ነፍሱ ከሥጋው የተለዬ፤ ሰላማዊ እረፍቱን የተነሳ የሰው ልጅ #አስከሬን ለፖለቲካ መደራደሪያ #የሚሰቃይበት ዘመን ያሳዝናል። «ትራምፕ እና ኔታንያሁ በጋዛ የሰላም ዕቅድ ላይ ተስማሙ» ዘገባው የBBC ነው። «የመካከለኛው ምሥራቅ እና የአውሮፓ መሪዎች የጋዛን የሰላም ዕቅድ እንደሚደግፉ ገለጹ»

 

 
 
ነፍሱ ከሥጋው የተለዬ፤ ሰላማዊ እረፍቱን የተነሳ የሰው ልጅ #አስከሬን ለፖለቲካ መደራደሪያ #የሚሰቃይበት ዘመን ያሳዝናል።
አቤቱ አምላኬ ሆይ! 
 
"በቸርነትህ ምራኝ።" አሜን።
 
 May be an image of 1 person and text that says 'PEACE THROUGH STRENGTH TheWHITEHOUSE SE WHITE HOU'Donald Trump standing in a suit and tie. The text "the PEACE PRESIDENT" is overlaid in large white letters above and below him.
 
 ፕላኔታችን ትሁን፤ ስለ ሰው ልጅ መብት መረገጥ ግድ የሚላቸው ደጎች ሁሉ፤ ቁመን ለምንሄደው ቢቀር በሥጋ የተለዩት አካላቸው ለየትኛውም ዓለም የፖለቲካ ቅድመ መደራደሪያ #መያዣ የማይሆንበት ዘመን እኔ ይናፍቀኛል። ሰቅጣጭ እና አሰቃቂ አቋም ነውና።
 
እኔ ከዚህ በተረፈም የሰውን ልጅ የሚጎዳ ማናቸውም #የመዳህኒት #ቅመማ ሁኔታም የዓለም መወያያ አጀንዳ ይሆን ዘንድ እመኛለሁኝ። ጎጂ እንሰሳት፤ ጎጂ አረሞችን የሚቋቋም መዳህኒት መፈልሰም ለሰው ልጅ መኖር #ጥበቃ ያደርጋል። መሰሉን ለሰው ልጅ መጠቀመም ግን #ሰውኛም#ተፈጥሮኛም አይደለም። አቅሙ ምን ያህል እንደ ሆን ባላውቅም #ተመድ በዚህ ላይ አትኩሮት ቢሰጥ የሚል ህልም አለኝ።
 
አስቦበት የሚያውቅ ግን አይመስለኝም። ምንጊዜም ለሰው ልጅ ደህንነት እና የውስጥ ሰላም ማግኜትን ጥበቃ የምታደርግ ፕላኔትን አዘውትሬ እመኛለሁኝ።
 
አሁን ቢቢሲ አማርኛውን ስጎበኝ መልካም ዜና፤ #ቸር ዘገባ አገኜሁኝ። ለፍፃሜ ከበቃ ያን ሁሉ የሰቆቃ ገጠመኝ ያስተናገደው የፍልስጤም እና የእስራኤል ጦርነት በመልክ በመልኩ መቋጫ ያገኛል። ብዙ እጅግ ብዙ ጉዳትን ያስተናገደ ጊዜ ነበር። አሁንም ጦርነቱ አልቆመም።
ይህ ዘገባ እንደሚያመለክተው ከሆነ በግራ ቀኙ በኩል #ይሁንታ አለ። 
 
ይሁንታው ታትሞ ዕንባ ሲቆም፤ መጨካከን ቀጥ ሲል፥ ትውልድ ተስፋን የማየት #ፍንጣቂ ብርሃን ሲወጣለት ከደስታ በላይ ሐሴት ይሆናል። ጥረቱ እንዲያፈራ ደግሞ ሁሉም ይህን የብሥራት #መቅድም ዕውቅና ሰጥቶ ሂደቱን በርታልን አጤ ሂደት ሊለው ይገባል። 
 
