የቦረና ዞን የድርቅ ሁኔታ ****

ከአቶ አሻግሬ ጌታቸው ዬተገኜ ነው።
የቦረና ዞን የድርቅ ሁኔታ
****

 
በቦረና ዞን ወራጅ ወንዝ ሆነ የተፈጥሮ ሐይቅ የለም፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብ እርሻ እና የመጠጥ ውሃ ምንጭ ከዝናብ የሚገኝ ብቻ ነው። በ2013 እና በ2014 ዓ.ም በተከታታይ ሁለት አመት የዝናብ ወቅቶች በማለፉ የተፈጠረ ድርቅ ነው፡፡ የመጀመሪያው አመት በእንስሳት ላይ ነበር ጉዳቱ የደረሰው ዘንድሮ ግን በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ማድረስ ጀምሯል።
1) ምሳሌ በአንድ ቀበሌ ውስጥ የምግብ ድጋፍ ማግኘት የሚገባቸው ሰዎች ውስጥ ለግዜው እርዳታ እየቀረበ ያለው ከ30 ቤተሰቦች ውስጥ 5 ቤተሰብ ብቻ ነው፡፡
2) ሕፃናት፣ አረጋውያን፣ ነፍሰ ጡር፣ የሚያጠቡ እናቶች በምግብ እጥረት ለተለያዩ በሽታዎች እየተጋለጡ ይገኛል ለዚህ እየተሰጠ ያለው ድጋፍና የአልሚ ምግብ አቅርቦት ያነሰ መሆኑን የእርዳታ ድርጅቶች ገልጸዋል፡፡
3) በ2014 ዓ.ም ህጻናት ተማሪዎች 3,166 ወንዶች እና 2,743 ሴቶች በድምሩ 5,809 ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ አይደሉም፡፡
4) አርብቶ አደር የሆነው ማህበረሰብ ለከብቶች ሳር እና ውኃ ፍለጋ፣ ከፊሉ ቤተሰብ ይዞ ከፊሉ ደግሞ አጎራባች ዞኖች ተሰደዋል፣ ወይም ወደሌላ ክልሎች ሂደዋል እስከ ጎረቤት ሀገር ኬንያ የተሰደዱ እንዳሉ ይገለጻል፡፡
5) እስከ ሐምሌ 2014 ዓ.ም ድርስ በዞኑ 117,422 ሕፃናት እና 9,591 ነፍሰ ጡር (አጥቢ) እናቶች የምግብ እጥረት አጋጥሞቸዋል።
****
የሶማሌ ክልል መረጃ ደሞ ከክልሉ ቢሮ ጠይቀን እናቀርባለን

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።