ጋሞዎቹ ደሞቼ የፍቅራዊነት መርሆ ወንጌልም/ ቁራዕንም ናቸው።

ብልህነት እንደ ጅረት ደግነቱ፤
 የውስጥነት አብነቱ ከእትብቱ።
„የእግዚአብሄር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦----
የሰው ልጅ ሆይ የወይን ግንድ በዱር ዛፎች መካከል
ያለ የወይንሐረግ ፣ ከዛፍ ሁሉ ይልቅ ብልጫው ምንድር ነው?“
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 21.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ


ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት አላችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ። ከሰሞናቱ የህፃናት፤ የእናቶች መከራ ጋር ሰውነቴን እዝሎት ስነበት፤ ምግብም በወጉ ሳልወስድ መዳህኒት እወስድ ስለነበር ተጎዳሁኝ፤ ከሁሉ ግን እንቅልፍ አልቦሽ መሆኔ ሰውኔትን አደከመው።

እናላችሁ እንቅልፍ አጥቶ የሰነባበተው አካሌ ከአቅሜ በላይ ሆኖ ዲሞ ወጣ እና የማለዳ ተለምዶዬን ከውኜ ገደም ስል ከጥዋቱ ሦስት ሰዓት (09.00) እንደኛው አቆጣጠር አስከ ምሽቱ 1.00 ሰዓት (ከ19 ሰዓት) የት እንደወደቀኩኝ ሳለውቀው ተኛሁኝ።

የሬቻም እልቂት መልዕክቴን ለተባባሩት መንግሥታት ልኬ ቤት መጥቼ ልክ እንደ ዛሬው እንዲህ ሆኜ ነበር። አድካሚ ሰሞን ነበር ያን ጊዜም። አድካሚነቱ በመንፈስ ነበር፤ ተስፋ ሲዝል፤ ራዕይ ሲጠወልግ፤ ያመናችሁት ባመናችሁበት ተገኘም አልተገኘም ከእንባ ጎን የመቆም አቅሙ በታመነው ልክ አለመሆን ራስን ይፈትናል።

እኔ „ለማውያን ነኝ“ ስል ሰዋዊነት እና ተፈጥሯዊነት ነፍሱን የገዛው መንፈስ ነው በሚል ነበር። የሆነ ሆኖ ውስጤ መወስን ባቀታው ወጀብ ሲንገለታ ነው የሰነባባተው፤ መታመንን ለመስጠት ቅንነት አስፈላጊ ቢሆነም፤ ቅንነት ተቀባዩ ዋጋውን መመዘን ሲሳነው ስስጥን ያዝላል። ሰላም የአንድ አካል፤ ፍቅር የአንድ ወገን ቅንነትም የአንድዮሽ አይደሉምና።

ፍቅር ስትሰጥ ተቀባዩ ለመስጠት መፍቀድ ብቻ ሳይሆን በዛ ውስጥ መገኘት ግድ ይለዋል።
ብቻ በማዬው፤ በማዳምጠው ነገር ሁሉ በሁሉም ነገር እኔ ከፍቶኛል። መንግሥት በሚመራው ሚዲያ በሚሰጠው መግለጫ፤ በደባባይ ድምጽ ለወገናቸው በሆኑት ላይ በባሩድ ማለቅ፤ ባለው ከፍ እና ዝቅ አድሎዊ ጉዞ፤ አንዱ የክት ሌላው ባይታዋርነት ብቻ በጥልቀት ማንኛውንም ነገር የእኔ ብሎ ለሚከታታል ወገን ከባድ ሰሞናት ነበር።

„አይደገመም“ ብለውና ዶር አብይ አህመድ እንደ አፋቸው ከማለት ሌላ ልሞግታቸው አይቃጣኝም፤ በነካ አፋቸው ቤንሻንጉል፤ ራያ፤ ባህርዳር ከተማ ቤተክርስትያን ተጠልለው ለተቀመቱትም ወገናቸው ከሆኑ ቅንጣቢ ትኩረት ቢኖራቸውም ይለመኑን እስኪ።

በሌላ በኩል የጋሞ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ወገኖቼ በመረጃ ቴሌቪዥን ያስተላላፉት መልዕክት ግን እንዴት ዓይነት የህጻን ልብ እንዳላቸው፤ እንዴትስ ሰብዕናቸው ድንግል እንደሆነ ማስተዋል በመቻሌ አንድዬን አመሰግናለሁኝ።