ሥርጉትሻ 2025/09/30
#ቅድሚያ ለሰላም!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
• «ትራምፕ እና ኔታንያሁ በጋዛ የሰላም ዕቅድ ላይ ተስማሙ» ዘገባው የBBC ነው።
«የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አዲስ የጋዛ የሰላም ዕቅድን በተመለከተ #ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።
የሁለቱ መሪዎች ዕቅድ፤ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች #በአፋጣኝ እንዲቆሙ እንዲሁም ሐማስ በ72 ሰዓታት ውስጥ 20 እስራኤላውያን ታጋቾችን እና የሞቱ ታጋቾችን #አስክሬን እንዲያስረክብ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል።
በምላሹም በመቶዎች የሚቆጠሩ የታገቱ የጋዛ ነዋሪዎች የሚለቀቁ ይሆናል። መሪዎቹ በዋይት ሀውስ ውይይት ካደረጉ በኋላ በሰጡት መግለጫ ትራምፕ "ለሰላም ታሪካዊ ቀን" ሲሉ ዕቅዱን አሞካሽተዋል።
ሐማስ በሰላም ዕቅዱ የማይስማማ ከሆነ ኔታንያሁ "የጀመሩትን ሐማስን የማጥፋት ዘመቻ" አሜሪካ እንደምትደግፍ አክለዋል።
ኔታንያሁም ሐማስ ዕቅዱን ካልተቀበለ ወይም ካልተገበረ እስራኤል "የጀመረችውን ትጨርሳለች" ሲሉ ዝተዋል። በእስራኤል ይዞታ ሥር የሚገኘውን ዌስት ባንክ የሚያስተዳድረው የፍልስጤም አመራር ትራምፕ እያደረጉ ያሉት ጥረት "#ቆራጥነት የተሞላው እና እውነተኛ ነው" ብሏል።
የፍልስጤሙ ዋፋ የዜና ኤጀንሲ ላይ በወጣው መግለጫ የፍልስጤም አስተዳደር "በጋዛ ላይ የተከፈተውን ጦርነት ለማስቆም ከአሜሪካ፣ ከቀጣናው አገራትና አጋሮቻችን ጋር በጋራ ለመሥራት አሁንም #ቁርጠኛ ነን" ሲል አቋሙን አስታውቋል። አስተዳደሩ፤ ጦርነቱን ከማስቆም በተጨማሪ ወደ ጋዛ ሰብአዊ #እርዳታ እንዲገባ እንዲሁም የታጋቾች እና እስረኞች ልውውጥ እንዲካሄድ እንደሚሠራ ገልጿል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ካታር፣ ግብፅ፣ ዮርዳኖስ፣ ቱርክ፣ ኢንዶኔዥያ እና ፓኪስታን በጋራ ባወጡት መግለጫ "ትራምፕ የጋዛን ጦርነት ለመግታት እያደረጉ ያሉትን ያላሰለሰ ጥረት #እንደግፋለን" ብለዋል። ስምምነቱ እንዲተገበር ከአሜሪካ ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆናቸውንም አክለዋል። የሰላም ዕቅዱ የሁለት አገራት መፍትሔ መስጠት እንዳለበት እና ጋዛ ከዌስት ባንክ ጋር ተሳስራ የጠቅላላው የፍልስጤም አስተዳደር አካል መሆን እንዳለባት አገራቱ ገልጸዋል።
ለተኩስ አቁም ስምምነቱ ቅርብ የሆኑ የፍልስጤም ምንጭ ለቢቢሲ አንደተናገሩት፣ ዋይት ሀውስ #ለሐማስ 20 ነጥቦችን አቅርቧል።
ሐማስ ጋዛን ከዚህ በኋላ ማስተዳደር እንደማይችል እና በጊዜ ሒደት ፍልስጤም እንደ አገር እንደምትመሠረት ተጠቅሷል።
የቀረበው የሰላም ዕቅድ የሚተገበር ከሆነ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች በአፋጣኝ #የሚገቱ ይሆናል። አሁን ያሉ "የጦር ግንባሮች" ባሉበት እንደሚቆዩና ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ በኋላ ወታደሮች #ለቀው እንደሚወጡ ይጠበቃል። ትራምፕ ባወጡት ዕቅድ መሠረት፣ ሐማስ ጦሩን ፈትቶ የመሣሪያ ማምረቻ ተቋማቱ ይወድማሉ።
 
የአንድ እስራኤላዊ ታጋች አስክሬን ሲለቀቅ እስራኤል #የ15 የጋዛ ነዋሪዎችን አስክሬን በምላሹ ታስረክባለች። ሁለቱም ወገኖች በሰላም ዕቅዱ የሚስማሙ ከሆነ ወደ ጋዛ "ሙሉ ሰብአዊ እርዳታ" እንደሚገባም ተገልጿል።
 
