ልጥፎች

ለሦስተኛ ጊዜ የሰማይ ምልክት።

ምስል
እዩት እስኪ ውዶቼ። „በረድኤታችን በእግዚአብሄር ደስ ይበላችሁ፤ ለያዕቆብ አምላክ እልል በሉ“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ© ሥላሴ 23.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲውዘርላንድ። በ2015 መግቢያ ወር ላይ ሰማይ ላይ ብዙ ሠረገላዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለብሰው አያለሁኝ። ለአንዲት መነኩሲት እህቴ ደውዬ ነገርኳት። ለቤተሰቦቼም ሲደውሉልኝ ውጪ አገር ለሚኖሩት እንዲሁ ነገርኳቸው።  ከዛ የካቲት 24 ቀን እዚህ ሲዊዘርላንድ የኢትዮጵያ አዬር መንገድ በጀግና ሃይለመደህን አበራ አማካኝነት ካለምንም እንከን ጄኔባ አረፈ። ያው አዬር መንገዳችን ነጹሁን ሰንደቅ ተሸላሚ ስለሆነ ከቤተሰቦቼ ጋር ይህን ነው ያሳዬሽ ተባብለን አለፍነው። ሌላ እውነት ደግሞ ልንገራችሁ። እዚህ ሲዊዘርላንድ የ193 አገሮች ገጽ በሚመለከት አንድ ጥናት ነበር። እኔ ለካስቲንግ ተጋብዤ ተሳታፊ ነበርኩኝ። ካስቲንግ ከመሄዴ በፊት ለብሼው የምሄደውን መምረጥ ፈልግኩኝ። ጉትቻው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ተገዝቷል። ልብስ ግን ከምገዛ በቤት ውስጥ ባለው ልጠቀም ብዬ የቤቱ ሁሉ ልብስ ወጣ። መዘነጥ ዋናው ሆቢዬ ነው ከምል መደበኛ ተግባሬ ነው ከልጅነት እስከ እውቀት። እርግጥ ነው ፎቶው ከአንገት በላይ ነበር - ገጽ ብቻ ነበር የሚፈለገው። ነገር ግን ከወገብ በላይ ያለው የፊትን ገጽ የማድመቅ ድርሻ የሚኖረው ልብስ አስፈልጎኝ ነበር። የቤቱ ሁሉ ልብስ ተዘርግፎ ተሞከረ፤ ሁሉም ሊያደምቀኝ አልቻለም። መጨረሻ ላይ ቲ ሸርት ነበርኝ የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ ያን አውጥቼ ስለብሰው ምኑን እነግራችሁዋለሁኝ ቦግ አደረገኝ። በቃ ደስ አለኝ። የሚገረመው ክረምት ላያ ስለነበር ስሄድ ደረብረብ ያለ የሚመጥን አለባባስ ነበረኝ። ስገባ ካስቲንግ ቲሙ ተመልክቶኛል።

ለውጥን ማስቀጠል በህግ የበላይነት እና በተጠያቂነት!

ምስል
ብልህነትን ከብልሆች ብቻ ሳይሆን ከሞኝዎችም መማር ይገባል። „ከቀረውም ብርና ወርቅ አንተ እና ወንድሞችህ ለማድረግ ደስ የሚያሰኛችሁን ነገር እንደ አምላከችሁ ፈቀድ አድርጉ።“ መጽሐፈ ዕዝራ ምዕራፍ ፯  ቁጥር ፲፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 23.90.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ የሰርክ ዕጣ ለቅሶ!ማን አብሶ? እንዴት አለችሁ አዱኛዎቼ። ደህና ናችሁ ወይ? አንድ ዜና ሰማሁኝ ዕውነት ከሆነ ወርቅ እርምጃ ነው። የጠ/ሚር አብይ አህመድ የስሜን አሜሪካ ጉዞ መሰረዝ ጉዳይ የልቤ የሚባልለት ነው።   በዚህ ስሌት የስሜን አሜሬካው የቀደመው ከሀምሌ 19 ጀምሮ የነበረው ጉዞም ተሰርዞ ቢሆን ለእኔ ምቾት የሚሰጠኝ ነበር። እኔ ተደሞዊ ነገር ነው ግጥሜ። ደመቅ ያለ ነገር አይወድልኝም። ብልጭልጩም እንዲሁ ...  ሌላው የሰኔ 16 የድጋፍ ስልፍም ወቅቱን ያልጠበቀ በፍርክርክ ትልም ዜጎቻችን ለመሰዋዕትን የቀለበ ነበር፤ ይህንንም ተቃውሜ ጽፌ ነበር። እንዲቀርም ተማጽኜ ነበር። በውስጡ ያልተደፈሩ ሽንቁር - ድፍርስ - የጎርፍ ክምሮች ነበሩቡት። ለአዲስ አባባ የበቀል ጥሪት ማከማቻም ነበር። ይሄው ድሃው ዋጋ እዬከፈለበት ነው። አስከፋዩ ደግሞ የቀናው፤ የተቃጠለው ወገን መሆኑ ነው የሚያቆስለው። ለዚህ ነው ወዮ አዲስ ስል የባጀሁት።  ሌላው ይህ አቀባባል ምንትሶ ቅብጥርሶም የሃይል አሰላለፉን መስመር ቀያሽ ስለነበር አስፈላጊ አልነበረም። ፍንትው ያለ መረጃ ይሰጥ ነበር።በዚህም ሆነ በዚያም፤ እንዲህም ሆነ እንዲያ መስዋዕት ከፋዩ ደሃው ነው። ሊሂቃኑ እማ ምን ሲነካቸው ነው። የሆነ ሆኖ ደስታን ቆጥቦ መያዝ ቀጣዩን ጉዞ የስኬት ዘውድ ይደፋለታል። ከመዋለ ንዋይ ይልቅ ደስታን በቅጡ ቆጥቡ መያዝ ከብዙ ነገር ይታደጋል ። ነፍስ ሆኖ ነፍስ ይ

እውን ለውጡ በማሸንፍ ወይንስ በንቃቃት ላይ?