አባቶቻችን እኛ ሳናውቀው ያጠፋት ነገር ከኖራቸው በግልጽ ይነገረን እና እና ይቅርታ እንጠይቅ የሁሉም አንድምታ ነበር። እኔ እንደማስበው እነሱ ጻድቃን እንጂ ሃጣን አለመሆነቸው ከአባት እናታቸው በወረሱት ትውፊት ውስጥ መሆናቸውን ተመልክቻለሁኝ። ዕውነት ለመናገር ያልተነገረላቸው፤ ያላወቅናቸው፤ ያልተንከባከብናቸው ግን የፍቅራዊነት ወንጌል/ የፍቅራዊነት ቁራን ናቸው።

በሌላ በኩል የጋሞ ሽማግሌዎችም በዚህ ላይ ድርሻቸውን እንዲወጡ የተደረገውም ወስጣቸው፤ ንጽህናቸውን ከደም ስለመሆኑ እያዬሁት ቢሆንም እንዲህ ዓይነት ሴሪሞናዊ ዲኮ ነገር ብዙም አይመቸኝም።

አሁን እኔ ኢትዮጵያ ለፕ/ ኢሳያስ ካደረገቸው እግጅ ግዙፍ የወዳጅነት መስተንግዶ እና አቀባበል፤ ይልቅ ኤርትራ ያደረገችው ምጥን መስተንግዶ ተፈጠሯዊ ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። ይህ ማለት ኢትዮጵያ የወሰደቸው ደፋር እርምጃ ቅናዊ እና እውነታዊ መሆኑን ካምንም ቀድሜ እኔ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን መጎቸዋለሁኝ፤ ሂደቱንም የ እኔ ብዬ ጽፌበታለሁኝ።

በሌላ በኩል ጎንደር ለአቶ ታማኝ በዬነ ካደረገው የትእዛዝ አቀባባል ይልቅ፤ ጎንደር ለአቶ አበበ በለው እና ለጥበብ እናት ለወ/ሮ አለመጸሐይ ወዳጆ ይደረገው ተፈጠራዊነቱን አሳይቶኛል። ድንግልናው ወስጤ ሆኗል። 

ሰው ፈቅዶ የሚያደርገው እና አድርግ ተብሎ ተጀብጅቦ ወይም በገንዘብ ተገዝቶ የሚያደረገው ብልጭልጭ ወይንም የሳሙና አረፋ ነው። ጤዛ። ያው ሥርጉትሻ ፈንገጥ ያለ ዕይታና ምልከታ ነው ያላት።

ስለሆነም ለመንግሥት ፕሮፖጋንዳ ይህ የጋሞ የሽማግሌዎች ጉዳይ ኗሪዎቹ እንኳንስ ቂም ሊይዙ ቀርቶ ያጠፋነው ካለ ንገሩን፤ እኛ ሳናውቀው አባቶቻችን ያጠፉትም ካለ ንገሩን ይቅርታ ዝቅ ብለን እንጠይቃለን ብለዋል። ሌላው ሸር ጉድ ብዙም ልበ ገብ አይደለም። ዋናው ነገር መሬት ላይ ላሉት ቅንጣቢ ዋስትና ሌላቸው ወገኖች ሆኖ መገኘት ነው። ሰክረው ነው የወደቁት የሚለውን የኦሮምያ ፖሊስ የጥላቻ ሀውልት መናድ ነው ቁምነገሩ።

የሆ ሆኖ የጋሞ ሽማግሌዎች መሰናዶ ቢዚህ ድርጅታው ሂደት 50 ዓመት ተኑሮበታል፤ ከተለመደው የግራ ዘመም አካሄድ ውጪ እኔ ልቤን ትር ትር አለደረገውም። 

ሌላ ምሳሌ ላንሳ ለምሳሌ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ በመጡ ጊዜ አንዲት እናት ወለጌ ይመስሉኛል ለፕ/ ወርቅ ሸልመዋል በቤተ መንግሥት።

