብዛት ምክንያት አዲስ ተመዝጋቢዎችን እንደማይቀበል አስታውቋል። ተፈናቃዮች፤ በጥላቻ የገነገነው ፋሺስቱ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት፣ ዘር ለይቶ ክልሌን ለቃችሁ ውጡ እያለ ያፈናቀላቸው፤ ከሞት የተረፉ ንጹሃን ናቸው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።