አሜሪካ በቀጣይ ጋዛን ማን ያስተዳድራል በሚለው ላይ የወጠነችውን ዕቅድ አስቀምጣለች። ጋዛን በጊዜያዊነት "#ከፖለቲካ ነጻ የሆነ ኮሚቴ" እንደሚመራት እንዲሁም "አዲስ ዓለም አቀፍ #የሽግግር ጊዜ ተቆጣጣሪ አካል" አስተዳደሩን እንደሚከታተል ተገልጿል።
ይህንን ተቆጣጣሪ አካል የሚሾሙት ትራምፕ ይሆናሉ። የቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር የዚህ ተቆጣጣሪ አካል እንደሚሆኑ ይጠበቃል።»
 
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------
 
• ተያያዥ አጋዥ ዘገባ።
 
«የመካከለኛው ምሥራቅ እና የአውሮፓ መሪዎች የጋዛን የሰላም ዕቅድ እንደሚደግፉ ገለጹ»
 
«የአውሮፓ እና መካከለኛው ምሥራቅ መሪዎች አሜሪካ የጋዛን ጦርነት ለማስቆም ያቀረበችውን የሰላም ዕቅድ እንደሚደግፉ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሐማስ ስምምነቱን መቀበል አለበት ብለዋል።
 
ትራምፕ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የተስማሙበት ዕቅድ፤ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች በአፋጣኝ እንዲቆሙ ያደርጋል ተብሏል።
 
ሐማስ በ72 ሰዓታት ውስጥ 20 እስራኤላውያን ታጋቾችን እና የሞቱ ታጋቾችን አስክሬን እንዲያስረክብ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል።
በምላሹም በመቶዎች የሚቆጠሩ የታገቱ የጋዛ ነዋሪዎች ከእስር የሚለቀቁ ይሆናል። የአውሮፓ ካውንስል ፕሬዝዳንት አንቶኒዮ ኮስታ "ኔታንያሁ ለሰላም ዕቅዱ አዎንታዊ ምላሽ መስጠታቸው አበረታች ነው" ብለዋል።
 
"ሁሉም አካላት ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው ለሰላም ዕድል መስጠት አለባቸው" ሲሉም አክለዋል። ለተኩስ አቁም ስምምነቱ ቅርብ የሆኑ የፍልስጤም ምንጭ ለቢቢሲ አንደተናገሩት፣ ዋይት ሀውስ ለሐማስ 20 ነጥቦችን አቅርቧል።
 
የፍልስጤሙ ዋፋ የዜና ኤጀንሲ ላይ በወጣው መግለጫ የፍልስጤም አስተዳደር "በጋዛ ላይ የተከፈተውን ጦርነት ለማስቆም ከአሜሪካ፣ ከቀጣናው አገራት እና አጋሮቻችን ጋር በጋራ ለመሥራት አሁንም ቁርጠኛ ነን" ሲል አቋሙን አስታውቋል።
 
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ካታር፣ ግብፅ፣ ዮርዳኖስ፣ ቱርክ፣ ኢንዶኔዥያ እና ፓኪስታን በጋራ ባወጡት መግለጫ "ትራምፕ የጋዛን ጦርነት ለመግታት እያደረጉ ያሉትን ያላሰለሰ ጥረት እንደግፋለን" ብለዋል።
 
አሜሪካ በቀጣይ ጋዛን ማን ያስተዳድራል በሚለው ላይ የወጠነችውን ዕቅድ አስቀምጣለች። ጋዛን በጊዜያዊነት "ከፖለቲካ ነጻ የሆነ ኮሚቴ" እንደሚመራት እና አስተዳደሩን "አዲስ ዓለም አቀፍ የሽግግር ጊዜ ተቆጣጣሪ አካል" እንደሚከታተል ተገልጿል።
 
ይህንን ተቆጣጣሪ አካል የሚሾሙት ትራምፕ ይሆናሉ። የቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር የዚህ ተቆጣጣሪ አካል እንደሚሆኑ ይጠበቃል። ይመሠረታል የተባለውን ተቆጣጣሪ አካል በተመለከተ ቶኒ ብሌር "በጣም ጥሩ ሐሳብ ነው" ብለዋል።
የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ዕቅዱን እንደሚደግፉ ገልጸዋል።
 
"ሁሉም ወገኖች አንድ ላይ ሆነው ስምምነቱ እንዲተገበር ከአሜሪካ መንግሥት ጋር እንዲሠሩ እንጠይቃለን" ሲሉም ተናግረዋል።
ሐማስ "የሰላም ዕቅዱን ተቀብሎ ሰቆቃው ሊቆም ይገባል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሐማስ "ጦር ማውረድ አለበት። የተቀሩትንም ታጋቾች ይልቀቅ" ብለዋል።
 