ከዛ ለመድረስ እንዴት ቻሉ? ማን ስላላቸው ነው ቤተ መንግሥት ከእንግዶች ጋር ታዳሚ እንዲሆኑ የተደረጉት? በምን ሁኔታ እሳቸው ተመረጡ? ለሚለው ለእኔ ፌክ ስለሆነ አልጻፍኩበትም። እርግጥ ነው የጠ/ ሚር አብይ አህመድን ዕንባ ጠራጊነት የውስጥ ነው ብዬ መቀበሉን ግን የዛሬ ሳይሆን የቀደመውን ሰብዕናቸው ስለማውቀው ተፈጥሯዊ መሆኑን ሳላወላዳ እቀበላለሁኝ። 

የሆነ ሆኖ እንኳንስ ከጠ/ ሚር ቢሮ ቀርቶ ከአንድ የተፎካካሪ ፓርቲን የአገር ውስጥም ይሁን የውጪ አገር ሊቀመንበር ለማግኘት እኔ ችግሩን ስለማውቀው ፕሮቶኮሉ ሴረሞኒው ስለሚገደብኝ ነው የሚሰማኝን በግልጽ ለህዝብ ብራና ላይ እምጽፈው። እንጂ አሁን በቀጥታ የዶር አብይ አህመድ ወይንም የፕ/ ብርሃኑ ነጋ ኢሜል ቢኖረኝ አደባባይ የሚያጽፈኝ ምንም ምክንያት የለም። 

ከግንቦቶች ከንጉሦሱ በታች ዝቅ ያሉትን ኢሜል ጠይቄ እንኳን እኔ ተከልክያለሁኝ። በሌላ በኩል ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ስሜን አሜሪካ በመነበሩበት ጊዜ "ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው" እነሱ ካሉት በላይ የሆኑት ትውልድ ከቶም የማይተካቸው ፕ/ ፍቅሬ ቶሎሳ ተገለው ለ አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎቹ ምን ያህል ሸርጉድ እንደተደረገም እዬተመለከትነው ነው። 

ባህላችን የሴራው ማሰሮ ይታወቃል ቅኖችን ይጸዬፋል፤ ንጹሃን ያገለል። የት ሄደች በዛ የመከራ ዘመን ብቸኛዋ የአገር ውስጧ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቿ አርቲስ አስቴር መዳኔ የጎዳና ተዳዳሪ ልጆቻችን የልብ ጓደኛ። የሆነ ሆኖ ከመሪዎች ለመድረስ ብረት መዝጊያ ወገን ከሌሌ ውልፍት እንደሌል ኑረንበታል። ለማድመጥ እንኳን አይፈቅዱም የምንጽፈውንም አያነቡትም። በሌላ ሁኔታ ትውውቁ የቀደመ ቢኖር እንኳን ክትር ይሰራበታል። 

ይህም ብቻ አይደለም አሁን ልጅ ስለሆነ የጠ/ሚር አብይ አህመድ ካቢኔ በከፋኝ ልክ ለውጬ መንግሥታት ላሳጣው አልፈቅድም፤ ቀደም ባለው ጊዜ ግን አድማጭም ስላልነበር የወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚፈጽመውን ኢ- ሰብዕዊ ድርጊት በቀጥታ ካለምንም ፕሮቶኮል ለምፈለገው የውጭ መንግሥታት እጽፍ ነበር።

ያ ማለት የአገሬን የተፎካካሪ በሉት የተቃዋሚ ገዢው ፓርቲን በተጨማሪም አውራው ፓርቲ የወያኔ ሃርነትን መኳንታት፤ መሳፍንታት ከማግኘት ይቅል የውጭ አገር ከፍተኛ መሪዎችን ማግኘት ቀላል ነበር። ፕሮቶኮል የለ ሴሪሞኒ የለ። 

ስለዚህም ነው ያቺን እናት ለዛ ደረጃ ያበቃት፤ የታቀደ የድርጅታዊ ሥራ እንጂ በራስ አነሳሽነት የተከወነ ተግባር ነው ብዬ አምኜ ለመቀበል ያደገተኝ። ስለዚህም የጋሞ ሽማግሌዎችን ሰብዕና ባከብርም፤ የሆነው ግን፤ የሚዲያው ሸርጉድ ግን ሆነ የጠ/ ሚር አብይ አህመድ በኦህዴድ ሥያሜ ስንበት ላይ ባደረጉት ንግግር ምስጋና ሲያቀርቡ ብዙም ያልደነቀኝ ለዚህ ነው። 

