ጋንቤላ ምርጥ ልጆቹ ለጋንቤላ ህዝብ መፍትሄው ናቸው!
ጋንቤላ ምርጥ ልጆቹ ለመፍትሄው ቁልፍ ናቸው።
„አንተ ለእኔ መሸሸጊያ ነህ ከጣርም ትጠብቅኛለህ፤
ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ
ነህ“
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፩ ቁጥር ፯
ከሥርጉተ©ሥላሴ
24.99.2018
ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።
- · እፍታ።
እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ። አንድ አስተያዬት ተልኮልኛል። እኔ እኮ በደረቅ ወንጀል
ላይ እርምጃ መወሰዱ የተጋባ አይደለም ማለት አለንበረም ዕይታዬ፤ ፖሊስ የተደራጀበት ምክንያት እኮ ለህግ አስፈጻሚነት ነው።
እንዲያውም ይህን መሰል
እርምጃዎች እምፈልጋቸው ናቸው። በወጣቶች ቀረጻ ላይ ልዩ አትኩሮትም ስለ አለኝ።
ነገር ግን አሁን ስለምን ይህ ወቅት ተመረጠ ብቻ ሳይሆን የቀደመው የላፍቶ ከተማ ፖሊስ ቢሮ
መግለጫ እና የአሁኑ አዲስ አባባው ኮሚሸነር መግለጫ አልተገናኘልኘም። ቶኑም አልተመቸኝም።
መረጃው ልጥ እና ልሙጥ ነው
የሆነው። የሆነን አካል ወንጀል ለመሸፈን ተብሎ የተሰናዳ ነው - ለእኔ። እጅግም ዘግይቷል። ሌላው ለወንጀልኝነት ለናሙና የቀረቡት ጎንደር፤ ወሎ እና አርባምንጭ ደግሞ ጉዳዩን ስለምን እንዚህ ከተሞች
ላይ ወንጀለኞች ቀረቡ? ሌሎች ከተሞች ወንጀለኞች የሉንም ያሰኛል፤ ለዛውም የሰው ልጅ ተገድሎ ተዝቅዝቆ ተሰቅሎም እያዬን ነው።
ይህን ሁሉ መፈናቀል እና ዝርፊያም ኦሮምያ ላይም እያዬን ነው።
ይህ እውነቱን ለማናገር ጓደኛ ፍለጋ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ በእንዚህ
ከተሞች ሆን ተብለው ስትራቴጅካዊ የማጥቃት ትልም እንዳለ ያሳያል። በጠቅላላው ለእኔ ታማኝ መረጃ አይደለም። መረጃውም ወጥ አይደለም።
በሌላ በኩል ይህን አቅዶ የሚከውነው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማህበረተኛም አለ፤ ፈቃጁም፤ነጋዴውም እነሱው ናቸው … ከሁሉ በላይ ሁሉም ክልል ሰው ይፈናቀላል፤ ይሞታል፤ ይሰደዳል ትግራይን ሳይነካ? ይህም ሌላው ልብጥ ጉዳይ ነው
…
- · ነፍሴ ጋንቤላ …
ወደ ቀደመው ምልስት ሲሆን ጋንቤላን በሚመለከት በተለያዩ ሁኔታዎች በተለያዬ ጊዜ አነሳዋለሁኝ።
የሆስፒታሉ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በአንድ ወቅት ጽፌያለሁኝ። የዛሬ ሁለት ሦስት ዓመት የኮንሶ እናት ዕንባም ከነፎቷዋ ለሚመለከተው
አካል ልኬያለሁኝ።
ከዚህ በተረፈ በተለይ ዶር አብይ አህመድ ጋንቤላ ሄደው ባደረጉት ውይይት ከሁሉም ክልሎች ነፍስ
ያለው ለእኔ ውስጥ የቀረበ በሳል ጥያቄ የቀረበብት ጋንቤላ ነበር። በዬክልሎች በቀረበው ጥያቄ እና በመልስ አቅጣጫ ጠቋሚ ጉዳይ
ደግሞ ጠ/ ሚር አብይ ከሚሰጡት ማጠቃለያ ዕይታ ያዬሁት የመጨረሻውን አፋርን ነበር፤ ብዙ ነገር አግኝቼበታለሁኝ።
መቼም ያን ጊዜ የሰናይ ጊዜዬ ነበር ማለት እችላለሁኝ። የኦን ላይን ተማሪ ነበርኩኝ ማለትም