ምስል
ስቅዛት በፈቃድ። „ጋሜል። ቀበሮች እንኳን ጡታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ።             የወገኔ ልጅ ግን እንደ ምደረ በዳ ሰጎን ጨካኝ ሆነች።“                    ሶቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 22.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=3KaJ74W-az0 Ethiopia: በቡራዮ ከተካሄደው ጥቃት የተረፉ ዜጎች ፖሊስ ሦስት ቀን ሙሉ ስንጨፈጨፍ አልደረሰልንም                       አሜኑ! ይቻላል ወይ በጃዋርውያን/ በኦነግውያን መንፈስ አገር እየታመሰ?  እንዴት ናችሁ ውዶቼ አንድ ኢሜል አንድ ወዳጄ ላኩልኝ። እኔ እኮ መሬት ላይ የጋሞ አዛውንታት የሠሩትን ማቃለሌ አይደለም። ያ መልካም ነገሩ ኦሮምያ ላይ ካልሠራ ምንድነው ፋይዳው ነው ጉዳዩ።  እነኛ ቅኖች መበደልን በበቀል አለመመለሳቸው በፈጣሪ ዘንድ ያስደግፋቸዋል። ነገር ግን መንግሥት የተጠቀመበት የቄሮ ወንጀል እንዲሸፈንለት መሆኑ ነው  እኔ የማይመቸኝ፤ ሌላው አባገዳዎች ኦሮምያ ላይ ጉዳት ሳይደርስ ለቃችሁ ውጡ ማለታቸውን ከኦሮምያ የተፈናቀሉ የአማራ ልጆች ከ6ወር በፊት ገልጸዋል። አባ ገዳዎች እንደ ጋሞዎቹ መሆን ተስነቿው ነው የማዬው። አባ ገዳዎችም የኦነጋውያን መንፈስ እንጂ ለአብይ ካቢኔ ክብካቤያቸውን አላዬሁም። ቡራዩ ላይ አባ ገዳዎች የሉንም? ቢያንስ ሬሳ አስነስተው በክብር ለማስቀብር ምን አገዳቸው? ሞትስ ቢሆን ምን አለ ቢቀበሉት። ሰማዕትነት ነው። ሊቢያ ላይ አኮ አንድ ሙስሊም ሰማዕት ራሱን ቀራኒዎ አውሏል ከወገኖቹ ጋር። አባገዳዎች ከተጠቂዎች ቀደመው ቢሰው የአቡነ ጴጥሮስ ትውፊታቸውን ከወኑ ነበር

ጋሞዎቹ ደሞቼ የፍቅራዊነት መርሆ ወንጌልም/ ቁራዕንም ናቸው።

ምስል
ብልህነት እንደ ጅረት ደግነቱ፤  የውስጥነት አብነቱ ከእትብቱ። „የእግዚአብሄር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦---- የሰው ልጅ ሆይ የወይን ግንድ በዱር ዛፎች መካከል ያለ የወይንሐረግ ፣ ከዛፍ ሁሉ ይልቅ ብልጫው ምንድር ነው?“ ከሥርጉተ©ሥላሴ  21.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት አላችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ። ከሰሞናቱ የህፃናት፤ የእናቶች መከራ ጋር ሰውነቴን እዝሎት ስነበት፤ ምግብም በወጉ ሳልወስድ መዳህኒት እወስድ ስለነበር ተጎዳሁኝ፤ ከሁሉ ግን እንቅልፍ አልቦሽ መሆኔ ሰውኔትን አደከመው። እናላችሁ እንቅልፍ አጥቶ የሰነባበተው አካሌ ከአቅሜ በላይ ሆኖ ዲሞ ወጣ እና የማለዳ ተለምዶዬን ከውኜ ገደም ስል ከጥዋቱ ሦስት ሰዓት (09.00) እንደኛው አቆጣጠር አስከ ምሽቱ 1.00 ሰዓት (ከ19 ሰዓት) የት እንደወደቀኩኝ ሳለውቀው ተኛሁኝ። የሬቻም እልቂት መልዕክቴን ለተባባሩት መንግሥታት ልኬ ቤት መጥቼ ልክ እንደ ዛሬው እንዲህ ሆኜ ነበር። አድካሚ ሰሞን ነበር ያን ጊዜም። አድካሚነቱ በመንፈስ ነበር፤ ተስፋ ሲዝል፤ ራዕይ ሲጠወልግ፤ ያመናችሁት ባመናችሁበት ተገኘም አልተገኘም ከእንባ ጎን የመቆም አቅሙ በታመነው ልክ አለመሆን ራስን ይፈትናል። እኔ „ለማውያን ነኝ“ ስል ሰዋዊነት እና ተፈጥሯዊነት ነፍሱን የገዛው መንፈስ ነው በሚል ነበር። የሆነ ሆኖ ውስጤ መወስን ባቀታው ወጀብ ሲንገለታ ነው የሰነባባተው፤ መታመንን ለመስጠት ቅንነት አስፈላጊ ቢሆነም፤ ቅንነት ተቀባዩ ዋጋውን መመዘን ሲሳነው ስስጥን ያዝላል። ሰላም የአንድ አካል፤ ፍቅር የአንድ ወገን ቅንነትም የአንድዮሽ አይደሉምና። ፍቅር ስትሰጥ ተቀባዩ ለመስጠት መፍቀድ ብቻ ሳይሆን በዛ ውስጥ መገኘት ግድ ይለዋል። ብ