አሁን ለእኔ የዓርማ የስያሜ፤ የመዝሙር ለውጥ እንጂ ሌላ ነው ለማለት አልችልም። ሌላ ስለመሆኑ ሊመሰከረልት የሚችለው የዛሬ  5 ዓመት ነው። ጣና ኬኛ እና ግባዕቱ በአማራ ተጋድሎ እና ውጤቱ ፈተናውን አለመቻሉ እያዬሁትም ነው። ራሱ የቀደመው ኦህዴድ ለ አማራ ህዝብ ያለው ውስጥነት ምንም ነው። ለችግራችን ቅርብ ሊሆን አልቻለም። አግሎናልም።  

ወደ ቀደመው ምልስት ሳደርግ ጋሞዎች በተፈጥሯቸው ለተፈጥሮ የሚመቹ ዕንቁ ስለመሆናቸው ከልቤ ገብተዋል። እንዲያውም ለጋሞ ህዝብ እኔ በግሌ ከዛሬ ጀምሮ በተለዬ ሁኔታ አትኩሮት ይኖረኛል። መታመኔን አበርክትላቸዋለሁኝ። የ አስተሳሰብ ድህንት ስሌለብኝ በዚህው ብራና ጉዳያቸውን አቀርባለሁኝ - እንዲህ።  

እንዲህ ዓይነት ንጽህና ያላቸው የጋሞ ሊሂቀ ሊቃውንታትም ወደ ፓለቲካው ዓለም ብቅ እያሉ በሴራ የበከተውን፤ በድል አጥቢያ አርበኞች ልቅና የሚሽሞነሞነውን የአላዛሯ ኢቲዮጵያ ፖለቲካ ማጽጃ ንጥረ ነገር እንዲሆኑ ምኞቴ ነው።

እንርግጥ ነው እኔ በድምጽ አልባዎቹ እናቶች አቤቱታዬ የጋሞም እናትም አለች። የጋሞ ህዝብ እንደ ወገኔ ደግሞ ጸጋው ከእናትነት ቢበልጥ እንጂ የሚያንስ አይደለም። ቅዱስ ህዝብ ነው። ሰማዕትነታቸውም ቅድስናቸው ያመጣው ነው።  የእነሱ ደም እንደፈሰሳ አንደማይቀርም በፈጣሪዬ እተማመናለሁኝ። የአይሲስ የሠራው ቤተ ሙለራ እንደ ሊቢያው የታዬው አሁን ነውና። ለዛውም በዘመነ አብይ እና ለማ ... 

መልካሞችን ለይቶ ስለሚችሉለት ይመስለኛል ልዑል እግዚአብሄር ፈተና በዬጊዜው ያመጣባቸዋል። መልካሞች ሁልጊዜ ለችግር ቅርብ ናቸው። ጋሞ ለጉርብትና፤  ለአበልጅነት፤ ለጋብቻ፤ ለላቅ አገራዊ ሃላፊነት አብነት ናቸው። ኢትዮጵያዊነት እንደ ቅኔው ልዑል ብላቴ ሎረቴ ጸጋዬ ገ/ መድህን ተርጉመውልኛል። ስለሆነም ውስጣቸው ታቦቴ ነው። 

መልስ ያለገኘሁለት ምን ስላደረጉ ነው እንዲህ የወል ጥቃት የሚፈጸምባቸው ስለሚለው ግን መልስ አላገኘሁለትም። እንዲህ ዓይነት ቅን እና የዋህ ደግ ህዝብ በውነቱ ለኢትዮጵያም ሽልማት ነው። ልዩ ስጦታ ነው ጋሞ ውስጤ ነው። 

ውስጤ በብዙ ነገር የተጎዳ ነው። በሰሞናቱ ብቻ ሳይሆን በነፃነት ተጋድሎ ታሪኬ ተካስኩ የምልበት ዘመን ቢኖር የጋሞን ንጽህና እንዳይ እግዚአብሄር የፈቀደልኝ የአሁንን ጊዜ ነው። የታዳጊ ወጣት አብሥራ ማሬ ዕንባ መድረቅንም አክሎ። ስለሆነም ልዑል እግዚአብሄር ከሰጠኝ የመጻፍ መክሊቴ ባለነሰ ይህ ልዩ ስጦታ ለህሊናዬ ሆኖል።