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን "ፈረንሳይ ጦርነቱ እንዲቆምና ታጋቾች እንዲለቀቁ ለመተባበር ዝግጁ ናት" በማለት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
 
"ይሄ ዕቅድ ለተጨማሪ ውይይት በር መክፈት አለበት። በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍንም ያስችላል" ሲሉም ማክሮን አክለዋል።
የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ባወጡት መግለጫ፤ የሰላም ዕቅዱ "ለውጥ የሚያመጣ ስለሆነ ሁሉም አካላት ሊቀበሉት ይገባል" ብለዋል።
 
የሰላም ዕቅዱ ሐማስ ጋዛን በማስተዳደር ረገድ "ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ" ሚና ሊኖረው እንደማይችል ያትታል። አብዛኛው የዕቅዱ ክፍል አሜሪካ ጋዛን መልሶ ለመገንባት የወጠነችው "የምጣኔ ሃብት እድገት" ላይ ያተኮረ ነው።
 
"እስራኤል ጋዛን አትቆጣጠርም፤ በግዳጅም የግዛቷ አካል አታደርግም" የሚል ነጥብም አካቷል። የሰላም ዕቅዱ ሲተገበር የእስራኤል ጦር ጋዛን ለቆ እንደሚወጣ ተጠቅሷል።
 
ትራምፕ ከዚህ ቀደም ከነበራቸው አቋም በተለየ ሁኔታ የጋዛ ነዋሪዎች ከተማውን ለቀው እንዲወጡ አይገደዱም። "ነዋሪዎች እዛው እንዲቆዩ እናበረታታለን። የተሻለች ጋዛን እንዲገነቡ እናግዛቸዋለን" በሚል በሰላም ዕቅዱ ላይ ሰፍሯል። ለስምምነቱ ቅርብ የሆኑ የፍልስጤም ምንጭ ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ የካታርና ግብፅ አመራሮች በዶሀ ለሚገኙ የሐማስ አመራሮች ዕቅዱን አቅርበዋል።
 
ቀደም ሲል አንድ ከፍተኛ የሐማስ አመራር፤ በጋዛ ጦርነትን የሚያቆም ዕቅድን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገልጸው ነበር።
ማንኛውም ስምምነት የፍልስጤማውያንን ፍላጎት የሚያስጠብቅ ሊሆን እንደሚገባ እንዲሁም የእስራኤል ጦር ከጋዛ ሙሉ በሙሉ መውጣት እንዳለበት አስምረውበታል። ትጥቅ መፍታትን በተመለከተ "በግዳጅ በይዞታ ሥር እስከሆንን ድረስ ትጥቅ መፍታት የሚለው ጉዳይ ቀይ መስመር ነው። ፍልስጤም የ1967ቱን ድንበር ተከትላ ነጻ አገር ሆና የምትመሠረትበት ፖለቲካዊ መፍትሔ ሲተገበር ነው ትጥቅ ስለመፍታት የምንነጋገረው" ብለዋል።
 
ባለፈው ሳምንት በኒው ዮርኩ የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ምዕራባውያን አገራት ለፍልስጤም አገርነት ዕውቅና መስጠታቸው ይታወሳል። ኔታንያሁ ይህንን በመቃወም ንግግር ሲያደርጉ በርካታ ዲፕሎማቶች እና አመራሮች ጉባዔውን ረግጠው ወጥተዋል።
 
እስራኤል በቅርቡ የአሜሪካ አጋር በሆነችው ካታር የሚገኙ የሐማስ አባላት ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ትራምፕን ደስ አላሰኘም። ኔታንያሁ ከትራምፕ ጋር ውይይት ከማድረጋቸው አስቀድመው በዋይት ሀውስ ሳሉ፣ ለካታር ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ቢን አብዱልራሕማን ቢን ጃሲም አል-ታሒኒ ደውለው በሚሳዔል ጥቃቱ የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።
 
1200 ሰዎች የተገደሉበትን የሐማስ ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 66,055 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።
የመንግሥታቱ ድርጅት በጋዛ ረሃብ መስፋፋቱን አስታውቋል። የድርጅቱ ኮሚሽን እስራኤል በጋዛ የዘር ጭፍጨፋ መፈጸሟን ቢገልጽም እስራኤል ክሱን አልተቀበለችም።»

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።