እችላለሁኝ። ወገኖቼን ማዬቴ በራሱ ልዩ ሐሴት ነበረኝ። በዬትኛው ክልል ምን ዓይነት ጥያቄ እና ምን ዓይነት መለስ የሚለውን በቃሌ
እስከ ማጥናት ደርሻለሁኝ። የልቤ የምለው ፕሮጀክት ነበር በጠ/ ሚር አብይ አህመድ የተከወነው። እሱ ያሳባዳቸው ናቸው አሁን አሳር
አማራች የሆኑት።
ያን ጊዜ ጋንቤላ ላይ የተነሳ አንድ ወሳኝ ጥያቄ ነበር። የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ዜጎች ከጋንቤላ
ከሚኖረው ህዝብ በላይ መሆን እና የቁጥጥሩ ሁኔታም ከመጪው የኢትዮጵያ ተስፋ ጋር ያለውን ስጋት ነዋሪዎቹ ጠይቀው ነበር።
እኔም
ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ ከ10 ዓመት በኋዋላ ከ20 ዓመት በኋዋላ ይህ ችግር ማህል አገር ሊደርስ እንደሚችል፤ እዬቆዬ ሲሄድ የአገር ይገባኛል ጥያቄ ሊኖር እንደሚችል
እና ልዩ ትኩረት ሊደረግብት እንደሚገባ ጠንከር ያለ ተጨማሪ ሃሳብ አክያለሁኝ።
የሆነ ሆኖ ጋንቤሌ ላይም ለውጡን ለመቀንጠስ የታቀደ ችግር መኖሩ ቀደም ባሉት ጊዜያቶች ተጠቅሰዋል፤ አሁን
የሰው ህይወትም መጥፋቱን እያዳመጥኩኝ ነው። ወጣቶችም ያነሱትን ጥያቄ ሰምቻለሁኝ። በጠቅላላ ሁኔታ ሲታይ ይህ ህዝብ 27 ዓመት
ሙሉ የሌላ እንጀራ አብሳይ ሆኖ የኖረ ህዝብ ነው።
በሌላ በኩል አኟክ የዘር ነቀላ የተካሄደብ የተበደለ ህዝብ ነው። አሁን ደግሞ
በድጋሚ ታቅዶ የባሩድ እራት መሆኑ እጅግ ለህሊና ይከብዳል። የሆነ ሆኖ መፍትሄ ከቅርብ አለ ብዬ አስባለሁኝ።
- · ቁልፉ መፍትሄ
ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ ሜቶ እኮ ኢትዮጵያ ነው ያሉት። ከሱዳን ተጠልፈው ታስረው ከእስር የተለቀቁት
አርበኛም አሉን። ስለምን የኢትዮ ሱማሌ ዓይነት የመፍትሄ እርምጃ በጋንቤላም አይወሰደም። የነፃነት አርበኛ አቶ ኦኬሎ አኳይናም
ምን አልባት ወደ የሚኖሩበት አውርፓ አገር ቢመለሱም/ ባይመለሱም አመራሩን በነዚህ ብርቅ ኢትዮጵውያን ቢቀዬር የዘላለም እረፍት
ይኖራል ብዬ አስባለሁኝ።
አሁን ኢትዮ ሱማሌ ላይ ያለው እረፍት እኮ ይህ ነው አይባልም፤ መፍትሄውም ዕጹብ ድንቅ ነው።
ሃላፊነት የሚሰማው፤ የሰብዕዊ መብት ተመጓች መሪ አሉ፤ በተጨማሪም የኢትዮ ሱማሌ አክቲቢስቶችም አዎንታዊና ውስጣዊ ስለሆኑ ለውጡን
በመደገፍ እረገድ የአብይ ሌጋሲ የአዎንታዎ አክቲቢዝም ላያ ሙሉ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ አምናለሁኝ።
ይህ ማለት ለተስፋችን የጀርባ
አጥንት የመሆን ቅናዊ አቅም አላቸው ማለት ነው።
ስለሆነም ጋንቤላ ላይ ዶር አቦንግ
ኢትዮጵያ ሜቶ + የነፃነት አርበኛው አቶ ኦኬሎ አኳይና + አብይ ሌጋሲ= አዲስ ጋንቤላዊ ተስፋን ይፈጥራል።
ከዚህ የተሻለ እና ምርጥ የሆነ መፍትሄ የለም። ጋንቤላ ወሳኝ ቦታ ነው። ህዝቡም በኢትዮጵያዊነቱ
የማይደራደር ጽኑ ህዝብ ነው። ስለዚህ የጠ/ ሚር ቢሮ ጊዜ ሳያጠፉ መፍትሄ ላይ ቢተጋ ጥሩ ይመስለኛል።
እርግጥ ነው ችግር ፈጣሪ እንጂ ችግር ፈቺ ማነሱ ይሰማኛል፤ ነገር ግን ባለው ሁኔታ የሚሰማንን
የመፍትሄ ሃሳብ መጻፉ ግን ግድ ይላል።
ልዑል ሆይ ለህዝባችን እባክህ ሰላሙን ስጥልን!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