ሌላ እኔ ምንም አቅም የለኝም፤ መጸለይ ብቻ ነው። ጋሞ የንጽህናው ያህል በአገሩ እንደ ዜጋ ሆኖ ዘላቂ ዋስትና የሚያገኝበትን ዘመን ልዑል እግዚአበሄር ያምጣልን። አንዲት እናት ልጇቻቸውን ከት/ ቤት አስቀርተዋል፤ ስለምን? ሲባሉ ወጥቶ ስላማይመሰሉ አሉ። አንዲት ሌላ እናትም ልጃቸውን ተነጥቆ ተወስዶባቸዋል፤ የት እንደደረስ አይታወቅም። 

አዎን! የእኛ ኢትዮጵያ እንዲህ ለዜጎቿ ዋስትና ለመሰጠት አቅመ ቢስ አገር ናት። ለዛውም አሁን በዘመነ መደመር? አሁን ባለው ሁኔታ ልጆቻቸውን የተነጠቁት በሞት ብቻ ሳይሆን እንደ ተዘረፉም አድምጫለሁኝ። የሁለመና ወረራ ነው የተካሄደው። ገና ዛሬ በጥዋቱ ይህ ከመጣ መባጃው ነገስ? መራራው ዕውነት ይህ ነው። ሬሳ የሚያነሳ ጠፍቶ ለኦሮምያ ፓሊስ ሲደወል ሰክረው ነው የወደቁት ነበር የተባሉት። 

እንዴት የጋሞ ሰው ሁሉ ጠጥቶ ሰክሮ ወደቀ ሊባል ይችላል? አሳዛኙ ነገር አንድም ዋቢ እና ተቆርቋሪ መንግሥታዊ አካል በ ኦሮምያ ምድር ማታጣቸው ነው አሳዛኙ ነገር። ለዚህ ንጹህ ህዝብ ዘብ መቆም የሁላችንም ግዴታ ነው እንበርታ … በዚህ ሂደት ተጠቃሚው የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሳፍንቶች ናቸው። ይህን እንኳን በማስተዋል መመርመር አልቻለም ኦረምያ? 

ዶር ለማ መገርሳ ሆኑ ዶር አብይ አህመድ በሰሚናር ሳይሆን ልጆቻቸውን በቤት ውስጥ ሚኒ መድረክ ከፍተው ስለፍቅር ማስተማር አለበቸው። ሰውኛ ያድርጓቸው። አፍሪካን ለመምራት ያላቸውን ስንዱነት አድምጫለሁኝ። 

በክፉ ነገር የተበከለውን የልጆቻቸውን መንፈስ መጀመሪያ ወደ ተፈጥሯዊነት ይቀይሩ - ትእዛዝ ሳይሆን ከቁስለት የመነጨ ማሳሰቢያ ነው። እንደሚመራቸው አውቃለሁኝ ግን ሊሆን የሚገባው ይህ ነው።

ፕሮጀክት ከፍተው፤ ካሪክለም ነድፈው በዚህ ጉዳይ በመደበኛ ቢሠሩበት ጥሩ ነው። ሰው ተገድሎ ተዝቅዝቆ ከመሰቀል ወዲያ ምን ይሆን የሚጠበቀው። አመራር የሚጀምረው ከቤተሰብ ነው። ቤት ነው የመጀመሪያው የህይወት ት/ ቤት።

አሁን ለእኔ የዓርማ፤ የመዝሙር ለውጥ ሳይሆን እነዚህ ልጆቻችን በሰውኛ በተፈጥሮኛ መንፈስ እያመለጡን ስለሆነ ከታመሙበት በሽታ እንዲፈውሷቸው እሻለሁኝ። የቲም ለማ አዲሱ ፍልስፋና ሰዋዊነት እና ተፈጥሯዊነትን ሥርዓተ ትምህርት ነድፎ ልጆችን መስተማር ነው ሊሆን የሚገባው። የሌላውን ሰው ነፃነት ማለትንም ማሰተማር። የሰው ልጅ የፈለገውን ቋንቋ የመናገር መብት አለው። 

ይህ ሁሉ ፍዳ ስለምን እንደገጠማቸው እነሱም ያውቁታል እኛም እናውቀዋለን። ከሥር መነቀል ያለበት መሰረታዊ በሽታ አለ። ለእኔ አዲሱ አመራር ስለሚባለው ብዙም አይደንቀኝም፤ እርግጥ ዶር አብይ አህመድ እንዲቀጥሉ መደረጉ ደስ ቢያሰኘም ግን መሰረታዊው ነገር ገና አልተነካም። በህሊና ውስጥ የታመቀው የሰው እና የተፈጥሮ ጥላቻ። 

አባ ገዳዎች ሳይቀሩ ለቃችሁ ውጡ፤ አደጋው ከመድረሱ በፊት ነው የሚሉት እንጂ እኛ እናድናችሁአለን አይሉም። መንግሥታዊ መዋቅሩም ከለላ አይሰጥም። ይህ ዕውነትን መድፈር ያስፈልጋል። „አለባብሰው ቢያርሱት ባረም ይመለሱ“ ነው ጉዳዩ። አሁን በሰሞናቱ እልቂት የተፈናቀሉት ይመለሱ ግን ምን ዋስትና አላቸው? ማን ከጎናቸው አለ? 

ለምሳሌ አማራ መሬት ላይ የሚታይ ድንቅ ነገር አለ። የአማራ ተጋድሎ እንደተነሳ በመካከለኛው አፍሪካ የአማራ መንግሥት እናቋቁማለን የሚሉ ሁለት ፍሬ ወጣቶች ተነሱ። በማህበራዊ ሚዲያ ብቻ ሳይሆን እኛን የማይደፍሩ ሚዲያዎች እነሱን አቅርበው ጠዬቁ መርዙ አብረው ረጬ አራቡትም ።

እኔም መሬት ላይ 10 ሰው ከተገኘ በመዶሻ ተደብድቤ ልሙት ብዬ ጻፍኩኝ። ምክንያቱም እኔ ገበሬ አደራጅ ነኝ። ገበሬዎቼን አውቃቸዋለሁኝ። እኔ ወጣት አደራጅ ነኝ ወጣቶቼን አውቃቸዋለሁኝ። እኔ ሴቶች አደራጅ ነኝ ሴቶቼን አውቃቸዋለሁኝ፤ እኔ የሠራተኛ ማህበር አደራጅ ነኝ ሠራቶኞችን አውቃዋለሁኝ። 

እኔ የሙያ ማህበራትን አደራጅ ነኝ እነሱንም አውቃለሁኝ። እኔ የከተማ ነዋሪዎች አደራጅ ነኝ እነሱንም አሳምሬ አውቃለሁኝ። እና ያ መርዝ ተንሳፎ እንደሚቀር አሳምሬ አውቃለሁኝ። እርግጥ እኔ የለሁም ዛሬ ትውፊቱ ግን መሰረት ያዬዘ መሆኑን አሳምሬ አውቃለሁኝ። መኖር አይባልም ከኢትዮጵያዊነት ክብር ተወጥቶ አማራ መሬት ላይ።

ወደ ቀደመው ምልስት ሳደርግ በመሃል ጠቢቡ ቴወድሮስ ወደ ባህርዳር ኮንሰርት ሲሄድ እንዳሄድ አስጠነቀቁ እነሱ ፈርስታውያን። ኢትዮጵያዊነት አማራነትን ይጫነዋል የሚል ስጋት አለባቸው። አልፈው ተርፈው አደጋ እንፈጥራለን ብለው ፎካከሩ። በገርድምዳሜም ማህል ላይ የሚገትር ጹሁፍም ተጽፎ አንብቤያለሁኝ፤ የፈሩት አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ብሄራዊ ሰንድቅዓለማ እና „ኢትዮጵያ፤ ካሳ ካሳ“ የሚለውን አስደመሚ ድንቅ ኪናዊ መንፈስን የገዛ የቅኔ ዕድምታ ነበር። የአማራ ወጣቶች ፈርስት ነን የሚሉት እነሱ በሠሩላቸው ማኖቆ ሸጎሬ ብቻ ተኮድኩደው  ወጣቶች እንዲቀመጡ ይፈልጉ ነበር።

እኔም ወጥቼ ሞገትኳቸው፤ ኮንሰርቱን ለማደናቀፍ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ወሎ ላይ ህዝብ ጨፈጨፈ ይህ ለእነሱም ምን እንደነበር ህሊናቸው ያውቃዋል፤ የወሎ ወጣቶች እንደ ጎንደሮቹ ኮንሰርቱን ሊቀላቀሉ አላስቻላቸውም፤ ድባቡም ሃዘናዊ ቅይጥ  ነበር። ብቻ  ኢትዮጵያ ነግሳ ከሚዩ ቢደናቀፍ ይመርጡ ነበር። ብአዴን ያን ጊዜ ወንድ ወጥቶት ደፈረው። ተዚህ ላይስ ይባረክ። ተከሶበትም ቆፍጣና መልስ ሰጥቶ አሽምድምዷቸዋል የቀደሙት ጌቶቹን። 

የሆነው ግን የአማራ ልጆች ለዛውም ወያኔ ከመገባ ከ10 ዓመት በኋላ የጠፈጠሩት እንደ ኳስ ሜዳ ልሙጡን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ሰንደቃቸውን አስከብረው ድል አደረጉ። የጥምቀት፤ የመስቀልም መሰሉን ከወኑ፤ የዶር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍም በታሪክ  ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ኢትዮጵያን አከበሯት - የአማራ ወጣቶች።


በድጋፍ ሰልፉ ላይ የአማራ ፈርስት አቀንቃኞች፤ ወይንም ኢትዮጵየዊነት እና አማራነት በወስጥነት የያዙትን የትኛውንም የአማራ ድርጅቶች ዓርማ ይዘው አልወጡም። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ይዘው አክብረው ወጣቶቹ በመነሰታቸው ፈርስት የሚሉት ይህን መልበስ እንዲገደዱ አደረጓቸው።  

ስለምን? ሃሳባቸው ከባህር የወጣ አሳ መሆኑን አወቁ። ህዝብ አልታገላቸውም፤ ወጥቶ ዲቤት አላደረገም ግን በተግባሩ አሸነፋቸው። አንድም ቀን አማራ መሬት ላይ የአንድ ድርጅት ዓርማ በህዝብ አደባባይ አይታይም።  ይህን ያደረገው የአማራ ወላጅ ነው።  የአማራ ወላጆች አሳምረው የቅድመ አያቶቻቸውን ሌጋሲ አስቀጠሉ። በዚህ መስመር አሳደጉ። በዚህ ሰንደቅ ወስጥ ደግሞ ያለው ፍቅር ብቻ ነው። ብሄራዊ ስሜት ብቻ ነው። መቻቻል ብቻ ነው። ነፃነት ብቻ ነው። አብሮነት ብቻ ነው። በራስ መተመን ብቻ ነው። 

ስለዚህ ኦሮምያ ላይ ሊሠራ የሚጋባው ይህ ነበር። የጀግናው ኮ/ አብዲሳ ክብርን ማስከበር።  ድካሞ አቧራ ልብሷል። ያን ሌጋሲ ማስቀጠል ይጠይቅ ነበር። የሆነው እዬሆነ ያለውን ደግሞ ያዬነው ግን የተገለበጠ ነው። ይህም ሆኖ እውነትን ሳይደፍሩ ዳርዳሩ ችግሩን ቢያስቀጥል እንጂ ችግሩን አይነቅለውም። ከራስ መጀመር የምስለኟ የመፍትሄው ማሃንዲስ። 

ለምሳሌ የኢትዮ ሱማሌ ጉዳይ እንዲህ ባለ መንገድ ይከወናል ብዬ እኔ እራሴ አላሰብኩም ነበር። ከድንቅ በላይ እርምጃ ነው የተወሰደው። ሌላው ቀርቶ እኔ  የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ኦብነግ ስንት ድርድርን አሻፈረኝ ያለው በአንድ ቀን እንደ ወሰነ ሰሞኑን ከማዕከላዊ ኮሜቴ አባል እና ከድርጅቱ ከፍተኛ የሥ/ ስ ኮሜቴ አባል ከሻለቃ አሊ ስመሬ ሲገድ ከፋና ቴሌቪዥን አገር ባድረጉት ውይይት ተረድቻለሁኝ።  

ሌላው ፍሬ ነገር ስለ ኦብነግ እኔ አንድም ቀን ጽፌ አላውቅም፤ ኢትዮጵያ ለማይል ድርጅት ጊዜ ማባከን አልፈልግም ነበር። ግለሰብም ቢሆን ጸረ ኢትዮጵያ ስለሆኑት ግለሰቦችም እንዲሁ ለምሳሌ ፕ/ ህዝቃዬል ጋቢሳ እና አቶ (ዶር?) ጸጋዬ አራርሳ፤ የካናዳውን የግራኝ መንፈስ ፕ/ አባሳንም እንዲሁ አልነካካቸውም ሰሞናቱ እንደሆን ሞት መሬት ላይ ስላወጁ ነው።

የሆነ ሆኖ በአሁኑ ውይይት ጥሩ መንፈስ አይቻለሁኝ ከኦብነግ፤ ሳርፕራይዝም ሆኛለሁኝ፤ ጃዋርውያንን ያሳበደውም ይህ ይመስለኛል አልተሳከላቸውም የ ኢትዮ ሱማሌ ችግር እንዲቀጥል ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ጋር ጀዋርውያን የመንፈስ ሃዲስ ነባረቸው።

ሌላው ግን የካሜራ ጥራቱን እምወድለት የፋና ቴሌቮዥ ጨቋኙን አዋያዩን በሚመለከት በሌላ ጹሑፍ እመለሰብታለሁኝ የኦብነግ ቃለ ምልልስን  ያዳመጥኩት እዛው ስለሆነ።

ወደ ቀደመው ምልስት ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶንም እንዲሁ ማዬት ይቻላል፤ ያልተሞከረ ነገር አልነበረም፤ ለአሁኑ ድርድር ራሱ ለ7 ቀን ሆቴል ተይዞ በሦስት ሰዓት ብቻ እንደ ተጠናቀቀ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ቃለ ምልልሱ ላይ አዳምጫለሁኝ። በእኛም ውስጥ ቢሆን በንፈሳችን ፍጹም የሆነ የጸዳ ታማኝነት ነው ያለው ለእርቀ ሰላሙ። እርቀ ሰላሙን ስንቀበለው በፍጹም ድንግልና ነው። የአብይን ካቢኔም በፍጹም ድንግልና አምነነው ነው። ይህም ጃዋርውያንን አሳብዷል ሬሳቸው አይገባም ነበር የተባሉት ብጹዕን አባቶቻችን ማለቱ ነበር።  

ስለምን የ ኤርትራው፤ የኢትዮ ሱማሌው፤ የቅድስት ተዋህዶ የመፍትሄ መንገድ  የእኔ ተባለ ቢባል ከእውነተኛ የችግሩ ምንጭ መነሳት ስለተቻለ መፍትሄውም ያን ያህል ሥር ነቀል ለውጥ በመንፈስ ደረጃ አመጣ። 

አሁንም ኦሮምያ ላይ ያለው እጅግ አሳዛኝ መከራ ከችግሩ መነሳት ነው መፍትሄ ሊያስገኝ የሚችለው እንጂ ሻታ ቢዞሮቱ አይሆንም፤ በዚህ ገነባን እዬተባለ ያን የሚንድ ሚዲያ፤ ያን የሚደረምስ አክቲቢስት፤ ያን ታጥቦ ጭቃ የሚያደርግ  የፖለቲካ ተንታኝ ደግሞ አለ።

እና ቀን የተገነባው በዛው ቅጽፈት እዬፈረስ፤ በራሱ ውስጥም ያለውን ሳንክ እንዳላዬ እያለፈ የትናንቱ ኦህዴኢድ በእንዴት እና በእንዴት አኳኋን ኦሮሞ አፍሪካን የመምራት ጥበቡን እንደሚሳይ እግዚብሄር ይርዳው … አሜን! በሉ ውዶቼ!
  • ·         ጋሞ ድንግሉ ህዝብን በዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል።


የጋሞ ህዝብ በአዱስ አበባ መኖር አልቻልም

በቡራዩ አሸዋ ሜዳ በደረሰባቸው በደል የመንግስት ያለ በማለት የመከራ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ

በሽሮ ሜዳ አከባቢ 17 ዜጎችን በቤቱ ሽሽጎ ከጽንፈኞች ጥቃት ከታደገው ኢትዬጵያዊ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

A resident who was displaced from Burayu and took shelter in Addis Ababa speaks with Mereja TV

አዲስ ነገር ወቅታዊ እና አዲስ መረጃ(የቡራዩ አካባቢ ተፈናቃዮች)/Whats new breaking News sept 16

Burayu residents demand answer  በቡራዩ ከተማ አሁንም ጥያቄው መልስ ይፈልጋል

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ጥቃት ይደርስብናል- የቡራዩ ነዋሪ

 

ፍቅር የመኖር የምሥራች እንጂ 

የስጋት መልዕከተኛ አይደለም!

 

አዱኛዎቼ ቅኖቹ ሰውኛዎቹ ኑሩልኝ።

በቃችሁ ይበልን አምላካችን!




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።